"የትብብር ቤት" የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ከገበሬው ሪል ስቴት "የትብብር ቤት" የተሰኘ የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት ፕሮጀክትን ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።
ይህ የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት በዓይነቱ ለየት ያለ የሪልስቴት ቢዝነስ ሞዴል አቅም ያላቸው ቤት ፈላጊዎች እንደአቅማቸው ገንዘባቸውን ያለምንም ስጋት በራሳቸው የቤት ዲዛይን ምርጫ እንዲሁም በራሳቸው ተቆጣጣሪነት በአጭር ጊዜ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት አገልግሎት እንደሆነ ተገልጿል።
የከገበሬው ሪል እስቴት ድርሻ ማደራጀት፣ ቦታ መፈለግ እና ማመቻቸት፣ ህጋዊ ሁነቶችን ማስፈፀም፣ ዲዛይን እና የዋጋ ዝርዝር መቅረብ፣ የግንባታ ስራ አስተዳደር፣ ንብረት አስተዳደር ሲሆን ምንም አይነት የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ እንደማይሳተፍ የተነገረ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ከዘርፉ አይነት ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪ 10% ከገበሬው ሪል እስቴት እንደሚያገኝ ተነግሯል።
የከገበሬው ሪል እስቴት በትብብር ቤት የሚደራጁ ዘርፎች ዳውንታውን አንደኛ ደረጃ መሃል ከተማ፣ ሚድታውን ሁለተኛ ደረጃ መሀል ከተማ፣ ሰብረብ ሶስተኛ ደረጃ ከተማ ጠርዝ፣ ሲንግል ፋሚሊ፣ ዳያስፖራ፣ የንግድ ቤቶች እንደሆኑ ተገልጿል።
ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሚሊኒየም አዳራሽ ለሁለት ቀን ባደረግነው የተመጣጣኝ ቤቶች ምዝገባ ላይ ከ3000 በላይ ሰዎች እንደተመዘገቡ ተገልጿል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ድምፃዊ ወንዲ ማክ አልበም ማጠናቀቁን አስታወቀ
ድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) በይፋዊዉ የማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳለው በአዲስ አልበም መምጣቱን ገልፆል::
ወንዲ ማክ "ፈጣሪ ፈቅዶ እነሆ በአዲስ ዐልበም መጥተናል በቅርብ ቀን ይጠብቁን" ብሎ ቢገልፅም መች አዲስ አልበሙ እንደሚወጣ በግልፅ አልተናገረም::
ድምፃዊዉ ከዚህ ቀደም በሰራቸው "ሺ ሰማንያ" "ታገቢኛለሽ ወይ?" "አባ ዳማ" "ገዳይ" ን ጨምሮ በተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎቹ ተወዳጅነትን አግኝቷል::
መረጃው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነው

"ትንሣኤ ዘ ቀበና አቦ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘው የቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን "ትንሣኤ ዘቀበና አቦ" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
መጽሐፉ መፃፍ ያስፈለገበት ምክንያት ደብሩ 110 ዓመታትን ያስቆጠረና በርካታ ቅርሶችን የያዘ በመሆኑ ይህ ታሪክ ተቀብሮ እንዳይቀር ለማድረግ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
መጽሐፉ በ 5 ምዕራፍና 12 ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ፤ በታሪክ ፣ በነገረ ሊቃውንትና ፣ በደብሩ ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተወስቷል ፤ ስያሜውን ያገኘበትን ምክንያት አዘጋጆቹ ሲያስረዱ የቤተክርስቲያኒቱ ልማት በከፍተኛ ሁኔታ በመሄዱና ከነበረበት ሁኔታ በልማት ዳግም ከፍ በማለቱ እንዲሁም አሁን የምንገኝበትን የትንሣኤ ዘመን በማገናኘት እንደሆነም ገልጸዋል ፤ መጽሐፉ በ 6 ሰዎች ተጽፎ ለመጠናቀቅና ለምርቃት ለመብቃት ችሏል።
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በመገኘት መጽሐፉን ባርከው መርቀዋል በተያያዘም በመርሐ ግብሩ የደብሩ አስተዳዳሪ ፣ ተጋባዥ የደብር አስዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፣ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ት ቤት መዘምራን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
መረጃው የ ተ.ሚ.ማ ነው

"ለእናቴ" አሸናፊዎች በድምቀት ይሸለማሉ!
በእናት ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀው " ለእናቴ" የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት ፕሮግራም ነገ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በሒልተን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ይፈፀማል።
በዕለቱ የተለያዩ የሥነጽሑፍና የኪነ ጥበብ ስራዎች የሚቀርብ ሲሆን ስራዎቻየውን ከሚያቀርቡት ውስጥ ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ፤አርቲስት ዘሪቱ ከበደ፤ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፤አርቲስት ትዕግስት ግርማ፤ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ይገኙበታል።
የተጣመሩበትን 25ኛ አመታቸውን በቅርቡ ያከበሩት የቫዮሊን ተጫዋቾች የመድረኩ ድምቀት ሆነው ያመሻሉ።

የሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት የፊልም ሰንጠረዥ
ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ
ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ
ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ
ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ
በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት እነዚህ ፊልሞችን ለተመልካቾች ያቀርባሉ!
መልካም ሳምንት!
https://t.me/EventAddis1

የሳምንቱ በእይታ ላይ የሚገኙ ቴአትሮች ሰንጠረዥ
በአዲስ አበባ ከተማ በቋሚነት ሁለት የቴአትር ማሳያዎች ብቻ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህም የቴአትር ማሳያዎች አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና ዓለም ሲኒማ ናቸው።
በእይታ ላይ የሚገኙ ተውኔቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል።
☑️ ሶስቱ አይጦች
ድርሰት: ኤልያስ ተስፋዬ
አዘጋጅ: ካሌብ ዋለልኝ
ቀን: ማክሰኞ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️ ሀሁ ወይንም ፐፑ
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
አዘጋጅ: ተስፋዬ ሲማ
ቀን: ረቡዕ
ሰዓት: 11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️ ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️ ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️ ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
☑️ የሚስቶቼ ባሎች
ድርሰት:አበባየሁ ታደሰ
አዘጋጅ: ተስፋዬ ገ/ማርያም
ቀን: ረቡዕ
ሰዓት:12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
☑️ የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1

በድምጻዊት ህሩት በቀል ላይ ያተኮረ "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል
በዐብይ ፈቅይበሉ የተዘጋጅውና በድምጻዊት ሒሩት በቀለ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9:00 ጀምሮ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያዋ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሚታሰብበት ቀን ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በዕለቱ የፌድራል ፖሊስ ማርሽ ባንድን ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ ኦኬስትራ እና የዳዊት ፅጌ ባንድ እንዲሁም የሒሩት በቀለን ስራዎች ከሚያቀነቅኑት ታዋቂ ድምፃዊያን ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
መፅሐፉ ተፅፎ እስኪጠናቅ ድረስ 2.5 ሚልዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት የመፅሐፉ ደራሲ ዐቢይ ፈቅይበሉ ገልጿል።
ከመጽሐፉም የሚገኘው ገቢ በስሟ ለሚቋቋመው በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ምስረታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

ውድነህ ክፍሌ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ረቡዕ ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዕለቱ ፀሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ይገኛል።
እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።
ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

በእናት ባንክ የተዘጋጀው"ለእናቴ" የተሰኘው የሥነጽሁፍ ውድድር የሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ
"ለእናቴ" የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት ፕሮግራም ግንቦት 19 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሒልተን አዲስ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ተካሄዷል።
በሽልማቱ ሥነሥርዓቱ ላይ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡት አሸናፊዎች ጽሑፎቻቸው መድረክ ላይ የተነበበ ሲሆን ለአሸናፊዎቹም የተለያዩ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::
በዚህ የሥነጽሑፍ ውድድር ላይ አንደኛ በመሆን ትዕግሥት በዛብህ 125 ሺ ብር ተሸላሚ ስትሆን ሁለተኛ እየሩሳሌም ነጋ 100 ሺ ሶስተኛ ፀጋዬ ደሳለኝ 75 ሺ አራተኛ ማርታ አበራ 50 ሺ አምስተኛ እንዳለማው ቶሎሳ 25 ሺ ተሸላሚ ሆነዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ የሥነጽሑፍና የኪነ ጥበብ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ፤ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ፤ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፤ አርቲስት ትዕግስት አለሙ ፣ ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ስራዎቻቸውን አቅረበዋል።
እናት ባንክ በቅርቡ "እማዬ" የተሰኘ ቅርንጫፍ ለመክፈት በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ በትላንትናው የሽልማት መድረክ ላይ ተናግረዋል።
ውድድሩ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር ፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ የገለጸበት ሲሆን በይዘት ደረጃም ተዋዳዳሪዎች "ለእናቴ" ብለው ስለእናታቸው ያጋሩበት ፍቅርና ስሜታቸውን ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንዴት እንደገለጹ ፣ ስሜታቸውን ወደ ሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የተዳኙበት አውደ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።
📸 Credit ተክሌ ማርኮን

"እየዳነ ሄደ" መጽሐፍ አርብ ይመረቃል
የደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ "እየዳነ ሄደ" መጽሐፍ የፊታችን አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች የሥነጽሑፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
ከሰሞኑ ለንባብ የበቃው የገጣሚና ደራሲ ምግባር ሲራጅ "እየዳነ ሄደ" መጽሐፍ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ280 ገፆች ተቀንብቦ በ450 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
ገጣሚና ደራሲ ምግባር ሲራጅ ከዚህ ቀደም "ዘንባባ" እና "መንደሪን መንደሪን" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቡ ይታወሳል።

