ቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ::
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከስፖርት ማህበረሰብ፣ አርቲስቶችና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን ጃንሜዳን የማጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ ከፒያሳ ወደ ጃንሜዳ የተዘዋወረውን የአትክልት መገበያያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ በማንሳት ለጥምቀት በዓልና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይመለሳል ብለዋል።
የአትክልት መገበያያ ስፍራዎችን በሌሎች አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች ከነገ ጀምሮ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ሙሉ በሙሉ ይሸጋገራሉ ብለዋል፡፡
ነጋዴዎች ወደ ጋርመንት በሚዘዋወሩበት ሁኔታዎች ዙሪያ ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎችን ተዘዋውረው አነጋግረዋል፡፡
በቦታው የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት የከተማ አስተደዳሩ ላደረገው ድጋፍ ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት በተዘጋጀው ቦታ ለመዘዋውር ዝግጁ መሆናቸውን የኢስ አበበ ከተማ ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ ነው
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ዳቪድ ስቴንማን ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ሃላፊነት በነበሩበት ወቅት ኢትዮጵያዊያን ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል በሚል የክስ አቤቱታ ማስገባቱን የዘ ታይምስ ዘገባ ያሳያል።
ዶክተር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ አባል የሆኑበት ፓርቲ ለፈጸማቸው የሰዎች መግደል፣ መታሰርና መገረፍ የእርሳቸው ውሳኔ ትልቅ ድርሻ ስለነበረው በዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ ይገባል ብሏል ዳቪድ ስቴንማን ለፍርድቤቱ ባቀረበው አቤቱታ።
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም አባል የሆኑበትና በኢህአዴግ ውስጥ አባል ድርጅት የነበረው ህወሓት በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ በነበረው የበላይነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች የእርሳቸው ውሳኔ ትልቅ ድርሻ ነበረው ብሏል ዳቪድ ስቴንማን።
ዳቪድ ስቴንማን በዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ላይ የዚህ አይነት ክስ በማቅረቡ ከእርሳቸው በተቃራኒ ላሉ ወገኖች ወግኖ ነው የሚሉ ድምጾች እንደሚሰሙ ጠቅሶ፤ “የእኔ ውግንና ለአንድ ነገር ብቻ ነው፤ እሱም ሰላም ነው” ብሏል።

የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሜ/ጄኔራል ከድር አራርሶ ፍርድ ቤት ቀረቡ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ።
ተከሳሹ የሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ከተባሉ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች ህገ-መንግስቱን እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል የመናድ ሙከራ በማድረግ እና የሀገር ክህደት ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠርጥረው የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ተጠርጣሪው መንግስት በትግራይ ክልል የነበረ የጦር መሳሪያ ወደ መሃል ሃገር እንዲመጣ ሲፈለግ መሳሪያው ከመቐለ እንዳይወጣ የተቃወሙና ሰዎችን ያደራጁ መሆኑን እና ከቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከነበሩት አቶ አብዲ ኢሌ ጋር በመሆን የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችን እንዳስጨፈጨፉ ማስረጃ እንደለው ፖሊስ አስታውቋል።
መርማሪ ፖሊስ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ባንኮች የገንዘብ ልውጦችን ለማጣራት፣ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ከያሉበት ለመያዝና ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ያላቸውን የወንጀል ግንኙነት በማስረጃ ለመለየት ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ከሰማ በኋላ የተጠርጣሪውን ምላሽ ያዳመጠ ሲሆን፣ ተጠርጣሪው ወንጀሉ ከተፈጸመበት ወቀት አስቀድሞ በሃምሌ 2012 ዓ/ም ጀምሮ ለህክምና ውጭ ሀገር እንደነበሩና የቀረበላቸውን ክስ የማይቀበሉት እንደሆነና የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና መብት ውድቅ አድርጎ ተጠርጣሪው ከተጠረጠሩበት ወንጀል አንጻር መረጃ ሊያጠፋ ይችላል ብሎ ስላመነ መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ስምንቱን ቀን በመፍቀድ ለታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ/ም መርማሪ ፖሊስ መረጃውን አጠናክሮ እንዲመጣ ችሎቱ ማዘዙን ከፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኳታራዊው ባለሃብት ለህዳሴ ግድብ የ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ገዙ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ኳታራዊው ባለሃብት አብደላህ ሳሌም አል ሱሌይቲን ኢትዮጵያ በሚገኘው ድርጅታቸው አማካኝነት የአንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዙ፡፡
ባለሃብቱ ቀሪው የህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያና ለታችኞቹ ተፋሰስ አገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በበኩላቸው አብደላህ ሳሌም አል ሱሌይቲን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፣ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖም በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የባለሃብቱ ተወካይም የቦንድ ሰርትፊኬቱን ከአምባሳደር ሳሚያ ተቀብለዋል።
ባለሃብቱ ከዚህ ቀደም በ2007 ዓ.ም ተመሳሳይ መጠን ያለው የህዳሴ ግድብ ቦንድ መግዛታቸውን በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጁንታው የህግ ታራሚዎችን በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስተወቁ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።
የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በመንግሥት የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዕርምጃ ተከትሎ የጁንታው አባላት በክልሉ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተይዘው የእስር ጊዜያቸውን እየፈጸሙ የነበሩ ታራሚዎችን መቀሌ ከተማ ለቀዋቸዋል። በዚህም በከተማዋ ውስጥ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈጽሙና ህዝቡ በስጋት ውስጥ እንዲወድቅ አድርገዋል።
“በበርካታ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓል” ያሉት ከንቲባው፤ ይሄን ያደረጉትም አንድም ተቋማትን በመዝረፍ ሰነዶችን ለማጥፋት፣ ሁለተኛም ሕዝቡ ወደ ስጋት እንዲገባና እንዲጠራጠር በማድረግ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በአዲሱ አስተዳደር ላይ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37507

“ከለውጡ በፊት ጀምሮ በነበረኝ የሃሳብ ልዩነት በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስብኝ ነበር”
-የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የህወሓት ጁንታ በአገሪቱ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረውን ጭቆና እና ግፍ በመቃወማቸውና የሃሳብ ልዩነት በማንጸባረቃቸው በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲደርስባቸው እንደነበር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ ገለጹ።
ተወካዩዋ የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱን ከተቀላቀሉበት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገሪቱም ሆነ በመላዉ የትግራይ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረው ጭቆና እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲቃወሙና ሲታገሉ ቆይተዋል።
በተለይም በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ሚዛኑን ያልጠበቀና እውነትን መሰረት ያላደረጉ ውሳኔዎች ላይ የሚያምኑበትን ሃሳብ በግልጽ በመናገራቸው ምክንያት በድርጅቱ አመራሮች የተመደቡ ግለሰቦች በስልክና በማሕበራዊ ሚዲያ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱባቸው እንደነበር ወይዘሮ ያየሽ ተናግረዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37517

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሰራዊት ልጆች 50 ሺህ ደብተሮችን፣ 5 ሺህ እስክርቢቶና 5 ሺህ እርሳሶችን አበርክቷል፡፡
የተደረገውን ድጋፍ የስፖርት ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ለመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ልዊጂ አስረክበዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በቀጣይ ሳምንትም ወደ ማይካድራ በመጓዝ ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሀገር ፍቅር - በሰባ ዓመቱ አርሶ አደር!!
