Eyoha Tv
10.8K subscribers
4.87K photos
488 videos
4 files
2K links
Join Eyoha Tv https://www.youtube.com/@eyoha24
|Make Change Happen with Your Phone!
Download Telegram
ጣሊያን ጾታን መሰረት ላደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ የሚውል 4.7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ሰጠች

#በኢትዮጵያ በሶስት ክልሎች ተግባራዊ ለሚደረግ ጾታን መሰረት ላደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ የሚውል የአራት ነጥብ ሰባት ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የጣሊያን መንግስት ማድረጉ ተገለጸ።

ድጋፉ በተለይም በግጭት በተጎዱ ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከጾታዊ ጥቃት፣ የአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ሁሉን ያማከሉ፣ ተደራሽነት ያላቸው እንዲሆን ለማስቻል የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ መፈራረማቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። (አዲስ ስታንዳርድ)
ጃዋር የመከላከያ ጄነራሎች ለድርድር ለመቀመጥ ለፋኖ ያደረጉትን ጥሪ፣ የፋኖ አመራርና የአማራ አክቲቪስቶች እንደበጎ እርምጃ እንዲመለከቱትና ለጥሪው ምላሽ ቢሰጡ ለሰላም አማራጭ ይሆናል ሲል በግል የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ ገለፀ።
መከላከያው እየተፈጠረ ያለውን ችግር በቅርበት የሚያውቅ በመሆኑ፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ጥሪ ማቅረቡ መበረታታት አለበት ብሏል። ከኦነግ ሸኔ ጋርም ሰላም ለመፍጠር ለሁለት ጊዜ የተደራደረው መከላከያው ነው ብሏል።
በቦምብ የተመቱት የጦር አዛዦች

በባህርዳር አቅራቢያ ፋኖ በወሰደው ኦፕሬሽ 52 የአገዛዙ ጦር አዛዦች በቦምብ መመታታቸው ተነገረ
የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለጦር የአሳምነው ጽጌ ብርጌድ በባህርዳር አቅራቢያ በደብረማይ ከተማ በወሰደው የተሳካ ኦፕሬሽን ከ52 በላይ የብልጽግና ጦር አመራሮች ተገድለዋል፡፡
በዚህ ኦፕሬሽን ፋኖ በፈጸመው የቦምብ ጥቃት የክፍለጦርና ብርጌድ አመራሮችን ጨምሮ  ከ52 የማያንሱ አመራሮችን ህይወታቸው አልፏል፡፡

ኦፕሬሽኑን በማስመልከት ማብራሪያ የሰጠው የአማራ ፋኖ በጎጃም አሳምነው ጽጌ ብርጌድ አመራር “በትናንትናው እለት ከጠዋቱ 12 ፡00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ ውጊያ ነበር” ብሏል፡፡
“በውጊያውም የአገዛዙ ጦር ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዷል ፤ መሳሪያ ማርከናል ፣ የአድማ ብትና እና የመካለከያ አባላትን በምርኮ ይዘናል” ሲል ገልጿል፡፡ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብልጽግና ጦር መደምሰሱንም ተናግረዋል፡፡

በዚህ በልዩ ኦፕሬሽን በተካሄደው ውጊያም ብልጽግና በአካባቢው ያሰፈረውን ወታደር የሚመሩ አዛዦች መደምሰሳቸውንም ተናግሯል፡፡ በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ጦርም ከወራት በፊት ያሰራቸውን የፋኖ ቤተሰቦች ከእስር አውጥቶ መረሸኑንም አመራሩ ተናግሯል፡፡ሮሃ
Tingirtu Gebretsadik Tekle

