የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት ይቅርታ ጠየቀ
*******************
( ኢ ፕ ድ)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት ይቅርታ መጠየቁን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሕዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለውጭ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው።
በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከተነሳው ጥያቄዎች አንዱ መንግስት በትግራይ ክልል በተመድ ሰራተኞች ላይ ተኩሷል መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ የሚል ነበር።
አምባሳደር ሬድዋን በትግራይ ክልል የፍተሻ ጣቢያዎችን የጣሱ የተመድ ሰራተኞች ላይ መተኮሱንና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ከተደረገ በኋላ መለቀቃቸውን ገልጸዋል።
የድርጅቱ ሰራተኞች ወዳልተፈቀደላቸው ቦታ ሲያመሩ እንደነበረና ሁለት የፍተሻ ጣቢያዎችን ካለፉ በኋላ ሶስተኛ የፍተሻ ጣቢያ ጥሰው ሊያልፉ ሲሞክሩ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ተመድን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስትን መመሪያ ማክበር እንደሚገባቸውና መንግስት ከስጋት ነጻ ናቸው ብሎ ቦታዎችን ከለየ በኋላ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ አምባሳደር ሬድዋን በመግለጫቸው አንስተው ነበር።
የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር በተመድ ሰራተኞች ድርጊትና በፍተሻ ጣቢያው በተፈጠረው ክስተት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
ተመድ በትግራይ ክልል የድርጅቱ ሰራተኞች ለፈጸሙት ድርጊት መንግስትን ይቅርታ መጠየቁንም ሰላም ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል።
የተመድ የኢትዮጵያ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ የጠየቁትን ይቅርታ የኢትዮጵያ መንግስት መቀበሉን ገልጿል።
ተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ትብብር የሚሸረሽሩና ከፍተኛ የአደጋ ስጋት የሚደቅኑ ተመሳሳይ ጥሰቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ የሚያስችሉ ስርዓቶችን እንደሚዘረጋ መግለጹንም አመልክቷል።
መንግስት ሕዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከተመድ ጋር በደረሰው ስምምነት አማካኝነት በትግራይ ክልል ለሚደረገው ድጋፍ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ነው የሚኒስቴሩ መግለጫ የሚያመለክተው።
በስምምነቱ መሰረት ድርጅቱ ከመንግስት ጋር በመሆን አስፈላጊውን የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችልም ጠቁሟል።
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት በትግራይ ክልል አስቸኳይ የድጋፍ አቅርቦት እንዲደርስ ያላቸውን ፍላጎት መንግስት እንደሚረዳና ተቋማቱ ድጋፉን ማድረግ የሚችሉት ከፌዴራል ተቋማት አስፈላጊውን ፈቃድ ሲያገኙ እንደሆነ ሊረዱት እንደሚገባ ገልጿል።
ሁሉም የሰብአዊ ድጋፍ ሰራተኞች መንግስት ያወጣውን መመሪያ መከተል እንደሚገባቸውና መንግስት ሰራተኞቹና የድጋፍ አቅርቦቶች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ያለበትን ግዴታ እንደሚወጣም ነው የሰላም ሚኒስቴር ያስታወቀው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከተመድ ኤጀንሲዎች ጋር ላለው ትብብርና ኤጀንሲዎቹ ለኢትዮጵያ የልማት ፕሮግራሞችና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች ለሚያደርጉት ወሳኝ ድጋፍ ትልቅ አክብሮት እንዳለውም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሚችለው አቅም በትግራይ ክልልና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ላሉ የሰብአዊ ጉዳይ ፈተናዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በአስፈላጊው ጊዜ ለተቸገሩ ዜጎች ለሚያደርጉት ወሳኝ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ምስጋውን እንደሚገልጽ የሰላም ሚኒስቴር በመግለጫው ያተተው።
መንግስት በትግራይ ክልል ያለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጠናቆ ተልዕኮው ወደ "ወንጀሎችን የማደንና መልሶ ግንባታ" ምዕራፍ መሸጋገሩን መግለጹ የሚታወስ ነው።

ከታጋቾች አንደበት
👉 ዋናው ነገር የሃገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም፤ ጓደኞቻችን ግን ነጻ አውጥተውናል፤
