ሳምንታዊ የስነጽሁፍ ውድድር
በስነጽሁፍ ስራ ፣ በቲያትር በፊልም የተለመደ ጭብጥ አለ—በጥሩ እና መጥፎ መካከል የሚደረግ የማያልቅ ጦርነት። ደራስያን ይህን ጦርነት ተንተርሰው ሚሊየን መጽሀፍት ጽፈዋል። ደሞ ይህ ጦርነት ህይወት ራሷ የተዳወረችበት ማግ ነው። በእርግጥ ሼክስፒር “ጥሩ እና መጥፎ ብሎ ነገር የለም። አስተሳሰባችን ነው እንደዚያ የሚያደርጋቸው” ብሏል።
ኒቼ ከተለመደ ው ግብረገብነት ፈቀቅ ብሎ ከጥሩ እና መጥፎ ከፍ ብሎ ምን እንዳለ ለማየት ሞክሯል። ህሊና የሚኮተኮት ነገር ነው ወይስ አብሮን የሚወለድ?
ከበደ ሚካኤል የኒቼ ተቃራኒ ናቸው፦
“ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” ብለዋል።
በአንድ ፊልም ላይ ደግሞ
“የሁላችንም መጨረሻ ያማረ ነው። ካላማረ ገና መጨረሻው ላይ አልደረስንም ማለት ነው።” ሲባል ሰምቼያለሁ።
ይህንን ተመርኩዘን አራት ጥያቄ እንጠይቅ፦
1)ደራሲዎች በተደጋጋሚ ይህንን ጭብጥ የሚመርጡበት ምክንያት ምንድነው?
2) በሀገራችን ውስጥ ይህንኑ ጉዳይ የሚያነሳ የስነጽሁፍ ስራ መርጣችሁ በአጭሩ ግለጹ
3) በልብወለድ ውስጥ በመጨረሻ ጥሩ ሁልግዜ ክፋትን ድል ሲያደርግ እናያለን። በገሀዱ አለም ደግነት ሁልግዜ ክፋትን ይረታል ወይስ ነገሩ ልብወለድ ብቻ ነው?
4)በገሀዱ አለም ያሉ ሰዎች እንደ ልብወለዶቹ እጅግ በጣም ጥሩ ወይም እልም ያሉ አጭበርባ፣ ዋሾ ፣ አታላይ ለምን አልሆኑም?
የመጻህፍት ሸላሚያችን ሀሁ የመጻህፍት መደብር
ለሽልማት የቀረቡ መጻህፍት
፩) ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ — ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ
፪) አዝማሪው ልቤ — ጌታነህ ደጉ
፫) ሸማቂው ኮማንዶ — ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ
በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦
የቆዩ እና አዲስ
መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ
ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ
የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ
አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን።
#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461

የብርሀኑ ዘርይሁን ልብወለዶች የራሱ ገጠመኞችና ልምዶች ውጤት ናቸው። ብርሃኑ ዘርይሁን 3ቱን “ማዕበሎች” ሲጽፍ ከወሎ የገጠር ቀበሌዎች ደሴ እስከነበረው የስደተኞች ካምፕ ድረስ ተዘዋውሮ በድርቅ የተጠቁትን ሰዎች በማየትና በማነጋገር መረጃዎችን ሰብስቧል፡፡ የልብወለዱ ዋና ገጸባህሪ ሙሄ ይባላል። ነገርን ከስሩ፣ ውሃን ከጥሩ እንዲባል ብርሃኑ ዘርይሁን የ66ቱን ድርቅ ምክንያት እና መነሻ ከስሩ ጀምሮ ይመረምራል። ሶስቱ የማእበል መጻህፍት እና የታተሙበት ዘመን የሚከተለው ነው፦
ማዕበል የአብዮት ዋዜማ በ1972
ማዕበል የአብዮት መባቻ በ1973
ማዕበል የአብዮት ማግስት በ1975
ብቻ ብርሃኑ ዘርይሁን ሊነግረን የፈለገው አንድ ቁም ነገር አለ። ድርቅ የትም አለም ላይ ይከሰታል። ድርቅ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ክስተት ነው። ግን ድርቅ ሁሉ ሁሌም ረሃብ አይወልድም፤ በሰቆቃ አይታጀብም። ሌላው ጉዳይ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን ብዙውን ግዜ ድርቅ የሚከሰተው ሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ወሎ ነው። ሁሉንም ጉዳይ ሬዱልፍ ኬ ሞልቬር እንዲህ ያጫውተናል፦
.
