(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 73)
----------
1፤ ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው።
2፤ እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ።
3፤ የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4፤ ለሞታቸው መጣጣር የለውምና፤ ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና።
5፤ እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6፤ ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት።
7፤ ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ።
8፤ አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።
9፤ አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
10፤ ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤
11፤ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ።
12፤ እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ።
13፤ እንዲህም አልሁ። በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
14፤ ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
15፤ እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16፤ አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።
17፤ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።
18፤ በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።
19፤ እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ።
20፤ ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።
21፤ ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤
22፤ እኔ የተናቅሁ ነኝ አላውቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23፤ እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24፤ በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።
25፤ በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ?
26፤ የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው።
27፤ እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።
28፤ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
@eyesusegziabhernewAmen

•ነቢዩ ዮናስና ምሳሌነቱ
ክፍል ፪
ነቢዩ ዮናስ የእግዚአብሔር ቃል በዘመኑ የመጣለት ነቢይ ነው።ቁ1 የእግዚአብሔርም ቃል
ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ ።” ዮናስ ማለት የሥሙ ትርጉም ርግብ
ማለት ነው። የአባቱ ሥም አማቴ “አሜት” ከሚለው ከዕብራይስጡ ቃል የመጣ ሲሆን
ትርጉሙም እውነት ማለት ነው። ስለዚህ ነቢዩ ዮናስ የእውነት ልጅ ነው። በሁለተኛ ነገስት
ላይ እንዳየነው በጋትሔፌር አገር ይኖር እንደነበር ይነግረናል። ጋትሔፌር ማለት ደግሞ
የወይን መርገጫ ወይም መጭመቂያ ሥፍራ ማለት ነው። ይህ ጋትሔፌር አገር የሚገኘው
በዛብሎን ግዛትና ከተማ ነው።ኢያሱ19፥10-14 ዛብሎን ማለት
ደግሞ ልዑል / Prince ማለት ነው።
እንደ ስሞቹ ትርጉም ነቢዩ ዮናስ የእውነት ልጅ የሆነ፣ ከእውነት የወጣ፣ ርግብ፣ ወይን
በሚረገጥበትና ገለባው ከወይኑ በሚለይበት በሰላም አለቃና ልዑል ግዛት ላይ የሚኖር
ነቢይ ነው።ይህ የሥሙ ትርጉም በራሱ ነቢዮ ዮናስን የመንፈስ ቅዱስም ጥላ
ያደርገዋል።ሉቃ 3፥22 የዚህን ነቢይ ሕይወት ታሪክ ፈጽሞ ድንቅ ነው።ዮናስ እንደ ርግብ
የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስም ጥላና ምሳሌም ነው።
በዘሌዋዊያን ምዕራፍ 14 ላይ ስለ ኢየሱስ በምድር ላይ ስለሚሰራቸው ሁለት ሥራዎች
የሚናገር በሁለት ርግቦች የተቀመጠ ትንቢታዊ ሕግን እናገኛለን።ሁለቱ ርግቦች የኢየሱስን
ሁለት አይነት መምጣት የሚያመለክቱ ናቸው።የኢየሱስ የመጀመሪያው ሆነ ሁለተኛው
ዳግም መጽዓቱ ከዚህ ሕግና ከነቢዩ ዮናስ ታሪክ ጋር ይያያዛል። አማርኛውም ሆነ
እንግሊዘኛው ዘለዋውያን ላይ ያሉት ርግቦች ወፍ ብሎ ተርጉሞታል። ነገር ግን ዋናው ቅጂ
የሚለው ርግብ ነው። ይህን ሌሎች እንደ ሕጉ የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን በማነጻጸርም
ትክክለኛው ቃል ርግብ እንደሆነ መረዳት እንችላለን።
ለምሳሌ፦ኢየሱስ በዮሐ 2፥16 ላይ በመቅደሱ ለመሥዋዕት የሚሆኑ ርግብ የሚሸጡ
ሻጮችን በጅራፍ አባሯል።ይህም በአዲስ ኪዳን ላይ የምናገኘው ታሪክ ለመሥዋዕት
በመቅደሱ መሠዊያ ላይ የሚቀርበው አንዱ ርግብ እንደሆነ የሚያመለክትና ሌላው
የትርጉም የሚደግፍ ቃል ነው። ስለዚህ ዮናስ የመንፈስ ቅዱስም እንዲሁ እንደ መሥዋዕቱ
