እይታችን:(ʘ‿ʘ)
459 subscribers
625 photos
48 videos
33 files
315 links
🎯@Eytachn
We can !
we can !
Don't be give up!
Download Telegram
The owner of the channel እይታችን:(ʘ‿ʘ) has accepted your ad post.

When a channel owner publishes a post, you will receive a link to the post here.

You will have 24 hours to accept or decline the ad placement.
ቆራጥ ሁን!

የትም አያደርስህም እንጂ የስሜትህ ባሪያ መሆን ቀላል ነው፤ ጊዜያዊ ደስታ የሚሰጡህን ነገሮች በጥበብ እለፋቸው፤ ለእውነተኛ ደስታህ ስትል አሁን የማይጠቅሙህን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ቦታዎች ሁሉ ከህይወትህ አውጣቸው!

የተመረዘ እጅ ወይም እግር የሚቆረጠው ባለቤቱ ስለማያስፈልገው አይደለም ግን ሌሎቹን የሰውነት ክፍሎች ስለሚመርዝ ነው፤ ስኬትና ደስታ መስዋዕትነት ይጠይቃል! ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ ቆራጥ ሁን!



ቆንጆ ምሽት ተመኘን😊


@Eytachn
ከሰው ብዙ አትጠብቁ!

ከራሳችሁ በቀር ሌላ ማንም የላችሁም። አንድ ሰው መጥቶ ችግሮቻችሁን እንዲፈታ እንዲረዳችሁ እየጠበቃችሁ ከሆነ፣ የራሳቸውን ችግሮች በመፍታት እንደተጠመዱ እና ስለእእናንተ ለማሰብ ጊዜ እንደሌላቸው ይገንዘቡ። ነገሮችን ሀላፊነት በመውሰድ ተጋፈጧቸው።




ቆንጆ ቀን ተመኘን😊


@Eytachn
የምትችለውን አድርግ!

አዎ ፈጣሪ ምንም እንኳን ሁሉንም ነገሮች የመቀያየር አቅምና መብት ቢኖረውም እንዲሁ ግን አይቀያይራቸውም።

እያንዳንዱ አዚህች ምድር ላይ ለሚቀያይራቸው ወይም እኛ ህይወት ውስጥ ለሚፈፅማቸው ነገሮች ሁሉ ምክንያት ይኖረዋል። ይህም ማለት ያንተንም ህይወት ከነበረበት እንዲቀየር ፈጣሪ ካንተ ሁለት ምክንያት ይፈልጋል።

1.የምትችለውን መጣር እና

2.ወደ ሀያሉ መማፀን

እነዚህን ማድረግ ስትጀምር ፈጣሪ ህይወትህን ይቀይረዋል።



ቆንጆ ምሽት ተመኘን😊


@Eytachn
    "የማትቆይ ከሆነ አትጠጋ"
🍂



@Eytachn
የደስታህ ምንጭ የምትሞላውና ሳታቋርጥ የምትፈሰው ከውስጥህ በሚፈልቁ ብሩህ አስተሳሰቦችና ስሜቶች ነውና ለአስተሳሰብህ እድገትና ለስሜትህ ስክነት ትኩረት ስጥ!።


ቆንጆ  ምሽት ተመኘን


@Eytachn
እንዴት አነጋችሁ ቤተሰቦቻችን 🥰
➨ ሰው ቢጠላህ
➨ ከአንተ በላይ ሌሎንነ ነገሮችን ቢያስበልጡ
➨ ስለአንተ ግድ ካልሰጣቸው አትጨነቅ

ስለሰው መጨነቅ ማቆም አለባችሁ ፤ አለበዚያ ግን እስከ ዕለተ ሞትህ ድረስ የህሊና እስረኛ ሆነህ ትቀመጣለህ ።

ስለዚህ ጀግኖችና አንተ ራስህን ማወዳደር ያለብህ ከራስህ ጋር ብቻ ነው ፤ እንደ ሰነፍ እና ጅል ሰው ራስህን ከሰው ጋር አታወዳድር ፤ ምክንያቱም አንተ ውስጥ ከባድ እና ማንም መቋቋም የማይችለው ትልቅ ሀይል አለ ።