እስከ አራት መቶ ኪሎሜትር ተጉዘው ለሰራዊቱ ድጋፍ አድርገዋል::
*******************
(ኢ.ፕድ)
አቶ ሙጬ ዓለም የባህዳር ከተማ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡ የሰባ ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ሲሆኑ መተዳዳሪያቸው ግብርና ሆኖ መጠነኛ ገቢ ያላቸው ናቸው፡፡
የሀገር ክብር መደፈርና ሰላም መጥፋት እንደ በርበሬ ከሚለበልባቸውና ከሚያንገበግባቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
መንግስት በወሰደው ህግን የማስከበር ርምጃ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ይገልጻሉ፡፡
ደስታቸውን ለመግለጽ ከሚኖሩበት ባህርዳር ዙሪያ በ25 ሺ ብር አንድ የእርድ ሰንጋ በመግዛት እስከ አራት መቶ ኪሎሜትር ተጉዘው ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት ለማስረከብ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ሙጬ ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ባሉበትም ሆነው መግለጽ ይችሉ ነበር፤ ግንባር ድረስ መገኘታቸው ግን የተለየ ደስታ ይፈጥርላቸዋል፡፡
በቦታው ተገኝተው ድጋፍ ማድረግ የፈለጉት ከወር በፊት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙጬ ሀሳባቸው ስለተሳካላቸው እጅግ ደስተኛ ሆነዋል፡፡
አቅም ኖሯቸው ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ህግ በማስከበር ስራው ላይ ተሰማርተው ቢሆኑ ኖሮ ደግሞ እጅግ ደስተኛ እንደሚሆኑ አርሶ አደሩ የእድሜ ባለጸጋ ይገልጻሉ፡፡
ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ የጠቀሱት አርሶ አደሩ፤ ሰላም በማስከበር ረገድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
"እኛ በሰላም የምንኖረው ልጆቻችን በሚከፍሉት መስዋዕትነት በመሆኑ በሕይወት እስካለን ድረስ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል" ብለዋል፡፡

በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ፈይሳ ተካ ይባላል፡፡ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡
ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት ለኦነግ ሸኔ ሰራዊትነት ተመልምሎ ጊንጪ አካባቢ ጭልሞ በምትባል ቦታ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ26 ባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡
ከስልጠና በኋላም ሁሉም ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱና ስልክ ሲደወልላቸው የሚፈለጉበት ቦታ ድረስ እንዲመጡ ትእዛዝ ተሰጣቸው፡፡ እንደተባለውም የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ማንነቱን በማያውቀው ሰው አማካኝነት ስልክ ተደወለለት፡፡
በተባለው ቦታ ተሰባሰቡና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ አደረጉ፤ በእግርም በተሸካርካሪም ከተጓዙ በኋላ ጨርጨር አካባቢ ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቀሉ፡፡
ፈይሳ ተካ ስም ተቀየረለትና የትግል ስሙ ብሩክ ተካ ሆነ ፡፡ ምግብና ትጥቅ ተሟላላቸው፤ በወር ከስድስት ሺህ እስከ ሰባት ሺ ብር እንደሚከፈላቸውም ተነገሯቸው ወደጥቃት እንዲገባ ስምሪት ተሰጠው፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርና እርሱ ግን አለመሳተፉን ፈይሳ ይናራል፡፡ አመራሮች የትግሉ ዓላማ ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት እንደሆነ ይነግሯቸው እንደነበረር ይገልጻል፡፡
ቃል የተገባላቸውን የወር ደመወዝ ሲጠይቁ ግን መንግስት የኢኮኖሚ ምንጮችን ስለዘጋብን መክፍል አንችልም የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ፈይሳ ይናራል፡፡ መከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር ርምጃ ሲጀምር ፈይሳ እጁን በሰላማዊ መንገድ ሰጥቷል፡፡ በማያውቀው ነገር በሰዎች ተታሎ በጥፋት ዓላማ ውስጥ መሳተፉ እንደጸጸተው ፈይሳ ገልጾልናል፡፡