የኢየሱስ ክርስቶስም ጥላ ነው።የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣትም ከነቢዩ ዮናስ ጋር
የተያያዘውና ለሁላችን አሁን ምልክት የሆነው ከሕጉና ከኢየሱስ ከራሱ ምስክርነት
በመነሳትና የመጀመሪያው ምጽዓቱን በእርሱ እንደ ምሳሌ ስለተገለጠ ነው።
ስለዚህ የዮናስ ትንቢት በዚህ ባለንበት ዘመን የሚፈጸምን እንዲሁም ወደ ፊት ገና
የሚጸምን ትንቢቶችን ስለያዘ አማኞች ሁሉ በጥልቀት ሊያጠኑት የሚገባ መጽሐፍ ሆኖ
አግኝቼዋለሁ።ዮናስን በእውነት/ በአባቱ አማቴ ወደዚህ ምድር መጣ። መንፈስ ቅዱስም
እውነት የሆነው ኢየሱስ ከአብ ዘንድ ተቀብሎ እንዲሁ ወደ እኛ ላከው። “33 ስለዚህ
በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን
እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።”ሐዋ2፥33 “7 እኔ ግን እውነት
እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤
እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።8 እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ
ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤9-10 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ
ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤11
ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥
ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ
እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ
አይነግርምና፤የሚመጣውንም
ይነግራችኋል። 14 እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። 15 ለአብ ያለው
ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።”ዮሐ 16፥7-15
አማቴ/እውነት ዮናስ/ርግብ ወደዚህ ምድር እንደ ወለደው። እውነት የሆነው ኢየሱስ
መንፈስ ቅዱስን ላከልን።መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግቡ ዮናስ የተላከው ስለ ኃጢአት፣ ስለ
ጽድቅም ስለ ፍርድም እዲናገር፣ እንዲወቅስ ሰዎች ሁሉ ወደ ንስሐ እውነት እንዲመራ
ነው። ስለ ኃጢአት በኢየሱስ
ክርስቶስ ስለማያምኑት አመንዝራና ክፉ ትውልድ ይወቅስና የሚመጣውንም ፍርድ
ሊያመላክት ነው።
ስለዚህ ዮናስ የእውነት ልጅ የእየሱስ ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ የእውነት መንፈስ
የመንፈስ ቅዱስም ምሳሌ ነው። ሁሉን በይበልጥ በዝርዝር ወደ ውስጥ እየገባን
በትምህርታችን ውስጥ እየተመከትነው ስንሄድ ወደ ማስተዋል እንመጣለን።
ይቀጥላል
ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ

(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 6)
----------
1፤ የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።
2፤ የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።
3፤ እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥
4-5፤ በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
6፤ ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤
7፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥
8፤ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል።
9፤ ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።
10፤ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
11፤ አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።
12፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።
13፤ ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤
14፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤
15፤ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል።
16፤ እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።
17፤ በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
18-19፤ እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው።
20፤ ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤
21፤ ይህ እውቀት አለን ብለው፥ አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን።

(ወደ ቲቶ ምዕ. 2)
----------
11፤ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
12-13፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
14፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