👉 የጁንታው ታጣቂዎች የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፉ አዘዟቸው፤
👉 “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” በሚል ለሰራዊቱ ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ፤
👉 በኦሮምኛ ደግሞ ለሰራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያዝዝ መልዕክት አስተላለፋ፤
ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን የመከላከያ ሰራዊት 20ኛ ክፍለጦር አዛዥ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በጁንታው ቡድን ታግተው ከቆዩ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ናቸው። ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፉ አዘዟቸው። እርሳቸውም “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” በሚል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚገልጽ ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ። አክለውም በኦሮምኛ ለሰራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያግዝ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያስታውሳሉ።
መከላከያ ሰራዊቱም ጥቃቱ ከተፈጸመ ማግስት ጀምሮ በመከላከልና የህግ ማስከበር እርምጃ በመፈጸም ህይወት የማዳን እና አጥፊዎቹን የመቅጣር እርምጃውን ገፋበት። በርካታ የሰራዊቱ አባላት እና አመራሮችም ከብዙ እንግልት በኋላ ከጁንታው እጅ ነጻ ወጡ። ከታጋቾች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ነጻ ከወጡ በኋላ ሲቃ በተሞላበት ንግግራቸው ሁናቴውን አስረድተዋል።
<<ከሁሉ በፊት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊትም እንኳን እንኳን ለዚህ ድል አበቃን ፤ እኛንም ከአንድ ወር ልፋትና እንግልት በኋላ እንኳን በሰላም አገናኘን። ዋናው ነገር የሃገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም በሚል ተስፋ ቆርጠን ነበር። ጓደኞቻችን ግን መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ኦፕሬሽናቸውን በመፈጸም ነጻ አውጥተውናል።
በርካታ ቀናትን ያለምግብ እና ውሃ በተለያየ መልከአምድር ላይ ተንገላተናል። በርካታ የሰራዊት አባላትም ይህን እንግልት ተቋቁመን አሁን የደረስንበት ደረጃ በመድረሳችን በታጋቾች እና በእራሴ ስም ለመከላከያ ሰራዊት ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።
በአጠቃላይ በሰራዊታችንም ሆነ በህዝባችን ሲከናወን የነበረውን ነገር በተለያየ መንገድ የሰማነው ስለሆነ እኛም ደስ ብሎናል። ለመከላከያ ሰራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለድል ያበቃችሁን አንድነታችሁን በማጠናከር የቀሩትን ስራዎችም እንድታጠናቅቁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፤
ለአንድ ወር ከስድስት ቀን በጁንታው ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ ታግተው በረሃብና በእንግልተ የቆዩት የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በሰራዊቱ አማካኘነት ነጻ ከወጡ በኋላ ህይወታቸውን ለማትረፍ ለተደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ
**********
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።
በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመቀሌ ቆይታቸው
👉ከሀገር መከለከያ ሰራዊት አመራሮች ጋርም በድሉ ዙሪያ ውይይት
አድርገዋል፤ በዚሁ ወቅት የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች
*********************
(ኢ ፕ ድ)
👉 ጠላት በርከት ያሉ የእኛን መኮንኖች ይዞ ስለቆየ እነሱን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ ስለሆነም ማታ ማታ በምናደርገው ኦፕሬሸን በርከት ያለ ሰው በሚኖርበት ሰአት ይህ ሀይል የእኛ ሃይል ሊሆን ይችላል በሚል ያቆየናቸው ሚሳየሎችና ቦንቦች ዛሬ ያኮሩኛል። ያንን ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመካከላችን ያሉትን መኮንኖች አናያቸውም ነበር፤
👉 ይህ ኢትዮጵያን የመታደግ ኢትዮጵያን የማኩራት ብቃት፤ ተልዕኮን በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት የተቋማችን የሁልጊዜ አርማ መሆን አለበት፤
👉 በተደጋጋሚ እንዳልኩት የመከላከያ ሰራዊት የብልጽግና ሰራዊት አይደለም፤ የአብይ ሰራዊት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መከታና ኩራት የሆነ ወታደር ነው፤
👉 እኛ የምንፈልገው ፕሮፌሽናል ጠንካራ አርሚ እንድትሆኑ እንጂ ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ እንድትሆኑ አንፈልግም፤
👉 ኢትዮጵያ ከብልጽግናም ከፓርቲም በላይ ናት፤ ትልቋን አገር የመታደግ ሃላፊነት ተጥሎባችኋል፤
👉 ፖለቲካው የተበላሸ ነው፤ የማያውቀውን የደም ስር እና ሀረግ እየፈለገ የሚቧደን ነው፤ እናንተ ግን ጀግኖች ብቻ ሳትሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤
👉 ጦርነቱን ስንጀምር በጣም ብዙ ሰዎች በአጠረ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍም ይከብዳል የሚል ግምግማና ግምት ይናገሩ ነበር፤ ይሄ አልሆነም፤
👉 እኛን የሚዋጉን ሰዎች ዘመናዊ ጦርነት አያውቁም፤ የጦርነት ሳይንስ አያውቁም፤ የሚያውቁት የሽምቅ ውጊያ ነው፤ እሱ የሽፍቶች ውጊያ ነው፤ እሱ በሰው ሃይልና በተተኳሽ ቁጥር ማሸነፍ የምናረጋግጠብት ውጊያ ነው፤
👉 የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስንት ሺህ ወጣት እንዳስከፈለን ስንት ጊዜ እንደወሰደ እናውቀዋልን፤ ይሄ የአሁኑ ኦፕሬሽን ደግሞ በምን ያህል ባነሰ የሰው ሃይልና መስዋዕትነት ለድል እንደበቃን ታውቃላችሁ፤
👉 ከሁመራ መቀሌ በእግር መጓዝ ማለት ብዙዎች አዲስ አባበ ሆነው ዝም ብሎ ጀግና እንደሚሉት አይደለም፤ በዚህ መልክዐ ምድር በዚህ ሙቀት ስንቅና ትጥቅ ተሸክሞ ይሄንን ያህል ጉዞ መጓዝ የማንም አገር ወታደር አይደግመውም፤
👉 ይሄንን ጀግንነት ወንጀለኞችን በመያዝ መድገም ያስፈልጋል፤ ወታደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መቶ በመቶ አሳክቷል፤ የሚቀረው ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ነው እሱንም በፍጥነት ማከናወን ያስፈልጋል፤
👉 ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የትግራይ ህዝብ ሃላፊነት አለበት፤ የተደበቁትን ሰዎች፣ ከመኪና ወርደው እግረኛ የሆኑትን ሰዎች በመያዝ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለትግራይ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፤ ያ ካልሆነ ወታደሩ አገር የመጠገን ጊዜውን ወንጀለኛ በማደን ስለሚያሳልፍ የሚጎዳው ራሱ ህዝቡ ነው፤
👉 ከኢትዮጵያ መንግስት ልማት ድጋፍ መጠየቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ወንጀለኞችን አሳልፈው መስጠት ደግሞ ግዴታ ነው፤ ይህ ስምምነት ካለ ነው ስራችንን በአጭር ጊዜ በማከናወን ወደልማት የምንገባው፤
በርካታ ወንጀለኞችን እንደተያዙ፤ የተቀሩትም የት እንዳሉ መረጃው አለኝ፤
👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝቦች ኩራት መሆኑን፤ በዚህ ቀጣና የሚነሳ ማንኛውንም አደጋ በሚፈለገው ልክ ለመመከት የሚያስችል ብቃት ያለው ጦር መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል፤
👉 የጁንታው ሃይል በቁጥር ከ80 ሺህ በላይ ይገመታል፤ አዳዲስ መሳሪያዎችን ታጥቋል፤ ከፍተኛ የተተኳሽ ዲፖዎች ነበሩት፤ ኮማንዶ ሜካናይዝድ ሮኬት መተኮስ የሚችሉም ሰዎችነበሩት፤ እኛ ግን መቀሌ እስከገባንበት ቀን ድረስ ሮኬት አልተኮስንም በእኛና በጁንታው መካከል ያለው ልዩነት ይሄ ነው፤ እኛ ያልተኮስነው ህዝባችን እዚህ እንዳለ ስለምናውቅ ነው፤
👉 እኛ ሮኬት የተጠቀምነው ጁንታው መቀሌን ለቆ በረሀ ለበረሃ ለማምለጥ ሲሞክር ነው፤ ይሄ የእውነት ይሄ የፍትሃዊነት ልዩነታችን አሸናፊ አድርጎናል፤

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ መቀሌ ላይ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከጁንታው መደምሰስ በኋላ በመላ ኢትዮጵያ ሰላም መስፈኑን የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።
ላለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ራሱን እያደራጃ በመላ አገሪቷ ግጭት እየለኮሰ የቆየው የህወሓት ጁንታ ከተደመሰሰ በኋላ በመላ ኢትዮጵያ ሰላም መስፈኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ዛሬ መቀሌ ላይ ሆነው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ፤ ጁንታው በመደምሰሱ የኢትዮጰያ ህዝብ እፎይታ አግኝቷል፤ በመላ አገሪቱ አሁን ሰላም ነው።
ቀደም ባሉት ሁለትና ሶስት አመታት በየቦታው እነሱ ግጭት ይለኩሱ እንደነበረ ያስታወሱት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በአሁኑ ወቅት እነሱ በመመታታቸው ምክንያት ሁሉም አካባቢ እፎይታ ሰፍኗል ሲሉም ነው ያስታወቁት።
“የኢትዮጵያ ህዝብ ከእነዚህ መሰሪና በጣም አስቸጋሪ ሰዎች ተገላግሏል” ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ የትግራይ ህዝብም ነጻ ወጥቷል፤ ከዚህ በሁዋላ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማግኘት የሚገባውና በጁንታው ተቋርጠው የነበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በፍጥነት ይከናወናሉ ብለዋል።
