Event Addis Media
9.07K subscribers
5.22K photos
5 videos
3 files
3.93K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ታሰረ

የ"እብድት በህብረት" የአንድ ሰው ቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ እንደታሠረ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።

የቴአትሩ አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በፖሊስ" ትፈልጋለህ" ተብሎ እንደተወሰደ እና በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ከወራት በፊትም "እብድት በህብረት" ቴአትርን ለማሳየት ወደ እስራኤል ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበረውን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት "ትፈልጋለህ" በሚል እንደወሰዱት እና እስካሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሳምንቱ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ጥቆማ

📍"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ  መድረክ ነገ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

📍"ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ መድረክ" የፊታችን እሁድ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መገናኛ ዋኣች ሕንፃ ላይ በሚገኘው "ጣዕም ባህላዊ ምግብ ቤት" ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን:

Telegram:https://t.me/EventAddis1

Website: https://eventaddis.com

Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/
የሳምንቱን የሥነጽሑፍ ውይይቶች በአጭሩ

📍በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት በገጣሚ እና ደራሲ ታገል ሰይፉ "ዝንቡላ እና ካሮት"በተሰኘው መጽሐፉ ላይ  ውይይት ይካሄዳል።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል።

📍በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ት/ቤት በየሳምንቱ የሚዘጋጀው የሀሳብ ውይይት በዚህም ሳምንት "አዲስ አፍላጦናዊነት በቅዱስ ኦገስቲን ኑዛዜ" የተሰኘ ርዕስ መርጧል ይህም ውይይት  ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው አፄ ናኦድ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።"አዲስ አፍላጦናዊነት በቅዱስ ኦገስቲን ኑዛዜ"በሚል ርዕስ በዘካርያስ ደበበ መነሻ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል።

📍የብራና ጁፒተር የንባብ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም በዶ/ር መላኩ አዳል "ለሉሲ ሀገር ሰዎች" መጽሐፍ ላይ ውይይት ያካሄዳል። ይህ ውይይት ከ9:45 እስከ 12:00 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል።

📍 "አውደ ፋጎስ" 37ኛው ዙር የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ ይካሄዳል።በዚህኛው ዙር "አደባባያችን እንደገና ሲብሰለሰል"በሚል ርዕሰ ጉዳይ በሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ባለሞያዋ ነዋል አቡበከር መነሻ ሀሳብ ይቀርባል።ውይይቱ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የሁለት ጌቶች አሽከር" ተውኔት ዛሬ ይሰናበታል

በካርሎ ጎልዶኒ "The servant of two Masters" በሚል የተጻፈውና ወደ አማርኛ"የሁለት ጌቶች አሽከር" በሚል ርዕስ በተስፋዬ ገ/ማርያም የተተረጎመ ተውኔት ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ከመድረክ ይሰናበታል።

በተውኔቱ ላይ ሚኪ ተስፋዬ ፣ እታፈራው መብራቱ ፣ሔኖክ ዘርዓብሩክ ፣ሳምራዊት ከበደ፣እንዳለ ብርሃኑና ሌሎችም ተሳትፈዋል።

ተውኔቱ ከጥቅምት 9 2016 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሲመደረክ እንደቆየ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን አልበም ዛሬ ይለቀቃል

የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ይለቀቃል።

የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም ከዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" ላይ በመክፈቻው ዕለት በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ይመረቃል ተብሏል።

በዛሬው ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ሸክላው ለሽያጭ የሚቀረብ ሲሆን ሙዚቀኛውም የሙዚቃ ስራውን እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ብርሃን ኮንሰርት" ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ገቢው ለሰበታ መርሐ የዓይነስውራን ት/ቤት እንዲውል የተዘጋጀውና ነገ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ ሲገለፅ የቆየው"ብርሃን ኮንሰርት" ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ላይ ድምጻዊያኑ አብዱ ኪያር ፣ ቀመር የሱፍ ፣ ይርዳው ጤና ፣ባልከው አለሙ፣ ኃይማኖት ግርማና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎችን እንደሚያቀረቡ ሲገለጽ ቆይቷል።

ኮንሰርቱ በምን ምክያንት እንደተራዘመ አዘጋጆቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጡበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በድምጻዊት ህሩት በቀል ላይ ያተኮረ "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ ቀጣይ ሳምንት ለንባብ ይበቃል