ሁልጊዜም ራሳችሁን ከ ራሳችሁ ጋር አወዳድሩ። 💪



ቆንጆ ቀን ተመኘን😊


@Eytachn
ወዳጄ ሆይ! ስለተደረገልህ እንጂ ስላልተደረገልህ፣ ሰለተሰጠህ እንጂ ስለተነፈገህ፣ስላስደሰቱህ እንጂ ስላስከፉህ፣ ስለሚወዱህ እንጂ ስለሚጠሉህ፣ ለሌሎች ማድረግ ስለሚጠበቅህ እንጂ ለሌሎች ስላደረክላቸው፣ ስለ ትልቁ ህልም እንጂ ስለሚገጥምህ አቧራ ችግር ፣ስለ ነገህ እንጂ ስለትናንትህ አብዝተህ አትጨነቅ!! በመጨነቅህ የምታተርፈው እንዳች በጎ ትርፍ የለም!።በመጨነቅ የምታገኘው ደስታህን፣ ህልምህን፣ ሰላምህን፣ ነገህን መቀማት ነው! ተው በቃህ! አሉታዊ እያሰብክ የምትፈልገውን አዎንታዊ ህይወት እዲመጣልህ አትጠብቅ! በሃሳብህ የሌለ አዎንታዊ ህይወት በተግባር እንዴት ይገለጣል ብለህ ትጠብቃለህ?!ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! የሀሳብህን ፍሬ እንድትበላ ቀና ቀና አስብ ለነገሮች የምትሰጠው ትርጉምም አዎንታዊ ይሁን!:

ለምታነቡት ለሁላችሁ መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ!




@Eytachn
ተሳስታችኋል!

•  አንድ ሰው ትቷችሁ ስለሄደ ብቻ ከዚያ ሰው ውጪ መኖር እንደማትችሉ የምታስቡ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

•  አንድ ሰው ስለጎዳችሁ ብቻ ሰው ሁሉ ሊጎዳችሁ እንደሚችል ወደማመን ፍርሃት የመጣችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

•  አንድና ሁለት ነገሮች ስላልተሳኩላችሁ ብቻ ስኬተ-ቢስ እንደሆናችሁ አምናችሁ ተቀብላችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

•  ፈተናን ስለወደቃችሁ ብቻ ውዳቂ እንደሆናቸው ወደማሰብ መጥታችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

•  አንድ ሰው ወይም ሁኔታ ስላስቆሟችሁ ብቻ ወደፊት መቀጠል እንደማትችሉ ወደማመን ዝቅታ ወርዳችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

ፈጣሪ የሰጣችሁ ሕይወት ከየእለት የልምምድ ውጣ-ውረዳችሁ በላይ ነች . . . ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ፣ ከሚያስቡባችሁና ከሚያወሩባችሁ በላይ ነች . . . ከሆነላችሁና ካልሆነላችሁ ነገር በላይ ነች . . . ከተሳካውና ካልተሳካው ነገር በላይ ነች!

ሕይወታችሁ የሚሽከረከረው ከሰዎችና ከሁኔታዎች መለዋወጥ አንጻር ወደሆነ ሕይወት የወረዳችሁ ጊዜ የስህተትን ሁሉ ትልቅ ስህተት እንደሰራችሁ አትዘንጉ፡፡

©Dr.eyob




ቆንጆ  ቀን ተመኘን😊
                             

@Eytachn
👉በራስህ ማድረግ በምትችለው ነገር ላይ እርግጠኛ ሁን። ውጤታችን የሚረጋገጠው በራሳችን ጀምረን በራሳችን ማስቀጠል በምንችለው ጉዳይ ላይ ብቻ ነው። የሰዎችን መምጣት እና መኖር የሚፈልግ ማንኛውም የስኬት መንገድ ቀጣይነቱ አይታወቅም። ሰዎች አብረውህ ቢኖሩም ባይኖሩም በራስህ ማስቀጠል እና መራመድ የምትችልበት የስኬት መንገድ ላይ መሆንህን ቆም ብለህ ማስተዋል አለብህ።



ቆንጆ ቀን ተመኘን😊



@Eytachn
የእናንተ ምክንያት ምን ይሆን ?
👉ነገሮችን ላለመከወን እና ውጤታማ ላለመሆን የምትደረድራቸው ምክንያቶች ምን ይሆኑ? ፦ ሀገር ? ፣ ድህነት፣ የፍቅረኛ ማጣት ? ወይስ ሌላ።

እነዚህ ሁሉ ግን አካለ ጎዶሎ ሆኖ ከመፈጠር ይብሱ ይሆን ? ምክንያቱም አካለ ጎዶሎ መሆን ሙሉ በሙሉ አይምሮህን የመቆጣጠር እና የመጣል አቅም አለው። ነገር ግን ሰው ምንም ነገርን ማድረግ ከፈለገ ከማድረግ ወደኋላ የማይል ፍጥረት መሆኑን በዚህ ምስል መረዳት እንችላለን።

የሰው ልጅ ከፈለገ ብቻ ተአምረኛ ከፈለገ ብቻ ደግሞ ሰበበኛ መሆን እንደሚችል መማር እንችላለን።
ለእናንተ ወደኋላ መቅረት እንደምክንያት የምታነሱት ነገር በሙሉ በአይምሮ መቀጨጭ እና ስንፍና የተነሳ እንጂ ውጫዊ ሁኔታው ስላልፈቀደላችሁ አይደለም።



ቆንጆ ቀን ተመኘን😊

@Eytachn
What's your reason ?
What are your reasons for not doing things and not being effective? : Country ? , Poverty, the loss of a lover ? Or else.

Will all of these be disabled ? Because being disabled has the potential to completely control and discard your mind. But in this image we can understand that if a man wants to do anything, he is a creation that does not hesitate to do.

We can learn that only if human beings want a miracle, and only if they want a preacher.
For you, all that you are looking for is because of your insecurities and laziness, not because your external circumstances allow you.



Wishing us a beautiful day😊

@Eytachn‌‌
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ብልጽግና ዛሬን ብቻ ሳይሆን ትውልድን አስቦ በኢትዮጵያ ልክ ትልቅ አድርጎ የሚሰራ ነው።
ከልክ በላይ አታስቡ

በህይወታችን ውስጥ ብዙ ውጣውረዶች ይገጥሙናል ነገር ግን ብዙወቹ በምናባችን የምንፈጥራቸው ችግሮች ናቸው:- የምጀምረው ንግድ ቢያከስረኝስ፡ከቤት ኪራይ ቢያስወጡኝስ፡ አለቃዬ ከስራ ቢያባረኝስ፡ በትምህርቴ ጥሩ ውጤት ባላመጣስ፡ ተመርቄ ስራ ባጣስ እና ሌሎችን ጥያቄወች ለራሳችን በመጠየቅ ስለማናቀው ነገ በመጨነቅ ነው ችግሮቻችንን የምናባብሰው።

ችግራችንን ልናልፍ የምንችለው ነገር በፍርሀት በመጠበቅ ሳይሆን ዛሬን በአግባቡ በመኖር ብሩህ ነገን ለመፍጠር ብቁ ስንሆን ነው። ዛሬ ላይ ትክክለኛ ነገርን እያደረክ እና በትክክለኛው መንገድ እየተጓዝክ ከሆነ ስለ ነገ አትጨነቅ!




ቆንጆ ምሽት ተመኘን😊



@Eytachn
ታልፈዋለህ!

በህይወት እስካለህ ድረስ ብዙ መሰናክሎችን ማሳለፍህ አይቀርም
ሁሉም ነገር የሚከሰተው በምክንያት ነው ብዬ አምናለሁ

እነዚህ መሰናክሎች እንዲያዋርዱህ አትፍቀድ። አንተ በጣም ጠንካራ እና ያሰብከውን ማንኛውንም ነገር ማሳካት የምትችል ነህ። መቀጠል ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ግን በመጨረሻው ዋጋ እንደሚሆንህ ቃል እገባልሃለሁ።

በጣም ብዙ አቅም አለህ፣ እና ያንን ማየት መቻል አለብህ። በራስዎ ማመን እና አጽናፈ ሰማይ ለእርስዎ እቅድ እንዳለው ማመን  ያስፈልግሀል። ወደፊት መግፋትህን ቀጥል፣ እና ማንም ወይም ምንም ነገር እንዲያደናቅፍህ አትፍቀድ።

ያስታውሱ ፣ እያንዳንዱ ውድቀት ለስኬት መወጣጫ ብቻ ነው። ከስህተቶችህ ተምረህ በርትተህ ትመለሳለህ። አንተ ተዋጊ ነህ, እና በመጨረሻ እንደሚሳካልህ አልጠራጠርም።

ስለዚህ መጥፎ አስተሳሰቦችህን አስወግድና በአዲስ መንፈስ ጀምር። የሚያጋጥሙህን ተግዳሮቶች በሚገባ ተጋፈጣቸው። ይህን አድርግና ለምን እንደተፈጠርክ ለአለም አሳይ!



ቆንጆ ቀን ተመኘን😊



@Eytachn
ወደኃላ አትመለስ!

ብዙዎቻችን ወደፊት መመልከት አቅቶን በትናንት እኛነታችን ውስጥ ነን።ትናንት ያሳለፍናቸው የማይሆኑ,ጊዜያችንን የበሉብን,በሱስ የተጠናወትንባቸው ጊዜያቶች አሁንም ነጋችንን እንዳንኖር እያደረጉን ነው ያሉት።

ሁሌም አንድ ነገር አስታውስ አንድ ህይወት ቢቻ ነው ያለችህ። ትላንትናህ ጥሩ ካልነበር ዛሬን ለመኖር ሞክር,ዛሬም ምንም ፈተናዎች ቢበዙብህ ነገን አስብ።ሁሌም አንዲት የመኖር እድልህን በአግባቡ ተጠቀማት።

              

ቆንጆ ምሽት ተመኘን😊


@Eytachn
የምትፈልገውን ህይወት ለመፍጠር ጊዜህን ካልሰጠህ ውሎ አድሮ ከማትፈልገው ህይወት ጋር ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ ትገደዳለህ።



ቆንጆ ቀን ተመኘን😊


@Eytachn