FastMereja
12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሊካሄድ ነዉ!
#FastMereja I 12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት መርሀ-ግብር ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግስት እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ። ድርጅቱ ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት መርኃ ግብር በመዘርጋት…
12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሊካሄድ ነዉ!
#FastMereja I 12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት መርሀ-ግብር ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግስት እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።
ድርጅቱ ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት መርኃ ግብር በመዘርጋት በኢትዮጵያ የሚሰሩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ዓለም አቀፍ የተወዳዳሪነት ብቃት ማሳደግ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ይህም ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማስፋት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራት ገልፀዋል።
በዘንድሮዉ 12ኛው የጥራት ሽልማት 65 ተቋማት የጥራት ውድድር ለመወዳደር ተመዝግበዋል ከእነዚህ ውስጥ 63 ተቋማት እስከ ውድድሩ ፍፃሜ መጓዝ የቻሉ ሲሆን ባስመዘገቡት ውጤት የጥራት ተሸላሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
ከዚህ ውስጥ 34 ተቋማት በአምራች ዘርፍ፣ 12ቱ ለትርፍ የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪዎች፣ 10 በጤና ዘርፍ፣ አምስት በአገልግሎት ዘርፍ፣ ሶስት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እና አንድ ተቋም ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደተወዳደሩ ተገልጿል።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም በሚካሄደዉ የሽልማት መርሀ-ግብር የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኩባንያ ባለቤቶችና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት የሽልማት ስነ-ስርአቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በአገራችን የጥራትን ጽንስ ሐሳብ ለማስረጽ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎትን ለማበረታታት እና በዓለም አቀፍ ገበያ ያለዉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከአሥራ ስምንት ዓመታ በፊት የተቋቋመ ድርጅት ነው።

❤5
ናይጄሪያ እገታ የሚፈጽሙ ሰዎችን በሞት የሚቀጣ ሕግ ልታወጣ ነው
የናይጄሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እገታ የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት መጣል የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ላይ መነጋገር ጀመሩ።
የሴኔቱ አባላት እገታ ፈጽመው የሚገኙ ሰዎች የሽብር ተግባር ላይ እንደተሰማሩ ተቆጥሮ የሞት ቅጣት እንዲጣልባቸው ለማድረግ የአገሪቱን የጸረ ሽብር ሕግን ለማሻሻል መወያየት ጀምረዋል።
የናይጄሪያ የሴኔት አባላት የሕግ ማሻሻያው ላይ መነጋገር የጀመሩት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚፈጸም የጅምላ ጠለፋ እና እገታ እንዲሁም ደም አፋሳሽ ጥቃቶች እየጨመሩ በመጡበት ወቅት ነው።
ባለፉት ሳምንታት የታጠቁ ሰዎች ሁለት ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት ከፍተው ከ300 በላይ ተማሪዎችን አግተዋል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

❤18👍11🙏4
ለወንጀል መንስኤ ናቸው ያላቸውን ሺሻና የሺሻ ማስጨሻ ከ750 በላይ ቁሳቁሶችን በቃጠሎ ማስወገዱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
👏8❤6
FastMereja
የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቀቀ
#FastMereja I ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ሳምንት በኢትዮጵያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል። በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ከ2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር የጀመረው የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የ2018 "በጋራ እንገንባ"…
የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቀቀ
#FastMereja I ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ሳምንት በኢትዮጵያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።
በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ከ2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር የጀመረው የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የ2018 “በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ የቆየ ሲሆን የመዝጊያ ስነ ስርዓት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር የሆነት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በተገኙበት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቋል።
የ2018 ሃካቶን ተወዳዳሪ አሸናፊዎች
ኤግሊፍት፣ ፋይዳ ሄልዝ እና ከእርሻ ወደ ጉርሻ የተሰኙ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ በመሆን ሽልማታቸውን ተቀብሏል።
በጥናት እና ምርምር ጽሁፍ አጸደ ተስፋዬ (ዶክተር) እና ቆንጂት ኃይሉ (ዶክተር) ተሸላሚ ሆኗል።
📌 የአመቱ ምርጥ ሴት ስራ ፈጣሪ በዓምላክ አለማየሁ ተሸላሚ ሆናለች።
📌 የአመቱ ወጣት የስራ ፈጣሪ ሙሉጌታ ውለታው
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ጅምር አብርሃም አሰፋ እና ፌኔሳ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ማህበራዊ ስራ ፈጣሪ ሚልኪ ማሞ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ስደተኛ ስራ ፈጣሪ አብዱልአዚዝ መሐሙድ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ አካል ጉደተኛ ስራ ፈጣሪ ዲንሰፋ ሚስባ
📌 የአመቱ ምርጥ ባንክ በሚቹ ዲጂታል የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
📌 ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ ኢቢሲ ሚዲያ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ቢሾፍቱ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

