ማርበርግ ቫይረስን አስመልክቶ ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የተላለፈ መልዕክት
እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ (ዘጸአት 15:26)።
ማርበርግ ቫይረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጅንካ ከተማ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፣ ይህ ወቅት በበሽታው ሕይወታቸውን ካጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች እና በቫይረሱ ተይዘው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተጎጂዎች ጎን ቆመን በአንድነት ድምፃችንን ወደእግዚአብሔር የምናሰማበት ጊዜ ነው።
ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ብንጮህ ይሰማናል፣ ይፈውሰናል፣ ጤናችንንም ይመልስልናል። እንደዚህ አይነት ፈታኝ ክስተቶች ለምን እንደሚከሰቱ ባናውቅም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ግን እንደማይለየን እናውቃለን። "እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ" (ዘጸአት 15:26) እንዳለ የፈውስ እጁ የታመሙትን ወገኖቻችንን ይዳስስልን፣ ያዘኑትን ያጽናናልን፣ ያረፉትን እረፍተ ነፍስ ይስጥልን፣ የዚህን ቫይረስ ስርጭትንም በምሕረቱ ያቁምልን። በጾምና በጸሎት ከመትጋት ባሻገር ማንኛውንም የጤና ባለሞያዎች እና የጤና ሥነ ምግባር የሚያዘውንና የሚፈቅደውን ሁሉ በማድረግ ለራሳችሁ: ለቤተሰቦቻችሁ: ለማኅበረሰባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የየድሻችሁን እንድትወጡ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት!
©EOTCTV

❤71🙏21👎1
"ከካንሰር ነጻ እንድሆን የረዳኝ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!!"
ዙፋን አዱኛ ትባላለች 3ኛ ደረጃ የደም ካንሰር እንደተያዘች ካወቀች በኋላ በ2ኛ ዙር ኬሞ ጸጉሯ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል እልህ አስጨራሹን ከደም ካንሰር ጋር መፋለሟን ቀጥላ በ4 ወር (ስምንት ዙር) ኬሞ በኋላ ጸጉሯ ማደግ ይጀምራል።
በመጨረሻም ከ6 ወር (12 ዙር ኬሞ) በኋላ ከካንሰር ነጻ መሆኗን ገልጻለች።
እግዚዓብሄር ይመስገን ብላለች።