እንደ ፈይሳ ሁሉ በርካታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከጁንታው ጋር አብረው ተሠልፈው የነበረ ሲሆን፤ እጃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውን በስፍራው የሚኘገው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ አረጋግጧል።

የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ
******************************
(ኢ.ፕ.ድ)
የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ ማሳወቅ አልያም በመከላከያ ሠራዊት የስልክ ቁጥር በ011 1 248573 መጠቆም እንደሚቻልም ተገልጿል።

የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ሠራተኞች "ደማችን ለድል አድራጊው ለመከላከያ ሰራዊታችን" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ አካሄዱ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በልገሳ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ድጋፉ የኤጀንሲው ሰራተኞች የሀገር ሉአላዊነትን በማስከበር የህዝብን ሰላም ለመጠበቅ መሥዋእትነት እየከፈለ ካለው መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን የሚያሳይ ሲሆን ኤጀንሲው ባሉት ሀያ አምስት ቅርንጫፎች የሚከናወን ይሆናል።
የኤጀንሲው ሠራተኞች ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር በማስታወስም ለቀጣይም የጁንታው ቡድን ተደምስሶ እስከሚያልቅ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው መብራት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው መብራት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የውቅሮና አዲግራት ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና በመጠናቀቁ የፍተሻ ስራ ተከናውኖ ከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል።
በህወሃት ጁንታው የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም በቅንጅት እየሰራ መሆኑንን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

“የትግራይ ወጣት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደ ኃላፊነት ሊመጣ፣ ሃገሩንና ህዝቡንም ሊያገለግል ይገባል”
- አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል
የትግራይ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ወጣት የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደኃላፊነት በመምጣት ሃገሩንና ህዝቡን እንዲያገለግል የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ።
የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት የትግራይ ህዝብም ሆነ ወጣት ውድቀት ሳይሆን የራሱ የጁንታው ብቻ ነው። በመሆኑም ወጣቱ በተፈጠረው ነገር መቆዘም ሳይሆን በተፈጠረው ትልቅ ዕድል በመጠቀም ወደ ኃላፊነት መምጣት፣ አገሩንና ህዝቡንም ለማገልገል መዘጋጀት ይጠበቅበታል።
እንደ አቶ ነብዩ ገለጻ፤ አንዳንድ ወጣቶች የህወሓት ጁንታ ቡድን ውድቀት እነርሱንም አብሮ የሚጥላቸው ስለሚመስላቸው በቁዘማ ውስጥ ገብተው ይታያሉ። ሊያውቁት የሚገባው እውነት ግን የህወሓት ጁንታ ከወጣቱ፣ ከህዝቡ፣ ከመንግሥትና ከተለያዩ አካላት ብዙ ምክርና ዕድል ተሰጥቶት አልጠቀምም ብሎ በራሱ እብደትና ቅሌት ለዚህ ማብቃቱ ሲሆን፤ የጁንታው ውድቀትም ከትግራይ ወጣቶችም ሆነ ከማንኛውም ትግራዋይ ጋር የማይገናኝ መሆኑ ነው። ይልቁንም የሆነ ቡድን በራሱ መንገድ ብቻ እያየ ሲሄድ የጠፋ አድርጎ መውሰዱ ይገባል።
ለጁንታው ቡድን ምክርና ሃሳብ ካዋጡ አካላት አንዱ የትግራይ ወጣት መሆኑን የገለጹት አቶ ነብዩ፤ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው” እንደሚባለው ሁሉ አሁን ላይ ጁንታው በራሱ መንገድ ተጉዞ የጠፋ እንደመሆኑ ወጣቱ ለዚህ ቡድን ምንም ማድረግ አይችልም። ስለዚህ ወጣቱ የጁንታው ቡድን ማንንም የማይወክል መሆኑን በመረዳት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምቶ መቀጠል እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37582