❤10👍1👎1
FastMereja
ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ አየር መንገድ ውስጥ ከፈተ!
#FastMereja I ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቀን ብዙ ሚልየን ህዝቦችን ይዞ በሚጓዘዉ እና የኢትዮጵያ አንዱ ብራንድ በሆነዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ዉስጥ ከፍቷል። በ8ኛዉ የጫካ ቡና መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ አየር…
ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ አየር መንገድ ውስጥ ከፈተ!
#FastMereja I ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቀን ብዙ ሚልየን ህዝቦችን ይዞ በሚጓዘዉ እና የኢትዮጵያ አንዱ ብራንድ በሆነዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ዉስጥ ከፍቷል።
በ8ኛዉ የጫካ ቡና መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሳምሶን አረጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የጫካ ቡና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ መከፈቱ የኤርፖርቱ ደንበኞች ፍላጎትንና ምቾትን እንደሚሰጥ ገልፀዉ በቅርቡ ቡናን ቆልቶ በማሸግ ወደ ተለያዩ ሀገራት ኤክስፖርት ማድረግ እንደሚጀምር የጫካ ቡና መስራች እና ባለቤት አቶ ብስራት በላይ ገልፀዋል።
ጫካ ቡና ወደፊት በተለያዩ የዉጭ ሀገራት የተለያዩ ብራንቾችን ለመክፈት እቅድ እንዳለዉ እና ዶሮ እርባታ ውስጥ በመግባት በቀን እስከ ሀምሳ ሺህ ዶሮና እንቁላሎች ለማምረት እቅድ እያወጣ መሆኑም ተነግሯል።
ጫካ ቡና ከተከፈተ 10 አመታት እንዳስቆጠረና ለ4000 ሰዎች የስራ እድል የከፈተ ድርጅት ነዉ።
#ቢዝነስ መረጃ

❤10
“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏
የራማው ልዑል፣ መጋቤ ሐዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡
ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል። መልአኩ ገብርኤል በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክን ሰው መሆን፣ ከእመቤታችን ከቅድሰት ድንግል ማርያም የመወለድ ታላቅ የምሥራች ይዞ የደረሰው መልአክ ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሀዲስ ኪዳን ስሙ ተደጋግሞ በመጠቀሱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚወልድ፣ የዘመናት ጸሎት ምላሽ እንዳገኘ የነገረው፣ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ ለሚያለቅሰው ለነቢዩ ዳንኤል ጸሎቱ መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡
አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡
ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

❤42👏3👎1
FastMereja
“የኔ ቆንጆ ኑሪ” በተሰኘ ነጠላ ዜማ የሚታወቀው አብርሃም አየለ “ዱዳ ሌብ” የተሰኘ ሙሉ አልበም ሊያወጣ ነው።
#FastMereja I አብርሃም አየለ "ዱዳ ሌብ" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሊለቀቅ መሆኑ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ ተገልጻል። ይህ "ዱዳሌብ" የተሰኘው አልበም በግጥም ግሩም ሀይሌ፣ የኔው አካሉ፣ ታመነ መኮንን፣ ሙሉቀን ዳዊት በዜማ የኔውአካሉ፣…
“የኔ ቆንጆ ኑሪ” በተሰኘ ነጠላ ዜማ የሚታወቀው አብርሃም አየለ “ዱዳ ሌብ” የተሰኘ ሙሉ አልበም ሊያወጣ ነው።
#FastMereja I አብርሃም አየለ “ዱዳ ሌብ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሊለቀቅ መሆኑ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ ተገልጻል።
ይህ “ዱዳሌብ” የተሰኘው አልበም በግጥም ግሩም ሀይሌ፣ የኔው አካሉ፣ ታመነ መኮንን፣ ሙሉቀን ዳዊት በዜማ የኔውአካሉ፣ አበበ ብርሃኔ፣ ታመነ መኮንን፣ ደረጄ በላይ፣ ሙሉቀን ዳዊት፣ ደስታ ከበደ ተሳትፈዋል፡፡
በቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ኤርሚያ ዳኜ ሰርተውታል፡፡
ድምጻዊ አብርሃም አየለ የኔ ቆንጆ ኑሪ፣ ያበጣው ይፈንዳ፣ ነይ እንዝናና፣ መሰደድ፣ ሰባት አርገው እና እንዲሁም በርከት ያሉ ነጠላ ዜማዎችን በመስራት ይታወቃል፡፡
“ዱዳሌብ” አልበም 15 Track ያሉት ሲሆን “ዱዳሌብ” አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 4 ዓመት እና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሆኖበታል።
አልበሙበሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊ አብርሃም አየለ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
አልበሙ ስለ ፍቅር፣ ስለ መለያየት፣ ስለ አብሮነት፣ስለሀገር ፣ ስለ ስደት እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የሚዳስስ ባህል ዘመናዊ አልበም መሆኑ ተነግሯል።
“ዱዳሌብ” የተሰኘው አልበም የፊታችን ማክሰኞ ህዳር 23/2018 ዓ.ም በአብርሃም አየለ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ይለቀቃል።
አልበሙን በሲዲ አሳትሞ የሚያከፋፍለው በኪነት ኢንተርቴይመንት መሆኑ ተገልጿል።
#ኪነ_ጥበብ መረጃ

