Event Addis Media
9.08K subscribers
5.26K photos
5 videos
3 files
3.97K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
#ሲኒማ_በሳምንቱ_መጀመሪያ_ቀናት!

ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ

ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ

ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ

ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ

በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት እነዚህ ፊልሞችን ለተመልካቾች ያቀርባሉ!

መልካም ሳምንት!

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1
በእይታ ላይ የሚገኙ ቴአትሮች ሰንጠረዥ

በአዲስ አበባ ከተማ በቋሚነት ሁለት የቴአትር ማሳያዎች ብቻ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ።

እነዚህም የቴአትር ማሳያዎች አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና ዓለም ሲኒማ ናቸው።

በእይታ ላይ የሚገኙ ተውኔቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል።

☑️ ሶስቱ አይጦች

ድርሰት: ኤልያስ ተስፋዬ
አዘጋጅ: ካሌብ ዋለልኝ
ቀን: ማክሰኞ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ ሀሁ ወይም ፐፑ

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
አዘጋጅ: ተስፋዬ ሲማ
ቀን: ረቡዕ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ የሁለት ጌቶች አሽከር

አዘጋጅ:ጂያንሉካ ባርባዶሪ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ መንታ መንገድ

ድርሰት: ቶፊቅ አል ሐኪም
አዘጋጅ:ተክሌ ደስታ
ቀን: እሁድ
ሰዓት:8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

☑️ የሚስቶቼ ባሎች

ድርሰት:አበባየሁ ታደሰ
አዘጋጅ: ተስፋዬ ገ/ማርያም
ቀን: ረቡዕ
ሰዓት:12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

☑️ የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለለኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር የፊታችን ረቡዕ ግንቦት 7 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን  "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀን የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት  መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው።

የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር የሙዚቃ ድግስ መሰናዳቱ ተነግሯል።

በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው የተጫወቱ ድምፃውያን በመርሐግብሩ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ታውቋል።

ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬን ጨምሮ ብርሃን ተዘራ፣ ሀይልዬ ታደሰ፣ ብስራት ሱራፌል እና ሌሎችም ድምፃውያን እንደሚሳተፉበት የሙዚቃ ባለሙያው አለማየሁ ደመቀ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረገው ቆይታ አንስቷል።

አለማየሁ ደመቀ በቆይታው ካነሳቸው ጉዳዮች መካከል

በቅርቡ ለአንባቢያን የሚደርሰው "ዮቶር ቁጥር 2" መፅሐፍ አሁን ያለን ኃይል ምንድነው?" የነብሳችን ኃይልስ የቱ ነው ?" የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያነሳ ነው ሲል ተናግሯል።

ዮቶርን እውን ለማድረግ ከዘጠኝ ወራት ላላነሰ ጊዜ ከተማ ውስጥም ሆኜ በራሴ ዋሻ ውስጥ ተሸሽጌ ፅፌዋለው።

እስከ አሁን ሰርቼ ለህዝብ ካደረስኳቸው ሙዚቃዎች በላይ ለህዝብ ያልደረሱ ስራዎች በቁጥርም በጥራትም የበረከቱ ሆነው ስለሚገኙ እነርሱን ለህዝብ ማድረስን እናፍቃለሁ።

ከእዚህ በኋላ በሚኖሩኝ ጊዜያት በእኔ ዘመን ካሉት እና አብሬያቸው ከሰራኋቸው ድምፃውያን በተጨማሪ ከአንጋፋዎቹ ጋር የመስራት ውጥን አለኝ" ሲል በቆይታው አንስቷል።

ዘገባው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነው

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የቅርስ ጉባኤና አውደርዕይ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የተዘጋጀው ዓመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባኤና አውደርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ እና ረቡዕ ይካሄዳል።

መርሐ ግብሩ ባለስልጣኑ ወደ ምርምር ተቋም መሸጋገሩን ተከትሎ የኢትዮጵያን ቅርስ ምርምር እና እንክብካቤ የ8ዐ ዓመታት ጉዞ መሰረት በማድረግ ከግንቦት 6 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በባለስልጣኑ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

የተለያዩ የጥናትና የውይይት መነሻ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን የምርምር ዘርፉን ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክር ይደረጋል መባሉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከትናንት እስከዛሬ በየመስኩ ያለበትን ሁኔታ የሚያስቃኙ እና የሚዳስሱ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት የመክፈቻ ሥነሥርዓት ነገ ማክሰኞ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው የባለስልጣኑ ዋ/ና መስሪያ ቤት ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የጋዜጠኞች መብት እንዳይጣስ የሚከራከር የህግ ባለሙያዎች ቡድን ሊቋቋም መሆኑ ተሰማ፡፡