15፤ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።

(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 2)
----------
13፤ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
14፤ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
15፤ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
16፤ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
17፤ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
18፤ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
19፤ በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።
20፤ ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
21፤ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
22፤ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
23፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
24፤ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤*ፍ1*
25፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

"ክርስቲያን ሁልጊዜም ቢሆን አንደበቱን ለህሊናው ወይም ለአእምሮው ማስገዛት አለበት::አእምሮውን ደግሞ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ሊያስገዛ ይገባል።"ብሂለ አበው
@eyesusegziabhernewAmen
@eyesusegziabhernewAmen
<<በአባቱ ጌትነት ተነሳ በሲኦል ተግዘው የነበሩ የቅዱሳን ነፍሳት አዳነ ÷ ንጉሱ ድል የማይነሳው ገዥም ነውና በፍፁም ክብር ጌትነት ወደ ሰማይ ዐረገ ÷ በማይመረመር በማይታወቅ ምስጢር ከመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው በከበረው ስጋው ከአብ ጋር በፅሪና ተቀመጠ ።>>
ሀይማኖተ አበው ዘ ዬሀንስ አፈወርቅ
ምዕ 2:9
@eyesusegziabhernewAmen
ሀይማኖተ አበው ዘ ዬሀንስ አፈወርቅ
ምዕ 2:9
@eyesusegziabhernewAmen
<<ሀይማኖት ለሚወዱት ይገለጣል ÷ ብሩህ በሆነ በአይነ ልቦናም ያዩት ዘንድ የበቁ እንደሆነ ያስረዳል ÷ ሃይማኖትን የሚወዱ ሰወች ንፅህት በሆነችው በልቦናቸው ቅንነት የእግዚአብሄርን ነገር ይመረምራሉና ።>>
ሀይማኖተ አበው ዘ ቅዱስ ቄርሎስ ምዕ 49 :40
@eyesusegziabhernewAmen
ሀይማኖተ አበው ዘ ቅዱስ ቄርሎስ ምዕ 49 :40
@eyesusegziabhernewAmen
… እየጾምኩ ነው የሚል ሰው …
@mkreabew @mkreabew
[ተወዳጆች ሆይ!] የምታደምጡ ብቻ አትኹኑ፤ ያስተማርኳችሁን ትምህርት ለሌሎችም በማስተላለፍ መምህራን ትኾኑ ዘንድ - ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አንዱ ሌላውን ያንጸው” (1ኛ ተሰ.5፥11)፤ ዳግመኛም “በፍርሐትና በመንቀጥቀጥም የራሳችኁን መዳን ፈጽሙ” ብሎ እንደ ተናገረው በስሕተት ጐዳና ያሉትን ታድኑ ዘንድ መረባችሁን ጣሉ ብዬ እማፀናችኋለሁ (ፊልጵ.2፥12)፡፡ ይህን ስታደርጉ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትሰፋለች፤ እኛም ይህን ዐይተን እጅግ ደስ እንሰኝባችኋለን፡፡ እናንተም ለወንድሞቻችሁ፣ ለእኅቶቻችሁ ባሳያችሁት ፍቅር በሰማያት ዘንድ ታላቅ ማዕረግና ክብር ታገኛላችሁ፡፡ እንደምታውቁት የእግዚአብሔር ፈቃድ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ ራሱ መዳን ብቻ እንዲያስብ አይደለም፤ ወንድሙንም እንዲያንጽ ነው እንጂ፡፡ ሲያንጸውም በቃል ብቻ አይደለም፤ በተግባርም ጭምር እንጂ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እያንዳንዳችን በአኗኗራችን ክርስቶስን መስለን ታምነን እንድንኖርና ፍጥረት ኹሉ ወደ #እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰዎች ከምንናገረው በላይ የምንኖረውን ስለሚያምኑና ስለሚማርካቸው ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በተዋቡ ቃላት ስለ ይቅርታ ብንናገር ነገር ግን በሕይወታችን እጅግ ቂመኞችና ይቅርታን የሚቀበል ልብ የሌለን ከኾነ ቃላችንና ሕይወታችን ስላልተስማማላቸው ሰዎች የምንለውን ነገር አያምኑንም፡፡ የምንናገረውንና የምናስተምረውን የምንኖረው ከኾነ ግን ያምኑናል፡፡ እውነቱን ለመቀበልም አይቸገሩም፡፡ በቃል መነገሩ፣ በልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ያለውን ክርስቲያን እንዲህ ሲል አመስግኖታል፡- “የሚያደርግም የሚያስተምርም እርሱ ንዑድ ክቡር ነው” (ማቴ.5፥19)፡፡ እንግዲህ ጌታችን ሲያስተምር በተግባር የሚሰጠውን ትምህርት በቃል ከሚሰጠው ትምህርት ይልቅ እንዳስቀደመው ታስተውላላችሁን? አያችሁ! ከተግባራችን በኋላ ቃላችን ባይከተል እንኳን ሰዎችን ወደ እውነት #ክርስቶስ ለማምጣት በቂ ነው፡፡
@mkreabew @mkreabew
