በኮሪደሩ ላይ ልብስ ያሰጡት ተቀጡ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በትላንትናው ዕለት በቀን 14/03/2018 ዓ.ም በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱ አስታወቀ።
ድርጊቱ የከተማው ገፅታ የሚያበላሽና ልማቱ ለታለመለት አላማ እንዳይውል የማውል የሚያደርግ በመሆኑ ጥፋቱን ፈፅመው የተገኙ የኮረደሩ ልማቱ መዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ በማድረግ ጉዳዩ እስኪወሰን ካፌው መታሸጉ ተገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤22😢6🙏2
በቡድን በመደራጀት በመዲናዋ በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል የሚፈፅሙ 36 ግለሰቦች እና 5 ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል፡፡
የምርመራ መነሻ የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኤሚግሬሽን አካባቢ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ነው።
የግል ተበዳይ ኢየሩስ ግርማ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ማ.ኢ 01058 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ይዘው በመንቀሳቀስ የት ነሽ? በማለት ካሳፈሯት በኋላ ሞባይል ስልኳን ለመቀማት ሲታገሉ በአካባቢው ላይ በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ዕይታ ውስጥ ይወድቃሉ፤ በፖሊስ ዕይታ ውስጥ መውደቃቸውን የተረዱት ተጠርጣሪዎች የግል ተበዳይን ገፍትረው በመጣል ለማምለጥ ቢሞክሩም ተጠርጣሪዎቹን እስከ መጨረሻው በመከታተል አራቱንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች መነሻ በማድረግ በተደረገ ሰፊ ምርመራ የማስፋት ተግባር የወንጀል ድርጊቱን የሚመራ እና የሚያስተባበር ቡድን እንዳለ ይደርስበታል፡፡ የወንጀለኛ ቡድኑን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ክትትልም በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ ስምሪት የሚሰጡ 11 ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡
ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ስምሪት በሚሰጠው ቡድን ላይ በተከናወነ ሌላ ጠንካራ ምርመራን የማስፋት ተግባርም በቡድኑ ስምሪት የተሰጣቸውን 8 ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B አ/አ 55902 ሚኒባስ ተሽከርካሪ በመጠቀም የሿሿ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኮካ እየተባለ በሚጠራው አደባባይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
ፖሊስ ምርመራውን በማጠናከር ባደረገው ብርቱ ክትትል ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ስምሪት የተሰጣቸው በኮድ 3 አ/አ 96708 አራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በኮድ3 ኦሮ A02639 ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 13 አባላት ያሉት ሁለት ቡድን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘ በኮድ 3B አ/አ 47364 በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ እየተዟዟሩ ከወንጀል ፈፃሚዎች የተሰረቀ እቃ ሲገዙ የነበሩ ሁለት የሌባ ተቀባዮች ተይዘው በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ እና ፍተሻ ከግለሰቦቹ መኖሪያ ቤት 30ሺ 700 ብር፣ 1 ላፕቶፕ፣ 1 ታብሌት፣ 11 ዘመናዊ ስልኮች፣ ተሰርቀው ቀፎዎቹ የተሸጡበት 188 የስልክ ከቨሮች በኤግዚቢትነት መያዙን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቆ በአጠቃላይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ 36 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንም ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።
በተለይም የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሚፈፀሙ የሿሿ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን እንደሚገባው ያሳሰበው ፖሊስ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል።
በወንጀሉ የምርመራ ሂደት አንዳንድ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ሆን ብለው ተሽከርካሪዎቻቸውን ለወንጀል ፈጻሚዎች እንደሚያከራዩ በምርመራ የተደረሰበት ሲሆን በግለሰቦቹ ላይ የሚያስከተለው የህግ ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ፊት የተሽከርካሪያቸውን አይነትና የባለ ንብረቶቹን ስም ዝርዝር ለህዝብ ግልፅ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች ጋር በተያያዘ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ግለሰብ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ማመልከት እና መረጃ መስጠት እንደሚችልም ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