ጁንታው ላለፉት ሶስት አመታት ህግ መንግስቱ የሚፈቅድለትን መብት በመጠቀም ራሱን በልዩ ሃይል ስም ሲያደራጅ መቆየቱን፤ በቅርብ ቀናትም አዲስ አበባ እንደሚገቡ ለህዝቡ መንገራቸውን፤ ለጎረቤት አገራትም 250 ሺ ሰራዊት አደራጅተናል፤ ሰሜን ዕዝን ደምስሰናል ትጥቅ ወስደናል ስለዚህ ፌዴራል መንግስት አቅም የለውም ከአሁን በሁዋላ ኢትዮጵያ በእኛ እጅ ናት በሚል ውስጥ ለውስጥ ፕሮፖጋንዳ ሰርተዋል” ያሉት ጄኔራሉ መከላከያ ሰራዊት ይህንን የትምክህት፣ የገዥ መደብና የድንቁርና አስተሳሰብ አምክኖታል ብለዋል።

የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችን የልማትና የጸጥታ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንደተናገሩት፤ ከህግ ማስከበር ዘመቻው ጋር ተያይዞ ጁንታው ሆን ብሎ በከተማዋ ዝርፊያ እንዲፈጸም አድርጓል፤ የመንግስት አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል። ይህንን ተከትሎ የተፈጠረውን የነዋሪዎችን የልማትና የጸጥታ ስጋት ለመቅረፍ አስተዳደሩ ከመከለከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የተጠናከረ ስራ እያከናወነ ይገኛል።
በመጀመሪያ ከዝርፊያ ጋር ተያይዞ የነበሩት ሁኔታዎች አሁን ላይ ቀንሰዋል ያሉት ከንቲባው፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችን ለማጥፋትና ለመውሰድ ሆን ተብለው በጁንታው አማካኝነት እንዲዘረፉ ተደርገዋል ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽፈት ቤት፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች፣ የፍትህ፣ የማዘጋጃ ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ አገልግሎት የሚሰጡባቸው ዶክመንቶችን አዘርፈዋቸዋል ያሉት ከንቲባው፤ ከዚያ በኋላ ተዘርፎ ነው እንዲባል ተቋማቱ ክፍት ተትተዋል፤ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሌሎች ዘራፊዎች እየገቡ ኮምፒውተሮችና አንዳንድ ነገሮችን መዝረፋቸውን አብራርተዋል።
በወንጀል ተይዘው እስር ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቆች ሳይቀሩ እንዲዘረፉ ተደርጓል ያሉት ከንቲባው፤ የዚህ ዝርፊያ ዓላማም ህዝቡ መከላከያ ሰራዊት ላይ እምነት እንዲያጣና በዚህ የተነሳ ወደ ስጋት እንዲገባ መሆኑን አብራርተዋል።
የመከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማ ከገባ በኋላ ከመከላከያ አመራሮች፣ ከክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን በመነጋገርና በመወያየት ቅድሚያ ሰጥተን መስራት ያለብን ጉዳይ ምንድን ነው? የሚለውን በቅደም ተከተል አውጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን” ያሉት ከንቲባው፤ የሕዝቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች የነበሩት የመብራት፣ እና የውሃ አገልገሎት ሙሉ በሙሉ ምላሽ እንዲያገኝም የተደረገ ሲሆን የስልክ አገልግሎትም በከፊል መመለሱን አስታውቀዋል።
የከተማ ውስጥ የታክሲ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ሌሎች የመስሪያ ቤት አገልግሎቶች በመጀመር ላይ ይገኛሉ ያሉት ከንቲባው፤ አብዛኛው አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ቦታዎች መከፈታቸውንና ህዝቡም ከስጋት እየወጣ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው መመለስ መጀመሩን አስታውቀዋል።
በየክፍለከተማው በተዋቀረው የአስተዳደር አካል በተመረጡ ተወካዮች፣ በአስተዳደሩ አመራር አማካኝነት ድጋፍ ለሚፈልጉ የከተማዋ ነዋሪዎች እርዳታ በማከፋፈል ላይ ነው የምንገኘው ያሉት ከንቲባው፤ የሕክምና ቁሳቁሶችም ለህክምና ተቋማት በማድረስ ላይ መሆናቸውንና ሆስፒታሎቹ በሙሉ በመደበኛ ስራቸው ላይ እንደሆኑ አብራርተዋል።
ጎደሉ የሚባሉ ነገሮች ካሉም በየጊዜው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ቅድሚያ ሰጥተን በመስራት ላይ ነው የምንገኘው ያሉት አቶ አታክልቲ፤ በመረጃ ማጣት ምክንያት ውዥንብር ውስጥ የገባው የህብረተሰብ ክፍል አሁን ላይ መብራት በመለቀቁ ምክንያት እወነታውን እየተረዳ ወደመደበኛ እንቅስቃሴው መመለስ መጀመሩን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል።
በመሀመድ ሁሴን

ግምታዊ ዋጋቸው አንድ ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 119ሺህ የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአምስት ወራት ውስጥ አንድ ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 119ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለቆመጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ባለፉት አምስት ወራት ከሀምሌ እስከ ህዳር 30/2013 ዓ/ም ግምታዊ ዋጋቸው አንድ ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 118 ሺ ብር የሆነ የወጪና የገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መቆጣጠር ተችሏል፡፡
ግምታዊ ዋጋቸው 981 ሚሊዬን 590 ሺህ የሚገመት የገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ አንድ ቢሊየን 100 ሚሊዬን 631 ሺህ ብር የሚገመት ገቢ ኮንትሮባንድን ተይዟል፡፡ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በተመሳሳይ 134 ሚሊዬን 708 ሲህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ 255 ሚሊዬን 487 ሺህ ዋጋ የሚያወጡ ወጪ ኮንትሮባንድ ተይዘዋል፡፡ አፈፃፀሙ 190 በመቶ ነው፡፡ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 107 ሚሊዬን 276 ሺህ ብልጫ ሲኖረው የ72 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በበአምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው አንድ ቢሊዬን 116 ሚሊዬን 298 ሺህ የሆነ ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ ታቅዶ ግምታዊ ዋጋቸው አንድ ቢሊዬን 356 ሚሊዬን 118ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ተችሏል፡፡
እነዚህ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመያዝ ቀን እና ሌሊት በመስራት ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጉምሩክ ኬላ እና መቆጣጠርያ ጣቢያ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይሎችና ጥቆማ በመስጠት ለተባበሩ አካላት ሁሉ የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ ወራትም ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ከገቢዎች ሚኒስቴር የጠገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን በ10 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡ ተገለጸ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከክልሎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የዘንድሮው የመኸር ወቅት በዘር ከተሸፈነው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን የሚጠጋ መሬት ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት የዘንድሮው የመኸር እርሻ በምርትና ምርታማነት በኩል እጅግ ጥሩና ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ በዘር የተሸፈነው መሬት 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ ሁሉም መረጃ ተጠናቅቆ ባይገባም 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል ተሰብስቧል፡፡ ከዚህ ጋር ታያይዞም አሁን ያለው የሰብል ይዞታ የምርታማነት መጠን በጣም ጥሩ በሚባል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡
ለዚህ የመኸር ወቅት ውጤታማ መሆን የነበረው የዝናብ መጠን ለሰብል ምርታነማነት የሚመች መሆኑ ተጠቃሽ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩልም ለግብርና ሥራው አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ ሰፊ ሥራ መሠራቱን አብራርተዋል፡፡
በመኸር የሥራ ወቅት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የጎርፍ አደጋዎች መብዛትና የአምበጣ መከሰት በአገሪቱ በተለይም በግብርና ሥራው ላይ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥን ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ተጽዕኗቸው ግን የተፈሩትን ያህል አልነበሩም ብለዋል ዶክተር ማንደፍሮ፡፡
እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ ማሳቸው በጎርፍ የተወሰደባቸው። በአምበጣ የተወረረባቸው አርሶ አደሮች ነበሩ በግለሰብ ደረጃም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሷል፡፡ ነገር ግን እንደ አገር በመኸሩ እርሻ ይገኛል ተብሎ ከታሰበው ውጤት አንፃር ሲገመገም ግን ያን ያህል ከባድ ተጽዕኖ አድርሷል ለማለት እንደማይቻል አብራርተዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=37393

www.press.et
በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን በ10 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡ ተገለጸ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጦር ኃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተዉ በህግ ማስከበር ዘመቻዉ የተካፈሉ የመከላከያ አባላትን ጎበኙ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ የሚኒስትሮች አብይ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን በጦር ኃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተዉ በህግ ማስከበር ዘመቻዉ የተካፈሉ ጀግና የመከላከያ አባላትን ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሯ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ እዚህ የተገኘነዉ በአጥንታቸዉና በደማቸዉ ስለ ሀገራቸዉና ህዝባቸ ዋጋ የከፈሉ ወገኖቻችንን ባይመጥንም አክብሮታችንን እና አብሮነታችን ለመግለጽ ነዉ ብለዋል።
የህግ የማስከበር ዘመቻው ብዙ ትምህርት የወሰድንበት ነዉ ያሉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፣ ዘመቻዉ ሀገርን የመዉደድ ምስጢር ምን ያህል መሆኑን ያየንበት ነዉ ብለዋል። ለዘላቂ ሰላም የህግ የበላይነትን ማስከበር ዋነኛ ተግባር መሆኑን ገልፀዉ ከዚህ በኋላ በአብሮነት የተሰጠንን ኃላፊነት እንድንወጣ መስመር ያስያዘ ሂደት ነው ብለዋል።
በህግ ማስከበር ዘመቻዉ የተሳተፋትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአማራና የአፋር ልዩ ኃይል ጨምሮ በሂደቱ የተሳተፉትን ሁሉ በመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ የሚኒስትሮች አብይ ኮሚቴ ስም አመስግነዋል።
በጉብኝቱ የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ እንዲሁም የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች መሳፋቸውን ከሰላም ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጁንታው ከመከላከያ ዘርፎ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ናቸው
************************
(ኢ ፕ ድ)
ጁንታው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
የምዕራብ ግንባር የጥገና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ እንደገለጹት፤ ጁንታው ከመከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ የሀገር ሀብቶች ከየመንገዱ እየተሰበሰቡ ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ ናቸው።
እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ሲከፍት ታንኮች፣ መድፎች እና በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፏል። ከባድ መሳሪያዎቹን ከዘረፈ በኋላ ይዞ ለመዋጋት ቢያስብም በመከላከያ ሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ እና በአየር ኃይል ኢላማቸውን የጠበቁ እርምጃዎች ምክንያት መሳሪያዎቹን እየጣለ ሊፈረጥጥ ግድ ሆኖበታል። አንዳንድ መሳሪያዎቹን በከፊል ሲያወድም የተቀሩትን ግን በየአስፓልት ዳሩ እና በየጫካው አስቀምጦ እግሬ አውጪኝ ብሏል።
ከሃዲው ቡድን ከመከላከያ ሰራዊቱ የደረሰበትን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ከሽሬ አንስቶ እስከ ሽራሮ እና ተንቤን ድረስ በየመንገዱ ያንጠባጠባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያየ አቅም ያላቸው መድፎች፣ ሎቤዶች እና ቢኤም መሳሪያዎች ተጓጉዘው ወደሽሬ የጥገና ማዕከል እየገቡ ይገኛሉ ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፣ የጥገና ባለሙያዎችም መሳሪያዎቹን በመፈተሽ ዳግም ወደስራ ለማስገባት በመረባረብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በርካታ ከባድ መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችም ከጥገናቸው በኋላ የተሳካ ሙከራ ተደርጎባቸው ወደስራ መመለሳቸውን ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ ተናግረዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37380

ጁንታዎቹ ኢትዮጵያን የማፈራረስና ድሮ የነበረውን የዝርፊያ ፍላጎታቸውን ለማስቀጠል፤ በተቻለ መጠን የተዳከመ ወይም የተበተነ መንግስት እንዲኖር ለማድረግና አገሪቱን ወደ እርስበርስ ጦርነት እንድትገባ ለማድረግ ነበር በመከላከያ ላይ ጥቃት የፈፀሙት፤
👉 በመንግስት ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የነበሩ የጁንታው ሰዎች የሚዘርፉትን ገንዘብ በራሳቸው ስም አያደርጉትም ነበር፤ አብረዋቸው በሚሰሩ ሌሎች ግለሰቦች ስም እያደረጉ ነበር የሚጠቀሙት፤
አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
👉 ለውጥ ያስፈልጋል የሚል ግምገማና ክርክር ሲደረግ፣ ህወሓት ከፍተኛ ተፅእኖ ለመፍጠር ሲጥር ነበር፤ ለውጡ በሚፈለገው አቅጣጫ እንዳይሄድ እንቅፋት እየሆነ በአንድ አጀንዳ ላይ ተወያይተን የውሳኔዎቹ ሃሳብ በመግለጫ ከወጡ በኋላ ህወሓት ለብቻው ወጥቶ እንደገና ሌላ መግለጫ ያወጣል፤
👉 አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሚል ፍልስፍና ጠላትና ወዳጅ ብሎ የሚለይ፣ ሰዎችን በአመለካከታቸው ብቻ ይሄኛው ጠላቴ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ወዳጄ ብሎ የሚያስቀምጥ ነበር፤
👉 በሕዝቦች መካከል የጥላቻ ግድግዳ ፈጥሯል፤ የሚገርመው ጠላት ወይም ወዳጅ ከሚለው ውጭ ሌላ ሶስተኛ መንገድ አለ ብሎ አያምንም፤
👉 የህወሻት ቡድን «የለውጥ ኃይሉ ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ነው ብልፅግናን የሚያቋቁመው፤ አሀዳዊ መንግስት ነው፤ የድሮውን ስርዓት ለመመለስ ነው፤ የፌደራል ስርዓቱን ለማፍረስ ነው» የሚሉ የማያቋርጥ ዘመቻ ሲያካሂድ ነበር፤
👉 በ2012ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው ምርጫ እንዲራዘም ሲደረግ፤ «ስልጣን ለማራዘም ነው» የሚሉ በርካታ የስም ማጥፋት ዘመቻቸውን ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤ ግን እነሱ ስለተቃወሙት ተግባራዊ ከመሆን አልቀረም፤ እናም ይሄን ተከትሎም ይህ ኃይል «በራሴ ክልል ምርጫ አደርጋለሁ» ብሎ ፍፁም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ተነሳስቶ አድርጎታል፤
👉 እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች ሁሌም ትንኮሳ ሲያደርጉ ቢቆዩም፤ በመጨረሻ ቀዩን መስመር አልፈው መከላከያ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤
👉 እጅግ ዘግናኝ የሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በዓለም ታይቶ የማይታወቅ አሳዛኝ ተግባር ፈፀሙ፤ የትግራይን ሕዝብ ለመጠበቅ ከ20 ዓመታት በላይ ጉድጓድ ውስጥ የኖረ፤ በክፉም ሆነ በደጉ ከትግራይ ህዝብ ጎን ቆሞ የኖረውን ወታደር ከጀርባው ጥቃት ፈጸሙ፤
👉 ኢትዮጵያን የማፈራረስና ድሮ የነበረውን የዝርፊያ ፍላጎታቸውን ማስቀጠል፤ በተቻለ መጠን የተዳከመ ወይም የተበተነ መንግስት እንዲኖር ማድረግና አገሪቱን ወደ እርስበርስ ጦርነት እንድትገባ ለማድረግ ነበር ይህንን ጥቃት የፈፀሙት፤
👉 ከፍተኛ የሆነ ጫና እየፈጠረ፤ ዘረፋ እየፈፀመ የቆየ ቡድን ነው፤ በቤኒሻንጉል፤ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሌ እና በአፋር ያሉ የእርሻ መሬቶችን ሲበዘብዝ የኖረ ቡድን ነው፤
👉 ሱማሌ ክልል ላይ በርካታ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ረሽኖ በአንድ ጉድጓድ እንዲቀበሩ በማድረግ ትልቅ ግፍ ፈጽሟል፤
👉 የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች በመከፋፈል በጠላትነት እንዲተያይ በማድረግ በጋራ የመሰረቱትን የአንድነት እሴታቸውን እያፈረሰ በልዩነቶቻቸው ላይ እያነጣጠረ በቀየሰው ዘዴ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ደርሷል፤
👉ስርዓቱን ይቃወማሉ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች እያሸማቀቀ፤ በሽብር ተሳትፈዋል ብሎ በእስር ቤት ያጉራቸዋል፤ ይገርፋቸዋል፤ አካላቸውን ያጎላል፤ ያኮላሻል፣ ይገድላል፤
👉 በኢኮኖሚ ረገድ ኢ-ፍትሃዊነቱን ያባባሰው በልማት ድርጅቶች አማካኝነት የሚደረግ ዘረፋ ነው፤ ለምሳሌ እንደባንክ፥ ቴሌና በመሳሰሉት ተቋማት ላይ በጣም ብዙ ዘረፋዎችና በደሎች ተፈፅመዋል፤
👉 ኢ-ፍትሃዊነት እየነገሰ፤ ግለሰቦች በአጭር ጊዜ እየከበሩ፤ ከምንም ተነስተው ባለሃብት እንዲሆኑ የተደረገበት ስርዓት ፈጥረዋል፤
👉 በመንግስት ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የነበሩ የጁንታው ሰዎች የሚዘርፉትን ገንዘብ በራሳቸው ስም አያደርጉትም ነበር፤ አብረዋቸው በሚሰሩ ሌሎች ግለሰቦች ስም እያደረጉ ነበር የሚጠቀሙት፤ በዚህ ምክንያት ኢ-ፍትሃዊነቱ እየሰፋ የመጣውና የለውጡ ዋነኛ ሰበብ የሆነው አንዱ ይኸው ጉዳይ ነው፤
👉 እያንዳንዱ ሰው ማንነቱን በራሱ ነው እንዲወስን ሊደረግ የሚገባው፤ የግለሰቦች መብት ሰለሆነ፤ እነዚህ ሰዎች ግን ይህንን መብት ነው የነፈጉት:: የእኔ ማንነት ነው ብለው በራሳቸው ለመወሰን የማይችሉበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው:: ስለዚህ ይሄ ቡድን በአገር ክህደት ወንጀል ውስጥ የገባው ቡድን የእነዚህን ሰዎች መብት አፍኖ ነው የኖረው፤
👉 ዛሬም ድረስ ሚዲያ ላይ እየወጡ የአማራ መሬት ማስመለስ ዘመቻ ነው እያሉ ነው በቅርቡ የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ሲጠቅሱት የነበረው:: ይህንን ሃሰተኛ ትርክት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ ለማስተላለፍ ሞክረዋል፤ አጀንዳና አቅጣጫ ማሳት ከድሮም ጀምሮ የተካኑበት ባህሪ ነው፤