ስለዚህ በቃላችን ከመናገር በላይ በተግባር ክርስቲያኖች መኾናችንን እናሳያቸው፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ብፁዕ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይወቅሰናል፡- “አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን?” (ሮሜ.2፥21)፡፡ አንድ ሰው መንፈሳዊ ሕይወቱ የተስተካከለ መኾን እንደሚገባው ለመምከር የምናስብ ከኾነ እኛው ቀድመን የራሳችንን ሕይወት በተግባር ልንስተካከል ይገባናል፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ የምንሰጠው ምክር ተአማኒነት አለው፡፡ የሌሎች ሰዎች ነፍስ መዳን የሚያስጨንቀን ከኾነ ከምንም በፊት እኛው ራሳችን ስለ ራሳችን መዳን እንጨነቅ፡፡ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ የምንሻ ከኾነ ከማንም በፊት እኛው ራሳችን ያንን አድርገን እናሳያቸው፡፡ ትክክለኛ ጾም ማለትም ይኸው ነው፡፡ ለተወሰነ ሰዓት ከምግበ ሥጋ የመከልከላችን ዓላማም ራሳችንን መግዛት እንድንችል ነው፡፡ ስለዚህ እየጾምኩ ነው የሚል ሰው ካለ ከምንም በፊት፡- ትዕግሥተኛ፣ ልበ ትሑትና የዋህ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ልቡና ያለው፣ የፍትወታትን ጅረት ከኹለንተናው የሚያስወግድ፣ ዘወትር በልቡናው ዕለተ ምጽአትን የሚያስብ፣ በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንደሚቆም የማይረሳ፣ በፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ተይዞ ምጽዋትን የማይጠላ፣ ወንድሙን ከልቡ የሚወድ ይኹን፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት ይኼ ነውና፡፡ “ሰው ራሱን ቢያሳዝን፣ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፣ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም ይህ ጾም እግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም፡፡” “ታዲያ እግዚአብሔር የመረጠው ጾም እንዴት ያለ ነው?” ትሉኝ እንደኾነም ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔር አፈ ንጉሥ ኾኖ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “የበደልን እስራት ፍታ፤ ለተራበው እንጀራህን አጥግበው፤ ድኾችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፡፡” እንዲህ ስታደርግ፡- “ያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፡፡ ፈውስህም ፈጥኖ ይወጣል” (ኢሳ.58፥5-8)፡፡
@mkreabew @mkreabew
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈውቅ፣ኦሪት-ዘፍጥረት፣ድርሳን-8፡13-14

(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕ. 2)
----------
1፤ ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች። ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።
2፤ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።
3፤ አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።
4፤ የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል።
5፤ ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።
6፤ እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
7፤ እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
8፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።
9፤ እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።
10፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡
በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት = ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13፡፡
ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24-18፤ 1ኛ.ነገ.19-8፤ ማቴ. 4-1-4/፡፡
✟🍀🌸 🌸🍀✟
💐 @beteafework 💐
🌺🍂 @beteafework 🍂🌺
💐 @beteafework 💐
🍂🏜💒🏜🍂

Forwarded from ምክረ አበው
ዛሬ ማለዳ የተነሣሁት ከወትሮው በተለየ ትጋት ነው፡፡ ይኸውም ይህን መንፈሳዊ ደስታ ከእናንተ ጋር እንድካፈልና ቀጣዩ ወራት ቁስለ ነፍሳችሁ ድኅነት የሚያገኝበት ወርሐ ጾም መኾኑን አበሥራችሁ ዘንድ ነው፡፡ የኹላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር፥ ልክ እንደ ደግ አባት ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚኾን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናልና፡፡
ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ (እግዚአብሔር) የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገንን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከእኛ መካከል ጾም በመግባቱ አንድስ እንኳን የሚከፋው ወይም የሚበሳጭ ሊኖር አይገባም፡፡ ወርሐ ጾሙን እንዲህ ደስ ተሰኝተን መቀበላችንን ዐይተውም አሕዛብ ይፈሩ፤ አይሁድም ይራዱ፡፡ በእኛና በእነርሱ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ዐይተውም ይማሩ፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በዓል የምትሠራው ምእመናን ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ፣ በበጎ ምግባር ያጌጡ ያሸበረቁ እንዲኾኑ እንደ ኾነ፥ እነርሱ ግን በዓላትን የሚያደርጉት በዘፈንና በስካር ይህንም በመሰለ በሌላ ጸያፍ ግብር ለመንከባለል እንደ ኾነ ለይተው ይወቁ፡፡ በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው፡- ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረጉበት፣ ዕለት ዕለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት፣ ያለ ሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከኾነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩት እንደ ኾነ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓል ተከበረ የሚባለው፡- አርምሞንና ጸጥታን፣ ፍቅርንና ደስታን፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸው ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ ያደረግንበት እንደ ኾነ ነው፡፡
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦሪት ዘፍጥረት፣ 1፥1-2

#ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ፤ ከላይ(ከሰማይ) #የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤(ቅ/ያሬድ)
@eyesusegziabhernewAmen
በቦታ የማይወሰነው አምላክ ሥጋን በመዋሐዱ ወረደ፣ ተወለደ፣ ተሰደደ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተሰቀለ እየተባለ ይነገርለታል። የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት በመወሰን ተወለደ፤ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን ዞሮ አስተማረ፤ በመስቀል ላይ መከራን ተቀበለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ፤ ዐረገ። ዘለዓለማዊ አምላክ በመሆኑም በሁለም ስፍራ ይኖራል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዐቢይ ጾም እግዚአብሔር ሊመሰገንበት የሚገባውን ምስጋና በጀመረበት ክፍሉ “ሃሌ ሃሌ ሉያ ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኵሉ ዘያሐዩ በቃሉ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ዛሬም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፤ ከላይ (ከሰማይ) የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤” ብሏል፡፡ ነገር ግን አላወቁም፤ በቃሉ የሚያድን የሁሉ ጌታ ነውና” በማለት ጾመ ድጓ በሚባለው ድርሰቱ ገልጿል።
@eyesusegziabhernewAmen
በዚህ ክፍለ ንባብ ሊቁ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ዛሬም ያለ፣ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር እንደ ሆነ፣ እንዲሁ ስለ ልዕልናው በሰማያት የምትኖር ይባላልና ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት አለ። እርሱ ራሱ ለደቀ መዛሙርቱ የጸሎት ሥርዓት ሲያስተምራቸው “አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር…” ብላችሁ ጸልዩ ብሎ የእርሱ አባትነት ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳልሆነና ከምድራዊ አባት የተለየ እንደሆነ በማስረዳት “በሰማያት የምትኖር በሉኝ” አለ፡፡ ሊቁም ይህን መሠረት አድርጎ “ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት” አለን።
@eyesusegziabhernewAmen
ከሰማይ የወረደው ቅድመ ዓለም አብ ያለ እናት በማይመረመር ጥበቡ የወለደው ድኅረ ዓለም ድንግል ማርያም ያለ አባት በማይመረመር ጥበብ የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው፡፡ ሥጋዊ ልደት የሆነ እንደሆነ ከአባት ዘር ከእናት ደም ተከፍሎ ይወለዳል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ግን ከአብ ያለ እናት፤ ከእናት ያለ አባት ሲሆን እንዲህ ነው ተብሎ አይመረመርም፡፡ በማይመረመር ልዩ ጥበብ ስለተወለደ ስለልዕልናው በሰማይ የምትኖር ይባላል፡፡ "ዘበእንተ ዕበይከ ትትሜሰል በደመናት፤ ስለልዕልናህ በደመናት ትመሰላለህ" እንዲል፤ ስለዚህ ከላይ ከሰማይ የወረደውን ማለት በልዕልና ያለውን የሚኖረውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት።
@eyesusegziabhernewAmen