.
.
ብርሃኑ የአዲስዘመን ዋና አዘጋጅ ሆኖ በጻፈው ጽሁፍ የንጉሱን ስርአት በማስቀየሙ ከስራው ለ8 አመታት ያህል ታግዶ ነበር። በነዚህ ስራ በፈታባቸው ዓመታት መጨረሻ አካባቢ አንድ ክስተት ትኩረቱን ሳበው፣ ዳግም ሀገሪቱ ውስጥ በዋነኛነት ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንዲያጤን አሳሰበው። ይህ ክስተት የ19666ቱ ድርቅ እና ረሀብ ነው።
የረሀቡ ሰለባዎች መናገሻ እና ለገዳዲ ላይ ቢኮለኮሉም ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ግን አልተፈቀደላቸውም። ስለዚህ እሱ ሊጎበኛቸው ሄደ፤ ከጎበኛቸው በኋላ ብዕሩን አንስቶ በድህረ–አብዮት ለጻፋቸው ሶስት ጥንድ ልብወለዶች ማስታወሻ መውሰድ ጀመረ።
በጊዜው መጽሀፉ የጎላ ፖለቲካዊ አንደምታ ይኖረዋል ብሎ አላቀደም ወይም አላሰበም።በ1965 ዓ.ም ለመጽሀፉ ማስታወሻ እየወሰደ ቅርፁን ቢያወጣም፣ገና በስርአቱ ዝርዝሩን ቁጭ ብሎ መፃፉን አልጀመረም ነበር። በመጀመሪያ መጽሐፉን ሲያዋቅር ያሰበው ስለ ረሀቡ ብቻ እንደነበረ ይናገራል። ስለዚህ ስለ መሬት ባለቤትነት ስርአት፣ስለ መደብ ልዩነት እና ለረሀቡ እንደ መንስኤ ሊሆኑ ስለሚችሉ ማህበራዊ ቀውሶች የመሳሰሉ ጉዳዮችን ጭራሽ አላሰበም።ቢያስብ እንኳን ያን መሰል ጉዳዮችን የያዘ መጽሐፍ በድሮው ስርአት ሊታተም አይችልም ነበር።በጊዜው አንድ ደራሲ የፃፈው ነገር መታተም እንዲችል፣ ሳንሱሩን ማለፍ እንዲችል የግድ መጨነቅ ነበረበት። ነገር ግን ስለ ማህበራዊ ችግሮች ያውቃል፤ በ1959 ዓ.ም ልክ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነቱ ከመነሳቱ በፊት፣ ወደ ሞስኮ በተጓዘበት ወቅት የካርል ማርክስን "ካፒታል" ስላነበበ ስለ መደብ ልዩነት በጥቂቱ ያውቃል፤ ቢሆንም ከአብዮቱ በፊት ይህንን አንስቶ መፃፍ አይችልም።
በሰኔ 1966 ብርሀኑ ወደ ወሎ ለመጓዝ ሲነሳ፣ አብዮቱ መፋፋም ጀምሯል። ወሎ በተለይ በድርቅና በረሐብ ክፉኛ ተመቶ ነበር፤ሐይቅ እና ዙሪያውን ከጎበኘ በኋላ ከሐይቅ የአንድ ቀን መንገድ በኋላ ወደምትገኘው ወርጠያ ተጉዞ በገበሬዎች መንደር ለሁለት ወራት ቆየ።በቆይታው ከአካባቢው ገበሬዎች ጋር ረዣዥም ውይይቶች በማድረግ የረሀቡ መነሻ የጉልት (የጭሰኛ) ስርአቱና የአስተዳዳሪዎቹ ቸልተኝነት መሆኑን ተረዳ። ብርሀኑ በጊዜው በኢትዮጵያ 40 ዐይነት የጭሰኛ ስርአቶች ነበሩ ይላል። ነገር ግን በወሎ የነበረው ስርአት ከተቀረው የሀገሩ ስርአት ይለያል። ከአልጋወራሹ ጀምሮ፣ የወሎ ገዢ እና ሌሎች ሹመኞች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ የገበሬውን ምርት በመቀራመት በክፉ የሚታወቁ ናቸው። ለሁሉም ገበሬዎች ስርአቱ ክፉ ቢሆንም፣ "ከደቡብ ኢትዮጵያ ይልቅ ወሎዎች ላይ ይብሳል"። በደቡብ ጭሰኛው "የሚከፍለው ቁርጥ ብሎ" ይታወቃል፤ በወሎ ግን ልክ የቤተሰብ ንብረት ይመስል ሁሉም እየመጣ የአቅሙን ያነሳል።