በዐብይ ፈቅይበሉ የተዘጋጅውና በድምጻዊት ሒሩት በቀለ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው "አንፀባራቂዋ ኮኮብ" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9:00 ጀምሮ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያዋ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሚታሰብበት ቀን ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በዕለቱ የፌድራል ፖሊስ ማርሽ ባንድን ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ ኦኬስትራ እና የዳዊት ፅጌ ባንድ እንዲሁም የሒሩት በቀለን ስራዎች ከሚያቀነቅኑት ታዋቂ ድምፃዊያን ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

መፅሐፉ ተፅፎ እስኪጠናቅ ድረስ 2.5 ሚልዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት የመፅሐፉ ደራሲ ዐቢይ ፈቅይበሉ ገልጿል።

ከመጽሐፉም የሚገኘው ገቢ በስሟ ለሚቋቋመው በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ምስረታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

ግንቦት 4 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ዝነኛዋ የፖሊስ ኦኬስትራ የቀድሞ ድምፃዊት በኋላም ዘማሪት ሒሩት በቀለ በሙያዋ ለሀገሯ ያበረከተችውን ጉልህ አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገራችን የኪነጥበብ ባለሞያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የአርቲስቷ ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለሚዲያዎች መልዕክት ከኤቨንት አዲስ አዘጋጅ !

የመረጃ ምንጭን መጥቀስ/ክሬዲት መስጠት

ሚዲያችን Event Addis/ሁነት አዲስ የኩነት እና መዝናኛ መረጃዎች ምንጭ መሆን ከጀመረ የፊታችን ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ሁለተኛ ዓመቱን ይይዛል።

በእነዚህ ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ በየዕለቱ የሥነጽሑፍ ፣ የኪነጥበብ ፣ የሥነጥበብ ፣ የእድ ጥበብ፣ የኩነት እና ሚዲያ መረጃዎችን ለተከታዮቹ በፍጥነት እና በጥራት ሲያቀረብ ቆይቷል።

አሁንም በኢትዮጵያ ለሚገኙ በርካታ የቴሌቪዥን ፣ ሬድዮ ፣ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ፣ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሁነኛ የመዝናኛ መረጃዎች ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። በዚህም እጅግ ደስተኞች ነን። ከልብ እናመሰግናለን።

ነገር ግን በበርካታ የሬድዮ ፕሮግራሞች፣ በቴሌቪዥን ዜና ሰዓቶች ፣ጋዜጦች እና ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ መረጃዎችን "እንደወረዱ" የሚጠቀሙ ነገር የመረጃውን ባለቤት  "Event Addis/ሁነት አዲስ" ሚዲያን በተገቢው መንገድ የመረጃ ምንጩነቱን የማይጠቅሱ ፕሮግራሞች ገጥመውናል።በዚህም እጅግ እናዝናለን።

በተደጋጋሚም የኤቨንት አዲስ/ሁነት አዲስ መረጃዎችን ምንም አይነት ምንጭ ሳይጠቅሱ( Credit ሳይሰጡ) የሚጠቀሙ የሬድዮ ፕሮግራሞችን ፣ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችን ፣ የጋዜጣ እና ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ከነማስረጃው ለይትን ያስቀመጥን ስለሆነ በተገቢው መንገድ ምንጭ በመጠቀስ ለመረጃዎቻችን እውቅና እንዲሰጡ እናሳስባለን።

የሚዲያችንን መረጃዎች በተገቢው መንገድ ምንጭ ጠቅሰው ለሚጠቀሙ ሚዲያዎች ደግሞ አክብሮታችን የላቀ ነው እናመሰግናለን።

በተጨማሪም ብዙ ዋጋ ከፍሎ ያለምንም ዋጋ በነፃ መረጃዎችን እያቀረበ የሚገኘውን ቻናላችንን በማስተዋወቅ ብታግዙን እጅግ ደስተኞች ነን።

https://t.me/EventAddis1
የሳምንቱን የመጻህፍት መረጃዎች በአጭሩ

📍የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል። መጽሐፉ "የጊዜ ሠሌዳ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሲሆን የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው። ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ ከሁለት ዓመት በፊት  "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

📍 የደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ "ዮቶር 2" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።በ207 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ450 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።መጽሐፉ ጃፋር መጻሕፍት መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።ከዚህ ቀደም በደራሲ አለማየሁ ደመቀ የተጻፈው "ዮቶር ኮባላይ ካህን" 15ተኛ ዕትም መጽሐፍ ከሰሞኑ በድጋሚ ለአንባቢያን መቅረቡ ይታወሳል።

📍የገጣሚ አይዳ ታደሰ "አልፅፍም" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል።የግጥም መጽሐፉ በ140 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል በዓይናለም መጻሕፍት መደብር ውስጥም ይገኛል ተብሏል።መጽሐፉ “ሰቆቃ ወ አይዳ” እና “ምናብና ትዝብት” በተሰኙ ንዑሰ ርዕሶች ተከፍሎ የቀረበ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።

📍የገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ "ባሻ አሸብር በጀርመን" የግጥም መፅሃፍ ለሀገር ውስጥ አንባቢያን ቀረበ።ገጣሚ ሰሎሞን ሞገስ ከዚህ ቀደም እውነትን ስቀሏት እና ሌሎችንም የግጥም መድብሎች ለንባብ ያበቃ ሲሆን ይህኛው መጽሐፉ አምስተኛ ስራው ነው።

📍የመጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ "37 አልፋ ገ3" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

📍የህይወት ተፈራ"ማማ በሰማይ" ፣ "ምንተዋብ" እና "ኀሠሣ" የተሰኙ ሶስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው በዚህ ሳምንት ለአንባቢያን ቀረበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አንጋፋው ድምጻዊ ነዋይ ደበበ "የለዛ ሽልማት" የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነ

13ኛው የለዛ ሽልማት ሥነሥርዓት በዚህ ሰዓት በሒልተን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ አንጋፋው ድምጻዊ ነዋይ ደበበ "የለዛ ሽልማት" የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል።

የሽልማት ሥነሥርዓቱን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የ"ለዛ ሽልማት" ተሸላሚዎች ዝርዝር በአጭሩ

13ኛው የ"ለዛ ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል ተካሄዷል።

በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ አንጋፋው ድምጻዊ ነዋይ ደበበ የለዛ ሽልማት "የህይወት ዘመን" ተሸላሚ ሆኗል።

"በስንቱ" ድራማ በሶስት ዘርፎች ሶስት ሽልማቶችን አሸንፏል።በሌላ በኩል በሁለት ዘርፎች የታጨችው አርቲስት መስከረም አበራ ሁለቱንም የሽልማት ዘርፎች በማሸነፍ በሽልማት መድረኩ እንደነገሰች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የዘንድሮ የ"ለዛ ሽልማት" ተሸላሚዎች ዝርዝር

1.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ፊልም

☑️ ዶቃ ፊልም 

2.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ

☑️ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም)

3.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት

☑️ አርቲስት መስከረም አበራ (የሱፍ አበባ ፊልም)

4.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም

☑️ በስንቱ

5.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ

☑️ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ (በስንቱ )

6.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት

☑️ አርቲስት መስከረም አበራ (በስንቱ )

7.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ አልበም

☑️የግርማ ተፈራ ካሣ " ግን የት ሀገር ?" አልበም

8.የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ)

☑️ ወግዳይት (አሳላፊ አልበም)

9.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን

☑️የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ናዕት" ዘፈን

10.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ዘፈን

☑️የድምጻዊት ሔዋን ገ/ወልድ "ሸሙና"  

11.የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ

☑️የድምጻዊት ራሔል ጌቱ "ኢትዮጵያዬ"

12.የለዛ ሽልማት የህይወት ዘመን ዘርፍ ተሸላሚ

☑️ አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የትብብር ቤት" የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ከገበሬው ሪል ስቴት "የትብብር ቤት" የተሰኘ የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት ፕሮጀክትን ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ይህ የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት በዓይነቱ ለየት ያለ የሪልስቴት ቢዝነስ ሞዴል አቅም ያላቸው ቤት ፈላጊዎች እንደአቅማቸው ገንዘባቸውን ያለምንም ስጋት በራሳቸው የቤት ዲዛይን ምርጫ እንዲሁም በራሳቸው ተቆጣጣሪነት በአጭር ጊዜ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት አገልግሎት እንደሆነ ተገልጿል።

