የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
#FastMereja I አሪፍ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ከኢትዮጵያ ፊንቴክ ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ፎረም (ETIFT) ጋር በመተባበር በዲኦሎፖል ሆቴል የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ አካሂዷል። የማይክሮ ፋይናንስ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለድርሻ አካላት የተገኙበት ጉባኤ ትኩረቱን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና የገጠር ዜጎችን የሚያገለግሉትን የኢትዮጵያን ወሳኝ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (MFIs) ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ማዋሃድ እንደሆነ ተገልጿል።
ተቋሟቱን ከዲጂታል ጋር የማስተሳሰር ስራው በአሪፍፔይ እየተሰራ ሲሆን ከስራዎቹ መካከል የአሪፋይ ኤምኤፍአይ ስዊች (MFI Switch) አንዱ መሆኑ ተነግሯክ። ይህ አዲስ፣ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሠረተ ልማት ሁሉንም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያለምንም እንከን ከብሔራዊ የክፍያ አውታረ መረብ ጋር ለማገናኘት የተነደፈ ነው።
የአሪፍፔይ ዲጂታል ዋሌት የማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ብድር እንዲቀበሉ እና በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።
በጉባኤው ላይ እነዚህ እና ሌሎች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በጋራ ለማልማት Arifpay እና EtIFT የአጋርነት ስምምነት ፈጽሟል።
አሪፍፔይ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሰራተኛ ይዞ በቀን እስከ 680 ሚሊዮን ብር በአሪፍፔይ በኩል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝበት ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

❤16👏1
በሐዋሳ የተፈጠረው ምንድነው?
ከቀኑ 08:00 ስዓት ላይ በተለምዶ ቦሌ በሚባል ሰፈር.. ሁለት ታርጋ የለሌዉን አፓች ሞተር የያዙ ሌቦች.. ከአንዲት Lifan ሞተር እየነዱ ከቦሌ መብራት ወደ ሻፌታ ባንክ እየሄዱ ባሉ #እናት በተጠራራ ፀሀይ ላይ ቦርሳዋን ነጥቆ.. እሷንም መንገድ ላይ ከነሞተር ሳይክሏ ጥሎዋት ይሮጣሉ። (እናትየዋ በጣም የተጎዳች ሲሆን /እጃ ላይ ከፍተኛ ጉዳት) ይደርሳል።
ህዝቡም መኪና ያለዉ በመኪናዉ.. ሞተር ያለዉ በሞተር ሳይ በማበረር.. በሻፌታ ባንክ ጎን ባለዉ ኮብልስቶን ላይ ይያዛሉ።
ህዝቡም ሌቦችን በመያዝ ያደረገዉ ርብርብ በጣም ከፍተኛ ነዉ። የሲዳማ ፖሊስም ቶሎ ቦታዉ ላይ በመድረስ እነዚህን ለእናት የማይራራ ድንጋይ ልብ ያላቸዉን ሌቦችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።
Via: Dige Wagiso

❤99👍22👏8🙏2
“ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ”…ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 88÷3
“ኪዳን” የሚባለው ቃል “ቃል” ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ “ኪዳን” ቃሉ “ተካየደ” ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ "ምሕረት” የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡
ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ” እንዳለ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላተ አንዱ ነው፡፡
እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብላ ስትጸልይ፣ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቁ ጌታችንም ከእልፍ አእላፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ላንቺ ይሁን እናቴ ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት። እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን፣ ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡
ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡ በቅዱሳን ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡ አልፎ ተርፎም ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው፡፡ ጌታችን በዮሐ.21÷39 እና 2ኛ ጴጥ.1÷14 ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟማት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ በሐዋ.20÷25 ለቅዱስ ጳዉሎስ ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡
ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ ስለምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል፤ ማለትም ትጠራበታለች፤ ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ አድርገው ላወቁትና ላላወቁት ጉድለቶቻቸው ሁሉ ስሟን ለሚጠሩ፣ ቃል ኪዳንን ለመቀበል ያበቃት ለሰው ልጆች ነጻነት ልጇ ለሰጠው ፍፁም መድኃኒት ምክንያት የሆነችበት ጸጋዋ ሁሉ በሥላሴ ፊት ይታሰብላቸዋል፡፡
ገዳማውያን በዚህ ቃል ኪዳኗ ታድናቸውው ዘንድ ቀንና ሌሊት በውዳሴዋም በቅዳሴዋም ቅድስት ሆይ ለምኝልን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጸናን ከበረክታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444