የአይሁድን ግብዝነት የጌታን ሁሉን ቻይነትም ሲያስረዳን፤ “ምንም አላወቁም፤ የሰቀሉት በቃሉ የሚያድነውን የሁሉን ጌታ ነው” ይለናል፡፡ በማቴዎስ ወንጌልም ፱፥፲፰ ታሪኩ ተመዝግቦ እንደምናገኘው የመቶ አለቃው ልጁ በታመመበት ጊዜ “እባክህ አድንልኝ” በማለት ተማጸነው፤ “እኔ መጥቼ አድንልኃለሁ” ብሎትም ነበር፡፡ የመቶ አለቃውም በበኩሉ ፍጹም እምነትን የተሞላ ስለነበር “ሁሉ ይቻልሃል፤ በቃልህ ብቻ ተናገር ልጄ ይድናል” ብሎ ስለሁሉን ቻይነቱ በምሳሌ ተናገረ፡፡ ጌታም የመቶ አለቃውን እምነት አድንቆ እንደወደድክ ይደረግልህ አለው፤ ልጁም ተፈወሰ፡፡ ይህንም የሚያውቀው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ “እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ የሚያድን የሁሉ ጌታ” በማለት ገልጾታል፡፡
@eyesusegziabhernewAmen
እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን ጌታ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ መሰደዱን፣ መጠመቁን፣ በገዳመ ቆሮንቶስ መጾሙን በአጠቃላይ የነገረ ድኅነት ጉዞ ብላ ትገልጸዋለች፡፡ ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ፵ መዓልት ፵ ሌሊት ጾመ፡፡ የዐቢይ ጾም ሳምንት መግቢያ የሆነውን የመጀመሪያውን ሳምንት “ዘወረደ፤ ከሰማይ የወረደው አምላክ” በማለት ታስበዋለች፡፡
@eyesusegziabhernewAmen
በዚህም ሳምንት ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ ለዓለም ቤዛ ሲል መከራ መቀበሉን የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባልም ይታወቃል፡፡ ጾመ ሕርቃል የተባለበትም ምክንያት ጌታችን የጾመው ፵ መዓልት ፵ ሌሊት ሲሆን እኛ ግን ፶፭ ቀናት እንጾማለን። ይህም የሆነበት ምክንያት ጌታ ከጾመው ፵ ቀን በተጨማሪ ቅዳሜና እሁድ ለብቻው ተቆጥሮ አንድ ሳምንት፡፡ በመጨረሻ ያለው አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በመሆኑ በመጀመሪያ ያለው አንድ ሳምንት ደግሞ ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ሐዋርያት፡- ጌታ ፵ መዓልት ፵ ሌሊት ከዘረጋ ሳያጥፍ ከቆመ ሳይቀመጥ ነው የጾመው፤ እኛ ደግሞ እሑድና ቅዳሜ አንጾምም በማለት በመጀመሪያ ያለውን አንድ ሳምንት ጨምረው ጹመውታል፡፡@eyesusegziabhernewAmen
@eyesusegziabhernewAmen
ሌላው በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፲፭ እንደምናገኘው በ፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ፎቃ፣ በሮም ደግሞ ሕርቃል የሚባሉ ነገሥታት ነበሩ፡፡ ይህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ ፎቃ ጨካኝና ለክርስቲያኖች የማይራራ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ፤ ለሮሙ ንጉሥ “እባክህ ከእንዲህ ካለው ጨካኝ ንጉሥ አድነን፤ እኛ ላንተ እንገዛለን” በማለት ይልኩበታል፡፡ እርሱም ለጊዜው ቸል ብሏቸው ቆይቶ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን “ግዙራን ይነሥእዋ ለመንግሥትከ፤ ክርስቲያኖች መንግሥትህን ይወርሷታል” የሚል ራእይ አይቶ፤ ይህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ ነው በማለት እንደገና የላካችሁብኝን ነገር አልረሳሁትም፡፡ ነገር ግን ሐዋርያት ነፍስ ያጠፋ ዕድሜ ዘመኑን ይጹም ብለዋልና፤ ያን ብፈራ ነው እንጂ አላቸው፡፡ እነሱም የአንድ ሰው ዕድሜ ፸ ፹ ነው፤ እኛ ተከፋፍለን እንጾምልሃለን ብለውት ጠላታቸውን አጥፍቶላቸዋል፡፡ እነሱም ተከፋፍለው አንድ ሳምንት ጹመውታል፡፡
@eyesusegziabhernewAmen
ስለዚህም በንጉሡ በሕርቃል ምክንያት ስለተጾመ ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ታሪክ ያላወቁት አንድ ጊዜ ብቻ ጾሙ፡፡ ታሪክ ያወቁት ደግሞ ቀድሞም ሐዋርያት ጹመውታል በማለት መጾም ቀጥለዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ይህን መሠረት አድርጋ ከጌታ ጾም መግቢያ ላይ እንዲጾም ሥርዓት ሠርታለች፤ በመሆኑም ምእመናን ከጾሙ በረከት ያገኙ ዘንድ እንዲጾሙ ታስተምራለች፡፡ በዘመኑ ክርስቲያኖች ከጨካኙ ግዛት የዳኑበት ነው፡፡ ዛሬም ምእመናን ከጨካኙ ዲያብሎስ ፈተና፣ መከራና የጭካኔ አገዛዝ ነጻ የሚወጡበት ነውና ሊጾሙት ይገባል፡፡
@eyesusegziabhernewAmen
በአጠቃላይ ይህ ጾም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማየ ሰማያት መውረድ፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለድና ወደዚህ ዓለም መምጣት የሚታሰብበት ስለሆነ “ዘወረደ” ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ “እስመ ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ዘሥጋ ፍትወታተ፤ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች፤ የሥጋን ፍላጎትንም ታስታግሳለች፡፡” ጾመን፤ ጸልየን፤ የሚታገለንን የሥጋ ፍላጎት ለማስታገሥ፣ ነፍሳችንን ለማዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት፣ የኃጢአት ስርየት ለማግኘት ይህን ጾም በመጾም በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን እናገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይፍቀድልን፤ አሜን።

Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝ via @like
"ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ።ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን #ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኢየሱስ፡-
ተወዳጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በግ ደሙም ወይን፤
እርሱ ሙሽራ ጎኑም የሕይወት ውሃ ምንጭ፤
እርሱ መምህር የአፉም ትንፋሽ የዕጣን መዓዛ፤
እርሱ መብራት መስቀሉም መቅረዝ፤
እርሱ የገነት ዛፍ የጸጋውም ወንጌል መዓዛው ያማረ አበባ፤
እርሱ የጽድቅ ፀሓይ ሐዋርያቱም የብርሃን ከዋክብት፤
እርሱ የበረከት ማዕድ ካህናቱም የምስጢር አገልጋዮች፤
እርሱ የቅድስና ልብስ ዲያቆናቱም በልብስነቱ ዘርፍ ሆነው ልብሰ ተክህኖውን የሚከብቡት የወርቅ ጸናጽል፤
እርሱ እረኛ ያመኑበትም የምስጢር በጎች፤
እርሱ ንጉሥ ሰማዕታቱም የመንግሥትን አዳራሽ የሚያስጌጧት ዕንቊዎች፤
እርሱ አውነተኛ የወይን ስፍራ መነኮሳቱም ለሚያዩት ሰዎች ለአይን ያማረ የጽድቃቸውም ፍሬ በሚያነብበው ሰው አፍ የሚጣፍጥ የወይን ዘለላዎች ናቸውና፤
ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱሳን ሁሉ ንጉሥ ነው፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ የጣፈጠ ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያዳምጠው ቃሉ የጣፈጠ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው ሥጋው የጣፈጠ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው ደሙ የጣፈጠ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዜናውን ለሚነግር መታሰቢያው የጣፈጠ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ የሰውም ልጅ ነው”
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
✟✟ @beteafework ✟✟

ሰላም የእግዚአብሄርን ልጆች ዛሬ የዘወረደ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ነው እንደማጠቃለያ ዘወረደ ብላ ቤተክርስቲያናችን ብላ የሰየመችውን ስንጠቀልለው
* ዘወረደ *
ዘወረደ እምሰማይ ...ከሰማይ ከወረደው በቀር፡ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። እርሱም
በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ( ኢየሱስ ) ነው። [ዮሐ 3፥13]
ተቀነዩ ለ እግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ።
ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ። ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ
በስብሐት አምንዎ እስመ ለዓለም ምሕረቱ። ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ።
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ እስመ ለዓለም ምሕረቱ። አክብሩ ሰንበተ
ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት እስመ ለዓለም ምሕረቱ። ምሕረተ
ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጽሕ እስመ ለዓለም ምሕረቱ። ለትውልደ
ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።
👉ትርጉም፦ እግዚአብሔር ን በመፍራት ተገዙለት ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ።
እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘላለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው። እኛስ ሕዝቡ
የመሰማሪያው በጎችነን፤ ወደ ደጁ በመገዛት፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ፤
ጾምን እንጹም፤ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤እርስ በርሳችንም እንፋቀር። ሰንበት ስለሰው
ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር። እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን
እቀኝልሃለሁ፤
እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ።
አቤቱ እግዚአብሔር አባት ሆይ ቀሪውን የፆሞችንን ጊዜያት ባርክልን ቀድስልን
በአንተ ዘንድ ደስ ብሎህ የምትቀበለውን ፆም እንድንፆም ቅዱስ መንፈስህ አይለየን አሜን።
መልካም ሰንበት

@popeshenoudaa @popeshenoudaa
ተወዳጆች ሆይ! የምታደምጡ ብቻ አትኹኑ፤ ያስተማርኳችሁን ትምህርት ለሌሎችም በማስተላለፍ መምህራን ትኾኑ ዘንድ - ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አንዱ ሌላውን ያንጸው” (1ተሰ.5፥11)፤ ዳግመኛም “በፍርሐትና በመንቀጥቀጥም የራሳችኁን መዳን ፈጽሙ” ብሎ እንደ ተናገረው በስሕተት ጐዳና ያሉትን ታድኑ ዘንድ መረባችሁን ጣሉ ብዬ እማፀናችኋለሁ (ፊልጵ.2፥12)፡፡ ይህን ስታደርጉ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትሰፋለች፤ እኛም ይህን ዐይተን እጅግ ደስ እንሰኝባችኋለን፡፡ እናንተም ለወንድሞቻችሁ፣ ለእኅቶቻችሁ ባሳያችሁት ፍቅር በሰማያት ዘንድ ታላቅ ማዕረግና ክብር ታገኛላችሁ። እንደምታውቁት የእግዚአብሔር ፈቃድ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ ራሱ መዳን ብቻ እንዲያስብ አይደለም፤ ወንድሙንም እንዲያንጽ ነው እንጂ፡፡ ሲያንጸውም በቃል ብቻ አይደለም፤ በተግባርም ጭምር እንጂ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እያንዳንዳችን በአኗኗራችን ክርስቶስን መስለን ታምነን እንድንኖርና ፍጥረት ኹሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰዎች ከምንናገረው በላይ የምንኖረውን ስለሚያምኑና ስለሚማርካቸው ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በተዋቡ ቃላት ስለ ይቅርታ ብንናገር ነገር ግን በሕይወታችን እጅግ ቂመኞችና ይቅርታን የሚቀበል ልብ የሌለን ከኾነ ቃላችንና ሕይወታችን ስላልተስማማላቸው ሰዎች የምንለውን ነገር አያምኑንም፡፡ የምንናገረውንና የምናስተምረውን የምንኖረው ከኾነ ግን ያምኑናል፡፡ እውነቱን ለመቀበልም አይቸገሩም፡፡ በቃል መነገሩ፣ በልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ያለውን ክርስቲያን እንዲህ ሲል አመስግኖታል፡- “የሚያደርግም የሚያስተምርም እርሱ ንዑድ ክቡር ነው” (ማቴ. 5፥19)፡፡ እንግዲህ ጌታችን ሲያስተምር በተግባር የሚሰጠውን ትምህርት በቃል ከሚሰጠው ትምህርት ይልቅ እንዳስቀደመው ታስተውላላችሁን? አያችሁ! ከተግባራችን በኋላ ቃላችን ባይከተል እንኳን ሰዎችን ወደ እውነት (ኢየሱስ) ለማምጣት በቂ ነው፡፡
@popeshenoudaa
ስለዚህ በቃላችን ከመናገር በላይ በተግባር ክርስቲያኖች መኾናችንን እናሳያቸው፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ብፁዕ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይወቅሰናል፦ “አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን?” (ሮሜ. 2፥21)፡፡
አንድ ሰው መንፈሳዊ ሕይወቱ የተስተካከለ መኾን እንደሚገባው ለመምከር የምናስብ ከኾነ እኛው
ቀድመን የራሳችንን ሕይወት በተግባር ልንስተካከል ይገባናል፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ የምንሰጠው ምክር ተአማኒነት አለው፡፡ የሌሎች ሰዎች ነፍስ መዳን የሚያስጨንቀን ከኾነ ከምንም በፊት እኛው ራሳችን ስለ ራሳችን መዳን እንጨነቅ፡፡ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ የምንሻ ከኾነ ከማንም በፊት እኛው ራሳችን ያንን አድርገን እናሳያቸው፡፡ ትክክለኛ ጾም ማለትም ይኸው ነው፡፡ ለተወሰነ ሰዓት ከምግበ ሥጋ የመከልከላችን ዓላማም ራሳችንን መግዛት እንድንችል ነው፡፡
@popeshenoudaa
ስለዚህ እየጾምኩ ነው የሚል ሰው ካለ ከምንም በፊት፡- ትዕግሥተኛ፣ ልበ ትሑትና የዋህ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ልቦና ያለው፣ የፍትወታትን ጅረት ከኹለንተናው የሚያስወግድ፣ ዘወትር በልቡናው ዕለተ ምጽአትን የሚያስብ፣ በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንደሚቆም የማይረሳ፣ በፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ተይዞ ምጽዋትን የማይጠላ፣ ወንድሙን ከልቡ የሚወድ ይኹን፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት ይኼ ነውና፡፡ “ሰው ራሱን ቢያሳዝን፣ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፣ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም ይህ ጾም እግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም፡፡” “ታዲያ እግዚአብሔር የመረጠው ጾም እንዴት ያለ ነው?” ትሉኝ እንደኾነም ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔር አፈ ንጉሥ ኾኖ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “የበደልን እስራት ፍታ፤ ለተራበው እንጀራህን አጥግበው፤ ድኾችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፡፡” እንዲህ ስታደርግ፡- “ያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፡፡ ፈውስህም ፈጥኖ ይወጣል” (ኢሳ. 58፥5-8)።

ትናንት መጋቢት1 በኢትዮጵያ አየርመንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኬኒያ በመጎዝ ላይ ሳሉ በደረሰው አደጋ ሂወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማንን ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲያድል እንጸልያለን ! እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ ይጠብቅ ።