Ethio telecom Family
6.26K subscribers
3.24K photos
7 videos
398 files
258 links
ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርናል ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
Download Telegram
10
የምስራች!!!

የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ LTE ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በሃገራችን 26 ከተሞች ማስጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን፡፡

በከተሞቹ የምትገኙ ደንበኞቻችን ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት በማቅረብ ምርታማነትን ለማሳደግ እና ቢዝነስን ለማቀላጠፍ በሚያስችለው አዲሱ 4G LTE የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በፈጣኑ 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎታችን እንድትደሰቱ እንጋብዛለን!

የሚገለገሉበት ሲም ካርድ 4G የሚያስጠቅም ከሆነ የሞባይል ሴቲንግዎን ኔትወርክ ሞድ LTE/3G/2G (Auto connect) በማድረግ ወደ ላቀው ፍጥነት ይቀላቀሉ!

ሲም ካርድዎ 4G የማያስጠቅም ከሆነ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የአገልግሎት ማዕከል ጎራ ብለው በነጻ በማስቀየር ልዩ የጥቅል ስጦታ ይግኙ!

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#4GLTE
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
8🔥2👏2
👍154🔥1
14👍1👏1
👍12
👍72
🍋 እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

🎉 በዓሉን አስመልክቶ በማይ ኢትዮቴል፣ በ*999# ወይም አርዲ ቻትቦት በ10% ቅናሽ የቀረቡትን ልዩ የጥምቀት በዓል ጥቅሎች ለራስዎ ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ ያበርክቱ!

🔗 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/telebirr ሲገዙ ተጨማሪ 30% ስጦታ ያገኛሉ!

መልካም በዓል!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #SmartAfrica #RealizingDigitalEthiopia
10👏1
መልካም የከተራ በዓል!
16🔥3
14
6👍6👏3
👍116
በኩባንያችን የደቡብ አዲስ አበባ ዞን በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ሴት ህግ ታራሚዎች ማረፊያ ማዕከል የመማሪያ ደብተር ደጋፍ አደረገ!

ኩባንያችን ማህበራዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ በኩባንያችን የደቡብ አዲስ አበባ ዞንም ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ስር በእርምት ላይ ለሚገኙ ሴት ህግ ታራሚዎች ማረፊያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል ከ4,800 በላይ የመማሪያ ደብተር ድጋፎችን አድርጓል፡፡

ይህም የህግ ታራሚዎችን ባህሪ አርሞና ዕውቀት አስጨብጦ ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ አድርጎ የማውጣት ተልዕኮ ላላቸው ማረሚያ ቤቶች ይህንን ዓላማ ለማሳካት የላቀ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን፣ በተለይም የህግ ታራሚዎችን በትምህርት ቁሳቁስ መደገፍ ስነ-ልቦናዊ ለውጥና ተስፋን እንዲገነቡና አዳዲስ ነገሮችን እንዲማሩ እንዲሁም ለነገ የተሻለ ዜጋ የመሆን ተስፋን እንዲኖራቸው የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡

የኩባንያችን የደቡብ አዲስ አበባ ዞን ኦፕሬሽናል ዳይሬክተር አብርሀም ታደሰ የመማሪያ ደብተሮችን ያስረከቡ ሲሆን፣ ኩባንያችን የህግ ታራሚዎች የሚማሩበትን ትምህርት ቤት በተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስና ቴክኖሎጂ በመደገፍ ታራሚዎች ከማረሚያ ቤት ሲወጡ መልካም ስነ-ምግባር የተላበሱ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጎች ሆነው እንዲወጡ ላበረከተው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና ቀርቧል፡፡

ለተጨማሪ፡https://bit.ly/VivaEngageInternalComm

#ESG #GSMA #Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #SmartAfrica #RealizingDigitalEthiopia
6👏6🥰1