መሬቱ ሁሉ በአልጋወራሹ፣ በሌሎች የንጉሳዊ ቤተሰቡ አባላት ወይም በአካባቢው ሹመኞች እጅ ነው።
ብርሀኑ ሁሌም የንጉሡ ተቃዋሚ ቢሆንም የንጉሡ ቤተሰቦች ግን ግድ አይሰጡትም ነበር።ስለ ኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ከተለያዩ መጽሀፍት የቃረመው እውቀት አለው። ለምሳሌ በጽህፈት ሚኒስትሩ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ተጽፎ በ1935 ዓ.ም የታተመው "የመሬት ስሪት በኢትዮጵያ" እና በማህተመሥላሴ ወልደመስቀል ተጽፎ በ1942 ዓ.ም የታተመው "ዝክረ–ነገር"ይገኙበታል። ወሎ ሄዶ የነበረውን ሁኔታ በአይኑ ሲመለከት፤ የገበሬዎቹን የጭሰኞቹን ችግር ከአፋቸው ሲሰማ፣ ያነበበው ሁሉ ግልጽ እና ልዩ ሆኖ ታየው። ከሁሉም የበለጠውን ጉዳት ያደረሱት የመንደሩ ተራ ሹመኞች (የዋና ሹመኞቹ እንደራሴዎች እና የመንደሩ መሪዎች)ናቸው ብሎ ያምናል።ገበሬዎቹ የመከላከል አቅም የላቸውም።በጊዜው ምንም የፖለቲካ ንቃትም አልነበራቸውም።
ብርሃኑ በዛው ዓመት ነሐሴ ላይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ፣ነገሮች "ተጋግለው" ጠበቁት። ሚኒስትሮቹ እና መኳንንቱ ተለቅመው እየታሰሩ፣ንጉሰ ነገስቱ ደግሞ ገለል እየተደረጉ ነበር። በየቀኑ አዳዲስ ነገር ይፈጠራል። በመስከረም 2፣ ንጉሰ ነገስቱ ከሥልጣን ተወግደው ታሰሩ። በዚህ ወቅት ብርሀኑ የሰበሰበውን መረጃና ጭብጥ በምን ዐይነት መንፈስ መጠቀም እንዳለበት እያወጣ እና እያወረደ በራሱ ጭንቅላት ውስጥ መጽሐፉ ኋላ ላይ የሚኖረው ቅርጽ አልቆ ሳይታየው በፊት አብዮቱ አዲስ የአመለካከት ፈር አመላከተው። በህዳር 1966 ዓ.ም የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነቱ ተመልሶለት ዳግም ተቆናጠጠው። አሁን በቢሮው እስከ ምሽቱ 5 ሰአት ድረስ እየቆየ ስለሚሰራ ለመፃፍ ምንም ጊዜ አልነበረውም። ለጊዜው የመጽሐፉን ነገር ወደ ጎን አድርጎ ቢተወውም፣ ስለመጽሀፉ ማሰላሰሉን ግን አላቋረጠም። ነገር ግን በ1970 ዓ.ም ብርሀኑ ለሶስተኛ ጊዜ ከአዲስ ዘመን አዘጋጅነቱ ተነሳ። “ምክንያቱ ፖለቲካ ሳይሆን አይቀርም።”