ወታደር መሩን የሰላም offer እንደዋዛ አትዩት ብትቀበሉት ይጠቅማል አለ አሉ አንዱ እዚህ መንደር። በወታደሩ በኩል የቀረበች የግልና የቡድን የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈፀሚያ ሰነድ ስለመሆኗ ምንም ጥርጥር አልነበረኝም።
ጥቂት ነጥቦች፦
አንደኛ፦ ENDF የሚባል ተቋም officially የለም። በፊትም ስለመኖሩ አላውቅም። ያለው አንድን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ፣ የጠላትን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ጥቃት ለማስፈጸም የሚተገባ ከአንድ ብሔረሰብ በተወጣጣ ኤሊት የተጠለፈና የሚዘወር የጥፋት ኢንደስትሪ ነው። Its not END, its your privately owned killing machine!
ሁለት፦ በምን ስልጣንና አግባብ ነው ወታደር የፖለቲካዊ መፍትሔና ፖለቲካ መር ሂደት ተሳታሳፊና መሪ የሆነው? የትኛው ወታደር? የማን ወታደር? የትኛውን የፖለቲካ ሀይል ወክሎ? በዚህ ልክ ወታደርና አገዛዙ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ የሆኑበት የፖለቲካና ወታደራዊ field በዛው በናንተው ወረቀት እንኳን ቢመዘን ትርጉም ይሰጣል ወይ?
ሶስት፦ Militarization of society ተፈጥሯል። Demilitarized ካልሆነ አደገኛ ይሆናል ብለህ በሰጠኸው አቅጣጫ መሠረት በአማራ ህዝብ ላይ ፍጹም ጦርነት ታውጆ እንሆ በውጤቱ አንተም መቃጠል ጀምረሐል። የእሳት ባህረ ነው። ሚስ ካልኩሌት የተደረገ ብቻ ሳይሆን ለውድቀት የታቀደ ነበር። እንሆ ዛሬ ከቋመጣችሁለት ስርዐት አልፎ ሀገርን ይዞ ሊወድቅ ከጫፍ ደርሷል። ዛሬስ አማራ Demilitarized ሆነ? ትናደዳለህ እንጂ አትጸጸትም አውቃለሁ!
አራት፦ ፕሪቶሪያ የናንተው የአያቶላዎቹ design ነበር። የትግራይ ሰላምም ጉዳያችሁ አልነበረም እናውቃለን። በውጤቱም ከትግራይ ሰላም ይልቅ በአማራ ላይ ለሚታወጅ ጦርነት አለማቀፋዊ ሽፋን ይሰጥልናል በሚል ደስታ በወቅቱ ተፍከነከናችሁ ነበር። በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም የማይሰፍንበትን ሁኔታ በቋሚነት የማይቻልና የማይታሰብ እንዲሆን ተረባረባችሁ። በፕሪቶሪያ ስም አማራን መውጫ መግቢያ አሳጥተን ከተለያየ ቦታ በምንሰበስበው ገንዘብና የደሃ ልጅ ደም በር ዘግተን ድምጽ አጥፍተን እናጸዳዋለን ነበር እቅዳችሁ። ያሰባችሁት ውጤት አመጣ ወይስ ምን ሆነ? አላመጣም። ከስህተቶች ሁሉ የከፋው አማራውን ከወታደሩ ጋር ያጋጫችሁት እለት ነበር። ለአማራው ወታደሩ ላይ መተኮስ በመጀመሪያ ቀላል ጉዳይ አነበረም። ውሎ አድሮ ግን የገባው ሀይል ወታደር አለመሆኑን ከተግባሩ ሲረዳ ግን ከእንቅልፉ ባነነ። በዚህ ረገድ ለአማራ ውለታ ዋላችሁለት ማለት ይቀላል።
አምስት፦ የአማራ ፋኖ ይህንን ወታደር መር የፖለቲካ የድርድር ጥያቄ ለመቀበል ማጤን አለበት የሚለው ምክረሀሳብ ለአማራ በመቆርቆር የተደረገ ዲስኩር ወይስ ዛሬም በዛው የንቀት አባዜህ ውስጥ ነህ? ግልጽ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ሲፈናቀልና ሲገደል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአማራ ልጅ ሲታሰርና ሲታደን እንዲሁም አጠቃላይ በጦርነቱ ሂደት ውስጥ ወታደሩን የሚዘውሩ ረጃጅም እጆችን ስንመለከት መችና እንዴት እንደምትናገር ተጠባቂ ነበር። ያ ረጅም እጅ በአንድ በኩል ወታደር፣ በሌላ በኩል የፖለቲካ ቁማር ተዋናይ ሆኖ መቀጠል ይችላል ብለህ ነው? እንጃ!
ስድስት፦ የአማራ ህዝብ አንተና የጦርነት ምክረሀሳብህን እየተዋጋ ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ፣ ታሪክና እና ስነልቦና ተቆጣጥረናል የምትል እብሪት በየለቱ የፖለቲካ ቁማሩን እንድትበሉ አንድ ምክንያት ሆኗል። አማራውን አንገት ለማስደፋት ያደረጋችሁት ነገር ሁሉ ውሎ አድሮ ውጤቱ ጥፋት ሆኗል። በአንተ የቸሸነፈ የጦርነት ምክረሀሳብ ውስጥ ያንተን የተሸነፈ ወታደር መር የድርድር ሀሳብ በመቀበል አማራ አንተን ከሽንፈት እንዲያድንህ መጠበቅህ አስገርሞኛል። አማራ ከፈጣሪው በታች በማንም ላይ ባለመንጠላጠል የሚያደርገውን ይሄን ታሪካዊ ተጋድሎ መችና እንዴት እንደሚያስፈጽመው ያውቃል። የዚህን የህልውና ተጋድሎ ግብ አማራ የሆነ ሁሉ ይገነዘበዋል ብዬ አምናለሁ። ራሱ አማራው ውጤቱንም ሆነ ሂደቱን የሚወሰንበት ታሪካዊ ዘመን ላይ ነን። የአንተ ምክረሀሳብና የፖለቲካ ቁማር እዛው እነተመስገንና እነ አገኘሁ ተሻገር ላይ ቢበቃ እላለሁ። በአማራና በብአዴን መካከል ምንም የስጋም ሆነ የእውቀት ግንኙነት እንደሌለ አልተረዳህም ማለት ነው።
ይህ የአማራ ትውልድ ሌላ ነው ስልህ። የአማራ ህዝብ ተጋድሎ የአማራ፣ በአማራ እና ለአማራ ነው።
ጫ በል ለማለት ኖ!
7 ቀን ብቻ ቀረው
🎁 ፍጠኑ: 💥 የማስታወቂያ ገንዘብ እየሰጠ ነው። 🎁🎁
Hamseter kombat ያልጀመራችሁ 7 ቀን ብቻ ቀርቶታል ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ቶሎ ጀምሩ የዛሬውን የ5 million coin ኮምቦ ውሰዱ👇👇
https://t.me/hamster_komBat_bot/start...
🔥የአማራ ፋኖ በጎጃም  ‼️