😢7❤4
ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ፣ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ ነበረ!
ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ እነሆም በፍታ የለበሰውን፣ ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡
አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ውሃ በተሞላውና ወላፈኑ በማያስቀርበው ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ አዳናቸው። ቅድስት ኢየሉጣ ልጇ እንዳይገደል ለራሷም ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው ሥጋዊ ፍርሀት ቢያድርባትም የሦስት ዓመት ልጇ እናቴ ከእቶን እሳቱ የተነሳ አትፍሪ ሶስቱን ሕጻናት ያደነው ያድነናል እያለ በቀሚሷ ጎተታት፤ ወደ ጌታችን ሲጸልይላት ፍርሃቱ ርቆላታል፡፡ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም ከሰማይ ወርዶ የሚንተከተከውን ውሃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በቈላስያስ 1÷16 በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” በማለት ነገደ መላዕክትን ይዘረዝራቸዋል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ መላዕክት ማን ፈጠረን ብለው ግራ ሲጋቡ ቅዱስ ገብርኤል ፈጣሪ ነኝ ያለውን ሳጥናኤልን በመቃወም “አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” በማለት አረጋግቷቸዋል፡፡ በኢሳይያስ 14÷16ም በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ተጽፏል፡፡
“አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ዛሬም ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማውያ አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን አምነው ሲጠሩት ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡

❤34👎1
FastMereja
የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር ተመሰረተ።
#FastMereja I የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር ምስረታን አስመልክቶ የማህበሩ አባላት ዛሬ ሕዳር 19/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል። የማህበሩ ምስረታ ዋና አላማ ይዘት ፈጣሪዎች በቀረጻ ወቅት ከሚደርስባቸው…
የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር ተመሰረተ።
#FastMereja I የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር ምስረታን አስመልክቶ የማህበሩ አባላት ዛሬ ሕዳር 19/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል።
የማህበሩ ምስረታ ዋና አላማ ይዘት ፈጣሪዎች በቀረጻ ወቅት ከሚደርስባቸው ጫና በጋራ ሆኖ መከላከል እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከማህበረሰቡ ባህል እና ወግ ውጪ የሚሰሩ ሰዎች ለመከላከል እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም ያለ አግባብ የሚዘጉ አካውንቶችን ለማስከፈት እና አሉታዊ መልዕክት ያላቸውን ይዘት የሚሰሩ አካውንቶችን ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
ስምንት ወራት የፈጀው የማህበሩ ምስረታ በ19 አባላት እንደተመሰረተ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ህዳር 12/2018 ዓ.ም ተመዝግቧል።
የማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ ከ5ሺህ በላይ ተከታይ እና ከ18 አመት በላይ ከሆነ አባል መሆን ይችላል ተብሏል።

ዲፕሎማት ባዛር ተከፈተ!
#FastMereja I ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየዉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ላይ ትኩረቱን ያደረገ "ዲ ኔክስት ኢቭ የዲፕሎማት ባዛር" በአዲስ አበባ ዲሊኦፖል ሆቴል በዛሬዉ እለት ተከፍቷል። የባዛሩ ዓላማ የተለያዩ ተቋማትን ማቀራረብ እንዲሁም በሥራቸው…
ዲፕሎማት ባዛር ተከፈተ!
#FastMereja I ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየዉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ላይ ትኩረቱን ያደረገ “ዲ ኔክስት ኢቭ የዲፕሎማት ባዛር” በአዲስ አበባ ዲሊኦፖል ሆቴል በዛሬዉ እለት ተከፍቷል።
የባዛሩ ዓላማ የተለያዩ ተቋማትን ማቀራረብ እንዲሁም በሥራቸው ጠንካራ የሆኑ ጀግና ሴቶችን ማበረታታት መሆኑን ተነግሯል።
በዚህ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ዲፕሎማት ባዛር የተለያዩ የቆዳ ምርቶች ፣ ከከበሩ ማዕድን የተሰሩ ጌጣጌጦች ፣ የሀገር ባህል ልብሶች ፣ ከተፈጥሮ እፅዋት የተዘጋጁ የፀጉር ቅባቶችና የተለያዩ ግብአቶች ይገኛል።
ከዲሊኦፖል ሆቴል እና ከኔክስት ፋሽን ዲዛይን ጋር በጋራ በመሆን ዲ ኔክስት ኢቭ (De-Next-Ev) ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ እንደሚቆዩም ተገልፆ ከ1500 በላይ ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሏል።
ባዛሩ ላይ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ የኤምባሲ ተወካዮች፣ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ እንግዶች ይገኛሉ።
ይህን ዝግጅት በዓመት ሦስት ጊዜ ለማካሄድ ዝግጅት እንዳለቀ የተገለፀ ሲሆን በአዲስ ዓመት፣ ገና እና ፋሲካ ሰሞንን ምክንያት በማድረግ በየጊዜው ይካሄዳል ተብሏል።
#ኹነት

❤16
FastMereja
አማራ ባንክ ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ።
#FastMereja I የአማራ ባንክ የባለአክስዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ። በጉባኤው የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮሐንስ አያሌው (ፒኤችዲ) ባደረጉት…
አማራ ባንክ ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ።
#FastMereja I የአማራ ባንክ የባለአክስዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ።
በጉባኤው የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮሐንስ አያሌው (ፒኤችዲ) ባደረጉት ንግግር፤ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ85 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ መገኘቱ ነው የተገለጸው።
የባንኩ አጠቃላይ ገቢ በ29 በመቶ በማሳደግ ወደ 5.6 ቢሊዮን ብር መጨመር መቻሉንም ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች ይፋ አድርጓል።
የዲጂታል ባንክ አማራጮችን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት፣ ከ134 በላይ አዲስ የኤቲኤም ማሽኖች ወደ አገልግሎት ያስገባ ሲሆን፣ 105,404 QR ኮድ ዘርግቷል፤ 308 በካርድ ክፍያ መፈፀሚያ ፖስ ማሽኞችን ስራ ላይ ማዋሉና ከ112,000 በላይ የኤቲኤም ካርዶች ማሰራጨት መቻሉ፣ የዲጂታል ባንክ ስነ-ምህዳርን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገው እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
የባንኩ ደንበኞችን ቁጥርም ወደ 2.4 ሚሊዮን በማሳደግ ላይ መሆኑ በአገልግሎቱ መተማመን እና እርካታ እያደገ መምጣቱን አመልክቷል ተብሏል።
የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበ በበኩላቸው ቦርዱ ለዘላቂ እድገትና ልቀት ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በመስጠት እየሰራ መሆኑን ገለፀዋል፡፡
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያከናወናቸውን አስደናቂ እመርታዎች በተለዋዋጭና ፈታኝ በሆነ የማክሮ ኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ እያለፈ ያስመዘገባቸው ሲሆን፣ ይህን አይነቱን መልካም ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ባንኩ አሳይቷል ብለዋል፡፡

❤15👍4
ብዙዎች የሚመኙት ዓለማዊ ክብር ቢኖረውም ክርስቶስን መረጠ
ቴዎድሮስ የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው፣ በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ፡፡
የተወለደው በምድረ አንጾኪያ ሶርያ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ ነው፡፡ የሰማዕቱ ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው፡፡ እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች፡፡ ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር፡፡ እሱ ክርስትና ለማስነሳት፣ ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ፡፡ ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው፡፡ ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ ሲያለቅስ እግዚአብሔር ልመናውን ሰማ፡፡ ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ፣ ተጠመቀ፡፡
በየዕለቱም ለጾምና ጸሎት፣ ለምጽዋት ጋር ያበዛ ድንግልናውንም ለመጠበቅ ይተጋ ነበር፡፡ ገና በ20 ዓመቱ ኃያልና ብርቱ፣ በጸባዩም የሚወደድ ቅን፣ መልከ መልካምም ሆነ፡፡ ከተወዳጅነቱ የተነሳም ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት፡፡ አሁንም ድረስ "የሠራዊት አለቃ" በሚለው ስያሜ የሚጠራው ማር ቅዱስ ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም፡፡ ይልቁኑ ጠላትን በመማረክ ነበር የሚታወቀው፡፡ በአንድ ወቅት ከፋርስ ሰዎች ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል፡፡ በዚህ ውጊያ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው፡፡ ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" ሲላቸው ተሳለቁበት፡፡ ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል ካማተበ በኋላ በመካከላቸው እየተመላለሰ በመልአኩ ሰይፍ ፈጽሞ አጠፋቸው፡፡
ማር ቴዎድሮስ አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ሲገባ 24 ክንድ የሚረዝም ዘንዶ ሲመለክና የአንዲት ክርስቲያን ልጆችንም ለመስዋዕትነት ሲያቀርቧቸው ተመለከተ፡፡ በፈረሱ ላይም እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትቦ ዘንዶውን በጦር ገደለው፡፡ ከጊዜ በኋላ ስለ አባቱ ያለውን እውነታ ሲሰማ አፈላልጎ አገኘው፡፡ ሕይወቱ እስኪያልፍም አብሮት ቆይቶ ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ክርስቶስ ተክዶ፣ ጣዖት ቁሞ፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው፣ የክርስቲያኖች ደም ፈሶ፣ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ፡፡ ማር ቅዱስ ቴዎድሮስም በዚያች ሰዓት የክብር ልብሱን አውልቆ ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆሞ “እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ፣ ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" አለ፡፡ ንጉሡም በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ፡፡ ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት፡፡
ብዙዎች የሚመኙት ዓለማዊ ክብር ቢኖረውም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ስጋን የሚያስመርር የተለያየ ስቃይ ሲያደርሱበት በደስታ ተቀበለው፡፡ በእሳት ሲያቃጥሉትም በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው፡፡ ከበዛ ስቃዩም በእግዚአብሔር ኃይል ጸና፣ ታገሠም፡፡ በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ፣ መታሠቢያህን ያደረገ፣ ገድልህን ዜናህን የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ፣ በስምህም ረድኤት ይደረጋል" ብሎት ዐረገ፡፡ ወታደሮቹ አንገቱን ሲሰይፉትም የክብር አክሊል ተቀብሏል፡፡ ተጋድሎውን አይተው ያመኑ እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል፡፡
ዓለምንና ክብራቸውን ስለክርስቶስ ፍቅር የናቁ ገዳማውያንም የጸሎታቸው በረከት ለብዙዎች ይተርፋል፣ የነፍስ ምህረት የስጋ ድህነት ያሰጣልና ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውንም እናጽና፡፡

❤28👎1
ሞባይል ስልክ ቀምቶ ወንዝ ውስጥ የገባን ተያዘ
ተከሳሽ ካሊድ አህመድ የሞባይል ስልክ ቅምያ ወንጀል በመፈጸም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል ድልድይ አካባቢ ነው።
አንድ ግለሰብ በአካባቢው መንገድ ላይ እየተንቀሳቀሰ ሳለ ተጠርጣሪ ካሊድ አህመድ በፍጥነት ቀርቦ ሞባይሉን ቀምቶ ለመሰወር ሲሞክር በወቅቱ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል አባላት ዓይን ውስጥ ገብቷል።
የፖሊስ አባላቶቹም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረጉት ብርቱ ክትትል ተከሳሽ ወደ ውሀ መውረጃ ድልድይ ውስጥ ገብቶ ቢደበቅም ከአንድ ሠዓት በላይ በፈጀ ፍለጋ ሊያዝ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።
ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ የማስፋት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቆ ክስ ተመስርቶበታል ።
ህዝባዊ ፖሊስ ምን ጊዜም አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል ለህግ የበላይነት መስፈን እንደሚቆም ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡ ለወንጀል ፈጻሚዎች ምቹ በሆኑ አካባቢዎች በቂ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክቱን አስተላልፏል።

❤17👏1