❤47👍4👎1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰጠውን የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰጠ
#FastMereja I ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በልዩ መልኩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ማግኘት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶክተር ) መናገራቸው ይታወሳል ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተሩ ባስቀመጡት መመሪያ መሰረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰቷል ።

❤10👎3
የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የመጀመሪያ ዙር ተሽከርካሪዎችን ተረከቡ!
#FastMereja I ጤግሮስ ትሬዲንግ ከኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በ20 ፐርሰንት ቁጠባ በኦሮሚያ ክልል ላሉ ወጣቶች ከቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖችን በማስመጣት ዛሬ የመጀመሪያ ዙር የቁልፍ ርክክብ ስነ ስርአት ተከናውኗል።
በመጀመሪያ ዙር 154 ተሽከርካሪዎችን ለማስረከብ የታቀደ ሲሆን በዛሬው እለት 79 ተሽከርካሪዎች የቁልፍ ርክክብ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከናውኗል።
ጤግሮስ ትሬዲንግ ከኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በክልሉ ያሉ ወጣቶች ተጠቃሚ ከሚሆኑበት ፕሮጀክቶች መካከል ይህ አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
ጤግሮስ ትሬዲንግ በአሁኑ ወቅት እየሰራቸው ካሉት ስራዎች መካከል ከኤዋይቢ መኪና ከሚባለው ካምፓኒ ከአስር አመት ውል በመፈራረም አብሮ እየሰራ ሲሆን ሁለተኛ ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ብርሃን ገበያ የተሰኘ ፕሮጀክት አለው ሶስተኛ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ ምንም አይነት ቁጠባ ሳይቆጥቡ የቤት ኪራይ ብቻ እየከፈሉ የቤት ባለቤት የሚሆንበት ፕሮጀክቶችን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

❤34
ገና በ15 ዓመቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ትልቅ ጥበብ ወይም ፍልስፍና በጥልቀት ተምሮ ተመልሷል፡፡
በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ፣ በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑም እንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ድረስ ለመናፍቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው፡፡ ነገዱ ከሶርያ ሲሆን፣ በ347 ዓ.ም በእስክንድርያ የተወለደው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ አትናስያ በትምሕርትና በጥበብ አሳድገውታል፡፡
ገና በ16 ዓመቱ ሃብት፣ ንብረት፣ ውበት፣ ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፡፡ ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ ሲኖርም ወደእርሱ የመጡት ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን፣ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ሰጥተውት ሄዱ፡፡
ከዚህች ዕለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ፡፡ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጓሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ገና በለጋ እድሜውና በዲቁና ማዕረግ ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት፣ ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ፣ የጻፋቸው ድርሳናት፣ መልዕክታትና ትርጓሜዎች 10 ሺህ ናቸው:: በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፡፡ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር ከጣዕሙ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡ ኋላም የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ መልዐከ ሞትን ገስፆ በሥልጣነ ቃሉ ለ10 ዓመት ያቆመው ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር ባገባበት ወቅት በጉባኤ መካከል ስለ ቅደስት ድንግል ማርያም በማቴ.1÷25 “አረጋዊው ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም መባሉ ስለ ምን ነው?” ጠየቀው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ሲመልስም “ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች፡፡ ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል፡፡ እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር፡፡ እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?’ እያለ ይጨነቅ ነበር፡፡ ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና፡፡ አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም፡፡ አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ፣ ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው” እያለ ሲተረጉምለት በዚያ የነበረች የእመቤታችን ስዕለ አድኅኖ “አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!” ስትል ተናገረች፡፡ እርሱም ባጭር ታጥቆ “እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . .” ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና አደረሰ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም፡፡ የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ የአንዲት ደሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ ስላወገዛት፣ ከተወገዙ መናፍቃን ጋር መክራ ሁለት ጊዜ አጋዘችው፡፡ በተሰደደበት ሀገርም ፍሬ አፍርቶ አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት፣ በ60 ዓመቱ ሲያርፍም ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ፡፡ ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን ኅዳር 17 ሥጋው ፈልሶ ቁስጥንጥንያ ሲደርስ ህዝቡ ከናፍቆት የተነሳ በታላቅ ዝማሬና እንባ ተቀብሎታል፡፡ ቅዱሱም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል፡፡ ምሳሌነቱ ሁሌም ሕያው ነውና ገዳማውያን እንደርሱ ዓለምን ንቀው ይመንነናሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