የከገበሬው ሪል እስቴት ድርሻ ማደራጀት፣ ቦታ መፈለግ እና ማመቻቸት፣ ህጋዊ ሁነቶችን ማስፈፀም፣ ዲዛይን እና የዋጋ ዝርዝር መቅረብ፣ የግንባታ ስራ አስተዳደር፣ ንብረት አስተዳደር ሲሆን ምንም አይነት የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ እንደማይሳተፍ የተነገረ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ከዘርፉ አይነት ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪ 10% ከገበሬው ሪል እስቴት እንደሚያገኝ ተነግሯል።

የከገበሬው ሪል እስቴት በትብብር ቤት የሚደራጁ ዘርፎች ዳውንታውን አንደኛ ደረጃ መሃል ከተማ፣ ሚድታውን ሁለተኛ ደረጃ መሀል ከተማ፣ ሰብረብ ሶስተኛ ደረጃ ከተማ ጠርዝ፣ ሲንግል ፋሚሊ፣ ዳያስፖራ፣ የንግድ ቤቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሚሊኒየም አዳራሽ ለሁለት ቀን ባደረግነው የተመጣጣኝ ቤቶች ምዝገባ ላይ ከ3000 በላይ ሰዎች እንደተመዘገቡ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ድምፃዊ ወንዲ ማክ አልበም ማጠናቀቁን አስታወቀ

ድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) በይፋዊዉ የማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳለው በአዲስ አልበም መምጣቱን ገልፆል::

ወንዲ ማክ "ፈጣሪ ፈቅዶ እነሆ በአዲስ ዐልበም መጥተናል በቅርብ ቀን ይጠብቁን" ብሎ ቢገልፅም መች አዲስ አልበሙ እንደሚወጣ በግልፅ አልተናገረም::

ድምፃዊዉ ከዚህ ቀደም በሰራቸው "ሺ ሰማንያ" "ታገቢኛለሽ ወይ?" "አባ ዳማ" "ገዳይ" ን ጨምሮ በተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎቹ ተወዳጅነትን አግኝቷል::

መረጃው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነው

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ትንሣኤ ዘ ቀበና አቦ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘው የቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን "ትንሣኤ ዘቀበና አቦ" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

መጽሐፉ መፃፍ ያስፈለገበት ምክንያት ደብሩ 110 ዓመታትን ያስቆጠረና በርካታ ቅርሶችን የያዘ በመሆኑ ይህ ታሪክ ተቀብሮ እንዳይቀር ለማድረግ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

መጽሐፉ በ 5  ምዕራፍና 12 ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ፤ በታሪክ ፣ በነገረ ሊቃውንትና ፣ በደብሩ ዙሪያ ያተኮረ  መሆኑ ተወስቷል ፤ ስያሜውን ያገኘበትን ምክንያት አዘጋጆቹ ሲያስረዱ  የቤተክርስቲያኒቱ ልማት በከፍተኛ ሁኔታ በመሄዱና ከነበረበት ሁኔታ በልማት ዳግም ከፍ በማለቱ እንዲሁም አሁን የምንገኝበትን የትንሣኤ ዘመን በማገናኘት እንደሆነም ገልጸዋል ፤ መጽሐፉ በ 6 ሰዎች ተጽፎ ለመጠናቀቅና ለምርቃት ለመብቃት ችሏል።

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በመገኘት መጽሐፉን ባርከው መርቀዋል በተያያዘም በመርሐ ግብሩ የደብሩ አስተዳዳሪ ፣ ተጋባዥ የደብር አስዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፣ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ት ቤት መዘምራን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

መረጃው የ ተ.ሚ.ማ ነው

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ለእናቴ" አሸናፊዎች በድምቀት ይሸለማሉ!
 
በእናት ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀው " ለእናቴ" የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት  ፕሮግራም  ነገ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ  በሒልተን ሆቴል  በደመቀ ሁኔታ ይፈፀማል።

በዕለቱ የተለያዩ የሥነጽሑፍና  የኪነ ጥበብ ስራዎች የሚቀርብ ሲሆን ስራዎቻየውን ከሚያቀርቡት ውስጥ ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ፤አርቲስት ዘሪቱ ከበደ፤ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፤አርቲስት ትዕግስት ግርማ፤ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ይገኙበታል።

የተጣመሩበትን 25ኛ አመታቸውን በቅርቡ ያከበሩት የቫዮሊን ተጫዋቾች የመድረኩ ድምቀት ሆነው ያመሻሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት የፊልም ሰንጠረዥ

ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ

ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ

ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ

ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ

በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት እነዚህ ፊልሞችን ለተመልካቾች ያቀርባሉ!

መልካም ሳምንት!

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1