Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሰራዊት ልጆች 50 ሺህ ደብተሮችን፣ 5 ሺህ እስክርቢቶና 5 ሺህ እርሳሶችን አበርክቷል፡፡
የተደረገውን ድጋፍ የስፖርት ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ለመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ልዊጂ አስረክበዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በቀጣይ ሳምንትም ወደ ማይካድራ በመጓዝ ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የሀገር ፍቅር - በሰባ ዓመቱ አርሶ አደር!!
እስከ አራት መቶ ኪሎሜትር ተጉዘው ለሰራዊቱ ድጋፍ አድርገዋል::
*******************
(ኢ.ፕድ)
አቶ ሙጬ ዓለም የባህዳር ከተማ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡ የሰባ ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ሲሆኑ መተዳዳሪያቸው ግብርና ሆኖ መጠነኛ ገቢ ያላቸው ናቸው፡፡
የሀገር ክብር መደፈርና ሰላም መጥፋት እንደ በርበሬ ከሚለበልባቸውና ከሚያንገበግባቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
መንግስት በወሰደው ህግን የማስከበር ርምጃ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ይገልጻሉ፡፡
ደስታቸውን ለመግለጽ ከሚኖሩበት ባህርዳር ዙሪያ በ25 ሺ ብር አንድ የእርድ ሰንጋ በመግዛት እስከ አራት መቶ ኪሎሜትር ተጉዘው ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት ለማስረከብ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ሙጬ ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ባሉበትም ሆነው መግለጽ ይችሉ ነበር፤ ግንባር ድረስ መገኘታቸው ግን የተለየ ደስታ ይፈጥርላቸዋል፡፡
በቦታው ተገኝተው ድጋፍ ማድረግ የፈለጉት ከወር በፊት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙጬ ሀሳባቸው ስለተሳካላቸው እጅግ ደስተኛ ሆነዋል፡፡
አቅም ኖሯቸው ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ህግ በማስከበር ስራው ላይ ተሰማርተው ቢሆኑ ኖሮ ደግሞ እጅግ ደስተኛ እንደሚሆኑ አርሶ አደሩ የእድሜ ባለጸጋ ይገልጻሉ፡፡
ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ የጠቀሱት አርሶ አደሩ፤ ሰላም በማስከበር ረገድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
"እኛ በሰላም የምንኖረው ልጆቻችን በሚከፍሉት መስዋዕትነት በመሆኑ በሕይወት እስካለን ድረስ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል" ብለዋል፡፡
በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ፈይሳ ተካ ይባላል፡፡ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡
ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት ለኦነግ ሸኔ ሰራዊትነት ተመልምሎ ጊንጪ አካባቢ ጭልሞ በምትባል ቦታ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ26 ባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡
ከስልጠና በኋላም ሁሉም ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱና ስልክ ሲደወልላቸው የሚፈለጉበት ቦታ ድረስ እንዲመጡ ትእዛዝ ተሰጣቸው፡፡ እንደተባለውም የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ማንነቱን በማያውቀው ሰው አማካኝነት ስልክ ተደወለለት፡፡
በተባለው ቦታ ተሰባሰቡና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ አደረጉ፤ በእግርም በተሸካርካሪም ከተጓዙ በኋላ ጨርጨር አካባቢ ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቀሉ፡፡
ፈይሳ ተካ ስም ተቀየረለትና የትግል ስሙ ብሩክ ተካ ሆነ ፡፡ ምግብና ትጥቅ ተሟላላቸው፤ በወር ከስድስት ሺህ እስከ ሰባት ሺ ብር እንደሚከፈላቸውም ተነገሯቸው ወደጥቃት እንዲገባ ስምሪት ተሰጠው፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርና እርሱ ግን አለመሳተፉን ፈይሳ ይናራል፡፡ አመራሮች የትግሉ ዓላማ ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት እንደሆነ ይነግሯቸው እንደነበረር ይገልጻል፡፡
ቃል የተገባላቸውን የወር ደመወዝ ሲጠይቁ ግን መንግስት የኢኮኖሚ ምንጮችን ስለዘጋብን መክፍል አንችልም የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ፈይሳ ይናራል፡፡ መከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር ርምጃ ሲጀምር ፈይሳ እጁን በሰላማዊ መንገድ ሰጥቷል፡፡ በማያውቀው ነገር በሰዎች ተታሎ በጥፋት ዓላማ ውስጥ መሳተፉ እንደጸጸተው ፈይሳ ገልጾልናል፡፡