ከዛሬ ጀምሮ ጎጃም ምድር ምንም አይነት የህዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘመቻ መመርያ ሀላፊዉ ለንስር አማራ ገለፁ‼️

ጠላት የመጨረሻ ዘመቻ በሚል በደጀን በረሀዉን ተሻግሮ ወደ ጉብያ በረሀ በረከት ያለ ሀይሉን አስገብቷል። እየተንቀሳቀሱ ያሉት በወታደራዊ ቋንቋ ከበባ በመፈፀም በየትኛውም ስትራቴጂ በአካባቢው የሚገኘዉን የዛምብራ ብርጌድን ለመደምሰስ መሆኑን መረጃዎች አስቀድመው ደርሰዉናል። እኛም ከበባዉን በመጣስ ብቻ ሳይሆን የሚመጣውን ጠላት ለመመከት ዝግጁ ነን። የአማራ ፋኖ በጎጃም ፈጣን የሆነ ወታደራዊ መመርያ አዉርዷል። ሁሉም ክፍለጦሮች በተጠንቀቅ ቁመዉ መመሪያ እንዲጠብቁ ተደርገዋል። በየቀጠናው ያለውን የጠላት አሰላለፍ ግምት ዉስጥ ያስገባ ስምሪት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በጎጃም አካባቢ ምንም አይነት የትራንስፖርት የተዘጋ መሆኑን እየገለፀን አሽከርካሪዎች የመኪና ባለንብረቶች ትዕዛዝ በመተላለፍ ለሚደርስባቹህ ማንኛውም አይነት ቅጣት ሀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናሳስባለን።
   

የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘመቻ መመርያ
      አበበ ሰዉመሆን
7 ቀን ብቻ ቀረው
🎁 ፍጠኑ 👉 የማስታወቂያ ገንዘብ እየሰጠ ነው። 🎁🎁
Hamseter kombat ያልጀመራችሁ 7 ቀን ብቻ ቀርቶታል ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ቶሎ ጀምሩ የዛሬውን የ5 million coin ኮምቦ ውሰዱ👇👇
https://t.me/hamster_kombAt_bot/start?startapp=kentId521700989
273,000 የታጠቀ ኃይል
አስከ 34 ታንኮች
ሌሎች ከባድና ቀላል መሣሪያዎችን የታጠቀው ህወሓት
ትግራይ መከላከያ ኃይል
Army mechanised
የውጭ ግንኙነት ቢሮ ከፍቶ ያለው  ቡድን
በቅርበ ጊዜ ወረራ 50ሽህ ሕዝብ ያፈናቀለው ድርጅት

በሰላማዊ ትግል ፖርቲ እንዲመዘገብ ብልጽግና ደብዳቤ ጽፏል።

የኦህዴድ-ብልጽግና የፖለቲካ ኢምፓዬር ህወሓት ባለው ወታደራዊ አቋም ቀጥታ ስጋቴ አይሆንም በሚል እንዲመዘገብ ያደረገው በምዕራባዊያን ጫና ህወሓት መሬት ላይ ባለው አቅም ብቻ ነው ብሎ መውሰድ ቢቻልም በዋናነት ግን የጋራ ጠላት በሚሉት የ"ዐማራ" ትግል ላይ ደራሽ ታክቲካል ግንባር መፍጠር መሆኑም ቀላል ግምት የሚሰጠው ሃሳብ አይሆንም።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃውሞ ያስነሳባቸውን "የግብር ማሻሻያ" እቅዳቸውን መሰረዛቸውን ለመላው የኬንያ ህዝብ አሳወቁ።

በ106 የተቃውሞ ድምጽ፣ በ195 አብላጫ ድምጽ በኬንያ ፓርላማ የጸደቀውን የግብር ማሻሻያ ዕቅዳቸው በኬንያ ሕዝብ ጠንካራ ተቃውሞ ምክንያት ለደም መፋሰስ ያበቃ ተቃውሞ ከተደረገ በኋላ በፓርላማ ጸድቆ አልፎ ለፊርማ ፕሬዘዳንቱ ጋር የመጣውን ዐዋጅ አልፈርምም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ "እኔ ሕዝብን ልመራ ነው በሕዝቤ የተመረጥኩት፣ የመረጠኝ ሕዝብ ከተቃወመኝ ሕዝቤን ማዳመጥ አለብኝ። ስለዚህ "ተሸንፌያለሁ። ሓሳቤንም ሰርዢያለሁ።" ብለዋል።

ሙስናን እዋጋለሁ
አላስፈላጊ የመንግስት ወጪ ቀንሳለሁ
አላስፈላጊ ድግስ አይኖርም
የውጪ ጉዞ ቀንሳለሁ
ከወጣቶች ጋር እመክራለሁ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ቃል ገብተዋል።

አዲሱ ህግ የኑሮ ውድነትን ያባብሳል በሚል የአገሪቱ ወጣቶች እያካሄዱት ባለው የተቃውሞ ሰልፍ የሰዎች ህይወት አልፏል።
ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ የላስታ አሳምነው ክፍለጦር “ዘመቻ አሳምነው ፅጌ” አውጇል፣ ሌሎቹም የፋኖ ኃይሎችም ይሄን ዘመቻ ሌሎች ዕዞችና ክፍለጦሮች እንዲቀላቀሉት ጥሪ አቅርቧል። [ethio251media]
"የአማራ ክልል ቀውስ እንዲፈታ በጦር አመራሮች የሚመራ ድርድር ዋጋ ሊሰጠው ይገባል" ጃዋር መሃመድ


ኦሮሞ ስልጣን ከእጁ እንዳይወጣ በማለት ለብልፅግናው መንግስት 77 ገፅ ምክረ ሃሳብ በማቅረብ ለጊዜውም ቢሆን ድምፁን ያጠፋ በመምሰል ሃገሪቱን ጠቅልሎ ለኦሮሞ ለመስጠት ሴራ ሲጎነጉን የሚያድረው ጃዋር መሃመድ ዛሬ ሰላም ፈላጊ በመምሰል ፋኖን ለድርድር እንዲቀርብ መለፈፉ ያስገርማል።

የቄሳርን ለ ቄሳር ፤ የእየሱስን ለእየሱስ
ሁሉንም ለአማራ ህዝብ መተው ይሻላል።

የመጨረሻውን ሳቅ የምስቀው እኛው ነው!!
የነፃነት ትግላችን መዳረሻችንም አራት ኪሎ ብቻ ነው።

ሞገሴ ሽፈራው
ሚኒስትር ዲኤታዋ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!!

ከጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሪት ሌንሳ መኮንን ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ታውቋል፡፡

የቀድሞ ሚኒስትር ድኤታዋ ቀጣይ ማረፊያ ሆነ በእርሳቸው ምትክ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ በይፋ አልተገለፀም።
የኦሮሙማው ተጨማሪ የአማራዎች የዘር ጭፍጨፋ አዎጅ...‼️

አራት ኪሎ ከመሸገው የኦነግ ብልፅግና ጋር በመተባበር "#ታሏቋ_ኦሮሚያ" የምትባል ሀገር ለማዋለድ እየሰራ ያለው ኦሮሙማ መንጋ ተጨማሪ የአማራዎች የዘር ጭፍጨፋ በኦሮሚያ እንዲፈፀም መግለጫ አውጥቷል::

በጃዋር መሀመድና ሌሎች የኦሮሙማ አካላት የሚመራው ኦፌኮ የሚባለው የኦሮሙማው ቅርንጫፍ ኦነግ ብልፅግና በሸዋ ኖኖ ወረዳ አማራዎች ላይ እያካሄደ ያለው ጭፍጨፋ ትክክል ነው ከማለትም ባለፈ በፍፁም ውሸት  አማራዎች ኦሮሞዎችን ጨፍጭፈዋል ብሏል::

ለባለፉት ሁለት ሳምንታት በኖኖ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦነግ ብልፅግና መከላከያ እና የኦነግ የጫካው ቅርንጫፍ የተጨፈጨፉና በነፍሳቸውን እንዳሉ የተቃጠሉ ሲሆን #ከ20ሺህ በላይ አማራዎች በዚህ ጭፍጨፋ ምክንያት ተፈናቅለዋል::  ይህን ለመሸፋፈንና ተጨማሪ የአማራ ጭፍጨፋዎችን ለመቀስቀስ የኦነግ ብልፅግና የአዲስ ሀገር ምስረታ #አጋር የሆነው ኦፌኮ በወለጋ ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ አማራዎችን በአስቸኳይ ሊገቱ የሚገቡ "ፅንፈኛ የፋኖ ታጣቂዎች" በማለት የኦነግ ብልፅግና እያካሄደ ያለውን የአማራዎች የዘር ፍጅት እንዲቀጥል ኦሮሙማው አዋጁን አስተላልፏል::

ብልፅግና = ኦፌኮ = ኦነግ‼️

የአማራን ነገድ አፅድቼ አዲስ ሀገር እመሰርታለሁ ብሎ በአራት ኪሎና በጫካ የመሸገው የኦሮሙማ መንጋ እስኪወገድ ድረስ #በየተኛውም ቦታ ያለ አማራ እራሱን ለመከላከልና መብቱን ለማስከበር #መታጠቅ መደራጀትና መዘጋጀት ይገባዋል‼️
"በስህተት ነው" ጠያቂ የሌለው የኛ ሃገር ፖሊስ ቅሌት!