የመኢሶንን አመለካከት የሚያንጸባርቅ ጽሁፍ በጋዜጣው ላይ ጽፎ ነበር። ነገር ግን መኢሶንና ደርግ በነሐሴ 1969 ዓ.ም"ተለያይተው" ስለነበር በመኢሶን፣ በብርሀኑና በጌታቸው አባዲ መሀል ግንኙነት ሳይኖር አይቀርም ተብለው “እንደተጠረጠሩ” ብርሀኑ በዝርዝር ያስታውሳል። በዚህ ወቅት የኢሕአፓ አባላትም “ከያሉበት እየታደኑ” ነበር።ብርሀኑ እና ጌታቸው ለዘጠኝ ወራት ታሰሩ (ብርሀኑ በከፍተኛ 15 ጌታቸው ደግሞ በከፍተኛ 4 ታስረዋል)።
እነኚህ የእስር ወራት እንዳለቁ ብርሀኑ እና ጌታቸው ወደ ደርግ “የምርመራ ክፍል” ተወስደው “አንዳንድ ጥያቄዎችን” ተጠየቁና “ወደቤታቸው ተሸኙ።” ከዚህ በኋላ ብርሀኑ የአማርኛው የካቲት መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሆነ። ብርሀኑ በከፍተኛ 15 ታስሮ ሳለ፣ እንዲጽፍ ተፈቅዶለት ስለነበር፣የ"ማዕበል"ን ሲሶ ያህል አጠናቀቀ። የየካቲት መጽሔት ዋና አዘጋጅነቱ ብዙ ጊዜ የሚፈልግ ባለመሆኑ፣ይህንኑ እየሰራ የመጀመሪያውን የ"ማዕበል" ክፍል ጽፎ ጨረሰ። ነገር ግን ረቂቁን ወደ ማተሚያ ቤት ከመላኩ በፊት፣ የአንድ ወር ፍቃድ ወስዶ ተመልሶ ወደ ወሎ ሄደ።ባያቸው አዳዲስ ለውጦች ላይ ተመርኩዞ ማሻሻያ ካደረገ በኋላ፣መጽሀፉን ሳንሱር ክፍሉ ተመልክቶ ያለ ምንም ለውጥ ታተመ።

ብርሀኑ ዘርይሁን በዚህ መጽሐፉ ከበኩር አብዮታዊ ልብወለድ ደራሲዎች መሀል አንዱ ሆኖ ታወቀ። "ማዕበል" በመጀመሪያው ህትመት ብቻ 10,000 ቅጂዎች ታተመ።መጽሐፉ በሃያስያን ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል። ብርሀኑ ዘርይሁን፣በአሉ ግርማ እና ታደለ ገብረሕይወት በተመሳሳይ ጊዜ አብዮቱን የሚመለከቱ አብዮታዊ ልብወለዶች አሳተሙ። ሶስቱም ደራሲዎች ይህንን በማድረግ ቀዳሚ ሲሆኑ ሶስቱም ከፍተኛ ሙገሳ እና ተቀባይነትን አገኙ።የባህል ሚኒስቴር በሶስቱ ደራሲዎች ስም እና ክብር የኮክቴል ግብዣ አዘጋጀ፣በዝግጅቱም ላይ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ሸዋዬ ተገኝተው ንግግር አደረጉ። በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ደረጃ ለመጽሐፍት እንዲህ ያለ እውቅና ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ሶስቱም ደራሲዎች በሁኔታው ተበረታቱ።
ብርሀኑ አሁንም የየካቲት ዋና አዘጋጅ እያለ ሁለተኛውን ማዕበል መፃፍ ጀመረ። ነገር ግን በዚህ መሀል በ1972 ዓ.