Eyoha Tv
1.95K subscribers
3.19K photos
284 videos
1 file
1.21K links
ለታማኝ፣ የተረጋገጡ እና ፈጣን መረጃዎች t.me/eyohatv - Facebook.com/eyohatv - youtube.com/@eyoha24
Download Telegram
#ሰበር
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል።

የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም።

ምንጭ፦ የማህበረ ቅዱሳን የፌስቡክ ገፅ
ሰበር የድል ዜና !!!

በወሎ ግንባር የሁለቱን ግዙፎች ዕዝ አንድነት ተከትሎ አማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ለሶስተኛ ቀን የቀጠለው ዉጊያ ድል በድል ሆኖ ቀጥሎል አማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አድማሱን በማስፋት ብዙ ታላላቅ ከተሞችን ከብልጽግናዉ አገዛዝ ነጻ እያወጣ ነው ትላንት በማለዳው 11ስአት አራዱም እና እራያ ቆቦን ከብልጽግናዉ አገዛዝ ለማላቀቅ ታላቅ ትንቅንቅ ላይ ነው።

የብልጽግና ምጣፍ ጎታች ቆቦ ከተማን እየለቀቀ እየወጣ ነው !!! ፋኖ ቆቦ ከተማ እየተቆጣጠረ ነው !!! አሁን ዉጌው ከተማላይ ነው ዋናው ከ አ አ መቀሌ የሚወስደው የፌደራሉ ጥቁር አስፓልት በፋኖወች ቁጥጥር ገብቶል።
በጎንደር ቀጠና በሊቦከምከም ወረዳ ሚካኤል ደብር በተባለ ቦታ ከባድ ውጊያ ሲደረግ አርፍዷል። በውጊያው መከላከያ በ Zu-23 ዲሽቃ ሞርተር ጨምሮ ሌሎች መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውሏል።

ከከባድ መሣሪያ ድብደባ ባሻገር በደፈጣ እና በጨበጣ የተደረገው ውጊያ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት አስከትሏል።

የአካባቢው የፋኖ ተወካይ በውጊያው በርካታ የመንግሥት ኃይሎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ተናግሯል። አክሎም 27 ወታደሮች መያዛቸውን አንድ ድሽቃ ጨምሮ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች በእጃቸው እንደገቡ ገልጿል። ሁለት ወታደራዊ ፒካፕ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ብሏል።
መረጃ 

ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጸሐፊነት በቅርቡ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ተደርገው የተዘዋወሩት ወንድማችን ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተ/ያሬድ በዛሬው እለት በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደዋል!

የመምህሩን አገልግሎት ለማደናቀፍ ሰሞኑን ብዙ ድርጊቶች ሲፈጽሙባቸው የነበረ ሲሆን ከዚህ ጀርባ እነማን እንዳሉ ደግሞ ግልጽ ነው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዐምሓራ ሳይንት(የጥንቱ ቤተ ዐምሓራ) የምትገኘውን  ጥንታዊቷ  የተድባበ ማርያም ገዳም ውድመት ሊደርስባት ነው።

የመንግሥት ወታደሮች የጦርነት ሕግ በመተላለፍ ደብረ ኤሊያስ ገዳም የፈፀሙትን ገዳም የመዝረፍ የማውደም እና መነኩሳትን መግደል ተግባር ሊፈፅሙ ወደ ገዳሙ በከባድ መሣሪያዎች በመታገዝ ከበባ አድርገዋል የሚል መረጃ ከአካባቢው ነዋሪዎች የመጣ ነው።

ድምፅ ሁኑን ይላሉ የገዳሙ አባቶች!
"ማንም ፈቅዶ የሰጠን መሬት የለም፤ ማንም ፈቅዶ ለእነሱም የሚሰጣቸው የለም። ከዚህ በኋላ በዚች አገር ላይ ሞተን እንቀበራለን እንጅ ለማንም አሳልፈን አንሰጥም፡፡ ፌደራል ተናገረ ማለት እግዚአብሔር ተናገረ ማለት አይደለም። "

አቶ አታላይ ዛፌ- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል ከሁመራ ለ ኢ ኤም ኤስ የተናገሩት።
የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ጀብዱዎች !

ታላቅ ውህደት የፈፀመው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ወደ ራያ ቆቦ ከተማ መግባቱ ተሰማ
የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የወሎ እዝ ጥምረት በፈጠሩ ማግስት የብልጽግናን ጦር የፈረካከሱ ታላላቅ ጀብዱዎችን እየተፈጸሙ ነው፡፡
ከወልዲያ እስከ ቆቦ ፣ ከመርሳ እስከ ወግዲ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን የብርሃኑ ጁላ ጦርም የወሎ ፋኖዎችን የህብረት ክንድ መቋቋም አቅቶት እየሸሸ ነው፡፡
ላለፉት ሶስት ቀናት በቀጠለው ጦርነት ድል በድል ሆኖ የቀጠለው የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ታላላቅ ከተሞችን ከብልፅግና ሰራዊት እያስለቀቀ መሆኑም እየተነገረ ነው።
በትናነትናው እለት ከጠዋቱ 11: 00 ጀምሮ አራዱምና ራያ ቆቦ ከተማን ከብልፅግናው አገዛዝ ለማስለቀቅ የተደረገው ትንቅንቅ በውጤት እየተቋጨ መስሏል።
በዛሬው እለት በቆቦ ከተማ እየተካሄደ ያለው ተጋድሎ የቀጠለ ሲሆን በርካታ የፋኖ ሃይልም ወደ ከተማዋ ገብቷል።
ሮሃ ቲቪ
አገዛዙ ኢትዮጵያን ሸጦም ኢትዮጵያን ያፈርሳል!!

"IMF (አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት) የኢትዮጵያ መንግስትን ካስገደደባቸው ቅደመ ሁኔታዎች አንዱ (Market liberalization) ወይም የመንግስት ድርጅቶች ወደግል ማዛወር ነው።

አገዛዙ አሁን እጁን ተጠምዝዞም ቢሆን ይሸጣል። ይህንን ካላደረገ ምንም አይነት የፋይናንስ እገዛ አያገኝም።
ሊሸጣቸው የተወሰኑ ድርጅቶች በአፈር ዋጋም ቢሆን ለግለሰቦች እንዲሸጡ ተወስኗል።

➩ Ethiopian Shipping & Logistics
➩ Ethiopian Insurance Company
➩ Berhanena Salam Printing Enterprise
➩ Education Production and Manufacturing Company
➩ Ethiopian Tourism Business
➩ Ethio Telecom 

በሙሉና በከፊል ከሚሸጡት መካከል ናቸው።
የአገር ውስጥ እና የውጭ ጦርነቶችን አዘጋጅቶ እየጠበቀ ያለ አገዛዝ በመሆኑ የግድ ተንበርክኮም አገር ሸጦም አገር ማፍረሱን ይቀጥላል።
አርቲስት አዲስአለም ጌታነህ ከ21 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተፈታለች።
በሚዲያ ዘመቻ እውነት ሊድበሰበስ አይችልም !

እን ጣሂር ሙሃመድ ተገምግመው ተነሱ እንጂ አመልክተው አልተነሱም

ከኃላፊነት መነሳት ባሻጋር የሙስና ወንጀል ምርመራ ሊጣራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ከወር በፊት ለክልሉ መንግስት በደብዳቤ አሳውቀናል !!