ትላን የአዲስ አበባ ፖሊስ መኪና ሰርቃ ያዝኳት ያላት ሴት ስህተት መሆኑ ተነገረ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መኪና አስነስታ ስትሄድ ያዝኳት ያላት ግለሰብ ከራሷ አልፋ ለቤብዙዎች የምትተርፍ መሆኗ እና ፖሊስ ተገቢውን ማጣራት ሳያደርግ ማሰሩ ሳያንሰው ፎቶዋን በማህበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ ስሟን እንዳጠፋ ቤተሰቦቿ አሳውዋል።

ህግ ቢኖር የጠፋውን ስሟን የሚያስመልስ ይቅርታ እና የሞራል ካሳ ይሰጥ ነበር. ወሬውን ሲያራግቡ የነበሩ የመንግስት ተቀላቢዎች እና ካድሬዎች ነጭ ውሸቱ ሲጋላጥ ባላየ ባልሰማ አልፈውታል።

ሲጀመር ተጠርጣሪ የሆነን ሰው ምስል እንዲታይ አድርጎ መልቀቅ አይቻለም።

> መረጃው የ Solomon amare kuch kuch ነው
7 ቀን ብቻ ቀረው
🎁 ፍጠኑ 👉 የማስታወቂያ ገንዘብ እየሰጠ ነው። 🎁🎁
Hamseter kombat ያልጀመራችሁ ከመጠናቀቁ በፊት ፈጥናችሁ ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ቶሎ ጀምሩ የዛሬውን የ1 million coin ውሰዱ👇👇
https://t.me/hamster_kombAt_bot/start?startapp=kentId521700989
#BOLIVIA

ቦሊቪያ ውስጥ ወታደሮች የሀገሪቱን ፕሬዜዳንት ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው በመግባት መውረራቸው ተሰማ።

እንቅስቃሴው " መፈንቅለ መንግሥት " ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴ የሀገሪቱን ጦር " መደበኛ ያልሆነ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው " በማለት አውግዘዋል።

ወታደሮቹ በአስቸኳይ ከቤተመንግሥት እንዲበተኑ ጠይቀዋል።

በቦሊቪያ ቴሌቪዥን ላይ የተሰራጨው ቪዲዮ አርሴ ከሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋ ጋር በቤተ መንግሥቱ ኮሪደር ላይ ሲፋጠጡና ሲነጋገሩ ታይተዋል።

አርሴ ፤ " እኔ የአንተ አለቃ ነኝ፣ ወታደሮቹንም እንድታስወጣ አዝዤሃለሁ እናም ለትዕዛዜ መገዛት አለብህ !! " ሲሉ ተደምጠዋል።

ዙኒጋ ወታደሮቹን ይዘው ወደ ቤተመንግሥት ሳይገቡ በፊት ውጭ ላይ ለሪፖርተሮች በሰጡት ቃል ፥ " ማጥፋት ይቁም፣ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም ፣ ሰራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ብለዋል።

የጦሩ አዛዥ ዙኒጋ ፥ " አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ ይዋቀራል ፤ በእርግጠኝነት ነገሮች ይቀየራሉ፣ ሀገራችን ከዚህ በኋላ አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል አትችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዜዳንት አርሴ በቪድዮ ባሰራጩት መልዕክት ፥ ሀገሪቱን ከሚታየው የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ ለመታደግ ህዝቡ ተሰባስቦ እና ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና ዲሞክራሲውን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።