❤79🙏44
በአስር አመት ህፃን ላይ እገታ እና በአሰቃቂ ሁኔታ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
የአቀቤ ሕግ የክስ ቻርጅ እንደሚያሳየው፣ ተከሳሽ ወርቅነህ አሰፋ ደርሰው የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ ቁጥር 539(1) (ሐ) እና 590/2//ሠ/ ስር የተደነገገውን ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የአስር አመት ታዳጊን በማገትና በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል።
ተከሳሽ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቻ ክፍለ ከተማ ዶይሳ ቀበሌ በተለምዶ ኒው ቪዥን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቀን 03/03/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ አስቀድሞ ማነኛውንም ህፃን ልጅ ጠልፎ በመያዝ ከተጠላፊው ቤተሰብ ገንዘብ በመውሰድ የራሴን ኑሮ እቀይራለሁ በሚል አደገኛ አስተሳሰብ ይሄንኑ አላማ ለመፈፀም እንዲያስችለው ፕላስቲክ ማሸጊያ እቤቱ አዘጋጅቶ ማኖሩን የአቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ያሳያል።
በእለቱ ተከሳሽ የሚያስተምርበት ት/ቤት ተማሪ የሆነውን የአስር አመት ህጻን ልጅ ሟች ናትናኤል ማይክል ከት/ቤት ሲመለስ መንገድ ላይ አስቁሞ እያዋራው ቆይቶ ተከራይቶ ወደ ሚኖርበት ግቢ ሟች እንዲመጣ ካደረገው በኋላ፤ ሟችን በቀኝ ግንባሩ ላይ በቦክስ በመምታት በአፍን ጫውና በአፉ ደም እንዲፈስ በማድረግ መሬት ላይ ከጣለው በኃላ ሟችን ተሸክሞ ወደ ሚኖርበት ቤት ክፍል ውስጥ በማስገባት የሟችን አፍ እና አፍንጫ ከማጅራቱ ጋር አጥብቆ በፕላስተር ማሸጊያ ካጠበቀው በኃላ የቤቱን በር በሟች ላይ ቆልፎ መውጣቱም በክስ ዝርዝሩ ተካቷል
ተከሳሽ ሟችን ይዞ ከአከባቢው ለመሰወር እንዲያመቸው የአከባቢውን ሁኔታ ሲቃኝ ሟች የታሸገበትን ፕላስተር ታግሎ በመፍታት ራሱን ለማትረፍ የድረሱልኝ ጩኼት በማሰማቱ ተከሳሽ ተመልሶ በመምጣት በድጋሚ አፍና አፍንጫውን አጥብቆ በማፈን ካሸገው በኃላ ሟችን በሕይወት እያለ ፎቶ ግራፍና ተንቀሳቃሽ ቪድዮ በስልኩ በመቅረጽ አመች ቦታ ሲደርስ ከሟች ቤተሰብ ጋር ገንዘብ ለመደራደር በማሰብ የሟችን አንገት በአንሶላ አንቆ ሕይወቱን እንዲያልፍ ካደረገ በኃላ አስክሬኑን የገደለበት ቤት መፀዳጃ ቤት ውስጥ እንደከተተውም በክስ ዝርዝሩ ተገልፆል።
ተከሳሽ አስክሬኑ እንዳይታይ የአንሶላ ጨርቅ ከላይ በመጣልና በመሰወር ከሚኖርበት ቤትና አከባቢ ሸሽቶ በቀን 05/03/2018 ዓ.ም በመኪና ተሳፍሮ ወደ ምዕራብ አባያ ወረዳ አቅጣጫ በማምለጥ ላይ እያለ ፉራ ቀበሌ ውስጥ በሕብረተሰቡ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ሊያዝ ችሏል።
በመሆኑም ተከሳሽ ሌላ ወንጀል ለመፈፀምና የፈፀመውን ወንጀል ለመደበቅ ጭካኔ በተሞላው መንገድ ተማሪውንና ራሱን መከላከል የማይችል ህፃን አስቦ በመግደል እና ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ልጅ በመጥለፍ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በዚህም መሰረት የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ክስ ፣ የሰውና የሰነድ የኤግዚቢት ማስረጃዎች በመሰማት ዐቃቤ ህግ በሁለቱም ክሶች ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ በተከሳሽ ላይ በማስረዳቱ ተከሳሽ እንዲከላከል ሲል ብይን ሰጥቷል።
በመሆኑም ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ሲል መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በቀን 18/3/2018 ዓ.ም በወዋለው ችሎት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።
ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን

👏27❤18😢4
ኦሪትን በሚገባ ተምሯልና የጌታችንን መምጣት በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡
አንድ ቀንም በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ "መሲሕ ቀረ" እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ቀርቦ "ተከተለኝ" አለው፡፡ ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት ሁሉን ትቶ ተከተለው፡፡ ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል ሰበከለት፡፡ የስሙ ትርጓሜ “መፍቀሬ አኃው ወይም ወንድሞችን የሚወድ" ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ባኮስን ያጠመቀው እርሱ ነው፡፡ ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር፡፡ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ በወቅቱ ከነበረው በርካታ ምሑራነ ኦሪትን ካፈራው ክቡር መምህር ገማልያል ኦሪትን ጠንቅቆ ተምሯል ሐዋርያው ቅዱስ ፊልዾስ፡፡ ለናትናኤል "ሙሴ በኦሪት፣ ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቼዋለሁ" አለው፡፡
ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል፡፡ ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልዾስም መልሶ “ታይ ዘንድ ና” አለው፤ ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ፡፡ ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 6÷5 በተለይ ደግሞ ጌታ የ5 ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡ እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ200 ዲናር እንጀራ ብንገዛም አይበቃንም" ብሎ ነበር፡፡ በኃላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ፡፡ በሐዋርያት አበው መካከልም ለጌታ እንደ "እንደራሴ" ሆኖ ያገለግል እንደ ነበር ተጠቅሷል፡፡ ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱንና እንድርያስን ያነጋግሩ ነበር፡፡ በዮሐ.14÷9 ደግሞ በፍጹም ንጽህናና የዋሕነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ ስለ አብ ሲነግራቸው ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ አስገራሚ ጥያቄ ጠይቋል፡፡
"እግዚኦ አርእየነሁ ለአብ ወየአክለነ" ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል፡፡ ጌታችን ግን “እኔን ያየ አብን አይቷል" ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩንም አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል፡፡ ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ፣ ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ፣ ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ፣ መንፈስ ቅዱስን ከ72 ቋንቋዎች ጋር ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ ወይም አፍሪካ ደርሳዋለች፡፡ ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው፡፡ በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ ክርስትና በረት ቀላቅሏል፡፡
ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌል እየሰበከ የክርስቶስን ብርሃን አብርቷል፡፡ ቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደሆነ ገድለ ሐዋርያት ቢገልጽም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ አይናገርም፡፡ በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ በስብከቱ ብዙዎችን አሳመነ፡፡ ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት፡፡ ከዚያም በእሳት ሊያቃጥሉት ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፡፡ በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ3 ቀናት በመጾም ምህላ አደረጉ፡፡ በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል፡፡ ራሳቸውን ለክርስቶስ ፍቅር ያስገዙ ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