❤68👍19👏7👎6🙏3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባታዩት ይመረጣል‼️‼️
ዘግናኝ በሀገራችን የተከሰተ የጭካኔ ተግባር ነው።
መወገዝ አለበት!!
ዘግናኝ በሀገራችን የተከሰተ የጭካኔ ተግባር ነው።
መወገዝ አለበት!!
😢1.1K👎88❤58👍23👏8
FastMereja
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር በኢትዮጵያ በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን በዛሬዉ እለት ህዳር 16/2018ዓ.ም አስታዉቋል። ድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሰየም የወሰነው ፕሮግራሞቹን እያሰፋ ባለበትና የአገር ውስጥ ሃብት...
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር በኢትዮጵያ በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን በዛሬዉ እለት ህዳር 16/2018ዓ.ም አስታዉቋል።
ድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሰየም የወሰነው ፕሮግራሞቹን እያሰፋ ባለበትና የአገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ ጥረቱን እያጠናከረ ባለበት ወቅት መሆኑ ተገልፆ ይህም ብዙ ማህበረሰቦችን ለመድረስ ሰፊ ተሳትፎን ለማነሳሳት እና ዘላቂነት ያለው ድጋፍን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል ።
አርቲስቱ የተመረጠውም በአቋሙ፣ ለረጅም ጊዜ በዘለቀው መልካም ስሙ፣ ለህጻናት ደህንነት ባለው ቁርጠኝነት እና ከድርጅቱ ተልዕኮ ጋር የሚጣጣም ስብእና ያለው ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል።
የብራንድ አምባሳደሩ ሚናም ድርጅታዊ አጋርነትን ለማስፋት የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረቶችን ለማጎልበት እና በቂ የወላጅ እንከብካቤ ሳያገኙ የሚያድጉ ህጻናት እና ወጣቶች የበለጠ የህዝብ ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
አርቲስት አለማየሁ ሹመቱን አስመልከቶም “የብራንድ አምባሳደር መሆን ከማዕረግ በላይ የሆነ እና ትክክለኛ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያበቃ ትልቅ ሃላፊነት እና እድል የተሰጠኝ ባገኘሁት መድረክ ሁሉ ድምፄን ለማሰማትና የድርጅቱን ተልዕኮ ለማጉላት ሙሉ ቁርጠኝነቴን እገልፃለዉም አሳያለዉም ብሏል።
የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሣህለማርያም አበበ እንደ ገለጹት “ይህ አጋርነት የህጻናትን እና የወጣቶችን ድምጽ ወደ ፊት የማምጣት የህብረተሰቡን ተሳትፎ የማነሳሳት እና ከለጋሾች እና ከተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የሚደረገውን ድጋፍ የማጠናከር አላማን ያገናዘበ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የአርቲስቱ የአምባሳደርነት አገልግሎትም እንደሁኔታው ሊራዘም የሚችል ሆኖ ከዛሬ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ይቀጥላልም ተብሏል፡፡

❤27👍1
ለእርሷ የተሰጣት ኪዳን፣ ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል
“ኪዳን” የሚባለው ቃል “ቃል” ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ “ኪዳን” ቃሉ “ተካየደ” ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ "ምሕረት” የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ” እንዳለ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላተ አንዱ ነው፡፡
እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብላ ስትጸልይ፣ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቁ ጌታችንም ከእልፍ አእላፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ላንቺ ይሁን እናቴ ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት። እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን፣ ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡
ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡ በቅዱሳን በቅዱሳን ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡ አልፎ ተርፎም ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው፡፡ ጌታችን በዮሐ.21÷39 እና 2ኛ ጴጥ.1÷14 ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟማት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ በሐዋ.20÷25 ለቅዱስ ጳዉሎስ ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡
ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ ስለምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል፤ ማለትም ትጠራበታለች፤ ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ አድርገው ላወቁትና ላላወቁት ጉድለቶቻቸው ሁሉ ስሟን ለሚጠሩ፣ ቃል ኪዳንን ለመቀበል ያበቃት ለሰው ልጆች ነጻነት ልጇ ለሰጠው ፍፁም መድኃኒት ምክንያት የሆነችበት ጸጋዋ ሁሉ በሥላሴ ፊት ይታሰብላቸዋል፡፡ ገዳማውያን በዚህ ቃል ኪዳኗ ታድናቸውው ዘንድ ቀንና ሌሊት በውዳሴዋም በቅዳሴዋም ቅድስት ሆይ ለምኝልን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጸናን ከበረክታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444