ም አዲስ ስራ ተሰጠው። ስራውም የአለም አቀፉ "World Marxist Review" አማርኛ እትም ዋና አዘጋጅነት ነው። ጽሑፎቹ የሚላኩት ከፕራግ ሲሆን መጽሔቱ በወር አንዴ የሚታተም ነው። የብርሀኑ ስራ ከፕራግ የሚላኩትን ጽሑፎች እየመረጠ ወደ አማርኛ መተርጎም ነበር ( በቃለመጠይቃችን ወቅት ይህንኑ ስራነበር የሚሰራው)። ስራው ብዙ ጊዜ እና አቅም የሚሻማ አልነበረም ፤ ነገር ግን በጎን ብዙ የኮሚቴ ስራ እንዲሰራይጠየቃል። ትንሽ ትንሽ መፃፍ ቢችልም፣ በብዛት የሚጽፈው ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ እስከጠዋቱ አንድ ሰአት ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ነበር።
የ"ማዕበል"ን ሁለተኛ ክፍል ከማጠናቀቁ በፊት "ሞረሽ" የተሰኘ ተውኔት ፃፈ። በ1972 ዓ.ም ተጽፎ በተስፋዬ ገሠሠ አዘጋጅነት በዚያው ዓመት መጨረሻ በብሔራዊ ቲያትር ቀረበ። በጣም ስኬታማ እና ጥሩ ተቀባይነት አግኝቶ ለሁለት ወር ያህል ታየ። በተመሳሳይ ወቅት፣ የ"ማዕበል"ን ሁለተኛ ቅጽ እየፃፈ ነበር። ይህንን መጽሐፍ በሚጽፍበት ወቅት ስለ ማህበራዊ እና አብዮታዊ ችግሮች የነበረው ንቃተ ህሊና እየጎለበተ መጣ። ነገር ግን፣ ይላል ብርሀኑ “አቢዮት እንዴት መካሄድ እንዳለበት ወይም እንደሚኖርበት የራሴ አመለካከት ነበረኝ። በሶሻሊዝም አምናለሁ ግን ኢትዮጵያዊ ሶሻሊዝም ማዳበር አለብን። እዚህም፣ እዚያም ስህተቶች ተሰርተዋል። ነገር ግን ሶሻሊዝም ብቸኛው መንገድ ነው። ያለ ምንም ምክንያት ቢሆንም ዘጠኝ ወር መታሰሬ ፀረ–አብዮተኛ ሊያደርገኝ አይችልም።” ለሱ ሶሻሊዝም “ሀይማኖት” ሳይሆን ለማህበራዊ እድገት መፍትሔ ነው። በ1973 ዓ.ም ሁለተኛው ክፍል የ"ማዕበል"በ10,000 ቅጂዎች ታትሞ ሲሰራጭ እንደ መጀመሪያው ሁሉ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠበቀው።በዚህ ወቅት የመጀመሪያው "ማዕበል" በሬዲዮ እየተተረከ ነበር (ቅጽ ሁለት እና ሶስትም ዘግየት ብለው ተተርከዋል )
ብርሀኑ ሶስተኛውን ቅጽ መፃፍ ከመጀመሩ በፊት ለዚሁ ለመጽሀፉ ሲል ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ወሎ ለመጓዝ ተነሳ።ኩታበር እያለ አንዳንድ ፀረ–አብዮታዊ እንቅስቃሴዎች ይካሄዱ ጀምረዋል። መሆነኛም ላይ እንደዚህ ያለ እንቅስቃሴ ነበር። እንቅስቃሴዎቹ በቀድሞ ባለስልጣናት የሚመሩ ሲሆን 20,000 ያህል ሰዎች ተሳትፈውበታል።“ትልቅ ጦርነት ነበር” ይላል ፤ እሱም ሁኔታዎችን እየታዘበ በኩታበር ለአንድ ወር ያህል ቆየ። ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ "ማዕበል" ቅጽ ሶስትን አጠናቀቀና በ1974 ዓ.ም ታተመ።ልክ እንደ ሁለቱ ቀደምት ቅፆቹ ሁሉ ይኼኛውም ደህና ተቀባይነት አገኘ። ነገር ግን ሶስቱ የ"ማዕበል" መጽሐፍቱ ተሰብስበው ያለፍቃዱ ወደ ሩስኪ በመተርጎማቸው ተበሳጭቶ ነበር።
.
.
.
.
.
Reidulf Molvaer ሬዱልፍ ኬ ሞልቬርን በጣም አመሰግናለሁ። ስለ ማዕበልም ሆነ ስለ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ደራሲያን እና ስራዎቻቸው በአግባቡ የተሰነደ መረጃ ከሚገኝባቸው ጥቂት መዛግብት መካከል ዋንኛው እርስዎ የጻፉት Black Lions ወይንም እኔና ጓደኛዬ Ephrem Jemal Abdu ኤፊ የተረጎምነው ጥቋቁር አናብስት ነው።
Endalegeta Kebede እንዳለጌታ የበአሉን ባዮግራፊ ሰፊና ጥልቅ ምርምርና ጥናት አድርገህ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ እንደጻፍክ የብርሃኑ ዘርይሁንንም ብትደግምልን ሁላችንም አንባቢዎች ደሲለናል። ብርሃኑ የታንጉት ሚስጥርን የሚያክል ግዙፍ ታሪካዊ ልብወለድ ያቀበለን ግሩም ደራሲ ነው። ብርሃኑና በአሉ የአማርኛ ልብወለድ ዘመናዊ አጻጻፍ ቀያሾች ናቸው።
በመጨረሻ የሀሁ መጻህፍት መደብር ባለቤት Fantahun Abie ፋንታሁን የምትፈልጉትን መጽሀፍ ጠይቁት። በደስታ፣ በቅልጥፍና በቅናሽ ያቀርብላችኋል።
በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦
የቆዩ እና አዲስ
መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ
ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ
የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ
አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን።
#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461
ብርሀኑ አሁንም የየካቲት ዋና አዘጋጅ እያለ ሁለተኛውን ማዕበል መፃፍ ጀመረ። ነገር ግን በዚህ መሀል በ1972 ዓ.ም አዲስ ስራ ተሰጠው። ስራውም የአለም አቀፉ "World Marxist Review" አማርኛ እትም ዋና አዘጋጅነት ነው። ጽሑፎቹ የሚላኩት ከፕራግ ሲሆን መጽሔቱ በወር አንዴ የሚታተም ነው። የብርሀኑ ስራ ከፕራግ የሚላኩትን ጽሑፎች እየመረጠ ወደ አማርኛ መተርጎም ነበር ( በቃለመጠይቃችን ወቅት ይህንኑ ስራነበር የሚሰራው)። ስራው ብዙ ጊዜ እና አቅም የሚሻማ አልነበረም ፤ ነገር ግን በጎን ብዙ የኮሚቴ ስራ እንዲሰራይጠየቃል። ትንሽ ትንሽ መፃፍ ቢችልም፣ በብዛት የሚጽፈው ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ እስከጠዋቱ አንድ ሰአት ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ነበር።
የ"ማዕበል"ን ሁለተኛ ክፍል ከማጠናቀቁ በፊት "ሞረሽ" የተሰኘ ተውኔት ፃፈ። በ1972 ዓ.ም ተጽፎ በተስፋዬ ገሠሠ አዘጋጅነት በዚያው ዓመት መጨረሻ በብሔራዊ ቲያትር ቀረበ። በጣም ስኬታማ እና ጥሩ ተቀባይነት አግኝቶ ለሁለት ወር ያህል ታየ። በተመሳሳይ ወቅት፣ የ"ማዕበል"ን ሁለተኛ ቅጽ እየፃፈ ነበር። ይህንን መጽሐፍ በሚጽፍበት ወቅት ስለ ማህበራዊ እና አብዮታዊ ችግሮች የነበረው ንቃተ ህሊና እየጎለበተ መጣ። ነገር ግን፣ ይላል ብርሀኑ “አቢዮት እንዴት መካሄድ እንዳለበት ወይም እንደሚኖርበት የራሴ አመለካከት ነበረኝ። በሶሻሊዝም አምናለሁ ግን ኢትዮጵያዊ ሶሻሊዝም ማዳበር አለብን። እዚህም፣ እዚያም ስህተቶች ተሰርተዋል። ነገር ግን ሶሻሊዝም ብቸኛው መንገድ ነው። ያለ ምንም ምክንያት ቢሆንም ዘጠኝ ወር መታሰሬ ፀረ–አብዮተኛ ሊያደርገኝ አይችልም።” ለሱ ሶሻሊዝም “ሀይማኖት” ሳይሆን ለማህበራዊ እድገት መፍትሔ ነው። በ1973 ዓ.ም ሁለተኛው ክፍል የ"ማዕበል"በ10,000 ቅጂዎች ታትሞ ሲሰራጭ እንደ መጀመሪያው ሁሉ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠበቀው።በዚህ ወቅት የመጀመሪያው "ማዕበል" በሬዲዮ እየተተረከ ነበር (ቅጽ ሁለት እና ሶስትም ዘግየት ብለው ተተርከዋል )
ብርሀኑ ሶስተኛውን ቅጽ መፃፍ ከመጀመሩ በፊት ለዚሁ ለመጽሀፉ ሲል ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ወሎ ለመጓዝ ተነሳ።ኩታበር እያለ አንዳንድ ፀረ–አብዮታዊ እንቅስቃሴዎች ይካሄዱ ጀምረዋል። መሆነኛም ላይ እንደዚህ ያለ እንቅስቃሴ ነበር። እንቅስቃሴዎቹ በቀድሞ ባለስልጣናት የሚመሩ ሲሆን 20,000 ያህል ሰዎች ተሳትፈውበታል።“ትልቅ ጦርነት ነበር” ይላል ፤ እሱም ሁኔታዎችን እየታዘበ በኩታበር ለአንድ ወር ያህል ቆየ። ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ "ማዕበል" ቅጽ ሶስትን አጠናቀቀና በ1974 ዓ.ም ታተመ።ልክ እንደ ሁለቱ ቀደምት ቅፆቹ ሁሉ ይኼኛውም ደህና ተቀባይነት አገኘ። ነገር ግን ሶስቱ የ"ማዕበል" መጽሐፍቱ ተሰብስበው ያለፍቃዱ ወደ ሩስኪ በመተርጎማቸው ተበሳጭቶ ነበር።
.
.
.
.
.