ይህንን የህግ ባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት እና ዩኔስኮ በጋራ በመሆን የሚቋቋሙት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል ።

አቶ መሱድ ገበየው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጋር በነበራቸው ቆይታ የሚዲያ ተቋማት እና ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው ብቻ የሚደርስባቸውን ችግር ለመፍታት የህግ የባለሙያዎች ቡድንን እያቋቋምን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሚዲያው ላይ ብቻ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ የተለያዩ ጋዜጠኛውን የሚጎዱ ህጎች ላይ በመከራከር ጋዜጠኛውን መብቱን ማስጠብቅንም ያጠቃለለ ነው ብለዋል፡፡

ጋዜጠኞቹ ሲታሰሩ መደበኛ ጥብቅናው እንዳለ ሆኗ የጋዜጠኞችን የዕውቀት ደረጃ ከፍ የሚያደርግ እና በእስር ላይ የሚገኙ የሚዲያ አካላትን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችል ተቋም ለመቋቋም መሰባቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሱድ ይህ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟጋት የህግ ባለሙያዎች ቡድን መላ የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልፀዋል፡፡

ማህበሩ ዋና ዓላማ የህግ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እንዲሁም የጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ የሚሰራ ነው ብለዋል።

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የለምለም ኃ/ሚካኤል አልበም አርብ ይለቀቃል

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ማያዬ" የተሰኘ  የመጀመሪያ አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።

በአልበሙ ላይ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዜማ ኤልያስ መልካ ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ ብስራት ሱራፌል፣ እሱባለው ይታየው(የሺ) ዘርዓ ብሩክ ሰማው የተሳተፉ ሲሆን

በግጥሙ በኩል ወንድሰን ይሁብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው  ሀብታሙ ቦጋለ፣ጥላሁን ሰማው እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።

በቅንብር አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ኤልያስ መልካ ፣ ሚካኤል ኃይሉ ፣ ታምሩ አማረ፣ ብሩክ ተቀባ፣ አዲስ ፍቃዱ በሌላ በኩል ሚክሲንግ እና ማስተሪንጉን ደግሞ ሰለሞን ኃ/ማርያም እንደሰሩ ተገልጿል።

“ማያዬ”አልበም 12 ያህል ሙዚቃዎች የተካተቱበት ሲሆን ናሆም ሬከርድስ ፕሮዲውስ አድርጎታል።አልበሙ ዘጠኝ ዓመትም እንደፈጀ ተነግሯል።ከአልበሙ ውስጥ ሶስት ያህል የሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርቷል።

ይህ የሙዚቃ አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል ይመረቃል።

ድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "የኛ" እና "እንደ እኛ" የተሰኙ የሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ በርካታ ሙዚቃዎችን በጋር ተጫውታለች።

በተጨማሪም “ላሊበላ”፣ “ገዳም”፣ “በላልበልሃ” የተሠኙ ነጠላ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሷ ይታወሳል።

ለምለም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቴአትር ጥበባት በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀች ሲሆን በዚሁ ትምህርት ክፍል በቴአትር ፎር ዴቨሎፕመንት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነች።

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
በኢትዮጵያ የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ ነው ተባለ

ለጥበብ ስራው መቃናት እና የጥበብ ባለሙያዎች መስራት በፈለጉት ሰዓት ስራቸውን ለመስራት እንዲረዳቸው ለማድረግ የሚያስችል የጥበብ መዳረሻ ሆቴል ሊገነባ መሆኑን የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

መዳረሻቸዉን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉ የበርካታ የዓለም ሃገራት ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በተለይም የጥበብ ሰዎች ለጉብኝት በመጡበት ወቅት የጥበብ ስራቸዉን እዚህ አከናዉነዉ መሄድ ቢፈልጉ ምቹ ቦታዎችን ማግኘት አዳጋች ይሆንባቸዋል፡፡

የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 የ100ኛ አመቱን ክብረ በዓል ሲያከብር ሊያሳካቸዉና በሜጋ ፕሮጀክትነት ከያዛቸዉ እቅዶች መካከል የአርት ሪዚደንስ ወይም የጥበብ ስራዎችን ማከናወኛ ማዕከል የመገንባት ነዉ፡፡  
የውጭ ዜጎች ለጉብኝት እና ለጥበብ ስራቸው ሲመጡ በማንኛው ሰዓት በሆቴሉ ተገኝተው ከእረፍታቸው ጎን ለጎን ስራቸውን ማስኬድ የሚችሉበት የጥበብ መዳረሻ ሆቴል አንድ ክፍለ ዘመን ለማስቆጠር በመንደርደር ላይ ባለው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደሚገነባ  የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ተናግረዋል፡፡

የጥበብ መዳረሻ ሆቴል በአፍሪካ በሰባት ሃገራት ውስጥ  ብቻ እንዳለ የሚናገሩት አቶ ተሾመ፤ ባለሙያዎቹ መስራት በሚፈልጉበት ልክ በነፃነት እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ እና ሙያውን ለማዘመንም እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡
             
መዲናችን  አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ ያሉት ሆቴሎች ለጥበብ ባለሙያዎች ምቹ እንዳልሆኑና እንዲህ አይነት ሆቴል መኖሩ ደግሞ በርካታ ቱሪስቶችን ለመሳብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የመናኸሪያ ሬድዮ ነው።

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
በ"6 ሠዓት ከሌሊቱ" ፊልም ላይ ውይይትና እይታ

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በ"6 ሰዓት ከሌሊቱ" ፊልም ላይ እይታ እና ውይይት ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የሚሳም ተራራ" መጽሐፍ ሀሙስ ይመረቃል

የአንጋፋው ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ "የሚሳም ተራራ" አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ከምሽቱ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።

በመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል ተብሏል።

"የሚሳም ተራራ" ሁለተኛ እትም ባሳለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 3 2016 ዓ.ም ገበያ ላይ እንደዋለ ይታወሳል።

ይህ መጽሐፍ የደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ የግለታሪክ መጽሐፉ ሲሆን ደራሲው የሕይወት ጉዞውን ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት የተረከበት ነው።

ፍቅርማርቆስ ደስታ ከዚህ ቀደም ከቡስካ በስተጀርባ፣ኢቫንጋዲን ጨምሮ የተለያዩ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የምግባር ሲራጅ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የገጣሚና ደራሲ ምግባር ሲራጅ "እየዳነ ሄደ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሰሞኑ ለንባብ በቅቷል።

የገጣሚና ደራሲ ምግባር ሲራጅ "እየዳነ ሄደ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ280 ገፆች ተቀንብቦ በ450 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚና ደራሲ ምግባር ሲራጅ ከዚህ ቀደም "ዘንባባ" እና "መንደሪን መንደሪን" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቡ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ጉባኤ በፈንድቃ ባህል ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል

የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስ፣ የባህል ድርጅት ( ዩኒስኮ ) ጋር በጋራ ያዘጋጁት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ጉባኤ በፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።

ከባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ጉባኤ ዩኔስኮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከውጭ በመጡ የዘርፉ ባለሞያ "ዳንስ፣ ባህል እና ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የማኅበሩ አባላት እና ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበብ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ድግሪና የፒኤች ዲ ተመራቂዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ተብሏል፡፡

ሌሎች ክውን ጥበባት ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሶስተኛ ድግሪ ትምህርት የሚሰጥባቸው ዘርፎች ያላቸው ሲሆን እስካሁን የውዝዋዜ ጥበብ ግን በድግሪ ደረጃ የትምህርት ዘርፍ እንደሌለው ተገልጧል።

የውዝዋዜ ጥበብ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ጥረት እንደተጀመረም ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።

“የኢትዮጵያ የውዝዋዜ ጥበብ ማኅበር" በ2010 ዓ.ም የውዝዋዜ ባለሙያዎችን መብት ለማስጠበቅና ሙያዊ አቅምን ለማጎልበት ታስቦ የተመሰረተ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በመላው ኢትዮጵያ የማኅበሩን ቅርንጫፍ ቢሮ በማቋቋም ለሙያተኞች ከውጭ ሀገር ከመጡ የዘርፉ ምሁራኖች ጋር የልምድ ልውውጥ መድረኮችን አና ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ተገልጿል።

እስከ ግንቦት 10 የሚቆየው ይህ የመጀመሪያው ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ጉባኤ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"በሦስቱ መንግሥታት ያጋጠሙኝ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች" መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ይመረቃል።

በኮሎኔል መርሻ ወዳጆ የተዘጋጀው "በሦስቱ መንግሥታት ያጋጠሙኝ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍት እና ቤተመዛግብት አግልግሎት (ወመዘክር ) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም ፋሲካ ሲደልል፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ፣ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ፣ ዶ/ር ሰይፈ ባህሩ ፣ መስፍን አሰፋ እና ኮ/ል በላይነህ ታዬ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
“የስዕል ደብተሬ” የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

በምዕራፍ ግሩም የተዘጋጀው “የስዕል ደብተሬ” የተሰኘ የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ የህፃናት መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይመረቃል።

መፅሃፉ ለኢትዮጵያውያን ልጆች የተዘጋጀ ሃብታም ከሆነው ባህላቸውና ታሪካቸው የሚያቀራርባቸው፣ የሚያጭውት፣ የሚያዝናና እንዲሁም የታዳጊዎችን የመፍጠር ችሎታ የሚያሳድግና እውቀት የሚሰጣቸው ብቻ ሳይሆን ስነምግባር የሚያስተምር ፣መረዳዳትንና መዋደድን የሚመክር ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን አዘጋጇ ለሸገር ታይምስ ሚዲያ ገልጻለች፡፡

የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ ግንቦት 11 ቀን ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል እንደሚደረግና ወላጆች በምርቃት ቦታ ከልጆቻቻው ጋር በመገኘት ልጆቻቻውን እያስተማሩና እያዝናኑ ለኢትዮጵያ ልጆች ጠቃሚና ገንቢ ተደርገው የተዘጋጁትን መጻሕፍት እንዲመርቁም አዘጋጆቹ ምዕራፍ ግሩምና ፈንድቃ የባህል ማእከል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አዲስ ከሚመረቀው "የስዕል ደብተሬ" በተጨማሪ በአዘጋጇ ከዚህ ቀደም የተዘጋጀውን በኢትዮጵያን ባህላዊ አልባሳት የማቅለሚያ መጽሐፍ ቁጥር 1 መጽሐፍ ም የማግኘት እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ትዝታ"ፊልም ዛሬ ይመረቃል

የዳንኤል አንማው "ትዝታ"ፊልም ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 7 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፒያሳ በሚገኛው ኤልያና ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ሥነሥርዓት ይመረቃል::

እንግዳሰው ሀብቴ(ቴዲ) ፣ቃልኪዳን ጥበቡ ፣ይመር አባተ፣ፋንታ ስንታየሁ ፣ዳግም ተዘራ ፣በሀይሉ እንግዳ እና ሌሎችም በተዋይነት ተሳተፈውበታል።

የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ዳንኤል አንማው ሲሆን በኤላዳን ፊልምስ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

የትዝታ ፊልም ምርቃት ግንቦት 9 10 11 እና ግንቦት 16 17 18 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል::

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመልከቱ ንፁህ አየር ይተንፍሱ »ልዩ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመልከቱ ! ንፁህ አየር ይተንፍሱ !» በሚል መሪ ቃል ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ውስጥ ልዩ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ሁለት ቀናት በሚቆየው መርሐግብር ላይ የአዋቂዎች የተራራ ላይ የእግር ጉዞ፣  አዝናኝ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የህፃናት መዝናኛ መጫዎቻዎች፣ የፈረስ እና ግመል ግልቢያ ፣ የማዕከሉ ሳቢና ማራኪ መልክአ-ምድራዊ አቀማመጥ ጉብኝት ፣ የመፅሀፍ ዓውደ-ርዕይ  እንዲሁም የተለያየ የዕደ-ጥበብ ስራዎች በተግባር የሚሞከሩበት
መሠናዶዎች ያለምንም  የመግቢያ ክፍያ በነጻ እንደተዘጋጁ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የደንበኛች ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን እነዚህ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ጨምረው  ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ705 ሄክታር ቦታ ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ይገኛል። የዕፅዋት ማዕከሉ ከባህር ጠለል ከ2600- 2950 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን  ከ950 በላይ ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎችን ይዟል።

Via ጌች ሀበሻ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ዛሬ ሐሙስ ነው

እነሆ የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ

ይህችን ሊንክ https://rb.gy/9fmwu6 በመነካት ብቻ የሐሙስ መረጃዎችን በድረገጻችን በጥሩ አቀራረብ ማንበብ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ: የኤቨንት አዲስ ድረገጽ መረጃዎችን በእርሶዎ ሚዲያ ላይ ሲጠቀሙ እባክዎ በተገቢው መንገድ ምንጭ ይጠቀሱ። በተገቢው መንገድ ምንጭ መጥቀስ የጋዜጠኝነት ብቃት አንዱ መለኪያ ነው።

የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን:

Telegram:https://t.me/EventAddis1

Website: https://eventaddis.com

Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/

Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL
መቅረዝ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ዛሬ ሀሙስ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም በእረኛዬ ፣ በታዛ ፣ ዶቃን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ጉማ "ፊልም በዲጂታላይዝድ መልክ ተደራጅቶ ድጋሜ ለመድረክ እንዲበቃ ተጠየቀ

በሚሼል ፓፓቲከስ የተደረሰው የ"ጉማ"ፊልም ዳራ እና ሒሳዊ ዳሰሳን በሚመለከት በቴአትርና ጥበባት መምህር ያሬድ ዘኪሮስ ጥናታዊ ጽሁፍና ሒሳዊ ምልከታ ቀርቧል፡፡

እንደ መምህር ያሬድ በኢቲኖግራፊ የፊልም ዘውግ የተሰራና በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የሚያጠነጥነው"ጉማ" በግጭት አፈታት ላይ የሚያተኩር ቢሆንም ከሁሉም ማህበረሰብ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል እምነትና አስተሳሰብ አጣምሮ የያዘ ድንቅ ኢትዮጵዊ ፊልም መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፊልሙን ከሥነ ምግባራዊ ሒስ አተያይ ረገድ ባህልንና ዕሴትን ያዋቀረ በመሆኑ ችግርን በራስ የመፍታት ባህልና ጥበብን ይናገራል ነው ያሉት፡፡

ሚሼል ፓፓቲከስ ሃገርኛ ታሪክን በ"ጉማ" ፊልም ላይ የደረሱት ከማህበረሰቡ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል ለማሳደግ እንደነበር መምህር ያሬድ አንስተዋል፡፡

ዛሬ ላይ እየተደረሱ ለህዝብ የሚበቁት ሃገርኛ ፊልሞች በአስተሳሰብና በፍልስፍና ከምዕራባዊያን የተቀዱ በመሆናቸውና፤ የበሰለ ምናባዊ አስተሳሰብ ስለሚጎድላቸው በታሪክ አወቃቀርና በአስተማሪነታቸው የጉማን የድርሰት መሰረት የያዙ አይደሉም ይላሉ፡፡

ፊልሙ ሀገር ዉስጥ  እንደማይገኝና በሀገረ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ተሰንዶ እንደተቀመጠ ተመላክቷል።

በዚሁ ምክንያት ዘመኑን በዋጀ መሳሪያና ባለሙያ ተሰንዶ ለእይታ እንዲቀርብ ቢሮው ጥረት እያደረገ ቢሆንም የኪነ-ጥበብ ተቋማትና ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ሠርፀ ፍሬስብሃት ጥሪ አቅርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያ ተቋማት የምስጋና ፕሮግራም አካሄድ

የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ነፃ የማስታወቂያ ሰዓት በመስጠት እንዲተዋወቅ እንዲሁም ማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኝ ስለአበረከቱትና እያበረከቱ ስላለው ድጋፍ እውቅና የመስጠት እና ምስጋና የማቅረብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ተካሄዷል።

ባለፉት ጊዜያት ነፃ የአየር ሰዓት ፣ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ በሚሊዮን ብሮች የሚያወጣ የሚዲያ አገልግሎት ለማዕከሉ እንደተሰጠም ተገልጿል።

ለማዕከሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የሚዲያ ተቋማት መካከል አርትስ ቲቪ፣ ኦቢኤን ፣ ኢቢሲ ፣ ኤፍቢሲ፣ኢቢኤስ፣አሻም ቲቪ ፣ ትርታ 97.6፣ ቲቪ 9 ፣ አሚኮ፣ አሐዱ ሬድዮ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በፕሮግራሙ ላይም በኢትዮጵያ ከ 7ሺ በላይ የልብ ህሙማን ህፃናት ወረፋ እየጠበቁ እንደሆነ እና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሹ ተገልጿል ።

የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል በሀገራችን የነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና በመስጠት ላይ የሚገኝ ብቸኛ ተቋም ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት ከ8000 በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና በማድረግ የነፍስ አድን ሥራዎችን እንዳከናወነ ተገልጿል።

ማዕከሉ ሁሉንም የሕክምና ወጪዎች ያለምንም ክፍያ በነጻ እንደሚያከናውን የገለፅ ሲሆን አስፈላጊ ወጪዎችንም በዋነኛነት ከማሕበረሰቡ በሚሰበሰብ ዕርዳታ በተጨማሪ ደግሞ ከሀገር በቀል እና የውጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ በመሸፈን ላይ እንደሚገኘ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1