❤32👎3
FastMereja
12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሊካሄድ ነዉ!
#FastMereja I 12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት መርሀ-ግብር ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግስት እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ። ድርጅቱ ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት መርኃ ግብር በመዘርጋት…
12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ሊካሄድ ነዉ!
#FastMereja I 12ኛዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት መርሀ-ግብር ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግስት እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።
ድርጅቱ ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት መርኃ ግብር በመዘርጋት በኢትዮጵያ የሚሰሩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ዓለም አቀፍ የተወዳዳሪነት ብቃት ማሳደግ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ይህም ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማስፋት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራት ገልፀዋል።
በዘንድሮዉ 12ኛው የጥራት ሽልማት 65 ተቋማት የጥራት ውድድር ለመወዳደር ተመዝግበዋል ከእነዚህ ውስጥ 63 ተቋማት እስከ ውድድሩ ፍፃሜ መጓዝ የቻሉ ሲሆን ባስመዘገቡት ውጤት የጥራት ተሸላሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
ከዚህ ውስጥ 34 ተቋማት በአምራች ዘርፍ፣ 12ቱ ለትርፍ የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪዎች፣ 10 በጤና ዘርፍ፣ አምስት በአገልግሎት ዘርፍ፣ ሶስት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እና አንድ ተቋም ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደተወዳደሩ ተገልጿል።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም በሚካሄደዉ የሽልማት መርሀ-ግብር የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኩባንያ ባለቤቶችና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት የሽልማት ስነ-ስርአቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በአገራችን የጥራትን ጽንስ ሐሳብ ለማስረጽ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎትን ለማበረታታት እና በዓለም አቀፍ ገበያ ያለዉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከአሥራ ስምንት ዓመታ በፊት የተቋቋመ ድርጅት ነው።

❤5
ናይጄሪያ እገታ የሚፈጽሙ ሰዎችን በሞት የሚቀጣ ሕግ ልታወጣ ነው
የናይጄሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እገታ የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት መጣል የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ላይ መነጋገር ጀመሩ።
የሴኔቱ አባላት እገታ ፈጽመው የሚገኙ ሰዎች የሽብር ተግባር ላይ እንደተሰማሩ ተቆጥሮ የሞት ቅጣት እንዲጣልባቸው ለማድረግ የአገሪቱን የጸረ ሽብር ሕግን ለማሻሻል መወያየት ጀምረዋል።
የናይጄሪያ የሴኔት አባላት የሕግ ማሻሻያው ላይ መነጋገር የጀመሩት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚፈጸም የጅምላ ጠለፋ እና እገታ እንዲሁም ደም አፋሳሽ ጥቃቶች እየጨመሩ በመጡበት ወቅት ነው።
ባለፉት ሳምንታት የታጠቁ ሰዎች ሁለት ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት ከፍተው ከ300 በላይ ተማሪዎችን አግተዋል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

❤18👍11🙏4
ለወንጀል መንስኤ ናቸው ያላቸውን ሺሻና የሺሻ ማስጨሻ ከ750 በላይ ቁሳቁሶችን በቃጠሎ ማስወገዱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
👏8❤6
FastMereja
የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቀቀ
#FastMereja I ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ሳምንት በኢትዮጵያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል። በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ከ2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር የጀመረው የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የ2018 "በጋራ እንገንባ"…
የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቀቀ
#FastMereja I ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ሳምንት በኢትዮጵያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።
በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ከ2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር የጀመረው የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የ2018 “በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ የቆየ ሲሆን የመዝጊያ ስነ ስርዓት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር የሆነት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በተገኙበት የስራ ፈጣሪዎችን በመሸለም ተጠናቋል።
የ2018 ሃካቶን ተወዳዳሪ አሸናፊዎች
ኤግሊፍት፣ ፋይዳ ሄልዝ እና ከእርሻ ወደ ጉርሻ የተሰኙ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ በመሆን ሽልማታቸውን ተቀብሏል።
በጥናት እና ምርምር ጽሁፍ አጸደ ተስፋዬ (ዶክተር) እና ቆንጂት ኃይሉ (ዶክተር) ተሸላሚ ሆኗል።
📌 የአመቱ ምርጥ ሴት ስራ ፈጣሪ በዓምላክ አለማየሁ ተሸላሚ ሆናለች።
📌 የአመቱ ወጣት የስራ ፈጣሪ ሙሉጌታ ውለታው
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ጅምር አብርሃም አሰፋ እና ፌኔሳ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ማህበራዊ ስራ ፈጣሪ ሚልኪ ማሞ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ስደተኛ ስራ ፈጣሪ አብዱልአዚዝ መሐሙድ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ አካል ጉደተኛ ስራ ፈጣሪ ዲንሰፋ ሚስባ
📌 የአመቱ ምርጥ ባንክ በሚቹ ዲጂታል የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
📌 ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ ኢቢሲ ሚዲያ
📌 የአመቱ ተስፋ ሰጪ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ቢሾፍቱ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

❤10👍1👎1
FastMereja
ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ አየር መንገድ ውስጥ ከፈተ!
#FastMereja I ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቀን ብዙ ሚልየን ህዝቦችን ይዞ በሚጓዘዉ እና የኢትዮጵያ አንዱ ብራንድ በሆነዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ዉስጥ ከፍቷል። በ8ኛዉ የጫካ ቡና መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ አየር…
ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ አየር መንገድ ውስጥ ከፈተ!
#FastMereja I ጫካ ቡና 8ኛ ቅርንጫፉን በቀን ብዙ ሚልየን ህዝቦችን ይዞ በሚጓዘዉ እና የኢትዮጵያ አንዱ ብራንድ በሆነዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ዉስጥ ከፍቷል።
በ8ኛዉ የጫካ ቡና መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሳምሶን አረጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የጫካ ቡና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ መከፈቱ የኤርፖርቱ ደንበኞች ፍላጎትንና ምቾትን እንደሚሰጥ ገልፀዉ በቅርቡ ቡናን ቆልቶ በማሸግ ወደ ተለያዩ ሀገራት ኤክስፖርት ማድረግ እንደሚጀምር የጫካ ቡና መስራች እና ባለቤት አቶ ብስራት በላይ ገልፀዋል።
ጫካ ቡና ወደፊት በተለያዩ የዉጭ ሀገራት የተለያዩ ብራንቾችን ለመክፈት እቅድ እንዳለዉ እና ዶሮ እርባታ ውስጥ በመግባት በቀን እስከ ሀምሳ ሺህ ዶሮና እንቁላሎች ለማምረት እቅድ እያወጣ መሆኑም ተነግሯል።
ጫካ ቡና ከተከፈተ 10 አመታት እንዳስቆጠረና ለ4000 ሰዎች የስራ እድል የከፈተ ድርጅት ነዉ።
#ቢዝነስ መረጃ

❤10
“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏
የራማው ልዑል፣ መጋቤ ሐዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡
ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል። መልአኩ ገብርኤል በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክን ሰው መሆን፣ ከእመቤታችን ከቅድሰት ድንግል ማርያም የመወለድ ታላቅ የምሥራች ይዞ የደረሰው መልአክ ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሀዲስ ኪዳን ስሙ ተደጋግሞ በመጠቀሱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚወልድ፣ የዘመናት ጸሎት ምላሽ እንዳገኘ የነገረው፣ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ ለሚያለቅሰው ለነቢዩ ዳንኤል ጸሎቱ መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡
አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡
ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

❤42👏3👎1