እንደ ፈይሳ ሁሉ በርካታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከጁንታው ጋር አብረው ተሠልፈው የነበረ ሲሆን፤ እጃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውን በስፍራው የሚኘገው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ አረጋግጧል።
የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ
******************************
(ኢ.ፕ.ድ)
የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ ማሳወቅ አልያም በመከላከያ ሠራዊት የስልክ ቁጥር በ011 1 248573 መጠቆም እንደሚቻልም ተገልጿል።
የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ሠራተኞች "ደማችን ለድል አድራጊው ለመከላከያ ሰራዊታችን" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ አካሄዱ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በልገሳ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ድጋፉ የኤጀንሲው ሰራተኞች የሀገር ሉአላዊነትን በማስከበር የህዝብን ሰላም ለመጠበቅ መሥዋእትነት እየከፈለ ካለው መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን የሚያሳይ ሲሆን ኤጀንሲው ባሉት ሀያ አምስት ቅርንጫፎች የሚከናወን ይሆናል።

የኤጀንሲው ሠራተኞች ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር በማስታወስም ለቀጣይም የጁንታው ቡድን ተደምስሶ እስከሚያልቅ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው መብራት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው መብራት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የውቅሮና አዲግራት ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና በመጠናቀቁ የፍተሻ ስራ ተከናውኖ ከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል።
በህወሃት ጁንታው የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም በቅንጅት እየሰራ መሆኑንን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
“የትግራይ ወጣት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደ ኃላፊነት ሊመጣ፣ ሃገሩንና ህዝቡንም ሊያገለግል ይገባል”
- አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል
የትግራይ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ወጣት የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደኃላፊነት በመምጣት ሃገሩንና ህዝቡን እንዲያገለግል የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ።
የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት የትግራይ ህዝብም ሆነ ወጣት ውድቀት ሳይሆን የራሱ የጁንታው ብቻ ነው። በመሆኑም ወጣቱ በተፈጠረው ነገር መቆዘም ሳይሆን በተፈጠረው ትልቅ ዕድል በመጠቀም ወደ ኃላፊነት መምጣት፣ አገሩንና ህዝቡንም ለማገልገል መዘጋጀት ይጠበቅበታል።
እንደ አቶ ነብዩ ገለጻ፤ አንዳንድ ወጣቶች የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት እነርሱንም አብሮ የሚጥላቸው ስለሚመስላቸው በቁዘማ ውስጥ ገብተው ይታያሉ። ሊያውቁት የሚገባው እውነት ግን የህወሓት ጁንታ ከወጣቱ፣ ከህዝቡ፣ ከመንግሥትና ከተለያዩ አካላት ብዙ ምክርና ዕድል ተሰጥቶት አልጠቀምም ብሎ በራሱ እብደትና ቅሌት ለዚህ ማብቃቱ ሲሆን፤ የጁንታው ውድቀትም ከትግራይ ወጣቶችም ሆነ ከማንኛውም ትግራዋይ ጋር የማይገናኝ መሆኑ ነው። ይልቁንም የሆነ ቡድን በራሱ መንገድ ብቻ እያየ ሲሄድ የጠፋ አድርጎ መውሰዱ ይገባል።
ለጁንታው ቡድን ምክርና ሃሳብ ካዋጡ አካላት አንዱ የትግራይ ወጣት መሆኑን የገለጹት አቶ ነብዩ፤ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው” እንደሚባለው ሁሉ አሁን ላይ ጁንታው በራሱ መንገድ ተጉዞ የጠፋ እንደመሆኑ ወጣቱ ለዚህ ቡድን ምንም ማድረግ አይችልም። ስለዚህ ወጣቱ የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምቶ መቀጠል እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37582
“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” - ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
*******************************
(ኢ ፕ ድ)
ከህወሓት ጁንታ ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚጥሩ የምዕራባውያን ጁንታዎችን ሴራ ለማጋለጥ በኢትዮጵያዊነት ስሜት በመቆም መታገል እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ።
አቶ ኦባንግ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የእኔ ብሔር ብቻ ማለት ባለፉት 27 ዓመታት የወረስነውና ያሳደግነው አስተሳሰብ ነው። ይህ ደግሞ ለነጭ ጁንታዎች ተጠቃሚነት ሰፊ ዕድል የሰጠና ኢትዮጵያን የችግር ቋት ውስጥ የከተተ ነው። በመሆኑም ከብሔር አስተሳሰብ ወጥቶ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቆሞ የነጭ ጁንታዎችን እጅ ማሳጠር ያስፈልጋል።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ከሚያስተላልፉት መልዕክት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማቆርቆዝ ያለመ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ኦባንግ፤ የነዚህን ኃይሎች ድርጊት ለማስቆም በቅንጅት መሥራት ካልተቻለ አደጋው የከፋ ይሆናል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37602
የአምስት አመቱ የጁንታው ታጋች ህጻን
👉ከጁንታው ታጋቾች ውስጥ መንታ ልጆችን የተገላገለች እናት ለማመን የሚከብድ ስቃይ አሳልፋለች፤
👉በቀን የሚሰጠው አንዲት ዳቦ እና ጥቂት ውሃ ብቻ ነበር፤
**************************
( ኢ ፕ ድ)
ቢንያም ጌታቸው ገና አፉን በቅጡ ያልፈታ ህጻን ነው። አባቱ ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው ቦሮዳ የሰሜን እዝ ሰራዊት አባል ነው፡፡ መቶ አለቃ ጌታቸው ልጁን መስከረም 17 ቀን ወደሚኖርበት የመከላከያ ካምፕ አመጣው። የአባት ሃሳብ የነበረው የልጁን አይን አሳክሞ እረፍት እንዲያገኝ ነበር። ይህ የአባት ሃሳብ ግን ሳይሆን ቀረ፤ ያልታሰበው የጁንታው ጥቃት በሰራዊቱ ላይ ተፈጸመ።
የጁንታው ታጣቂዎች ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈጽመው በርካቶችን ሲያፍኑ ህጻን ቢንያምም ከአባቱ ጋር ታገተ፡፡ በእገታው ወቅት ጁንታው የሚያቀርበው ምግብ ለህጻን ቢኒያም ተጨማሪ ፈተና ነበር፡፡ በቀን የሚሰጣቸው አንድ ዳቦ እና ጥቂት ውሃ ህጻኑን በምግብ እጥረት ሠውነቱ እንዲጎዳ አድርጎታል፡፡
የታገቱ የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች እና አዛዦች ከቢኒያም አባት ጋር እየተጋገዙ በእግራቸው ቢኒያምን በትከሻ ተሸክመው በረሃውን ያለ በቂ ምግብና ውሃ ለቀናት እንዲጓዙ ተፈርዶባቸዋል። የጁንታው አባላት በወቅቱ በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ሆነው አቧራውን ታጋቾች ላይ እያቦነኑ ሲጓዙ ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው ቦሮዳ ልጁን አስቀምጦት ከታጋቾቹ ጋር አብሮ እንዲሄድ ይጠይቁታል።
የተሽከርካሪ ጋቢና ውስጥ አድርገው እዚሁ ይደር አሉት። ይህንን ሃሳብ ያልተቀበለው አባትም የበኩር ልጁን አንጠልጥሎ የድካም ጉዞውን ገፋበት። ህጻን ቢንያም ገና በለጋ እድሜው ከጦርነት አውድማ መሃል ገብቶ የተኩስ ድምጹንም ሆነ የፈንጂ አይነቶችንም ፊት ለፊት መጋፈጡ አይቀሬ ሆነ። የጁንታው ታጣቂዎች ሲታኮሡ የአየር ሃይል ድሮኖች እና ሄሊኮፐተሮች በሰማይ ሆነው እርምጃ ሲወስዱም ተመልክቷል።
ህጻን ቢንያም በዚህ እድሜው አሻንጉሊት ይዞ መጫወት እና ከእድሜ እኩዮቹ ጋር መቦረቅ ቢሆንም ፍላጎቱ በጁንታው እኩይ አላማ ግን ከአባቱ ጋር ታግቶ መራር ቀናትን ለማሳለፍ ተገዷል። ምን እየተፈጠረ እንዳለ እንኳን በውል የማያውቀው ህጻን በአቧራው እና በፀሐዩ የቀሉ አይኖቹን እያሸ ከታገቱ የመከላከያ መኮንኖች ጋር ችግሩ ተጋፍጧል፡፡
በወዲያኛው ማዶ ደግሞ ሌላም ግፍ አለ። አንዲት እናት መንታ ልጆችን ተገላግላ ልጆቿን ይዛ ለማመን የሚከብድ ስቃይ ስታሳልፍ ነበር። ለሀጻናቱ እንኳን ያልራሩት የጁንታው አባላት ወላጆቹን እንኳን ከእገታው ነጥለው ወደሰላማዊ ቦታ ለመላክ ቅንጣት ታክል ርህራሄንእንዳላሣዩ መቶ አለቃ ጌታቸው ይናገራል፡፡
በጁንታው የታገቱ የሰራዊት መኮንኖች ህጻን ቢንያምን እና አባቱን እያበረታቱ ዳገት ቁልቁለቱን፣ ወንዝ ጢሻውን እያቋረጡ አዴት ከተባለ ስፍራ ደረሱ። በወቅቱ የነበረው ሁኔታ መቶ አለቃ ጌታቸው እንዲህ ያስታውሳል፤ “ ህጻኑ ሄሊኮፕተሯን ግዳጅ ስትፈጽም አይቶ ‘አባዬ ምንድነው? አለኝ፡፡ ዶክተር ዐብይ ልኮልን ነው፣ ከዚህ ልትወስደን ነው አልኩት፡፡ ኦፕሬሽኑ ሲጀመር ልጄን ይዤ ከለላ ያዝኩ” ይላል፡፡
በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት እና የአየር ሃይል በተቀናጀ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ የጁንታው አባላት ላይ በወሰዱት እርምጃ የጁንታው ታጣቂዎች በየቦታው ተበታተኑ። አዴት ላይ ለቀናት የታገቱት ህጻን ቢንያም እና አባቱን ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ መኮንኖች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ነጻ ወጡ።
"በአፈናው ወቅት ሰራዊቱ ለህጻን ልጄ ያደረገው ድጋፍ እና እንክብካቤ ትልቅ ነው" የሚለው ምክትል መቶ አለቃ ጌተቸው፤ "የሀገር አደራ አለብኝና ልጄን አስተምሬ ለቁም ነገር ለማብቃት የማላደርገው ጥረት የለም" ሲል ተናግሯል።
