Easy world capital market and Business consult
66 subscribers
10 photos
2 videos
1 file
18 links
Easy
Download Telegram
Forwarded from 𝐅ree 𝐈nternet
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወደ ትግበራ እንዲገባ መደረጉ ታውቋል።

ይህ መመሪያ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያን ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የመንግስትና የግል ድርጅቶች ገበያውን በመጠቀም የድርጅቶችን የድርሻ እና የብድር ስነዶችን በመሸጥ እና ገንዘብ በመስብሰብ ፕሮጀክቶችን ለመስራት አቅም ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርላቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው መውጣቱ የድርሻ ወይም የብድር ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ኢንቨስተር ፈቃድ ካለው ገበያ አስፈላጊው ቁጥጥርና ግልጸኝነት በተሟላበት የግብይት አሰራር፣ ፈቃድ ባለው ተገበያይ አማካኝነት የተፈቀዱ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት እና ለመሸጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል ተብሏል።


It has been reported that the first directive to issue a license for the capital market in Ethiopia has been implemented by the capital market authority.

This directive is for the first time in our country to license the Securities Market and Decentralized Table Market.

It has been shown that public and private organizations use the market to create a favorable environment for them to build capacity for projects by selling shares and loans of companies and collecting funds.

On the other hand, it is said that the issuing of the directive will create a favorable environment for any person or investor who wants to buy shares or loan documents from a licensed market to buy and sell licensed securities through a licensed trader, with the necessary control and transparency.
📈ብሄራዊ ባንክ ትናንት ባወጣው አዲስ መመሪያ፣ ባንኮች ከባንክ ዘርፍ ውጭ በሚሠማሩባቸው ኢንቨስትመንቶች ውስጥ የሚያፈሱት ገንዘብ ከአጠቃላይ ካፒታላቸው 15 በመቶ እንዳይበልጥ ደንግጓል።

መመሪያው፣ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ውጭ ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ በላይ የሚኾን ገንዘብ በሪልስቴት ዘርፍ ባለቤት እንዳይኾኑም አግዷል። ባንኮች የባንክና የኢንሹራንስ አገልግሎት በማይሰጥ አንድ ኩባንያ ውስጥ እስከ 10 በመቶ ድርሻ ሊኖራቸው እንደሚችልና ማናቸውም ባንክ የኢንሹራንስ አክሲዮን ባለቤት ሊኾን የሚችለው ባንድ ኩባንያ ውስጥ ብቻ እንዲኾን መመሪያው ደንግጓል። አዲስ የሚቋቋሙ ኢንቨስትመንት ባንኮች በካፒታል ገበያ ውስጥ ለሚሳተፉ አካላት የማማከር አገልግሎት መስጠትና መንቀሳቀሻ ገንዘብ ለሚፈልጉ ኩባንያዎችና ነጋዴዎች በካፒታል ገበያው ውስጥ ገንዘብ የማፈላለግ ሥራ መስራት ይችላሉ ተብሏል።

አዲስነገር
👍1
🇪🇹 ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ?

1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል።

2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉ። ይህ ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይጠበቃል።

3ኛ. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

4ኛ. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡ በሂደት የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው የሚያስቀሩበት አሰራር ይዘረጋል።

5ኛ. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

6ኛ. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

7ኛ. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ተነስተዋል።

8ኛ. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

9ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ስዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሃሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

10ኛ. ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል።

11ኛ. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

12ኛ. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

13ኛ. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡


[National Bank Of Ethiopia]
t.me/empirebot/game?startapp=hero1363191910
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium
it's remain 20day to list
t.me/empirebot/game?startapp=hero1363191910
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium
ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ

ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።

በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)

ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።

የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።

ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።

የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።

የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል
የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታወቀ

ግዙፉና መንግሥታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክስዮን ሽያጭ 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን አስታውቋል፡፡

📌 ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን የገለጸ ሲሆን፤ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸውን ገልጿል፡፡

ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺሕ 333 እንደሆነና የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ በአክስዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ለሽያጩ ከማመልከታቸው በፊት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅደመ-ሁኔታዎች መካከል፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆን እንደግዴታ ተቀምጧል።

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ መቆየቱ ይታወቃል።
- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  🔹 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

💠 ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 🔹999,900 ብር ይሆናል።

💠መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

💠የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

💠ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል
Live stream finished (286 days)
Live stream finished (10 seconds)