❤60👎6
FastMereja
9ኛው ኦዳ አዋርድ በሙዚቃ ዘርፍ ብቻ እንደሚሸልም ተነገረ
#FastMereja I በኪነጥበቡ ዘርፍ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩን የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እየሸለመ እና እያበረታታ የዘለቀው ኦዳ አዋርድ ዘንድሮም 9ኛው የሽልማት እና የእውቅና የመስጠት ሥነ ሥርዓት የፊታችን ሕዳር 30 ቀን…
9ኛው ኦዳ አዋርድ በሙዚቃ ዘርፍ ብቻ እንደሚሸልም ተነገረ
#FastMereja I በኪነጥበቡ ዘርፍ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩን የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እየሸለመ እና እያበረታታ የዘለቀው ኦዳ አዋርድ ዘንድሮም 9ኛው የሽልማት እና የእውቅና የመስጠት ሥነ ሥርዓት የፊታችን ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይከናወናል፡፡
ኦዳ አዋርድ በሻቱ መልቲ ሚዲያ ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከባህልና ስፖርት ሚንስቴር ኢንዲሁም ከቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በጥምረት የሚዘጋጅ ይሆናል።
ኦዳ አዋርድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው የሽልማት መርሃግብር ከቀደምት ዓመት ውድድሮች ለየት ባለ መልኩ በመቅረብ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በሙዚቃው ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር የሽልማት ስነስርዓቱን እንደሚያከናውን ተነግሯል።
በመሆኑም በሙዚቃው ዘርፍ ብቻ ከሀገር ውስጥ 30 እጩዎችን በ6 የሽልማት ዘርፎች ለምርጫ ያቀረበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እጩዎች በተጨማሪ ከ12 አፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ እጩዎችን ለህዝቡ ይፋ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም እጩዎች ለሽልማት የሚበቁት ሙሉ በሙሉ በህዝብ ምርጫ መሆኑ ተገልጿል።
ከአፍሪካ ሃገራት በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ በ”AFRICAN SUPER STAR” ዘርፍ ላይ ተሸላሚ ለመሆን የሚሳተፉት 12 የአፍሪካ ሃገራት፦
ሩዋንዳ፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ማዳጋስካር፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሼልስ፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ ናቸው።
በተጨማሪም 9ኛው ኦዳ አዋርድ ከሃገር ውስጥ የሙዚቃ ስራዎች ለሽልማት አጩዎችን የሚያቀርብበት ስድስት ዘርፎች ሲኖሩት እነሱም፡
📌 የህይወት ዘመን ተሸላሚ
📌 የአመቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት
📌 የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ
📌 የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት
📌 የአመቱ ምርጥ ወንድ ድምፃዊ
📌 የአመቱ ምርጥ ምርጥ ሀገርኛ ዘፋኝ ናቸው
የ2018 ዓ.ም. እጩዎቹ ተሸላሚ የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ከአድናቂዎቻቸው በሚያገኙት ድምጽ ሲሆን ድምጽ የሚሰጥበት ሂደትም ለዚሁ ዝግጅት በሚያገለግለው የኦዳ አዋርድ ድረ ገጽ oddaaward.com መሆኑ ተገልጿል።

❤20👍2👏1
የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
#FastMereja I አሪፍ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ከኢትዮጵያ ፊንቴክ ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ፎረም (ETIFT) ጋር በመተባበር በዲኦሎፖል ሆቴል የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ አካሂዷል። የማይክሮ ፋይናንስ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለድርሻ አካላት የተገኙበት ጉባኤ ትኩረቱን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና የገጠር ዜጎችን የሚያገለግሉትን የኢትዮጵያን ወሳኝ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (MFIs) ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ማዋሃድ እንደሆነ ተገልጿል።
ተቋሟቱን ከዲጂታል ጋር የማስተሳሰር ስራው በአሪፍፔይ እየተሰራ ሲሆን ከስራዎቹ መካከል የአሪፋይ ኤምኤፍአይ ስዊች (MFI Switch) አንዱ መሆኑ ተነግሯክ። ይህ አዲስ፣ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሠረተ ልማት ሁሉንም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያለምንም እንከን ከብሔራዊ የክፍያ አውታረ መረብ ጋር ለማገናኘት የተነደፈ ነው።
የአሪፍፔይ ዲጂታል ዋሌት የማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ብድር እንዲቀበሉ እና በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።
በጉባኤው ላይ እነዚህ እና ሌሎች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በጋራ ለማልማት Arifpay እና EtIFT የአጋርነት ስምምነት ፈጽሟል።
አሪፍፔይ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሰራተኛ ይዞ በቀን እስከ 680 ሚሊዮን ብር በአሪፍፔይ በኩል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝበት ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

❤16👏1
በሐዋሳ የተፈጠረው ምንድነው?
ከቀኑ 08:00 ስዓት ላይ በተለምዶ ቦሌ በሚባል ሰፈር.. ሁለት ታርጋ የለሌዉን አፓች ሞተር የያዙ ሌቦች.. ከአንዲት Lifan ሞተር እየነዱ ከቦሌ መብራት ወደ ሻፌታ ባንክ እየሄዱ ባሉ #እናት በተጠራራ ፀሀይ ላይ ቦርሳዋን ነጥቆ.. እሷንም መንገድ ላይ ከነሞተር ሳይክሏ ጥሎዋት ይሮጣሉ። (እናትየዋ በጣም የተጎዳች ሲሆን /እጃ ላይ ከፍተኛ ጉዳት) ይደርሳል።
ህዝቡም መኪና ያለዉ በመኪናዉ.. ሞተር ያለዉ በሞተር ሳይ በማበረር.. በሻፌታ ባንክ ጎን ባለዉ ኮብልስቶን ላይ ይያዛሉ።
ህዝቡም ሌቦችን በመያዝ ያደረገዉ ርብርብ በጣም ከፍተኛ ነዉ። የሲዳማ ፖሊስም ቶሎ ቦታዉ ላይ በመድረስ እነዚህን ለእናት የማይራራ ድንጋይ ልብ ያላቸዉን ሌቦችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።
Via: Dige Wagiso

❤99👍22👏8🙏2