Reidulf Molvaer ሬዱልፍ ኬ ሞልቬርን በጣም አመሰግናለሁ። ስለ ማዕበልም ሆነ ስለ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ደራሲያን እና ስራዎቻቸው በአግባቡ የተሰነደ መረጃ ከሚገኝባቸው ጥቂት መዛግብት መካከል ዋንኛው እርስዎ የጻፉት Black Lions ወይንም እኔና ጓደኛዬ Ephrem Jemal Abdu ኤፊ የተረጎምነው ጥቋቁር አናብስት ነው።
Endalegeta Kebede እንዳለጌታ የበአሉን ባዮግራፊ ሰፊና ጥልቅ ምርምርና ጥናት አድርገህ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ እንደጻፍክ የብርሃኑ ዘርይሁንንም ብትደግምልን ሁላችንም አንባቢዎች ደሲለናል። ብርሃኑ የታንጉት ሚስጥርን የሚያክል ግዙፍ ታሪካዊ ልብወለድ ያቀበለን ግሩም ደራሲ ነው። ብርሃኑና በአሉ የአማርኛ ልብወለድ ዘመናዊ አጻጻፍ ቀያሾች ናቸው።
በመጨረሻ የሀሁ መጻህፍት መደብር ባለቤት Fantahun Abie ፋንታሁን የምትፈልጉትን መጽሀፍ ጠይቁት። በደስታ፣ በቅልጥፍና በቅናሽ ያቀርብላችኋል።
በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦
የቆዩ እና አዲስ
መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ
ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ
የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ
አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን።
#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461
ጥሩ የአማርኛ መጻሕፍት (ጣመን ጣመን ድገሙን)
እነዚህን መጻሕፍት ያካተተ መደርደሪያ ምርጥ ነው።
ክፍል አንድ—ልብወለድ
1)አደፍርስ—ዳኛቸው ወርቁ
2)ፍቅር እስከ መቃብር—ሀዲስ አለማየሁ
3)ሀዲስ—በአሉ ግርማ
4)የታንጉት ሚስጥር—ብርሀኑ ዘርይሁን
5)ሌቱም አይነጋልኝ—ስብሃት ገብረእግዚአብሔር
6)ጉንጉን—ሀይለመለኮት መዋዕል
7)ግራጫ ቃጭሎች—አዳም ረታ
8)ከቡስካ በስተጀርባ—ፍቅረማርቆስ ደስታ
9)አንድ ለናቱ—አቤ ጉበኛ
10) የስንብት ቀለማት—አዳም ረታ
ክፍል ሁለት—ግጥም
1)እሳት ወይ አበባ—ጸጋዬ ገብረ መድኅን
2)ልጅነት—ሰለሞን ደሬሳ
3)የግጥም ጉባኤ—መንግስቱ ለማ
4) ኗሪ አልባ ጎጆዎች—በእውቀቱ ስዩም
5)የቅኔ አዝመራ—ከበደ ሚካኤል
6)እንጉርጉሮ—መስፍን ወልደማርያም
7)አፈር ያነሳ ስጋ—ሰይፉ መታፈሪያ
8)ፍንዳታ—ኅይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው)
9)መንገድ ስጡኝ ሰፊ—ገብረክርስቶስ ደስታ
10) እስቲ ተጠየቁ—ዮሐንስ አድማሱ
ክፍል ሶስት—ታሪክ
1)የኢትዮጵያ ታሪክ(ወደ ስምንት የሚጠጉ ሁሉም መጽሀፍት)—ተክለጻዲቅ መኩሪያ
2)የዕትዮጵያ ህዝብ ታሪክ—ታዬ ገብረማርያም
3)አጼ ቴዎድሮስ—አለቃ ዘነብ
4)የኢትዮጲያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን—ይልማ ደሬሳ
5)የኤርትራ ጉዳይ—ዘውዴ ረታ
6)አጼ ምኒልክ—ጳውሎስ ኞኞ
7)የታሪክ ማስታወሻ—ደጃዝማች ከበደ ተሰማ
8)የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1868 እስከ 1966—ባህሩ ዘውዴ
9)Ancient and Medieval History of Ethiopia —ስርግው ሀብለስላሴ
10)Church and State in Ethiopia ታደሰ ታምራት
ክፍል አራት—ትርጉም
1)ነገም ሌላ ቀን ነው—ነብይ መኮንን
2)መከረኞቹ—ሳህለስላሴ ብርሀነማርያም
3)እፎይታ—ተሾመ ዳምጠው
4)ሀምሌት—ጸጋዬ ገብረመድኅን
5)ሮምዮና ዡልየት—ከበደ ሚካኤል
6)ታራስ ቡልባ —በካፋ ሀይለ እየሱስ
7)እናት—ግእዛን የማነ
8)ሲራኖ—ባሴ ሀብቴ
9)ወንጀልና ቅጣት—ካሳ ገብረህይወት እና ፋንቱ ሳህሌ
10)ሳቤላ—ኃይለስላሴ መሀሪ
11)ካፒታል
እነዚህን መጽሀፍት ያካተተ መደርደሪያ ምርጥ ነው።