የክልሉን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በቢሮ ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጣሂር መሃመድ ከሰሞኑ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወቃል። በግሌ አመራር ይመጣል፤ አመራር ይሄዳል ብዬ ስለማምን በተነሱት አመራር ዙሪያ ምንም የተለየ ነገር የማለት ፍላጎት አልነበረኝም። በመሆኑም የተነሱትን አመራር ለሰጡት አገልግሎት አመስግኖና መልካም ነገር እንዲገጥማቸው በመመኘት፤ አዲስ የተሾሙትን አመራር ደግሞ እንኳን ደህና መጡ በማለት ቢሯችን የፃፈውን ዜና በግል ገፄ አጋርቼ ነበር።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሚዲያዎች "በግል ምክንያታቸው" አመልክተው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን በስፋት ዘግበው ተመለከትኩ። በአደረኩት ማጣራትም በአላማ የተሰሩ ዘገባዎች መሆኑን አረጋግጫለሁ። በሚገርም ሁኔታ ስለ አመራር መነሳት የማይመለከታቸው አንድ የቢሯችን አመራር ጭምር የመልቀቂያ ደብዳቤ የተቀበሉ ይመስል አቶ ጣሂር ከ6 ወር በፊት መልቀቂያ ማስገባታቸውን ሚዲያ ላይ ወጥተው ሲመሰክሩ ሰምቻለሁ። በሌላ በኩል ዜናውን ቀድሞ የሰራው ቢቢሲ አማርኛ ሚዲያ፣ አባይ ሚዲያ እና ሌላ አንድ ሚዲያ በትናንትናው ዕለት (ሚያዝያ 23/2016) ደውለው "ትክክለኛውን መረጃ ይንገሩን" የሚል ጥያቄ አቅርበውልኝ ትክክለኛውን መረጃ ነግሬያቸዋለሁ። ነገርግን ሚዲያዎች እስከአሁን አላስተላለፉትም።

በመሆኑም በተደራጀና የተናበበ የሚዲያ ስምሪት እውነት መደበቅ ስለሌለበት በግል ገፄ ለመፃፍ ተገድጃለሁ። ላለፈው አንድ አመት ተቋሙ በአንድ በኩል በአግባቡ እየተመራ ባለመሆኑ በሌላ በኩል ከፍተኛ የሃብት ብክነት አለ ብለን በማመናችን ተደጋጋሚ ግምገማዎችን አድርገናል። ለሁለት አመት ከ8 ወራት አዲስ አበባ ተቀምጠው በ3 ወር አንዴ እየመጡ ለዛውም ተደብቀው ገብተው ህገወጥ ድርጊት ፈፅመው ይሄዳሉ። በመሆኑም በቢሮው ማኔጅመንት፣ የዘርፍ ማኔጅመንት፣ በክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ በከተማ ክላስተር ደረጃ በርካታ ግምገማዎች አድርገናል። በመጨረሻም ከኃላፊነት እንደተነሱ ከተገለፀልን ቆይቷል፤ ደብዳቤው በእሳቸው ጥያቄ መሰረት ቢዘገይም።

ይህ ብቻ ሳይሆን ከወር በፊት የክልሉ መንግሰት ልዩ የኦዲት ምርመራ አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ ለርዕሰ መስተዳድሩ በደብዳቤ አሳውቂያለሁ። በመሆኑም ውሳኔው ከተወሰነ የቆየ ቢሆንም አንዳንድ የጥቅማጥቅም ጉዳዮችን ለመጨረስ ጊዜያቸው እንዲሞላ በጠየቁት መሰረት ጥቂት ሳምንታት በኃላፊነት እንዲቆዩ የተደረገውን የክልሉ መንግስት መታገስ Abuse በማድረግ በርካታ ነገሮችን ፈፅመዋል። ስለዚህ እውነታው [እዚህ መዘርዘር በማያስፈልግ ሌሎች ተጨማሪ በርካታ ምክንያቶች] ተገምግመው ተነሱ እንጂ በግል ምክንያት በእሳቸው ጠያቂነት አልተነሱም። ብዙ ጉዳዮችን በትዕግስት እና በጊዜ ይፍታው ስሜት በውስጥ ከመታገል ባለፈ ወደ አደባባይ ላለማውጣት በዝምታ ባልፍም አይን ያወጡ ቅጥፈቶችን ግን በዝምታ ማለፍ ተገቢ ሆኖ አልታየኝም ።