❤70👎5👍3
ማርበርግ ቫይረስን አስመልክቶ ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የተላለፈ መልዕክት
እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ (ዘጸአት 15:26)።
ማርበርግ ቫይረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጅንካ ከተማ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፣ ይህ ወቅት በበሽታው ሕይወታቸውን ካጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች እና በቫይረሱ ተይዘው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተጎጂዎች ጎን ቆመን በአንድነት ድምፃችንን ወደእግዚአብሔር የምናሰማበት ጊዜ ነው።
ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ብንጮህ ይሰማናል፣ ይፈውሰናል፣ ጤናችንንም ይመልስልናል። እንደዚህ አይነት ፈታኝ ክስተቶች ለምን እንደሚከሰቱ ባናውቅም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ግን እንደማይለየን እናውቃለን። "እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ" (ዘጸአት 15:26) እንዳለ የፈውስ እጁ የታመሙትን ወገኖቻችንን ይዳስስልን፣ ያዘኑትን ያጽናናልን፣ ያረፉትን እረፍተ ነፍስ ይስጥልን፣ የዚህን ቫይረስ ስርጭትንም በምሕረቱ ያቁምልን። በጾምና በጸሎት ከመትጋት ባሻገር ማንኛውንም የጤና ባለሞያዎች እና የጤና ሥነ ምግባር የሚያዘውንና የሚፈቅደውን ሁሉ በማድረግ ለራሳችሁ: ለቤተሰቦቻችሁ: ለማኅበረሰባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የየድሻችሁን እንድትወጡ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት!
©EOTCTV

❤71🙏21👎1
"ከካንሰር ነጻ እንድሆን የረዳኝ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!!"
ዙፋን አዱኛ ትባላለች 3ኛ ደረጃ የደም ካንሰር እንደተያዘች ካወቀች በኋላ በ2ኛ ዙር ኬሞ ጸጉሯ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል እልህ አስጨራሹን ከደም ካንሰር ጋር መፋለሟን ቀጥላ በ4 ወር (ስምንት ዙር) ኬሞ በኋላ ጸጉሯ ማደግ ይጀምራል።
በመጨረሻም ከ6 ወር (12 ዙር ኬሞ) በኋላ ከካንሰር ነጻ መሆኗን ገልጻለች።
እግዚዓብሄር ይመስገን ብላለች።