www.press.et
“የትግራይ ወጣት ራሱን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ወደ ኃላፊነት ሊመጣ፣ ሃገሩንና ህዝቡንም ሊያገለግል ይገባል” – አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የትግራይ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ | የኢትዮጵያ ፕሬስ…
“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” - ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
*******************************
(ኢ ፕ ድ)
ከህወሓት ጁንታ ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚጥሩ የምዕራባውያን ጁንታዎችን ሴራ ለማጋለጥ በኢትዮጵያዊነት ስሜት በመቆም መታገል እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ።
አቶ ኦባንግ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የእኔ ብሔር ብቻ ማለት ባለፉት 27 ዓመታት የወረስነውና ያሳደግነው አስተሳሰብ ነው። ይህ ደግሞ ለነጭ ጁንታዎች ተጠቃሚነት ሰፊ ዕድል የሰጠና ኢትዮጵያን የችግር ቋት ውስጥ የከተተ ነው። በመሆኑም ከብሔር አስተሳሰብ ወጥቶ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቆሞ የነጭ ጁንታዎችን እጅ ማሳጠር ያስፈልጋል።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ከሚያስተላልፉት መልዕክት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማቆርቆዝ ያለመ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ኦባንግ፤ የነዚህን ኃይሎች ድርጊት ለማስቆም በቅንጅት መሥራት ካልተቻለ አደጋው የከፋ ይሆናል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37602

የአምስት አመቱ የጁንታው ታጋች ህጻን
👉ከጁንታው ታጋቾች ውስጥ መንታ ልጆችን የተገላገለች እናት ለማመን የሚከብድ ስቃይ አሳልፋለች፤
👉በቀን የሚሰጠው አንዲት ዳቦ እና ጥቂት ውሃ ብቻ ነበር፤
**************************
( ኢ ፕ ድ)
ቢንያም ጌታቸው ገና አፉን በቅጡ ያልፈታ ህጻን ነው። አባቱ ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው ቦሮዳ የሰሜን እዝ ሰራዊት አባል ነው፡፡ መቶ አለቃ ጌታቸው ልጁን መስከረም 17 ቀን ወደሚኖርበት የመከላከያ ካምፕ አመጣው። የአባት ሃሳብ የነበረው የልጁን አይን አሳክሞ እረፍት እንዲያገኝ ነበር። ይህ የአባት ሃሳብ ግን ሳይሆን ቀረ፤ ያልታሰበው የጁንታው ጥቃት በሰራዊቱ ላይ ተፈጸመ።
የጁንታው ታጣቂዎች ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈጽመው በርካቶችን ሲያፍኑ ህጻን ቢንያምም ከአባቱ ጋር ታገተ፡፡ በእገታው ወቅት ጁንታው የሚያቀርበው ምግብ ለህጻን ቢኒያም ተጨማሪ ፈተና ነበር፡፡ በቀን የሚሰጣቸው አንድ ዳቦ እና ጥቂት ውሃ ህጻኑን በምግብ እጥረት ሠውነቱ እንዲጎዳ አድርጎታል፡፡
የታገቱ የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች እና አዛዦች ከቢኒያም አባት ጋር እየተጋገዙ በእግራቸው ቢኒያምን በትከሻ ተሸክመው በረሃውን ያለ በቂ ምግብና ውሃ ለቀናት እንዲጓዙ ተፈርዶባቸዋል። የጁንታው አባላት በወቅቱ በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ሆነው አቧራውን ታጋቾች ላይ እያቦነኑ ሲጓዙ ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው ቦሮዳ ልጁን አስቀምጦት ከታጋቾቹ ጋር አብሮ እንዲሄድ ይጠይቁታል።
የተሽከርካሪ ጋቢና ውስጥ አድርገው እዚሁ ይደር አሉት። ይህንን ሃሳብ ያልተቀበለው አባትም የበኩር ልጁን አንጠልጥሎ የድካም ጉዞውን ገፋበት። ህጻን ቢንያም ገና በለጋ እድሜው ከጦርነት አውድማ መሃል ገብቶ የተኩስ ድምጹንም ሆነ የፈንጂ አይነቶችንም ፊት ለፊት መጋፈጡ አይቀሬ ሆነ። የጁንታው ታጣቂዎች ሲታኮሡ የአየር ሃይል ድሮኖች እና ሄሊኮፐተሮች በሰማይ ሆነው እርምጃ ሲወስዱም ተመልክቷል።
ህጻን ቢንያም በዚህ እድሜው አሻንጉሊት ይዞ መጫወት እና ከእድሜ እኩዮቹ ጋር መቦረቅ ቢሆንም ፍላጎቱ በጁንታው እኩይ አላማ ግን ከአባቱ ጋር ታግቶ መራር ቀናትን ለማሳለፍ ተገዷል። ምን እየተፈጠረ እንዳለ እንኳን በውል የማያውቀው ህጻን በአቧራው እና በፀሐዩ የቀሉ አይኖቹን እያሸ ከታገቱ የመከላከያ መኮንኖች ጋር ችግሩ ተጋፍጧል፡፡
