ሀሁ መጻሕፍት ( Hahu books )
3K subscribers
1.12K photos
12 videos
2 files
177 links
የሚፈልጉትን ማንኛውንም መፅሐፍት ካሉበት ቦታ እናመጣልዎታለን
በ 0911006705 ደዉለዉ ይዘዙን
አድራሻ :- አራት ኪሎ አብርሆት ቤተ መጻህፍት
Download Telegram
በዕውቄ
ይስጥህ ከቁመቴ ፣ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምህ አንተን ፣እኔን አሳንሶ
ከቀጭኔ እረዝመህ ፣ስትቆም ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼህ ፣አንተን ላክል እኔ😂
ይስጥህ ከጸጉሮቼ ፣ከአናቴ ላይ ሰፍሮ
ይገጠብ ራሴ ፣ ያንተ ተጎፍሮ
አወይ ጸጉሩ ብለው ፣ ሲያወድሱህ አመት
ድጥ ራስ ነህ ብለው ፣ ይዝለፉኝ በኮመንት😂
።።።
ጋሼ
ይስጥህ ከወዜ ላይ ፣ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልህ ከደሜ፣ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣህ እያለ ፣ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ፣ ይበለኝ ጠያቂ።

።።።
በዕውቄ
እጄን ብትፈልግ
እግሬን ብትፈልግ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
እድሜዬን ምናቤን
ያደምቀኛል ብለህ
ያኖረኛል ብለህ ፣ ያሰብኸውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ፣ከሰጠህ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
ያንተን ፅሁፍ ማንበብ ፣ ያኖረኛል እኔን።
።።።
የፊታችን ሰኔ 6 በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ ሰማይ ስር Bewketu Seyoum ጥበብ ያዘንባል ። እንዳትቀሩ!!!
© በላይ በቀለ ወያ

ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 09 11 00 67 05
የዚህ ዘመን መልካም ምልክት ከኾኑት አንዱ ዛሬ ተሞሽሯል።
መልካም ጋብቻ ብዕሩም፣ አንደበቱም መንፈሱም ድንቅ ለኾነው ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌና ባለቤቱ።
*
በትውልዴ ደስ ከምሰኝባቸው ሰዎች አንዱ ነው። እንደ ተማሪ መንፈሳዊ ዕውቀቱ ይማርከኛል። እንደ ዘመኑ ሰው ለዘመኑ ልክክ ያለ ኾኖ አገኘዋለሁ። ትውልዱ ባለበት ሁሉ ለመኖር በሁሉም ስልት ይደርሳል። ደርሶ አንጀት ያርሳል።

መልካም ምልክት ነው። መንፈሳዊነቱን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመውጣት ብቻ የጠበቀ። የእስከአሁኑ ጉዞው የሚነግረን ይሄንን ነው።

ዝና አላደናቀፈውም፤ መወደድ ለመጠላት አሳልፎ አልሰጠውም። ብዕሩም፣ አንደበቱም፣ መንፈሱም ድንቅ ነው። እሱ ነገ ይሞሸራል። መልካም ጋብቻ ለዲያቆን ሄኖክ ኃይሌና ለሙሽራይቱ፤

ዲያቆን ሄኖክ በመልዕክቱ ስለሚተማመን የሌላን መልዕክት ከማደናቀፍ ይልቅ ተልዕኮውን ይገልፃል።

ሰባኪ ነው፤ አንደበተ ርቱዕ። ስለ ሃይማኖቱ መልካም መንገድ ይጮሃል እንጂ ሌላን በማደናበር ጊዜውን አያጠፋም።

ደግሞ ፀሐፊ ነው፤ ግሩምና ድንቅ ፀሐፊ። በተለይም “ህማማት” እና “የብርሃን እናት” ክፉ አይንካብን ያስባሉን ስራዎቹ ናቸው። የትምና መቼም አድራሻው አንድ ነው፤ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና አስተምሮዋ ጉዳይ።

በዚህ ትውልድ ልብ ውስጥ መልካም ስፍራ ያሰጠው ጉዳይ፤ የማይዋዥቅ የመንፈሳዊነት ዓላማው ነው። በሀገር ጉዳይ ከመንፈሳዊ እሴቶች በሚቀዱ የሞራል ሀሳቦች ለሁሉ በሚጠቅም ርዕሰ ጉዳይ ሰውም ሀገርም ይሰራል። ከአውደ ምህረት መራቅ አይፈልግም።

ወደ ቤተ ክርስቲያን እንጂ ወደራሳቸው ከሚስቡ ወገን የሚመደብ አይደለም።
መገናኛ ብዙኃን ለሚፈልጉት ይጠሩታል። ለሚፈልገው ይደርስባቸዋል። የትም ቀርቦ ሁሌም ቢያወራ ከእምነቱ ሀሳብና መድረሻ አያፈነግጥም። ዲያቆን ሄኖክ የተወደደ ብቻ ሳይኾን የተባረከ አገልግሎት ያለው ሰው ነው።

