Ethio telecom Family
6.24K subscribers
3.26K photos
7 videos
404 files
258 links
ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርናል ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡

ይህ ኩባንያችን የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ሀገራዊ ጥረት አካል ሲሆን፣ የላቀ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት በማዳረስ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት ዕድሎች በር ለመክፈት ያስችላል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ሉሲ ሆቴልና ደሴ ሙዚየም አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

በኮምቦልቻ ደግሞ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

አገልግሎቱ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግና ዲጂታል ክህሎትን ለመጨመር ያስችላል።

5ጂ የግል እና የመንግስት ተቋማትን አሰራር ያዘምናል፤ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ማኑፋክቸሪንግን፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝምን የመሳሰሉ ቁልፍ ዘርፎችን በማዘመን ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

በአዲስ አበባ በ2022 እ.ኤ.አ ያስጀመርነው 5ጂ ደሴ እና ኮምቦልቻን ጨምሮ በ14 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ፣ ቢሾፍቱና ጅማ አገልግሎት ላይ ውሏል።

ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/3F2QyJe
👏12👍8🥰1
ውድ ቤተሰቦቻችን መልካም ቀን! ስኬታማ የሥራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
#MondayMotivation
#Ethiotelecomfamily
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
የቪቫ ኢንጌጅ ቻናላችንን ለመቀላቀል: https://bit.ly/3NoMbcx
👍13🥰1
በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን የተመራ የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ አመራር የደሴ ከተማ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት አፈጻጸም ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ የደሴ ከተማን አስተዳደር በስማርት ሲቲ ለማዘመን በምዕራፍ በመካሄድ ላይ ያለው ፕሮጀክት በጥሩ ትግበራ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱ ሥራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ትግበራ በመሆኑ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ የግብር አሰባሰብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች አገልግሎቶች ክፍያዎችን ከእጅ ንክኪ በጸዳ መልክ በቴሌብር መከናወን እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም ስማርት ሲቲ የከተማን ደህንነት አስተማማኝ ከማድረግ እና ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባሻገር የነዋሪዎች አሰፋፈር፣ የአካባቢ ጽዳትና የትራፊክ ፍሰት የመሳሰሉ መረጃዎችን በቀላሉ በማግኘት የመልሶ ልማትን እንደሚያፋጥን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ኢ-ጋቨርናንስ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የዲጂታል መሰረተ ልማት መደላድል መፈጠሩን የተገለጸ ሲሆን ይህም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡


#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#Dessie #SmartCity #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍12👏2🥰1
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን የሥራ አመራር ልዑክ ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መሀመድ አሚን የሱፍ ጋር በመሆን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ትግበራን ጎብኝተዋል።

ኩባንያችን ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጋር የሚያከናውነው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን፤ ቀሪ ስራዎችም በአፋጣኝ ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ፕሮጀክቱ ኮምቦልቻን ለኢንዱስትሪና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ይበልጥ ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ ሲሆን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ እንደሚያደርጋት አጽንዖት ተሰጥቷል።

በተጨማሪም የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቱ የመስተዳድሩን አገልግሎቶች፣ የግብር አሰባሰብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቴሌብር በማቀላጠፍ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ ከመቆጠብ ባሻገር የአሰራር ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ይጨምራል።

በመጨረሻም ልዑኩ በከተማዋ ከሚገኙ ውብ እና አርአያነት ያላቸው የአረንጓዴ ልማት ፓርኮች መካከል አንዱን ጎብኝቷል።

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ!

#RealizingDigitalEthiopia #SmartCity #Kombolcha #DigitalEthiopia
👍10👏4🥰2