ሁኔታውን አልፎ ሲያወሩት ቀልድ ይመስላል የሚለው ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው፤ ሰራዊቱ ለወሰደው ወገን የማዳን የጥንቃቄ እርምጃ ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል። ህጻን ቢንያምም "ዶክተር ዐብይን ነው የምወደው፤ የእኛ መከላከያ ነው ያዳነን" ሲል በስፍራው ለሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በሚኮላተፍ አንደበቱ ነግሮታል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የህግ ማስከበር ዘመቻውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ወንጀለኛው ጁንታ ከታጋች የሰራዊቱ መኮንኖች ባሻገር ሴቶችና ህጻናትን አግቶ መያዙን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ታጋቾቹን ከጁንታው በመነጠል ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ ኦፕሬሽኑን ለማካሄድ መንግስታቸው በትኩረት እየሰራ መሆኑን መግላጻቸው ይታወሳል፡፡
በመቐለ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ ሊያውለው በድብቅ ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ።
በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱ ታውቋል።
በመከላከያ ሰራዊት የ25ኛ ፈንቅል ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ ምክትል ኦፕሬሽናል አዛዥ ሻምበል ዮሐንስ ማቲዎስ እንዳስታወቁት፣ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ አስቦ በድብቅ ቀብሮት የነበረው 13 የነዳጅ ታንከር በመከላከያ ሰራዊቱ አሰሳ በቁጥጥር ውሏል፡፡
ጁንታው የትግራይ ህዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲቸገር በማድረግ ዘርፎ ለራሱ እኩይ አላማ ቀብሮት ቆይቷል ብለዋል።
ሆኖም ጥቅመኛው ሃይል የደበቀው ታንከር እንዲገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል ብለዋል።
በአከባቢው ተቀብሮ ለነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊውል የነበረ ተጨማሪ ዘጠኝ ታንከር መገኘቱንም ሻምበል ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡
የህወሃት ጁንታ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች እየተገኙ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በመቐለ በተደረገው አሰሳ ለህገ ወጥ ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች መያዛቸውን እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ በአዲስ አበባ ተጀመረ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስጀምረዋል።
በመርሐግብሩ ማስጀመሪያ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ውብ፣ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ መሆን ይኖርበታል ብለዋል ።
በቀጣይ አራት ወራት በሚቆየው የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ የበጎፍቃድ አገልግሎት ከ28ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች በሣምንት ሁለት ቀናት እንደሚሳተፉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።
አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ መዲናነቷን ፣የቱሪዝም እና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ነዋሪዎች ጽዳቷን በመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስተባባሪነት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ እንክብካቤ በአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሚከናወን መሆኑን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ገልጿል፡፡
“አሁን ያለችው ትግራይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ናት ”
-አቶ ሊላይ ኃይለማርያም፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር
************************
(ኢ ፕ ድ)
አሁን ላይ ያለችው ትግራይ የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ እምብዛም የማይታይባት 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት መሆኗን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ተናገሩ።
የህወሓት ጁንታ ከአሁን በኋላ እንደማይመለስና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ገሀነም መውረዱን በመገንዘብም ደጋፊዎችና አባሎቻቸው ወደ ህዝባቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሰርቱና በጋራ አገር ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ሊላይ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ አሁን ትግራይ በአጠቃላይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ሆናለች። የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ የሚታይበት ሁኔታ ብዙም የለም። አውሮፕላንን ጨምሮ ትራንስፖርት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይንቀሳቀሳል።
መብራት እስከ አዲግራት እየሠራ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ዓደዋና አክሱም ይገባል። አብዛኛው ከተሞችም መብራት ያገኛሉ። የውሃና የኔትዎርክ አገልግሎትም እየተዳረሱ ነው። በሚቀጥለው ሳምንትም የባንክ አገልግሎት በሰፊው ይጀመራል።
መቀሌም በጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው። ወደ ቀደመ መልኳ ተቀይራለች።
የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንጻር መቶ በመቶ እንዲከፈቱ ተደርገዋል። በሰለማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታው ገብቷል።
ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሥራ ያልገቡ ሠራተኞች ላይ በአገሪቷ ህግ መሠረት ዕርምጃ ይወሰዳል። ይሄ ደግሞ የተሾሙት ካቢኔዎች ኃላፊነት ነው። ትጥቅን የማስፈታት እንቅስቃሴውም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። ታጥቆ የነበረው ትጥቅ በየቦታው እየተፈታ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=37618
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቀቀ
*****^^***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቋል፡፡
ኮሚቴዉ በሰላም፣ በልማት፣ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መጪዉን አገራዊ ምርጫ በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
በዋናነት ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በአገራችን የታየዉ ለዉጥ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የአገራችንን ብልጽግና እዉን ለማደረግ ሰፊ እድል የፈጠረና አገራችንን ከብተና አደጋ ያዳነ መሆኑ በዉይይቱ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
በተለይም ብልጽግና ዉሁድ ህብረ ብሄራዊ አገራዊ ፓርቲ ሆኖ መደራጀቱ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ እድል ከመፍጠሩም በላይ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተገለዉ የዳር ተመልካች የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቀፍና ለማሳተፍ የቻለ የመጪዉ ትዉልድ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
በአገራዊ ለዉጡ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የፓርቲዉን መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግና ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
ኮሚቴዉ በሁለቱ ቀናት መደበኛ ስብሰባዉ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡
1. አገራችንን ለመበታተን በከፍተኛ ሁኔታ ሲዘጋጅ ቆይቶ ፍጹም አረመኔያዊ በሆነ መልኩ በአገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል፡፡ ይህ ስግብግብ ጁንታ በአጭር ጊዜ እንዲፈርስና አገራችን ከዚህ ከሃዲ ሃይል ነጻ እንድትወጣ ጀግናዉ መከላከያ ሰራዊታችን፣ የአማራና አፋር ክልሎች ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ ድጋፍ ላደረጉ መላዉ የሀገራችን ህዝቦች ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ ጀግንነት ልምዳችን ስለሆነ በዚህ ድል ሳንኩራራ ይህንን አገራዊ የአንድነት ስሜትና ቁርጠኝነት በሌሎች የልማት ዘርፎችም በመድገም የአገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
2. የወንጀለኛዉን ከሃዲ ጁንታ አባላት ከተደበቁበት አድኖ ለፍርድ ለማቅረብ ከሚደረገዉ ርብርብ ጎን ለጎን በህግ ማስከበር እርምጃው ሂደት ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬያቸዉ ተመልሰዉ እንዲቋቋሙና እብሪተኛው ጁንታ ያፈራረሳቸዉ የህዝብ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት ተጠግነዉ ለአገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ የተጀመረዉ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በትግራይ ክልል የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር፣ የእለት ደራሽ ሰብዓዊ አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማድረስና ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ የእለት ተእለት ህይወቱ እንዲመለስ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ የፓርቲዉ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና መላዉ የአገራችን ህዝቦች የቻሉትን አስተዋጽዖ ሁሉ እንዲያደርጉ ኮሚቴዉ ጥሪ ያቀርባል፡፡
3. በኢትዮጵያ የሀገረ መንግስትና ብሄረ መንግስት ግንባታ ሂደት የተለያዩ የፖለቲካ ሃይል አሰላለፎች የሚታዩበት ነዉ፡፡ በአገራችን የሚታየዉን ዉስብስብ ብዝሃነት የሚያስተናግድ አገራዊ አንድነት ከመገንባት አንጻር በወንድማማችነት እሴት ላይ የተመሰረተ ህብረብሄራዊ አንድነትን የሚያረጋግጥ የፌዴራል ስርዓት ግንባታ እዉን እንዲሆን የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት በቁርጠኝነት እንዲታገሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
4. በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቦች የሚያነሷቸዉ የማንነት ጥያቄዎች ተገቢነት ያላቸዉ ፍትሃዊ የህዝብ ጥያቄዎች መሆናቸዉን ኮሚቴዉ ያምናል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ነባራዊ ሁኔታዉን መሰረት በማድረግ የህዝቦችን ወንድማማችነትና አብሮነት እንዲሁም የህዝቡን ነጻ ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ ምላሸ እንዲሰጣቸዉ ኮሚቴዉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
5. በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ተገቢዉ እርምጃ ሁሉ እንዲወሰድ ኮሚቴዉ ከስምምነት ደርሷል፡፡ እነዚህን እኩይ ተግባራት የሚፈጽሙ የጥፋት ሀይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋልና እርምጃ ለመዉሰድ በሚደረገዉ ርብርብ በየደረጃዉ የሚገኙ የብልጽግና አመራሮች በከፍተኛ ጽናትና ቁርጠኝነት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
6. የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች በየትኛዉም ቦታ የሚገኙ የብልጽግና አመራሮችና አባላት ከሚለያዩ ጥቃቅን ጉዳዮች ወጥተዉ ከፍ ያለ አገራዊ እይታ በመያዝ ኢትዮጵያንና የሁሉንም ዜጎቿን ሁለንተናዊ ብልጽግና እዉን በሚያደርግ መልኩ እንዲደጋገፉ፣እንዲረዳዱ፣በአብሮነትና በትብብር መንፈስ መስራት እንደሚገባቸዉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
7. በ2013 ዓ.ም የሚካሄደዉ ምርጫ አገራችን ወደ እዉነተኛ የዲሞክራሲ ስርዓት ለምታደርገዉ ሽግግር ያለዉ ትርጉም እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል፡፡ የሚካሄደዉ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና በሂደቱም ሆነ በዉጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የብልጽግና አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
8. ብልጽግና ፓርቲ በመጪዉ ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆኖ በዉጤታማነት እንዲያጠናቅቅ በፓርቲዉ ማኒፌስቶ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አጽድቆታል፡፡ መላዉ የፓርቲዉ አመራሮችና አባላት የጸደቀዉን ማኒፌስቶ መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
9. በአገራችን በህጋዊ መንገድ ተመዝግበዉ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ እዉነተኛ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመሸጋገር የተወሰዱ የአገራዊ ለዉጥ እርምጃዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መጪዉ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና በሂደቱም ሆነ በዉጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸዉን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
10. መላዉ የአገሪቱ ህዝቦች ባለፉት ሁለት ተኩል አመታት በኢትዮጵያ የታዩ ለዉጦችና የተገኙ ድሎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ፣መጪዉ አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻና ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የዜጎች ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና የተረጋገጠባት ጠንካራ አገር ለመገንባት በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ የሚጠበቅባቸዉን አስተዋጽዖ ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ብልጽግና ፓርቲ
ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም
የህወሓት አመራሮች በስብሰባዎች ላይ ባለስልጣናትን ያሰልሉ ነበር- አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ
--------------------------------------------------
(ኢ ፕ ድ)
የህወሓት አመራሮች በስብሰባዎች ጭምር ሰላይ በማስቀመጥ ባለስልጣናትን ያሰልሉ እንደነበር አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ተናገሩ፡፡
የህወሓት አመራሮች በማዕከላዊ ስበሰባዎች ጭምር ሰላይ ያስቀምጡ ነበር ያሉት አምባሳደር ኩማ፣ ጉንጭ አልፋና ተጠያቂነት የሌላቸው ስብሰባዎች ይበዙ እንደነበር እና ኦህዴድ በተገመገሙ አመራሮች እርምጃ ሲወስድ ጣልቃ በመግባት ይረብሹ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
የህወሓት ዘራፊ ቡድን የቁልቁለት ጉዞን የጀመረው በ1993 ዓ.ም መሆኑንም አምባሳደር ኩማ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውሰዋል፡፡
በ1983 ዓ.ም ወደ ስልጣን የመጣው ኢህአዴግ በህወሓት መሪነት ሶስት መሰረታዊ አላማዎችን አንግቦ መንገዱን ጀመሯል የሚሉት አምባሳደሩ፣ በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ዴሞክራሲና ልማት ማረጋገጥ የቤት ስራው መሆኑን አስቀምጦ ሀገር መምራት ቢጀምርም ግልጽ የሆነ የርዕዮትዓለም ሳይኖረው ለአስር ዓመታት በጭፍን ሲጓዝ ነበር ብለዋል፡፡
ከ10 አመታት በኋላ በ1993 ዓ.ም ሰነዶች ተዘጋጅተው ለውይይት እንደቀረቡ ገልጸው፣ የውይይት ሃሳቡና ኢህአዴግ የሚመራበት ሰነድ በህወሓት ቡድኖች መሃል የልዩነት መስመር ማበጀቱን ጠቁመዋል፡፡
ዴሞክራሲን በሰነድ ከማስፈር ውጪ በተግባር የማያውቀው ህወሓት በሀገሪቱ ዴሞክራሲ እንዳይኖር አድርጓል ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ ውድቀቱን አፋጥኖታል፤ ሌሎችም ፓርቲዎችም ከህወሓት ውደቀት ሊማሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ሦስት ሳተላይቶችን ታመጥቃለች
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ለተለያየ አገልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ እንደገለፁት፤ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን ለማምጠቅ ታቅዷል። በአሥር ዓመቱ ከሚመጥቁት ሳተላይቶች ውስጥ አንደኛው የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሲሆን፤ የተቀሩት ሁለቱ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ናቸው።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሳተላይት የሚባለው በብሮድካስት ሚዲያዎች ለኢንተርኔት፣ ለስክልና ለኮሚዩንኬሽን አገልግሎት የሚውል ነው። በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን እነዚህን አገልግሎቶች ከውጭ በመከራየት በሚሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታወጣለች።
ለአብነትም፣ ከብሮድካስቲንግ በዓመት እስከ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል። ለቴሌ ኮሚዩንኬሽን ደግሞ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ወጭ ይሆናሉ። ስለዚህ ሳተላይት የመገንባት እቅዱን በተግባር በማረጋገጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪን መቀነስ ተገቢ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=37690
ለ30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሻለላቸው
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንደተሻሻለላቸው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በኤምባሲው ተጠልለው የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት ሌተናል ኮለኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄነራል አዲስ ተድላ ሲሆኑ፤ በሁለቱም ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንደተሻሻለላቸው ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡
ማሻሻያውንም ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በፊርማቸው ማጽደቃቸው ተገልጿል፡፡
ኦነግ ሸኔን በመደምሰሱ ሂደት የህዝቡ ድጋፍ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በሰላም ለመታገል ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ወደ ትጥቅ ትግል የተመለሰው ኦነግ ሸኔን በመደምሰስ ሂደት ህዝቡ ከጸጥታ አካሉ ጎን ሆኖ በአሰሳ እያገዘ፤ በሰላማዊ ሰልፍም ቡድኑን እያወገዘ መሆኑ ተገለጸ።
ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 846 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ፤ ከ3ሺህ 700 በላይ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ተናግረዋል።
ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኦነግ ሸኔ ቡድን ኃይሉን ለማጠናከር በክልሉ ጠረፋማ አካባቢዎች ተደብቆ የጥፋት ኃይሎችን በመመልመል ሲያሰለጥን፤ እንዲሁም በህወሓት ጁንታ ኃይል የሎጀስቲክ ድጋፍ ተደርጎላቸው በትግራይ ክልል ጭምር በመሄድ ስልጠና ሲወስድ ነበር።
አሁን ላይ ግን ጁንታው በመደምሰሱ የቡድኑ ኃይል እየተዳከመ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ ባለፉት ሦስት ወራት የክልሉ መንግሥት ህዝቡን በጎኑ በማሰለፍ በወሰደው እርምጃ 413 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እጅ ባለመስጠታቸው ሲገደሉ፤ እጅ የሰጡና የተያዙ ደግሞ 433 ናቸው። በዚህም በጥቅሉ 846 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል።
የኦነግ ሸኔ ቡድን እጅግ ጨካኝ ከመሆኑ የተነሳ ስልቱን በመቀያየር አንዳንድ አካባቢዎች እንደ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በብሔር ላይ ያነጣጠሩ ጥቃት ይፈጽማል፤ በምስራቅ ኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ሀይማኖታዊ መልክ ያለው ጥቃት በመፈጸም አገርን ለማተራመስ ይጥራል። በዚህ መልኩ እስካሁን መንግሥት ሹመኞችና በንጹኃን ዜጎች ላይ በወሰዳቸው እርምጃዎችም ከ500 በላይ ንጹኃን ህይወታቸውን አጥተዋል።
አሁን ግን አንዳንድ እንደ ቄለም ወለጋ ያሉ አካባቢዎች ህዝቡ ወጥቶ አሰሳ እያደረገ፣ በሠላማዊ ሰልፍም እያወገዘ በመሆኑ እንደ ከዚህ በፊቱ ጉልበቱን አጠናክሮ የጥፋት ስራውን መፈጸም አይችልም። እንደከዚህ በፊቱም መንገድ ዝጉ እንዲ አድርጉ የሚሉ ትዕዛዞችን ህዝቡ እየተቀበለ አይደለም። የክልሉ ጸጥታ አካላትም ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት አካባቢን ተቆጣጥረው እንዳሉ፤ እና ህዝቡም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ነው ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ የተናገሩት።
https://www.press.et/Ama/?p=37765
የእናቶች ሰላም!!
የሕግ ማስከበር ዘመቻው ውጤት በእናቶች ምስጋናና ሰላም እንዲህ ተገልጧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የፈጸመው የህግ ማስከበር ሥራ የአገሪቱን አንድነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ የወሰደው እርምጃ ነው ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ተናገሩ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ የወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ የአገሪቱን አንድነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ የወሰደው ነው ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ተናገሩ።
ሙሳ ፋኪ ማሐማት ይህንን የተናገሩት ትናንት ጂቡቲ ውስጥ በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) 38ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው።
የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ጨምረውም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ "የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስከበር" መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ሁሉም አገራት የሚጠበቅባቸው ሕጋዊ ኃላፊነት መሆኑንም አመልክተዋል።
ሙሳ ፋኪ እንዳሉት በዚህ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው መፈናቀል መከሰቱን ገልጸው፤ በዚህ ረገድ ኢጋድ ለስደተኞችና ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ ከምታደርገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ኮሚሽነሩ ፋኪ ማሐማት ከዚህ በፊት፣ የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል ወደ ድርድር እንዲመጡና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ለአንድ ቀን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢጋድ አባል አገራት ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር በተጨማሪ ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፋቸውን መግለጻቸው ይታወቃል።