አመሰግናለሁ

አየለ አናውጤ (ዶ/ር)
የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
ም/ቢሮ ኃላፊ
ወይ ዘንድሮ መቸም የማንሰማው ጉድ የለም?
መልካም የስቅለት ቀን 🙏
መልካም ጁምአ ሙባረክ 🙏
ሰበር ዜና‼️
በደ/ጎንደር ከአዲስ ዘመን ተነስቶ ወደ ደጎማ በለሳ አቅጣጫ ሚካኤል ደብር ሲጓዝ የነበር 7 ኦራል ሙሉ የጠላት መከላከያ በተደረገ የፋኖዎቻችን የደፈጣ ጥቃት አንድም ሳይተርፍ ከእነሙሉ ትጥቁ እረግፈዋል 3ኛ ቀኑ ነው አስከሬናቸው አልተነሳም!
በአንድ ወረዳ በተመሣሣይ ቀን የአስራ ሁለት ሚሊሺያ አባለት የቀብር ስነ ሥርዓት ተፈፀመ።

በሰሜን ወሎ ዞን አሁን ተገኝ ወረዳ ተረፌ በተባለ ቦታ በተደረገ ውጊያ በርካታ የሚሊሺያ አባለት ሲገደሉ። በርካታ ቁጥር ያላቸው በፋኖ ኃይሎች ተይዘው ተወስደዋል። ከሁለት ቀናት በፊት ተረፌ በተባለች ቦታ በፋኖ ኃይሎች እና በሚሊሽያ አባላት መካከል በተደረገ ውጊያ 11 የሚሊሺያ አባላት ሲሞቱ የተረፌ ቀበሌ ሊቀመንበር እንዲሁ በውጊያ ላይ መሞቱ ተሰምቷል። 19 የሚሊሺያ አባላት በፋኖዎች ተይዘው ተወስደዋል። ፋኖዎች በዚህ ውጊያ 41 በላይ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል።
ጅማ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው ሊመልስ እንደሆነ ተሰምቷል።
የኤርትራ ባህር ሃይል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ኮለኔል መልአከ ተክለማርያም (ወዲ ፊታውራሪ) በኢሳያስ አፈወርቂ ላይ በማመጹ ወደ እስር ቤት ተወርውሯል።
የአህመድ ደጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት፣ የህወሃት ተዋጊዎች ከጄነራል ቡርሃን ጋር በመወገን ጦሬን እየወጉት ነው በማለት ከሰሰ። ይህ የሆነው የወልቃይት ጉዳይ በተባባሰበት ወቅት መሆኑ በቀጠናው ላይ የአሰላለፍ ለውጥ መከሰቱን ያሳያል።
በሶማሊያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጥቃት ደረሰበት‼️

በሶማሊያ ለሰላም ማስከበር የገባው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በባይ ክልል ዳንሶር ቀበሌ በታችኛው ሸበሌ ወንዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሊተሪ ቤዝ ላይ በደረሰ ጥቃት 8 የሚሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ያሉበት መገደላቸው ተነግሯል።

የሶማሊያ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡት ሲሆን እስካሁን ከኢትዮጵያ በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም።
ባልታወቁ ሰዎች ተመቱ

በሰሜን ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ የመሬት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ወንድማገኝ ባልታወቁ ሰዎች በሽጉጥ ተመተው ሆስፒታል ገቡ።

ግለሰቡ የፋኖ ኃይልችን ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በማሳደድ የተጠመደ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና በሸዋ ሮቢት እና በአርማንያ አካባቢ በፋኖ ኃይሎች እና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን  የደረሰ መረጃ ያመለክታል።

negede_amhara
ደብረ ማርቆስ 17 የብልፅግና አመራሮች ተይዘው 11 ተሃድሶ ተሰጥቷቸው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን 6 ቱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ናቸው !