Ethio telecom Family
6.24K subscribers
3.27K photos
7 videos
405 files
259 links
ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርናል ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም የእንስሳት አያያዝን የሚያዘምን እና የሚገኙበት ቦታ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አደረገ!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት በላቀ አይ.ኦቲ (IoT) የተደገፈ እና የሀገራችን የእንሰሳት አስተዳደርን ለማዘመን የሚያስችል ክላውድን መሰረት ያደረገ ዲጂታል የእንሰሳት መከታተያ ሶሉሽን (Digital Cattle Tracking Solution) ተግባራዊ ማድረጉን በታላቅ ደስታ ይገልጻል።

ይህ ዘመናዊ ሶሉሽን አርሶ አደሮች እና እንሰሳት አርቢዎች በቀላሉ እንስሳቶቻቸውን መከታተል፣ ያሉበትን ቦታ መለየት እና የጤና ሁኔታቸውን መገምገም እንዲችሉ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ በተለይም የእንስሳት ባለቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገበሬዎችን እና ሌሎች እንስሳት አርቢዎችን ለማበረታታ፣ የእንስሳት እርባታ አያያዝን እና የግብርና ዘርፉን ለማዘመን በተለይም የእንስሳትን ዋጋ እና ጤንነትን መገምገም የፋይናንስ ተቋማትም የእንስሳትን ሀብት እንደ መያዣ በመቀበል አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች የብድርና የኢንሹራንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ እና ይበልጥ የቴክኖሎጂ ትስስር ወዳለው ግብርና በመግባት የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን እውን ለማድረግ የምታደርገውን ሁሉገብ ግስጋሴ የሚያጠናክር ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica
👍14🥰1
በስማርት ስልክ የሚሰራ የፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ሶሉሽን ለድርጅት ደንበኞች በይፋ አስጀምረናል!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት ድርጅቶችና ተቋማት የግንኙነት ስርዓታቸውን በእጅጉ ለማዘመን የሚችሉበት ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ (PTT/PTV) የተሰኘ የቡድን ኮሙኒኬሽን ሶሉሽን ይፋ አድርጓል።

ይህ በክላውድ ላይ የተመሰረተ የኮሙኒኬሽን ሶሉሽን በማንኛውም ስማርት ስልክ እና የሞባይል ኔትወርክ ባለበት ቦታ ሁሉ የሚሰራ መሆኑ እንዲሁም ከድምጽ ባሻገር የጽሑፍ፣ ምስል እና ቪዲዮ መለዋወጥ ማስቻሉ ከቀድሞው የፑሽ-ቱ-ቶክ ሬዲዮ አገልግሎት የላቀ ያደርገዋል፡፡

ሶሉሽኑ እንደ ሎጅስቲክስ፣ ደህንነት፣ በግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መስተንግዶ እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች የቡድን ቅንጅትን እና ደህንነትን ለማሳደግ ቅልጥፍናቸው እና ምላሽ ሰጪነታቸው ፈጣን ያደርጋል።

አገልግሎቱ ድርጅቶች ግንኙነታቸውን እንዲያቀላጥፉ፣ ስራቸውን እንዲያሳልጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲገናኙ የሚያስችል የቡድን መገናኛ መፍትሔ ይዞ ቀርቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍18👏51🥰1
ለፋይናንስ ተቋማት አዲስ በክላውድ ላይ የተመሰረተ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ይፋ አድርገናል!

ኩባንያችን የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን እና የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራትን በዘመናዊ የዲጂታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ለማስታጠቅ የሚያስችል የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ሶሉሽኑ የፋይናንስ ተቋማት አሰራራቸውን በማቀላጠፍ፣ የደንበኛ ተሞክሮን በማሻሻል እና አገልግሎታቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ክላውድ አማካኝነት ለብዙኃን ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማት ወጪዎችን እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል።

ኩባንያችን አስተማማኝ የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን በማቅረብ የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገለግሉ እና በሀገራችን የፋይናንስ አካታችነት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica
👏7👍6🥰2
👍7🥰2
የትምህርት ተቋማት አሰራርን የሚያዘምን ዲጂታል የትምህርት አስተዳደር ሶሉሽን ይፋ አድርገናል!

ይህ በክላውድ የተደገፈ ሶሉሽን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የትምህርት ተቋማት አስተዳደርን፣ መምህራንን፣ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በዲጂታል ፕላትፎርም በማስተሳሰር ጠንካራ የትምህርት ተቋም ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላል፡፡

ሶሉሽኑ የተማሪዎችን ውጤት ክትትል፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የተማሪ-ወላጅ-መምህር ተሳትፎን በማጎልበት እንዲሁም የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት በማቅረብ የትምህርትን ጥራት በእጅጉ ለማሳደግ ያግዛል።

በተጨማሪም፣ ሶሉሽኑ የክፍያ ሂደቶችን በቴሌብር በማቀናጀት የወላጆችን ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል፤ የትምህርት ተቋማትን አስተዳደራዊ ቅልጥፍና ያሳድጋል።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia
👍13🥰1