በወዲያኛው ማዶ ደግሞ ሌላም ግፍ አለ። አንዲት እናት መንታ ልጆችን ተገላግላ ልጆቿን ይዛ ለማመን የሚከብድ ስቃይ ስታሳልፍ ነበር። ለሀጻናቱ እንኳን ያልራሩት የጁንታው አባላት ወላጆቹን እንኳን ከእገታው ነጥለው ወደሰላማዊ ቦታ ለመላክ ቅንጣት ታክል ርህራሄንእንዳላሣዩ መቶ አለቃ ጌታቸው ይናገራል፡፡
በጁንታው የታገቱ የሰራዊት መኮንኖች ህጻን ቢንያምን እና አባቱን እያበረታቱ ዳገት ቁልቁለቱን፣ ወንዝ ጢሻውን እያቋረጡ አዴት ከተባለ ስፍራ ደረሱ። በወቅቱ የነበረው ሁኔታ መቶ አለቃ ጌታቸው እንዲህ ያስታውሳል፤ “ ህጻኑ ሄሊኮፕተሯን ግዳጅ ስትፈጽም አይቶ ‘አባዬ ምንድነው? አለኝ፡፡ ዶክተር ዐብይ ልኮልን ነው፣ ከዚህ ልትወስደን ነው አልኩት፡፡ ኦፕሬሽኑ ሲጀመር ልጄን ይዤ ከለላ ያዝኩ” ይላል፡፡
በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት እና የአየር ሃይል በተቀናጀ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ የጁንታው አባላት ላይ በወሰዱት እርምጃ የጁንታው ታጣቂዎች በየቦታው ተበታተኑ። አዴት ላይ ለቀናት የታገቱት ህጻን ቢንያም እና አባቱን ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ መኮንኖች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ነጻ ወጡ።
"በአፈናው ወቅት ሰራዊቱ ለህጻን ልጄ ያደረገው ድጋፍ እና እንክብካቤ ትልቅ ነው" የሚለው ምክትል መቶ አለቃ ጌተቸው፤ "የሀገር አደራ አለብኝና ልጄን አስተምሬ ለቁም ነገር ለማብቃት የማላደርገው ጥረት የለም" ሲል ተናግሯል።
ሁኔታውን አልፎ ሲያወሩት ቀልድ ይመስላል የሚለው ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው፤ ሰራዊቱ ለወሰደው ወገን የማዳን የጥንቃቄ እርምጃ ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል። ህጻን ቢንያምም "ዶክተር ዐብይን ነው የምወደው፤ የእኛ መከላከያ ነው ያዳነን" ሲል በስፍራው ለሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በሚኮላተፍ አንደበቱ ነግሮታል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የህግ ማስከበር ዘመቻውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ወንጀለኛው ጁንታ ከታጋች የሰራዊቱ መኮንኖች ባሻገር ሴቶችና ህጻናትን አግቶ መያዙን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ታጋቾቹን ከጁንታው በመነጠል ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ ኦፕሬሽኑን ለማካሄድ መንግስታቸው በትኩረት እየሰራ መሆኑን መግላጻቸው ይታወሳል፡፡

በመቐለ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ ሊያውለው በድብቅ ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ።
በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱ ታውቋል።
በመከላከያ ሰራዊት የ25ኛ ፈንቅል ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ ምክትል ኦፕሬሽናል አዛዥ ሻምበል ዮሐንስ ማቲዎስ እንዳስታወቁት፣ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ አስቦ በድብቅ ቀብሮት የነበረው 13 የነዳጅ ታንከር በመከላከያ ሰራዊቱ አሰሳ በቁጥጥር ውሏል፡፡
ጁንታው የትግራይ ህዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲቸገር በማድረግ ዘርፎ ለራሱ እኩይ አላማ ቀብሮት ቆይቷል ብለዋል።
ሆኖም ጥቅመኛው ሃይል የደበቀው ታንከር እንዲገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል ብለዋል።
በአከባቢው ተቀብሮ ለነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊውል የነበረ ተጨማሪ ዘጠኝ ታንከር መገኘቱንም ሻምበል ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡
የህወሃት ጁንታ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች እየተገኙ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በመቐለ በተደረገው አሰሳ ለህገ ወጥ ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች መያዛቸውን እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ በአዲስ አበባ ተጀመረ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስጀምረዋል።
በመርሐግብሩ ማስጀመሪያ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ውብ፣ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ መሆን ይኖርበታል ብለዋል ።
በቀጣይ አራት ወራት በሚቆየው የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ የበጎፍቃድ አገልግሎት ከ28ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች በሣምንት ሁለት ቀናት እንደሚሳተፉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።
አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ መዲናነቷን ፣የቱሪዝም እና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ነዋሪዎች ጽዳቷን በመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስተባባሪነት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ እንክብካቤ በአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሚከናወን መሆኑን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ገልጿል፡፡

“አሁን ያለችው ትግራይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ናት ”
-አቶ ሊላይ ኃይለማርያም፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር
************************
(ኢ ፕ ድ)
አሁን ላይ ያለችው ትግራይ የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ እምብዛም የማይታይባት 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት መሆኗን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ተናገሩ።
የህወሓት ጁንታ ከአሁን በኋላ እንደማይመለስና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ገሀነም መውረዱን በመገንዘብም ደጋፊዎችና አባሎቻቸው ወደ ህዝባቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሰርቱና በጋራ አገር ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ሊላይ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ አሁን ትግራይ በአጠቃላይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ሆናለች። የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ የሚታይበት ሁኔታ ብዙም የለም። አውሮፕላንን ጨምሮ ትራንስፖርት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይንቀሳቀሳል።
መብራት እስከ አዲግራት እየሠራ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ዓደዋና አክሱም ይገባል። አብዛኛው ከተሞችም መብራት ያገኛሉ። የውሃና የኔትዎርክ አገልግሎትም እየተዳረሱ ነው። በሚቀጥለው ሳምንትም የባንክ አገልግሎት በሰፊው ይጀመራል።
መቀሌም በጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው። ወደ ቀደመ መልኳ ተቀይራለች።
የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንጻር መቶ በመቶ እንዲከፈቱ ተደርገዋል። በሰለማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታው ገብቷል።
ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሥራ ያልገቡ ሠራተኞች ላይ በአገሪቷ ህግ መሠረት ዕርምጃ ይወሰዳል። ይሄ ደግሞ የተሾሙት ካቢኔዎች ኃላፊነት ነው። ትጥቅን የማስፈታት እንቅስቃሴውም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። ታጥቆ የነበረው ትጥቅ በየቦታው እየተፈታ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=37618

“አሁን ያለችው ትግራይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ናት ” -አቶ ሊላይ ኃይለማርያም፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አስተዳደር | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት