ሃይማኖተ አበው
2.71K subscribers
13 photos
2 videos
21 links
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 28)
----------
8፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።

9፤ ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፤ ጠብቃቸው፥ ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
Download Telegram
"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"
1ጴጥ. 4÷3
ንግስት እሌኒን እናወድሳት ዘንድ ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን
የአምላካችንን የጌታችንን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡ ንግስትነቷን በአለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፤ እጅግ የከበረውን መቅደስ ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፤ ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

#ታምራት_ፍስሐ
8👂👉፤ ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።

9፤ እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።👂👈
ትንቢተ ሚልኪያ :3
መዝሙር 15

የዳዊት መዝሙር።

1 አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?👈👈🗣

2 👉በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።

3 👉በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።

4 👉ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።

5 👉ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።🙏🙏🙏
የቅኔ አፍታ

"ኅቡረ ልህቁ በገራህተ ወንጌል ሉዓሌ
ክርዳድ ይሁዳ ወጴጥሮስ ስንዳሌ
እስከ ይበጽሕ ማእረር ዘዕለተ ዐርብ ወይሌ"
ትርጉም
"እንክርዳድ/ ይሁዳና ስንዴ /ጴጥሮስ
የአርብ ቀን አዝመራ / ለቅሶ እኪደርስ ድረስ
በወንጌል /እርሻ ላይ በአንድነት አደጉ"
በዚህ ቅኔ ላይ ይሁዳ በእንክርዳድ ጴጥሮስ ደሞ በስንዴ እንዲሁም እርሻ በለቅሶ ተመስለው እናገኛለን::
የቅኔውም ሐሳብ እንክርዳድ እና ስንዴ የአዝመራ ወቅት እስኪደርስ ድረስ አብረው እንደሚቆዩ ነገር ግን በኃላ ላይ እንዲለዩ::ጴጥሮስና ይሁዳም የመከራ ቀን የሆነችው እለተ አርብ እስክጥመጣ ድረስ በአንድ ላይ ነበሩ ይሁንና የመከራው ሰአት ሲደርስ ከልብ ይከተል የነበረውና በአፍአ ሲከተል የነበረው ሊለይ ችሏል በማለት ቅኔው ያትታል ::
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በዚህ ቤተክርስቲያን ላይ ትልቅ መከራ እየደረሰ ባለበት ወቅት ክርስቲያኖችም ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ግፍ እየደረሰባቸው መሆኑን ስናይ እኛስ ውስጣችንን መርምረናል?
እውነት በነእስጢፋኖስን በነጳውሎስ እና በሌሎቹ ደቀመዛሙርት የደረሰውን መከራ ለመቀበል የሚያስችል መንፈሳዊ ደረጃ ላይ መድረሳችንን አረጋግጠናል ?
ወንድሞችና እህቶች እውነተኛ ክርስቲያን መሆናችን የሚለካበት ጊዜ ደርሷልና በእምነት እንበርታ ወገባችንንም በእውነት ወንጌል ታጥቀን እንቁም የእምነትንም ጋሻ እናንሳ በጸሎትና በልመናም ሁሌ እንትጋ( ኤፌ 6)
የሰላም አለቃ መድሃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሀገራችን ሰላም ለኛም ፍቅርና አንድነት ያድለን አሜን!!
መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
የሉቃስ ወንጌል 2 : 10 -15
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
" ተጠምቀ ሰማያዊ በ እደ መርየታዊ"

በመጀመርያ እንካን ለ አምላካችንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳቹ አደረሰን።
በመቐለ ከተማ እና አካባቢዋ ለምትገኙ ምዕመናን ደብራችን ደብረ ፅጌ ቅድስት ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል ዓዲሹምዱሑን ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጥምቀትና በዓለ መስቀል ሲያከብር ከቀድሞው ጀምሮ በ ደብሩ ቤተክርስቲያን አፀድ እንደሚያከብር ይታወቃል። ዘንድሮም በዓለ ጥምቀትና በማግስቱ በደብሩ የሚከበረው የቃና ዘገሊላ ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ከ 11/05/2012 ዓ/ም እስከ 13/05/2012 ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ልዩ መርሐ ግብር ስላዘጋጀ ሁላችን መጥተን ቃሉን እንማር።
* ሰዓት ከምሽቱ 11፡30 ይጀምራል።
Share share share
ነህምያ 4:2
የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?

ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው ነገር ባሻገር ማየት አቃተኝና ጥልቅ የሆነ ሃዘን ዉስጥ ገባሁ። ተስፋዬም እያሽቆለቆለ ሲሄድ ድምፅ አልባ በሆነ መቃተት ወደ እግዚአብሔር ተማፀንኩ።
ወዲያውኑም አንድ ቃል ወደ ውስጤ መጣ። ነህምያ እና ሕዝቡ ኢየሩሳሌምን እንደገና መስራት እንደጀመሩ እነ ሳናባላጥ በሰሙ ጊዜ እንዲህ ብለዉ ተሳለቁባቸው “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሰሩ ነውን? መስዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው ሊጨርሱ ነውን? እንደዚያ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?” ነህምያ 4፡2።

በርግጥም ከተማይቱ የፈረሰችበትን መጠን ላየ ሰው ቅጥሩ ሊታደስ ከተማይቱም እንደገና ልትታነፅ ትችላለች ብሎ ማሰብ ዘበት ነበር። በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አልነበረም። እግዚያብሔራዊው መልስ ’አዎ ይቻላል‘ ሆነ። ለኔም በጊዜው የመጣልኝ መልስ ‘ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና አዎ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነው ድንጋይ ነፍስ ሊዘራበት ይችላል፣ አዎ ተስፋ የተቆረጠበት ነገር እንደገና ሊታደስ ይችላል’ የሚል ነው።

ዛሬ በሚያጋጥሙን ነገሮች ልባችን ዝሎና ተስፋ ቆርጠን ወደኋላ እንዳንመለስ እግዚአብሔር የገባልንን እንዲህ ያለውን ህያው ተስፋ አጥብቀን እንያዝ። በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳን ይህ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ በቂ ምክንያት አይደለም። በእውነት እግዚአብሔር ከአእምሮአችን በላይ ትልቅ ነው፣ ለእኛም የገባው ተስፋ በሰው አእምሮ ከመገመትና ከመወሰን ያልፋል። ‘ነፍሴ ሆይ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክሽ ላይ አድርጊ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና’ መዝሙር 42፡5-6።
Forwarded from ምክረ አበው
አልተጎዱም!
የነነዌ ሰዎች፥ ምንም እንኳን አሕዛብ፣ እስራኤላውያን ያገኙትን ዓይነት ነገር - በጥቂቱም ይኹን በብዛት፣ በቃልም ይኹን በተአምራት ወይም በድርጊት - አንድም ቀን አግኝተው የማያውቁ ቢኾኑም፥ ከመርከብ አደጋ የተረፈ አንድን ሰው ሲያዩ፣ ከዚህ በፊት የማያውቁትን አንድን ሰው ሲመለከቱ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ መጥቶና ወደ ከተማቸው ገብቶ፡- “ነነዌ በሦስት ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ባለ ጊዜ በእነዚህ ቃላት ብቻ የቀድሞ ክፋታቸውን ትተው፣ በንስሐ መንገድም ወደ ምግባር ወደ ትሩፋት ተፋጥነው ተለወጡ፤ ታደሱ /ዮና.3፥4/፡፡ እግዚአብሔር ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር እንዲጸጸት አደረጉት፡፡ በከተማይቱ ላይ ታስቦ የነበረው ጽኑ መቅሰፍት እንዲቀር አደረጉት፡፡ ታስቦ የነበረውን ሰማያዊ ቍጣ አስቀሩት፤ ከክፉ ነገርም ኹሉ ዳኑ፡፡ እንዲህ ነውና የሚለው ቃሉ፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን ዐየ፤ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ ተመለሰ፤ አላደረገውምም” (ዮና.3፥10)፡፡ እንዴት ተመለሰ? ንገሩኝ! ምንም እንኳን ክፋታቸው ታላቅ፣ በደላቸው እንዲህ ነው ተብሎ ሊናገሩት የማይቻል፣ ነቢዩ፡- “ክፋታቸው ወደ ፊቴ ወጥቶአል” ብሎ እንደ ተናገረው ሞራላዊ ግብራቸው እጅግ የታመመና ሊያክሙትም አስቸጋሪ /ዮና.1፥2/፣ ክፋታቸው ይኼን ያኽል በዝቶና ገዝፎ መንበረ ጸባዖት ድረስ ደርሶ የነበረ ቢኾንም - በሦስት ቀን ውስጥ፣ እጅግ በጣም አጭር በኾነ ጊዜ፣ ከመርከብ አደጋ ተርፎ መጥቶ በነገራቸው በአንድ እንግዳ ሰው እጅግ ጥቂት ቃላት - ከሊቅ እስከ ደቂቅ ራሳቸውን ስላዋረዱ፣ ማቅ ስለ ለበሱ የእግዚአብሔርን ቍጣ አበረዱት፤ “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን ዐየ፤ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ ተመለሰ፤ አላደረገውምም” የሚል ደስ የሚያሰኝ ቃል አደመጡ፡፡ እንግዲህ ራሱን የሚገዛና ንቁ የኾነ ሰው በሰው ጉዳት ሊደርስበትስ ይቅርና ሰማያዊ ቍጣ እንኳን እንዴት ሊያስቀር እንደሚችል ታያላችሁን? ከዚሁ በተቃራኒ በገዛ ራሱ ራሱን የሚጎዳ ሰው ግን ምንም ያኽል ርዳታ ቢደረግለትም ምንም ጥቅም ሊያገኝ አለመቻሉንስ ትመለከታላችሁን? አዎ! አይሁዳውያኑ በእነዚያ ታላላቅ ገቢረ ተአምራት አንዳች አልተጠቀሙም፡፡ ሰብአ ነነዌም እነዚያን ተአምራት ባለማየታቸው አልተጎዱም፡፡ ከዚያ ይልቅስ በውሳጤያቸው ስለ ተለወጡ፣ ባገኙዋት ጥቂት ዕድል ስለ ተቀየሩ - ምንም እንኳን አሕዛብና ከእስራኤል ውጪ የነበሩ፣ የእግዚአብሔር መገለጦችን የማያውቁ፣ ከፍልስጥኤም እጅግ ርቀው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ቢኾኑም አንዳች አልተጎዱም፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልእክታት)
@mkreabew
@mkreabew
@mkreabew
@mkreabew
✞✞✞

ከዚህ ውጪ እድለ ቢስነት የለም! ፦

ትምህርት ብርሃን ካልፈነጠቀልህ፣ ማወቅ ዓይንህን ካልገለጠልህ ዘልአለም በጨለማ ውስጥ የሚመላለስ እድለ ቢስ ሰው አንተ ነህ!!!

ካነበብኩት

✞✞✞
Forwarded from ምክረ አበው
🌻
"፰፤ አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና #የምሄድበትን_መንገድ_አስታውቀኝ።"
...
(መዝሙረ ዳዊት ፻፵፫፤)
👉 #ፆምን_ቀድሱ

ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በእኛ ለዘልዓለሙ በእውነት ይደርብን።
🛑 ለጥንቃቄ🛑


🅾አንብባችሁ ለሌሎችም አስተላልፉ
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ
ያቆመዋል!

◾️በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው
ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ
የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ
ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ
የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው
አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል
የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም
የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ
...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን
ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ!

የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ
ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ
በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት
ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና
ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው::

አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ
ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ
ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12
ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ
እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም
መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን
በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት
ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር
በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡
በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው
ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡
በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ
ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት
ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ
ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን
በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት
የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!!
በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?
1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን
ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ
መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ
በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን
ያስገነዝበናል፡፡
< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ
ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን
ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ
ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ
ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡
< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ
በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡
2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም
መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን
መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ
አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም
ሊቀንሰው ይችላል፡፡
3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

© ምንጭ : ዶ/ር ቤዛ አያሌዉ
መዝሙር 91

የዳዊት የምስጋና መዝሙር።

1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

2 እግዚአብሔርን። አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

5 ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

6 በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

7 በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8 በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

9 አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።

10 ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።

11 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

12 እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

13 በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14 በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

15 ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

16 ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።

እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።


ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።

ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤

እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤

ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።

እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።

እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥

በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥

በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።

ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤

በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።

እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።

በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።

እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።

እንግዲህ። እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤

በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።

ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤

መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።

ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።

እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።

ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።


በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥

የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤

ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።

ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።

ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?
ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤

እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥
ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥

የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥

ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

የማቴዎስ ወንጌል 24 : 1 - 51
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 26 : 20
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
የዮሐንስ ወንጌል 14 : 1

@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa