EBS TV
4.53K subscribers
7.13K photos
185 videos
48 files
409 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በሙሉ ዐቅም ወደ ሥራ ለመግባት ያሉ የደመወዝ፣  የደንብ ልብስ፣  የትጥቅና የተሽከርካሪ ጉድለቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊሟሉ ይገባል " - የፖሊስ አባላት

የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ወደ መደበኛ ሥራው ለመግባት የሚያስችለውን ውይይት ከትግራይ ፖሊስ አባላት ጋር ማካሄዱ ተገለጸ።

የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮሎኔል ገብረየውሃንስ አባተ (ወዲ አባተ) ፥ ፖሊስ ከአንድ አካል ወገንተኝነት ወጥቶ ሁሉንም በእኩልነት ሊያገለግል በሚችልበት መንገድና ዐቅም ባለመገንባቱ የፖሊስና የፀጥታ አካላት ተዓማኒነት ሲጎድል መቆየቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ይህ ለዓመታት የዘለቀው የተሳሳተ አካሄድ ሊያበቃ እንደሚገባና ፖሊስ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱንና ሙያዊ ኃላፊነቱን በተግባር ለመወጣት ሙሉ ዝግጁነት ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀና የሕዝብን ፀጥታ በብቃት የሚጠብቅ የፖሊስ መዋቅር ለመገንባት ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመሆን የሀገር ውስጥና የውጭ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት እንዲሁም ቁሳቁሶችን ለማሟላት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮሎኔል ንጉሥ ወልደገብርኤል (ወለጋ) በበኩላቸው፣ አብዛኛው የትግራይ ፖሊስ አባል የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ስራ መግባቱን በመግለጽ፣ አሁንም ያሉ ክፍተቶችን በማሟላት ወደ ሙሉ የማስፈጸም ዐቅም ለመግባት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ እና ሀሳባቸውን የሰጡት የፖሊስ አባላት፣ በሙሉ ዐቅም ወደ ሥራ ለመግባት ያሉ ፦
- የደመወዝ፣
- የደንብ ልብስ፣
- የትጥቅና የተሽከርካሪ ጉድለቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሟሉ ጠይቀዋል።

ያሉት እጥረቶች ተሟልተው የሚያጋጥሙ የሰው ሕይወት፣ የሀብትና ንብረት አደጋዎችን ለመጠበቅ በሕዝብና በመንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአባላቱ የተነሱት ጥያቄዎች ከፌዴራል መንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት እንደሚሠራ በመድረኩ የተገኙ የሚመለከታቸው አካላት መግለጻቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ሳቅ እና ጨዋታ !📞

እንደልባችን ለማውራት የሚያስችለን በ20 ብር ብቻ የሳምንት 60 ደቂቃ በመግዛት እንደውል።

አሁኑኑ *777*1# ብለው ይደውሉ!

#SafaricomEthiopia
#VoicePackage
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle ⛽️ ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ አቅርቦት ወደ ትግራይ መግባት መጀመሩ ተገለጸ። ዛሬ ነዳጅ በመቐለ በሁለት ማደያዎች በመደበኛነት መከፋፈል መጀመሩ ተመላክቷል።

የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስፈጻሚ ቴድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) የነዳጅ ዕደላው በቀጣይ በሌሎች ማደያዎችና ወደ ሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በተከታታይ እንደሚዳረስ ገልጸዋል።

የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በበኩላቸው ፥ ከአንድ ዓመት በላይ ነዳጅ ወደ ትግራይ ባለመግባቱ በእነርሱም ሆነ እንደ ትግራይ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥም መቆየቱን ጠቅሰው ፤ ይህ ጅማሮ ቀጣይነት ያለውና የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የፀጥታ አካላት ደግሞ " በነዳጅ ክፍፍሉ ሂደት ፍትሐዊነት እንዲኖር እንሰራለን " ማለታቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ፣ በነዳጅ መጥፋት ምክንያት ተሰቅሎ የቀረው የትራንስፖርት ታሪፍ ወደ ቀድሞው ዋጋ ተመልሶ የሕዝቡን ኑሮ በማቃለል የነዳጅ መግባቱ ትርጉም ሊሰጥ ይገባል። እንዲሁም ደግሞ ነዳጁ በጥቁር ገበያ እየተቸበቸበ ፤ የጥቂቶችን ኪስ እንዳያደልብና ሕዝቡም እንዳይበዘበዝ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል።

ፎቶ፦ Tigray TV

ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ቤተልሔም ተስፋዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ የነበረችው ቤተልሔም ተስፋዬ ባጋጠማት ድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ተቋሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ከተቋሙ ባገኘው መረጃ ለቤተልሄም ህልፈት ምክንያት ተብሎ የተገለጸው መታጠቢያ ቤት (ሻወር ቤት) ውስጥ በተፈጠረ የመውደቅ አደጋ ምክንያት መሆኑን ተረድቷል።

ቤተልሔም ተስፋዬ እድሜዋ 39 እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ባለትዳርና የሦስት ሴት ልጆች እናት ነበረች።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በባልደረባው ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ባወጣው መግለጫ ቤተልሔም በጋዜጠኝነትና በሕዝብ ግንኙነት ሙያዋ ለሀገሯና ለሕዝቧ በትጋት ያገለገለች ባለሙያ እንደነበረች አስታውሷል።

በቆይታዋም ፦

• በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

• በብሔራዊ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት

• በቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

• በሁዋዌ እና በመጨረሻም በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በተለያዩ የሙያ ኃላፊነቶች ማገልገሏ ተገልጿል።

ስርዓተ ቀብሯ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተፈጸመ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ከነገ ጀምሮ ወደ ሽረ መደበኛ በረራ ዳግም እንጀምራለን "-የኢትዮጵያ አየር መንገድ(ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የቆየውን የሽረ ከተማ መደበኛ በረራ በነገው ዕለት (ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም) ዳግም እንደሚጀምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

አየር መንገዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ መሠረት ከነገው የሽረ በረራ መጀመር ባሻገር ወደ ታሪካዊቷ የአክሱም ከተማ የሚደረገውን በረራም በድጋሚ ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም መሠረት የአክሱም ከተማ በረራ ከሰሞኑ ዳግም አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ተከስቶ ከነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቐለ፣ ሽረ እና አክሱም ከተሞች ያደርጋቸው የነበሩ መደበኛ በረራዎችን በጊዜያዊነት ማቋረጡ ይታወሳል።

ከነዚህ መዳረሻዎች መካከል ወደ ክልሉ መዲና መቐለ የሚደረገው መደበኛ በረራ ከሁለት ሳምንታት መቋረጥ በኋላ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ዳግም መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን የነገው የሽረ በረራ መጀመርና በቅርቡ የሚጀመረው የአክሱም በረራ የክልሉን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው የሚመልስ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን አየር መንገዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

አቶ አደም ፋራህ ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት ከዚህ ቀደም የአየር መንገዱን ቦርድ በሰብሳቢነት ሲመሩ ከነበሩት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ነው።

ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ሰኔ 2015 ዓ.ም ነበር።

በከፍተኛ የመንግሥትና የፖለቲካ አመራርነት እርከን ላይ የሚገኙት አቶ አደም ፋራህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia