የሞት ጥላ አያርፍብህም እንደኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ
በምንኩስና ስማቸው ዘሚካኤል ተብለው የሚጠሩትና ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ አባታቸው ይስሃቅ የሮም ነገሥታት ወገን ስለሆኑ ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢትታጭላቸውም እምቢ ብለው ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ገቡ፡፡ አዳጊው አቡነ አረጋዊ መመንኮስ ቢፈልግም የንጉሥ ልጅ ነውና የአባቱ ንግስና ወራሽ ይሆናል፤ በማለት ዓለምን ንቆና ቆርጦ የመጣ መሆኑን በተለያዩ ፈተናዎች ካረጋገጠ በኋላ በ14 ዓመቱ አመነኮሰው፡፡ ዘሚካኤልም ከእንጦንስና ከመቃርስ ከጳኩሚስም የምንኩስና መንፈሳዊ ሐረግ 4ኛ ትውልድ ሆኑ፡፡ የአባ ዘሚካኤል እናት ንግሥት ዕድናም የልጃቸውን ዜና ሰምተው መንኩሰው የሴቶች ገዳም ገብተዋል፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት በዘሚካኤል መሪነት በ460 ዓ.ም አክሱም ከተማ ገቡ፡፡ እናታቸው ቅድስት ዕድናም ልጃቸውን ተከትለው መጥተዋል፡፡
ቅዱሳኑ አባ ዘሚካኤልን የበላይ አድርገው ሾሙትና ስሙንም አረጋዊ አሉት፡፡ ከሰንበት በስተቀር እህል የማይቀምሱት እነዚህ ቅዱሳን የሀገሬውን ቋንቋ እስኪማሩ በአክሱም ከመቆየታቸው ውጪ ወደ ሀዋርያዊ አግልግሎት ፈጥነው ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባርከዋታል፣ በትምህርታቸው የእምነቷን መሠረት አጽንተውታል፡፡ ተስዐቱ ቅዱሳን ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት በጸሎት እየተጉ አብረው ከተቀመጡ በኋላ ለብሕትውና ተጋድሎና ወንጌልን ለማስፋፋት ተለያዩ፡፡ አቡነ አረጋዊ ከሩቅ ሆነው የዳሞን ተራራ ባዩት ጊዜ እጅግ ወደዱትና ቢጠጉት ረጅሙን ገደል ወጥቶ ከጫፉ ላይ ለመድረስ መውጫ ቢያጡ ሌሊቱና ቀኑን ሁሉ በጸሎት አሳለፉ፡፡ ከሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በኋላ ቅዱስ ሚካኤል “እግዚአብሔር ወደ ተራራው ጫፍ የምትወጣበትን ነገር እስኪያዘጋጅልህ ጥቂት ታገስ” ብሏቸው ሁለት ሱባኤ በዚያ ቆዩ፡፡
ከዚያም ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ዘንዶ በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አስወንጭፏቸው ደብረ ዳሞ ላይ ሲወጡ መስቀላቸውና መጎናጸፊያቸው ያረፈበትና ቅርጽ ዛሬም ድረስ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ አባታችንም ተራራው ላይ እንደወጡ በጸሎት አምላካቸውን በእጅጉ ስላመሰገኑበት ቦታው ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ መጠነኛ ቤትም ሠርተው ያመጡትን ታቦት አኖሩት፡፡ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ምድራዊ ኅብስት ፈጽመው አልቀመሱም፡፡ መላእክትም ለመሥዋዕት የሚያስፈልጉትን ንዋያተ ቅድሳት፣ ኅብስትና ወይን ከሰማይ ያወርዱላቸው ነበር፡፡ ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀልም ወደ አቡነ አረጋዊ ሄዱው ተባረኩ፡፡ አሁን በስፍራው የምትገኘውን ቤተክርስቲያንም በሁለት ዓመት ሠርተው የእመቤታችንን ታቦት አስገቡ፡፡ 12 የወርቅና የብር መስቀሎችን ጨምሮ ብዙ ንዋያተ ቅድሳቶችንና ሰጧቸው፡፡ አቡነ አረጋዊም በሰማያዊ ኅብስትና ወይን ቀድሰው አቆረቧቸው፡፡
ጌታችንም ለአቡነ አረጋዊ ተገለጠለትና ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ የገድልህን መጽሐፍ አምኖ በንጽሕና በቤቱ ያስቀመጠ ምንም አይነት በሽታ በቤቱ አይገባም፣ ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም፣ የእህል ችግርም አይኖርበትም፡፡ በጥቡዕ ልብ ሆኖ የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል ያሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ፣ አንተም የሞት ጥላ አያርፍብህም፣ እንደነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ እንጂ” ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ አረጋዊም ደቀ መዝሙራቸው ማትያስን ጠርተው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን ከገድላቸው ጋር ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆን አዘዙት፡፡ ጌታችን እንደነገራቸውም በጥቅምት 14 ቀን ተሰውረዋል፡፡
ገዳማውያን ዓለምን ትተው የክርስቶስን መንግስት ሽተዋልና ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንካፈላለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

❤33👎2🙏1
FastMereja
ተክለኃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል አርቲስት ቸርነት ፍቃዱን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ!
#FastMereja I "አላማችን ህሙማንን መርዳት ነዉ" በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው ተክለኃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል 25ኛ አመት የምስረታ በአሉን በዛሬዉ እለት ህዳር 14/2018ዓ.ም በተለያዪ ፕሮግራሞች በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በደማቁ አክብሯል። በ25ተኛ አመት…
ተክለኃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል አርቲስት ቸርነት ፍቃዱን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ!
#FastMereja I “አላማችን ህሙማንን መርዳት ነዉ” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው ተክለኃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል 25ኛ አመት የምስረታ በአሉን በዛሬዉ እለት ህዳር 14/2018ዓ.ም በተለያዪ ፕሮግራሞች በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በደማቁ አክብሯል።
በ25ተኛ አመት የምስረታ በአሉ ላይ አርቲስት ቸርነት ፍቃዱን የሆስፒታሉ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን የፌርማ ስነ-ስርአትም አከናዉኗል።
ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ከክሊኒክ ተነስቶ ዛሬ ላይ በሀገራችን አሉ ከሚባሉ ዓለም የደረሰበትን የህክምናዉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች፣ ስፔሻሊስቶች እና ሰብስፔሻሊስቶችን በመያዝ እየሰራ ያለ አንጋፋ ጠቅላላ ሆስፒታል ለመሆን እንደበቃ ተገልጿል።
ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል በውስጥ ደዌ ፣ በሰርጀሪ፣ በማህጸን እና ጽንስ ፣ በህጻናት እና ልጆች ህክምና ፣ ከአንገት በላይ፣ በቆዳ እና አባላዘር ህክምና እና ሌሎችንም አገልግሎቶች በተሳካ መልኩ እየሰጠ የሚገኝ ሆስፒታል ነዉ።
ሆስፒታሉ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከህዳር 14 እስከ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ፣ የነፃ ሀክምና ፣ በሆስፒታላችን በተመረጡ ቀናት ለሚወልዱ እናቶች ልዩ ሽልማት እንዲሁም ልዩ የህክምና ክፍያ ቅናሽ በማድረግ እንደሚያከብርም ተገልጿል።
ተክለሀይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል በ1993 ዓ.ም በዶ/ር ሞላ ብርሃኑ ተቋቋመ።
ሆስፒታሉ 551 ሰራተኞችን የያዘ ሲሆን ከነዚህም 423ቱ የሙሉ ጊዜ ሰራተኞች እና 128ቱ የትርፍ ሰአት እና የኮንትራት ሰራተኞች መሆናቸዉ ተገልጿል።

❤19👏1
የነቢያት ትንቢት የተፈጸመበት የበረከት ጾም
ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ ወደ ግብፅ ስለ መሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለመጠመቅ፣ በትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ቅዱስ ኤርምያስ ድንግል ትጸንሳለች ብሎ ትንቢት በተናገረ በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡
ዘመኑ ጾመ ነቢያት የተባለውም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያሰበውን ድህነት ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ በእምነት ዓይን ያዩት እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡ ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር “የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር” ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ እናም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት የተፈጸመበት ይህ ጾም “የነቢያት ጾም” ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆችን ተስፋ የተመሰከሩበት የምሥራቹን የተነገሩበት ስለሆነም “ጾመ ስብከት” ይባላል፡፡ ከታኅሣሥ 7 እስከ 13 ድረስ ያሉት ቀናት ስብከት ይባላሉ፡፡ ስብከት ማለት ዐዋጅ ትምህርት ማለት ነው፡፡ ከአብርሃም ልደት እስከ ዳዊት ልደት ያለው ትውልድ፤ ሙሴ በኦሪት፣ ነቢያት በትንቢት፣ ዳዊት በመዝሙሩ በብዙ ምሳሌ ይወርዳል ይወለዳል ሲሉ የተናገሩት የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡
መዝ 143-7፤ ኢሳ 64-1 የሚዘመረው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር “ከዓለም በፊት የነበረውንና መድኃኒት የሆነውን ወልድን እንሰብካለን” የሚል ነው፡፡ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት የተናገሩለትንና ሱባዔ የቆጠሩለትን፤ ሐዋርያት ያላቸውን ሁሉ ትተው ተከተሉት ፈቃዱንም ፈጸሙ፡፡ ስለዚህ ምእመናን ክፉ ሐሳባቸውን አርቀው ርኩሰትን አስወግደው ፍጹም ለእግዚአብሔር እንዲገዙ ትምህርት ይሰጣል፣ ስብከት ይሰበካል፡፡ ከስብከት ቀጥሎ ያለችው ሰንበት ብርሃን ትባላለለች፡፡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን አስተምህሮ ከልደተ ዳዊት እስከ ፍልሰተ ባቢሎን ያለው 14 ትውልድ ይታሰብበታል፡፡ ክቡር ዳዊት በመዝሙር 42÷3 “አቤቱ ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ” እያለ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ከርሱ ወገን እንዲወለድ ትንቢት ስለተናገረ ይህ የሚታሰብበት ነው፡፡
ነቢዩ ዓለም ጨለማ ስለሆነች ብርሃን ወልድን ላክልን ማለቱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም “ብርሃን ወደ ዓለም መጣ” ብሎ ሲመሰክር ጌታም ራሱ በዮሐ 8÷12 “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናግሯቸዋል፡፡ ብርሃንን ላክልን ሲል ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ስደድልን ማለቱ ነው፡፡ ከብርሃን ቀጥሎ ያለው ሳምንት ኖላዊ ተብሎ ይጠራል፡፡ ትርጓሜው እረኛ ማለት ነው፡፡ እረኞች ለበጎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውኃ ሳያጓድሉ እንዲጠብቁ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነውና፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ የወረደ ወደ ዓለም የመጣ እረኛ ነውና በዮሐ. 10÷1-22 ያለው ይነበባል፡፡ በዚህ የጾም ወቅት በጎ ምግባር ይጠበቃልና ገዳማውያኑን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

❤34🙏4👎3
በኮሪደሩ ላይ ልብስ ያሰጡት ተቀጡ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በትላንትናው ዕለት በቀን 14/03/2018 ዓ.ም በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱ አስታወቀ።
ድርጊቱ የከተማው ገፅታ የሚያበላሽና ልማቱ ለታለመለት አላማ እንዳይውል የማውል የሚያደርግ በመሆኑ ጥፋቱን ፈፅመው የተገኙ የኮረደሩ ልማቱ መዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ በማድረግ ጉዳዩ እስኪወሰን ካፌው መታሸጉ ተገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤22😢6🙏2
በቡድን በመደራጀት በመዲናዋ በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል የሚፈፅሙ 36 ግለሰቦች እና 5 ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል፡፡
የምርመራ መነሻ የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኤሚግሬሽን አካባቢ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ነው።
የግል ተበዳይ ኢየሩስ ግርማ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ማ.ኢ 01058 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ይዘው በመንቀሳቀስ የት ነሽ? በማለት ካሳፈሯት በኋላ ሞባይል ስልኳን ለመቀማት ሲታገሉ በአካባቢው ላይ በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ዕይታ ውስጥ ይወድቃሉ፤ በፖሊስ ዕይታ ውስጥ መውደቃቸውን የተረዱት ተጠርጣሪዎች የግል ተበዳይን ገፍትረው በመጣል ለማምለጥ ቢሞክሩም ተጠርጣሪዎቹን እስከ መጨረሻው በመከታተል አራቱንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች መነሻ በማድረግ በተደረገ ሰፊ ምርመራ የማስፋት ተግባር የወንጀል ድርጊቱን የሚመራ እና የሚያስተባበር ቡድን እንዳለ ይደርስበታል፡፡ የወንጀለኛ ቡድኑን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ክትትልም በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ ስምሪት የሚሰጡ 11 ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡
ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ስምሪት በሚሰጠው ቡድን ላይ በተከናወነ ሌላ ጠንካራ ምርመራን የማስፋት ተግባርም በቡድኑ ስምሪት የተሰጣቸውን 8 ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B አ/አ 55902 ሚኒባስ ተሽከርካሪ በመጠቀም የሿሿ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኮካ እየተባለ በሚጠራው አደባባይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
ፖሊስ ምርመራውን በማጠናከር ባደረገው ብርቱ ክትትል ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ስምሪት የተሰጣቸው በኮድ 3 አ/አ 96708 አራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በኮድ3 ኦሮ A02639 ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 13 አባላት ያሉት ሁለት ቡድን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘ በኮድ 3B አ/አ 47364 በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ እየተዟዟሩ ከወንጀል ፈፃሚዎች የተሰረቀ እቃ ሲገዙ የነበሩ ሁለት የሌባ ተቀባዮች ተይዘው በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ እና ፍተሻ ከግለሰቦቹ መኖሪያ ቤት 30ሺ 700 ብር፣ 1 ላፕቶፕ፣ 1 ታብሌት፣ 11 ዘመናዊ ስልኮች፣ ተሰርቀው ቀፎዎቹ የተሸጡበት 188 የስልክ ከቨሮች በኤግዚቢትነት መያዙን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቆ በአጠቃላይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ 36 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንም ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።
በተለይም የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሚፈፀሙ የሿሿ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን እንደሚገባው ያሳሰበው ፖሊስ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል።
በወንጀሉ የምርመራ ሂደት አንዳንድ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ሆን ብለው ተሽከርካሪዎቻቸውን ለወንጀል ፈጻሚዎች እንደሚያከራዩ በምርመራ የተደረሰበት ሲሆን በግለሰቦቹ ላይ የሚያስከተለው የህግ ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ፊት የተሽከርካሪያቸውን አይነትና የባለ ንብረቶቹን ስም ዝርዝር ለህዝብ ግልፅ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች ጋር በተያያዘ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ግለሰብ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ማመልከት እና መረጃ መስጠት እንደሚችልም ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

❤68👍19👏7👎6🙏3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባታዩት ይመረጣል‼️‼️
ዘግናኝ በሀገራችን የተከሰተ የጭካኔ ተግባር ነው።
መወገዝ አለበት!!
ዘግናኝ በሀገራችን የተከሰተ የጭካኔ ተግባር ነው።
መወገዝ አለበት!!
😢1.1K👎88❤58👍23👏8
FastMereja
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር በኢትዮጵያ በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን በዛሬዉ እለት ህዳር 16/2018ዓ.ም አስታዉቋል። ድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሰየም የወሰነው ፕሮግራሞቹን እያሰፋ ባለበትና የአገር ውስጥ ሃብት...
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር በኢትዮጵያ በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን በዛሬዉ እለት ህዳር 16/2018ዓ.ም አስታዉቋል።
ድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሰየም የወሰነው ፕሮግራሞቹን እያሰፋ ባለበትና የአገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ ጥረቱን እያጠናከረ ባለበት ወቅት መሆኑ ተገልፆ ይህም ብዙ ማህበረሰቦችን ለመድረስ ሰፊ ተሳትፎን ለማነሳሳት እና ዘላቂነት ያለው ድጋፍን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል ።
አርቲስቱ የተመረጠውም በአቋሙ፣ ለረጅም ጊዜ በዘለቀው መልካም ስሙ፣ ለህጻናት ደህንነት ባለው ቁርጠኝነት እና ከድርጅቱ ተልዕኮ ጋር የሚጣጣም ስብእና ያለው ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል።
የብራንድ አምባሳደሩ ሚናም ድርጅታዊ አጋርነትን ለማስፋት የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረቶችን ለማጎልበት እና በቂ የወላጅ እንከብካቤ ሳያገኙ የሚያድጉ ህጻናት እና ወጣቶች የበለጠ የህዝብ ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
አርቲስት አለማየሁ ሹመቱን አስመልከቶም “የብራንድ አምባሳደር መሆን ከማዕረግ በላይ የሆነ እና ትክክለኛ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያበቃ ትልቅ ሃላፊነት እና እድል የተሰጠኝ ባገኘሁት መድረክ ሁሉ ድምፄን ለማሰማትና የድርጅቱን ተልዕኮ ለማጉላት ሙሉ ቁርጠኝነቴን እገልፃለዉም አሳያለዉም ብሏል።
የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሣህለማርያም አበበ እንደ ገለጹት “ይህ አጋርነት የህጻናትን እና የወጣቶችን ድምጽ ወደ ፊት የማምጣት የህብረተሰቡን ተሳትፎ የማነሳሳት እና ከለጋሾች እና ከተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የሚደረገውን ድጋፍ የማጠናከር አላማን ያገናዘበ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የአርቲስቱ የአምባሳደርነት አገልግሎትም እንደሁኔታው ሊራዘም የሚችል ሆኖ ከዛሬ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ይቀጥላልም ተብሏል፡፡

❤27👍1
ለእርሷ የተሰጣት ኪዳን፣ ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል
“ኪዳን” የሚባለው ቃል “ቃል” ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ “ኪዳን” ቃሉ “ተካየደ” ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ "ምሕረት” የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ” እንዳለ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላተ አንዱ ነው፡፡
እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብላ ስትጸልይ፣ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቁ ጌታችንም ከእልፍ አእላፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ላንቺ ይሁን እናቴ ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት። እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን፣ ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡
ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡ በቅዱሳን በቅዱሳን ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡ አልፎ ተርፎም ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው፡፡ ጌታችን በዮሐ.21÷39 እና 2ኛ ጴጥ.1÷14 ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟማት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ በሐዋ.20÷25 ለቅዱስ ጳዉሎስ ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡
ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ ስለምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል፤ ማለትም ትጠራበታለች፤ ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ አድርገው ላወቁትና ላላወቁት ጉድለቶቻቸው ሁሉ ስሟን ለሚጠሩ፣ ቃል ኪዳንን ለመቀበል ያበቃት ለሰው ልጆች ነጻነት ልጇ ለሰጠው ፍፁም መድኃኒት ምክንያት የሆነችበት ጸጋዋ ሁሉ በሥላሴ ፊት ይታሰብላቸዋል፡፡ ገዳማውያን በዚህ ቃል ኪዳኗ ታድናቸውው ዘንድ ቀንና ሌሊት በውዳሴዋም በቅዳሴዋም ቅድስት ሆይ ለምኝልን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጸናን ከበረክታቸው እንካፈል፡፡

❤60👎6