ለራሱ ስለማይቆም በሚፈለግበት ሁሉ የለም። በሚያስፈልግበት የማይሸሽ የአባቶቻችንን መንገድ እየሄደበት ያለ ሰው ነው።
ብዙ ተስፋ አደርጋለሁ። የዶኪማስን ቤት አስመልክቶ ሀሳቡን የገለፀባትን መንገድ እቀናባታለሁ። እንደ አንባቢና ተማሪው መልካሙን እመኝለታለሁ።

ለበለጠ አገልግሎት ይተጋ ዘንድ ምክንያት የኾነ ትዳር ይሁንለት። የጎደለውን ደግሞ የብርሃን እናት ገብታ ትሙላው።
መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ!!
© ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም
ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 09 11 00 67 05/ 0924 40 84 67
በቅርብ ቀን በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
#የግእዝ_ቁጥሮች_በአኀዝና_በፊደል_ተለማመዱ!
================================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
አንብቡኝ
ላትሮኖስ ስጋዬ ብራና ነው ገፄ፤
ብእር ነው እድሜዬ፤ ቀለሙ ናት ነፍሴ፤
ዝም ብላችሁ አን'ቡኝ!
ግጥም ነኝ እራሴ።
አከፋፋይ ፦
ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2. ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ .09 11 00 67 05/0924 40 84 61
የቤተ ምርምሩ ጣሪያ ከውስጥ ሲታይ ሰማያዊ መሠረት ባለው የአልማዝ ቅርጽ ማዕዘን መካከል ከስምንቱም አቅጣጫ መኻል “አ” ፊደል በጥበብ ተሥሏል፡፡ አቅጣጫዎች፡-ምሥራቅና ምዕራብ፣ሰሜንና ደቡብ እንዲሁም መስዕና አዜብ፣ሊበና ባሕር፣ሁሉም አ ከሚገኝበት መኻል ነጥብ ላይ ይገናኛሉ፡፡
የአልማዝ ቅርፅ ያለውን ስምንት ማዕዘን ኮከብ የከበበውን ክብ ሁለት ባለ ዐራት ማዕዘን ጫፎች ይነኩታል፡፡ይህ ኮከብ የመልከጼዴቅ ኮከብ ሲሆን ሁለቱ ዐራት ማዕዘናዊ ዑደቶች የምድርና ሰማይን ሥርዓት እና ተፈጥሮ ወቅረውታል፡፡የመጀመሪያው ዐራት ማዕዘን ዋና ዋና አቅጣጫዎችንና አካላዊ ባሕሪያትን በመያዝ፤ ዋና አቅጣጫዎቹ ምሥራቅ፣ምዕራብ፣ ሰሜን እና ደቡብ ሲሆኑ ባሕሪያት ደግሞ ነፋስ፣መሬት፣እሳትና ውኃ ናቸው፡፡ሁለተኛው ዐራት ማዕዘን ንዑስ አቅጣጫዎችን እና ሦስቱን ባሕሪያት ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር አሰናስሎ ይዟል፡፡እነዚህ አቅጣጫዎች፡-መስዕና አዜብ ሊበና ባሕር ሲሆኑ፤ባሕሪያት ደግሞ ሐልዮ፣ነቢብ እና ገቢር ናቸው፡፡በአጠቃላይ ኮከቡ የአልማዝ ዕንቁ ይመስላል፡፡

ከዘ ግዕዝ ኮድ መፅሀፍ የተወሰደ
ሀሁ መጻሕፍት መደብር

አድራሻ፥ አ.አ ቁ. 1 ስታድየም ናሽናል ታዎር
2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705
እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publications
ሥዕል:- ቤተ አብ ዓለሙ
ኬኒያ ጃንሆይን ለምን አከበረቻቸው?

ኬኒያ ሰሞኑን ዘመናዊ ኤክስፕረስ መንገዷን መውጫ እና መግቢያውን በኢትዮጵያዊው ንጉስ በአፄ ኃይለስላሴ ስም ሰይማለች። ለምን? በጥቂቱ እንክዋን፣ ንጉሱ አለም ላይ እንዲህ ገናና ነበሩ።

20 የክብር ዶክተሬት ያላቸው ንጉሳችን!
በጥበቡ በለጠ

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በአለማችን ካሉ 20 ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ ተቀብለዋል! በየዩኒቨርሲቲዎቹም ተገኝተው ታላላቅ መሪዎችና ምሁራን በታደሙበት ውብ ንግግሮች አድርገዋል፡፡ ንግግሮቻቸውን አልፎ አልፎ እጽፋቸዋለሁ፡፡ እኚህን ታላቅ ንጉስ የሚከተሉት የምድሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ አበርክተውላቸዋል፡፡
1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ
3- ግንቦት 28 ቀን 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት
4- ግንቦት 30 ቀን 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
5- ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
6- ሐምሌ 16 ቀን 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
7- ሐምሌ 29 ቀን 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሐራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ድግሪ
8- 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
9- ጥቅምት 10 ቀን 1947 ዓ.ም ከኢክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
10- ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
11- ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ድግሪ
12- ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
13- ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ድግሪ
14- ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
15- መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
16- መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድሪ
17- መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት ክብር ዶክተሬት
18- ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ የህግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
19- ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
20- ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ድግሪ ተቀብሏል፡፡
( የምንጭ ስብስብ ከአጼ ኃይለስላሴ የታሪክ መጻሕፍት)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ
ስም አሜን
እንኳን አደረሳችሁ!!!

ሰኔ 12-የቅዱስ ላሊበላ በዓለ ዕረፍት ሲሆን የመላእክት
አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ደግሞ ዕጥፍ ድርብ በዓሉ ነው፡፡ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል
ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ ዳገመኛም ይህች ዕለት የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ ለታላቅ ክብር ያበቃባት ዕለት ናት፡፡ ዳግመኛም ይህች ዕለት ቅዱስ እለ እስክንድሮስ አንድን ቤተ ጣዖት አፍርሶ
ከቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን
አግብቶ በዓሉን በደስታ በሐሴት አሳለፈባት ዕለት ናት፡፡
ዳግመኛም ዛሬ የጻድቁ የቅዱስ ላሊበላ በዓለ ዕረፍት
ነው፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት
በማሰብ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ
ገብርኤል ላሊበላን ኢየሩሳሌም ወስዶት በዚያ ያሉ
ቅዱሳን መካናትን ሁሉ አሳይቶ አሳልሞታል፡፡ ወደ ሰማይም ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን
ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ‹‹ሕዝቦቼ
የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሔድ
በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ
ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን
አሠራር በዝርዝር ነግሮታል፡፡ ከነገሠም በኋላ ሱባኤ ገብቶ
ቤተመቅደስ የሚሠራበትን ቦታ በጸሎት ሲጠይቅ ዛሬ ቤተማርያም ካለችበት ቦታ ላይ የብርሃን አምደ ወርቅ ተተክሎ
መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ስላየ ቦታው እግዚአብሔር
የፈቀደው መሆኑን አውቆ ሥራውን ጀመረ፡፡ ጌታችን
ቀድሞ ‹‹እኔ ራሴ ነኝ እንጂ ቤተ መቅደሶቹን
የምትሠራቸው አንተ አይደለህም፣ ነገር ግን በአንተ ስም
እንዲጠራ ስለፈቀድኩ ሄደህ ሥራ›› ብሎ እንዳዘዘው
ቅዱስ ገድሉ ይናገራል፡፡ ላሊበላ ዓሥሩን ቤተመቅደሶች
ሲሠራ እርሱ አንድ ስንዝር ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን ዓሥር
ስንዝር ሆኖ ያገኘው ነበር፡፡ ቀንም ሲሠራ ቅዱሳን
መላእክት በማይታወቁ ሰዎች አምሳል ሆነው ይራዱት
ነበር፡፡ በመጨረሻም ጌታችን በገሃድ ተገልጦለት በቦታው
ላይ እጅግ አስገራሚ ቃልኪዳኖችን ሰጥቶታል፡፡ ቤተ መቅደሶቹን ሠርቶ ከጨረሰ በኋላ ጌታችን
የሰጠው ቃልኪዳን፡- ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን ባሳየውና
ባዘዘው መሠረት አብያተ ክርስቲያናቱን አንጾ ከጨረሰ
በኋላ በቀኝና በግራው ዓሥር ዓሥር ኪሎ የሚመዝን
የዓለት ድንጋይ ተሸክሞ ለ7 ዓመት ሲጾም ሲጸልይ ከኖረ በኋላ ጌታችን ተገልጦለት በፊት የገባለትን ቃልኪዳንበዚህም ጊዜ በድጋሚ አረጋግጦለታል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ ‹‹…ወደ ደጅህ የመጡት ሁሉ አስራት
ይሁኑልህ፣ አንተ ከገባህበትም ይግቡ፣ አንተንም ከ12ቱ
ሐዋርያት ጋር በፍርድ ቀን 13ኛ አደርግሃለሁ፡፡
ያነጽካቸውን ቤተ መቅደሶች የተሳለመውን ኢየሩሳሌምን
እንደተሳለመ አደርግለታለሁ፤ መታሰቢያህን ያደረገውን፣
ገድልህን የጻፈውን ያጻፈውን፣ በዚህ ቦታ ላይ መጥቶ
አማልደኝ ያለውን፣ በአማላጅነትህ የተማጸነውን ሁሉ እስከ 15 ትውልድ ምሬልሃለሁ›› ብሎ የመጨረሻውን ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛንም በአማላጅነታቸው የምንታመን ሁላችንንየመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልንእና የቅዱስ ላሊበላን በረከታቸውን ያድለን በጸሎታቸውይማረን አሜን!!!

(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ላሊበላና
ስንክሳር)
ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 09 11 00 6705