Ethiopian Lecturers Voice
9.59K subscribers
328 photos
15 videos
20 files
216 links
Download Telegram
======Inbox=======
ሰላም ውድ መምህራን

አኔ አዲስ አበባ ለስብሰባ ትሄዳለህ ብለው የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት መርጠውኛል።

አሁን ላይ ሳየው መምህራን ምርጫው በድብቅ የተደረገ ነው እያሉ ባለበትና እንደተባለው እኔን የመምህራን ተወካይ ( የመምህራን ማህበሩ ተወካይ) ነህ ብለው ከሆነ የመረጡኝ ትክክል አለመሆኑን በመገንዘቤ ከውይይቱ ቀርቻለው ። በመምህራን፣ በተማሪወችና በማህበረሰቡ መገለል አልፈልግም ።

እባካችሁ ስሜና መረጃየ ደርሷችሁ ስለሚሆን እንዳትለጥፉኝ ።
🙏119👍194👏4
ብልጽግና 40 አባላቱን_ከወሎ ዩኒቨርሲቲ?
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -

በትህነግ ሲዘወር የነበረውን ኢህአዴግን ገዝግዞ የጣለው፤ በየወረዳ፣ እና ዞኑ የነበሩት አባላቱ ስለመሆናቸው አይካድም።

ድርጂቱን ዋሽተውት፦ እንደ መልአክ ሰግደውለት፣ መሬት ላይ ያለውን እውነት ደብቀውት፥ አመታትን ከወረዳ ዞን_ከዞን ክልል_ከክልል ፌደራል መድረኮችን ተሳትፈው አልፈዋል፤ ጉድጓድ ሲቆፍሩለትም ነበር።

የህዝቡን መልክ ለላይኛው የውሳኔ ሰጭ አካል ከማሳየት፤ሮሮውን በአግባቡ ከመግለጽ ይልቅ፤ ገባሪነታቸውን ለማስረገጥ ሲሉ ሲዋሹት ነበር ፤ ድርጂቱን ከመሞገት ይልቅ መድረኮችን ሁሉ በጭቦጫቦ አናግተው ይመለሱ እንደነበር የሚረሳ አይመስልንም። የብልጽግናም አካኼድ የተለዬ አይመስልም።

የመምህራኑን ጥያቄ ለማስገንዘብ በሚል ኺደት፤ ሰሞኑን በየዩኒቨርሲቲው የሚላኩ መምህራን ፤ በግልጽ የማይታወቁ ፣ እና የራሱ የብልፅግና አባላት እስከሆኑ ድረስ፤ የእኛን (የመምህራንን) ጥያቄዎች አስመልክቶ በውይይቱ እውቅና የሚቸራቸውም ሆነ የሚፈቱ ችግሮች እንደማይኖሩ ሊታወቅ ይገባል።

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ፓርቲነቱ ፤ በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙ አባላቶቸን አወያያለሁ ከሆነ ጉዳዩ ይችላል።


ርዕሷን "በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የብልጽግና አባላት ውይይት" በሚል መርሃ ግብር የመንቀሳቀስ መብቱ የድርጂቱ ሲሆን፤ መድረኩ በማንኛውም መንገድ የመምህራንን፣ እና ረዳቶቻቸውን ትግል፣ እና ጥያቄ የሚመለከት ስላለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ትግላችን ቀጣይነት አለው፤ የመምህራኑ ጥያቄ ፍትህ ይሻል።

#ወሎ ዩኒቨርሲቲ
👍75💯2
==========ምስጋና=======

ምስጉን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ምርጫ ማካሄዳቸውን ገምግመናል ። በዚህም ብዙ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር አመራሮች ውይይቱ ላይ ይገኛሉ ።

የመምህራን ማህበር አመራሮችን ያላካተቱ ጥቂት ዩኒቨርሲቲወች ወይም ፕሬዝዳንቶች ሲሆኑ ነገ በ 14/05/2015 ዓ.ም የማስተካከያ ስራ ይሰራሉ ብለን እናስባለን ። ከሌሎች ተለይታችሁ የመምህራን ተወካዮችን ያላሳተፋችሁበት የትኛውም ምክንያት ጠቃሚ አይደለም ።