❤79🙏44
በአስር አመት ህፃን ላይ እገታ እና በአሰቃቂ ሁኔታ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
የአቀቤ ሕግ የክስ ቻርጅ እንደሚያሳየው፣ ተከሳሽ ወርቅነህ አሰፋ ደርሰው የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ ቁጥር 539(1) (ሐ) እና 590/2//ሠ/ ስር የተደነገገውን ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የአስር አመት ታዳጊን በማገትና በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል።
ተከሳሽ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቻ ክፍለ ከተማ ዶይሳ ቀበሌ በተለምዶ ኒው ቪዥን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቀን 03/03/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ አስቀድሞ ማነኛውንም ህፃን ልጅ ጠልፎ በመያዝ ከተጠላፊው ቤተሰብ ገንዘብ በመውሰድ የራሴን ኑሮ እቀይራለሁ በሚል አደገኛ አስተሳሰብ ይሄንኑ አላማ ለመፈፀም እንዲያስችለው ፕላስቲክ ማሸጊያ እቤቱ አዘጋጅቶ ማኖሩን የአቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ያሳያል።
በእለቱ ተከሳሽ የሚያስተምርበት ት/ቤት ተማሪ የሆነውን የአስር አመት ህጻን ልጅ ሟች ናትናኤል ማይክል ከት/ቤት ሲመለስ መንገድ ላይ አስቁሞ እያዋራው ቆይቶ ተከራይቶ ወደ ሚኖርበት ግቢ ሟች እንዲመጣ ካደረገው በኋላ፤ ሟችን በቀኝ ግንባሩ ላይ በቦክስ በመምታት በአፍን ጫውና በአፉ ደም እንዲፈስ በማድረግ መሬት ላይ ከጣለው በኃላ ሟችን ተሸክሞ ወደ ሚኖርበት ቤት ክፍል ውስጥ በማስገባት የሟችን አፍ እና አፍንጫ ከማጅራቱ ጋር አጥብቆ በፕላስተር ማሸጊያ ካጠበቀው በኃላ የቤቱን በር በሟች ላይ ቆልፎ መውጣቱም በክስ ዝርዝሩ ተካቷል
ተከሳሽ ሟችን ይዞ ከአከባቢው ለመሰወር እንዲያመቸው የአከባቢውን ሁኔታ ሲቃኝ ሟች የታሸገበትን ፕላስተር ታግሎ በመፍታት ራሱን ለማትረፍ የድረሱልኝ ጩኼት በማሰማቱ ተከሳሽ ተመልሶ በመምጣት በድጋሚ አፍና አፍንጫውን አጥብቆ በማፈን ካሸገው በኃላ ሟችን በሕይወት እያለ ፎቶ ግራፍና ተንቀሳቃሽ ቪድዮ በስልኩ በመቅረጽ አመች ቦታ ሲደርስ ከሟች ቤተሰብ ጋር ገንዘብ ለመደራደር በማሰብ የሟችን አንገት በአንሶላ አንቆ ሕይወቱን እንዲያልፍ ካደረገ በኃላ አስክሬኑን የገደለበት ቤት መፀዳጃ ቤት ውስጥ እንደከተተውም በክስ ዝርዝሩ ተገልፆል።
ተከሳሽ አስክሬኑ እንዳይታይ የአንሶላ ጨርቅ ከላይ በመጣልና በመሰወር ከሚኖርበት ቤትና አከባቢ ሸሽቶ በቀን 05/03/2018 ዓ.ም በመኪና ተሳፍሮ ወደ ምዕራብ አባያ ወረዳ አቅጣጫ በማምለጥ ላይ እያለ ፉራ ቀበሌ ውስጥ በሕብረተሰቡ እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ሊያዝ ችሏል።
በመሆኑም ተከሳሽ ሌላ ወንጀል ለመፈፀምና የፈፀመውን ወንጀል ለመደበቅ ጭካኔ በተሞላው መንገድ ተማሪውንና ራሱን መከላከል የማይችል ህፃን አስቦ በመግደል እና ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ልጅ በመጥለፍ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በዚህም መሰረት የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ክስ ፣ የሰውና የሰነድ የኤግዚቢት ማስረጃዎች በመሰማት ዐቃቤ ህግ በሁለቱም ክሶች ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ በተከሳሽ ላይ በማስረዳቱ ተከሳሽ እንዲከላከል ሲል ብይን ሰጥቷል።
በመሆኑም ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ሲል መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በቀን 18/3/2018 ዓ.ም በወዋለው ችሎት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።
ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን

👏27❤18😢4