በአርቲስት ሒሩት በቀለ ስም የስኳር ሕመምተኞች ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው
በአርቲስት ሒሩት በቀለ ስም የስኳር ሕመምተኞች ፋውንዴሽን ሊቋቋም መሆኑ ተነገረ።
የአርቲስቷን የግል የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታትሞ በግንቦት 19 2016 ዓ.ም ለገበያ የቀረበ ሲሆን፥ የመጽሐፉ የሽያጭ ገንዘብ ለስኳር ሕሙማን ወገኖች መርጃ ይውላል ነው የተባለው።
በመርሐግብሩ ላይ የአርቲስቷ ወዳጅ ዘመዶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አንጋፋ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
የሂሩት በቀለን የጥበብ ስራዎች፣ በፌደራል ፖሊስ የማርቺንግ ባንድ ኦርኬስትራና በዳዊት ፅጌ ባንድ በሚታጀቡ ድምፃውያን በልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ ክንውኖች እየተዘከረ ይገኛል።
አርቲስት ሂሩት በስኳር ህመም ምክንያት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው።
መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

"ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ" ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን የፊታችን ሐሙስ ይከፈታል
ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን "ኢትዮጵያን እንገንባት" (ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ) በሚል መሪ ሀሳብ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን ከግንቦት 22 እስከ 24 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
በኤግዚቢሽኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ከ156 የአገር ውስጥና የውጪ አገር ድርጅቶች እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ ጎብኚዎች በኦንላይን ተመዝግበዋል ተብሏል ።
በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴርና እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ይቅርታ ጠየቀ
ባሳለፍነው ቅዳሜ ለአንባቢያን የደረሰው የአድማስ አድማስ ጋዜጣ የሌላ ጋዜጣ( የአዲስ ልሳን ጋዜጣን) ገፆችን ይዞ መውጣቱ በጋዜጣ አንባቢያን ዘንድ ውዥንብር እንደፈጠር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍሉም ስለተፈጠረው ጉዳይ ማብራሪያ ከሰጠ በኃላ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
የአድማስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል መልዕክት የሚከተለውን ይመስላል
"ለውድ አንባቢያን፡-ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ፣ ከዚህ ቀደም ያላጋጠመ ትልቅ ስህተት ተፈጥሯል፡፡ በብርሃንና ሰላም ማተምያ ቤት በተከሰተ “የቴክኒክ ችግር” ሳቢያ፣ የሌላ ጋዜጣ ገጾች ተቀላቅለው (ከእኛ ዕውቅና ውጭ) ለሥርጭት በቅቷል፡፡
ጋዜጣው ለሥርጭት ከመብቃቱ በፊት ስህተቱን ብናውቅ ኖሮ፣ ከሥርጭት ማገድ እንችል ነበር፡፡ ነገር ግን እኛም መረጃው የደረሰን ከውድ አንባቢያን በመሆኑ ከማዘንና ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻልንም፡፡ ከማተምያ ቤቱ ጋር በነበረን የ25 ዓመት ገደማ የጠበቀ የሥራ ግንኙነት፣ በየጊዜው ትናንሽ ስህተቶች ቢፈጠሩም፣ የአሁኑን ያህል ከባድ ስህተት አጋጥሞን አያውቅም፡፡
ከማተምያ ቤቱ ማናጅመንት ጋር በመነጋገር ስህተቱ የተፈጠረበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅና ዳግም መሰል ስህተቶች እንዳይከሰቱ ለማድረግ እየጣርን ነው፡፡ የራሳችንንም መፍትሄዎች እናበጃለን፡፡
ለአሁኑ ስህተት ግን ውድ የጋዜጣውን አንባቢያን በድጋሚ ከልባችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ የጋዜጣችንን የጥራት ደረጃ የማሳደግና ተነባቢ የማድረግ ጥረታችንን እንቀጥላለን፡፡"

"ለተሻለ ነገ እናንብብ" አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል
በኢትዮጵያ የኤፍ ኤም ሬድዮ ታሪክ ቀዳሚው የሆነው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የ24ኛው ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው "ለተሻለ ነገ እናንብብ " የተሰኘ የመጻሕፍት አውደርዕይ ከዛሬ ግንቦት 21 እስከ 27 2016 ዓ.ም ሸጎሌ በሚገኘው በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሚዲያ ኮምፕሌክስ ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
በርካታ የመጻሕፍት አቅራቢዎች ቅናሽ የተደረገባቸውን መጻሕፍት በአውደርዕዩ ላይ ይዘው ይገኙበታል።
በየዕለቱ አንባቢያን ከሚያደናቋቸው ደራሲያን ጋር የሚገናኙበት ዝግጅቶችም ተሰናድተዋል።
መግቢያው በነፃ ስለሆነ ማንኛውም የመጻሕፍት ወዳጅ እዚህ የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ መሳተፍ ይችላል ተብሏል።
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላለፉት ወራት "ለተሻለ ነገ እናንብብ" የተሰኘ የ100 ቀናት የንባብ ዘመቻ ሲካሄድ እንደቆየ ይታወሳል።

ውድነህ ክፍሌ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።