በተረፈ ከተመረጡ ሰወች ውስጥም በጣም እንቁ መምህራን አሉበት ። የምትሄዱ ሰወች ትልቅ ሀላፊነት አለባችሁና በትልቅ ሞራልና ወኔ ጥያቄወቻችንን እንድታነሱ አንጠይቃችኃለን ። በተቻለ መንገድ ከየዩኒቨርሲቲው የምትሄዱ ተወካዮች ጠንካራ ፅሁፍ አዘጋጅታችሁ እድል የሚሰጠውን ሰው መርጣችሁ አስቀምጡ ። እድል በሚሰጥበት ጊዜ በየዩኒቨርሲቲው እድል የተሰጣቸው ብቻ እጅ እንዲያወጡ በማድረግ መታገል ስለሚቻል እንተጋገዝ።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ከታች እስከ ላይ ወጥተው ወርደው ት/ት ሚ/ር ፣ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፣ የሰው ሀብት ቋሚ ኮሚቴ ፣ ገንዘብ ሚ/ር ፣ ገቢወች ሚኒስቴር ፣ ብልፅግና ፅ/ቤት ፣ ጠ/ሚ/ፅ/ቤት በመመላለስ ጥያቄ አቅርበው ብዙ እርቀት መሄዳቸውን እና ብዙ መስዕዋት በመክፈል ለዚህ አንድነት አብቅተው እንዳይሳተፉ ያደረጉ አካላት መኖራቸውን እንደ መምህር እናወግዛለን ።

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ተወካዮቻችንን አደራ ላኩልን ። በእናንተ እምነት አለን ። ፍትሀዊ ምርጫ ያደረጉ ፕሬዝዳንቶች እናመሰግናለን ።

በሰሞኑ ስብሰባ የተወሰነውን ውሳኔ ለመስማት መሄድ ጥሩ ቢሆንም ምላሽ የማይሰጥባቸውን ጉዳዮች ማንሳት ተገቢ ነው ።

@EUASAs

Share
🔥37👍29👏4🙏4
ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲደርሱላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄወች በፅሁፍ መወያያ ገፁ ላይ በማስቀመጥ ተሳታፊወችም እድሉን ሲያገኙ እንዲያነሱት አሳስቧቸው ።

ያነቡታል
በተረፈ ስድብ አይፈቀድም ።
👍36👏3🔥1
Forwarded from Asnake Teshome
Ethiopians Acadamic technical assistant qustion.pdf
923.1 KB
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወያት በየዩኒቨርስትቲዉ የተመለመላችሁ የዩኒቨርስቲ አመራሮች እና የመምህራን ተዎካዮች የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በዉይይቱ ተሳታፊ ባለመሆኑ ቴክኒካል ረዳቱን የሚመለከቱ ከዚህ በታች የተቀመጡ ጥያቄወችን ከቻላችሁ በዝረዝረ ካለበለዚያ ደግሞ መሰረታዊ ጥያቄወችን ለይታችሁ እነድታቀርቡልን አደራ ሰጥተናችኋል፡፡
👍44🙏71
የዩኒቨርስቲ መምህራን መግለጫ.pdf
1.8 MB
ከዚህ Pdf ደግሞ ጠቅላላ ሀሳቦችን ወስደው ማቅረብ ይችላሉ ።
👍23
Today's general meeting will begin at 2:30 LT, so please be informed and be on time.
👍394
Hey! Join our video chat: https://t.me/+ZCuDwWUf4XQyMjZl
👍15
👉 በየዩኒቨርሲቲው የተመረጡ ተወካዮች የተመረጡት እንዴት ነው ?

👉 ምን ምን መልዕክት እንዲያስተላልፉላችሁ ትፈልጋላችሁ?

👉 የቀጣይ ትግሎቻችን ምን መሆን አለበት?

Mic ከፍታችሁ ሀሳብ ስጡ ።
👍34
ድንቅ ውይይት

ወንድሞቻችንን እናመሰግናለን ።
👍38🙏12
👍16👏81💯1
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
ሁሉም በሚፈለገው ልክ እየሄደ ነው ። መምህራን ማህበር ማስመረጥ ፣ በቦርድ መሰብሰብ ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር እንዲሰበስቡ ማድረግ ። የቀረው ለጥያቄወች መልስ ነው ። እሱም በመምህራን ጠንካራ አቋም መሰረት እንዲመለስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ከፍተኛ ሀላፊወች ከፍተኛ ግፊት ጫና ተደረጎ የሆነ ደረጃ ቢደርስም ውጤቱን ለማየት ግን አሁንም መታገል እና አቋምን ማሳወቅ ግድ ይላል ።

መንግስት በሰላማዊ እንቅስቃሴ አለማመኑ እና ህጋዊ መንገድን ተከትለው ሲደክሙ እና ሁሉንም መስሪያ ቤቶች ሲያንኳኩ መመለስ አለመቻሉ በጣም ያሳዝናል ።

ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ተወካዮቻችን ተደራድረው በጀት አስተክለው ብዙ ውጣ ውረድ ወጥተው ከተፈቀደ በኃላ ቃልን ማጠፍም እንደዛው ።
👍62👏3🔥1
👍532😢1
======ትብብር =======
አጣብቂኝ ችግር ውስጥ ስለሆንኩ ብቻ ችግሬን ሳልፈልግ እንድትጋሩኝ
ፈኩ!

አበበ ጉሌ ግርማ እባላለው በወልድያ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህር ስሆን በአሁኑ ሰሀት በሀገር አዘርባጃ ካዛር ዩኒቨርስቲ ውስጥ የፒኤችዲ ትምህርቴን እየተክታተልኩ እገኛለው።

ወደ አጀንዳየ  ስመጣ እ. ኤ. አ   ታህሳስ 31/2022 ዓም ለሊት ላይ በተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ   ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ህይወቴን ከማትረፍ ውጭ ምንም አይነት ነገር ማትረፍ አልቻልኩም   ፓስፖርትና የመኖሪያ ፈቃድ የትምህርት ማስረጃ ሰርተፍኬት፡ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶቸ እና ልብስ የሚባል ነገር በሙሉ ወድሞብኛል ፡፡ በዚህም ምክንያት የወደሙብኝ አስፈላጊ ዶክመንቶች እንዲተኩ ከምማርበት ዩኒቨርስቲ ቀጥታ ቱርክ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን ለዚህም ኢምባሲው ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጠፉብኝ የትምህርት ማስረጃወችና ፓስፖርቴ እንዲተኩልኝ  ደብዳቤ ጽፏል፡፡ አሁን ላይ ከኢምባሲው በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ተጽፎ  እንደተቀመጠና ነገር ግን ይህን  የሚያስፈጽምልኝ ሰው እንደሚያስፈልገኝ ተነገረኝ። ነገር ግን ውልደቴና እድገቴ ገጠር እደመሆኑ መጠን ይህንን የሚያስፈጽምልኝ ሰው በማጣቴ ምክንያት አየር ላይ ተንሳፍፌ እገኛለው፡፡
የተደራጀ  የመምህራን ማህበር  ካለ ወይንም ከትምህርት ሚኒስቴር እንደዚህ አይነት ነገሮችን የሚከታተል ቢሮ ካለ  ጉዳዩን ብታደርሱልኝና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተጻፉ ደብዳቤወችን ተቀብሎ ከሚመለከተው አካል ጋር በመውሰድ እንዲያስፈጽሙልኝ ብተተባበሩኝ ስል ከአክብሮት ጋር እጠይቃለው።

አመሰግናለው! ፈቃደኞች WhatsApp +994508946234 @Cufed አውሩት
👍88💯92
ውድ የስብሰባው ተሳታፊዎቻችን

እንኳን ወደ ውቢቷ አዲስ አበባ በሰላም መጣችሁ ። ቆይታችሁ ያማረ እና ፍሬያማ ይሁንላችሁ ።

Edited and Just FYI

"Good Evening,

This is a kind remember for tomorrow's meeting.

Please be informed that mobile phones and any kind of electronic devices are not allowed. Kindly communicate the same to your respective team member."


@EUASAs
🙏47👍32🔥3