👉 ይሄ አፋኝ ቡድን ላይመለስ ወደመቃብሩ ወርዷል፤ ከዚህ በኋላ መብት ማፈን፥ መርገጥ ፤ እኔ ብቻ አውቅልሃለሁ ማለት አይፈቀድም፤ አሁን በጀመርነው ለውጥ እንኳን ሊታሰብም አይችልም፤
👉 «ለእኛ ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው» የሚሉ ትዕቢት የተሞላባቸው ንግግሮችን በድፍረት ይናገሩ ነበር:: እውነት ለመናገር እነዚህ ቡድኖች የእብሪታቸው ልክ ወሰን የለውም:: ሁሉም በሚባል ደረጃ ትዕቢትና እብሪት ወጥሮ የያዛቸው ሰዎች ናችው፤
👉 «ከእኛ በላይ ለጦርነት የተፈጠረ የለም፤ ከእኛ በላይ ውጊያ ላሳር ነው» የሚሉ እብሪት የተሞሉ ሰዎች ነበሩ:: ግን ይህንን እብሪታቸውን እንዲፈፀም ያደረጉት በሚያሳዝን ሁኔታ በደሃው ልጅ ላይ ነው፤
👉 የእነሱ ልጆች በዚህ ጦርነት አይማገዱም፣ አይለበለቡም፣ እነዚህ አረመኔ ሰዎች እድሜ ልካቸውን ድሃውን የትግራይ ወጣት በጦርነት ውስጥ እየማገዱ የኖሩ፤ በሕግ ማስከበሩ ዘመቻ የተማረኩት ህፃናት ልጆች ከትምህርት ገበታ ላይ ተነቅለው ተወስደው የተመለመሉ ናቸው፤
👉 ከሃዲው ቡድን ሽንፈቱ አይቀሬ መሆኑን እየተገነዘበ ሲሄድ የያዛቸውንና ምሽግ የሰራባቸውን ቦታዎች እየለቀቀ በሚሄድበት ጊዜ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን አፈራርሷል፤
👉 በተለቀቁ ቦታዎች ላይ የፈፀሙት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አለ፤ ለምሳሌ ማይካድራ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋና በደል ታሪክ ይቅር የማይለው በጣም ትልቅ ወንጀል ነው፤
👉 አንዳንዶቹ «ምርጫ መካሄድ የለበትም» የሚል አቋም አላቸው፤ ግን ደግሞ የመንግሥትን ሥልጣን ይፈልጋሉ፤ እነዚህ ሃሳቦች እርስበርሳቸው ይጣረሳሉ፤ ስልጣን የሚፈልጉት በሌላ መንገድ ነው፤
👉 የሽግግር መንግስት እናቋቁም፤ የባላደራ መንግስት ይመስረት የሚል ፍላጎት ያላቸው ፓርቲዎች አሉ፤ ሁሉንም ፓርቲዎች ግን አይገልፅም፤
👉 ስልጣን የሚያዘው በምርጫ ብቻ ብሎ ስለሚደነግግ፤ ከምርጫ ውጭ የሚመጣ ስልጣን ስለሌለ ያንን ታሳቢ አድርጎ ነው እንጂ መሰራት ያለበት በአቋራጭ እንዲህ አይነት መንግስት እናቋቁም የሚለው ነገር አያስኬድም፤
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከአቶ ብናልፍ አንዱዓለም ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ሙሉውን ሊንኩን ተጭነው ያገኙታል።
https://www.press.et/Ama/?p=37198
www.press.et
“ማንነታቸው እውቅና ያልተሰጣቸው ዜጎች ለ30 ዓመታት ሲበደሉና ሲገፉ ቢኖሩም በአመጽ ለመፍታት አንድም ቀን ተንቀሳቅሰው አያውቁም” – አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

“ማንነታቸው እውቅና ያልተሰጣቸው ዜጎች ለ30 ዓመታት ሲበደሉና ሲገፉ ቢኖሩም በአመጽ ለመፍታት አንድም ቀን ተንቀሳቅሰው አያውቁም” – አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ዋና ጽሕፈት ቤት…
ባለፉት አራት ወራት ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ያልተገ ታው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ድጋፍ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በልማት ባንክ የተረጋገጠ በህዳሴው ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ።
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቀላል የማይባል የህዝብ ለህዝብ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠሩ መሆኑንም ነው የታላቁ የህዳሴ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ያስታወቀው።
የጽህፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ከወቅታዊ የህግ ማስከበር ሂደት ጋር በተያያዘ የሚዲያው ትኩረት ቢቀንስም አሁንም ድጋፉ ሳይቋረጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም ከመላ ሀገሪቱ ባለፉት አራት ወራት ብቻ በልማት ባንክ የተረጋገጠ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገብቷል።
እንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ፤ ላለፉት አራት ወራት የነበረው የህዝብ ተሳትፎ እጅጉን ከፍ ያለ ሆኖ ተስተውሏል። ለአብነትም የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተጠናቀቀ በኋላ በሀምሌ ወር 119 ነጥብ 9 ሚሊዮን፣ በነሐሴ ወር 152 ሚሊዮን፣ በመስከረም ወር 197 ሚሊዮን እና በጥቅምት ወር 155 ሚሊዮን ብር የተጣራ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ በዋናነት ቦንድ በመሆኑ ህብረተሰቡ የቦንድ ግዥን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ኃይሉ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያየ መልኩ እያገዙ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም ዲያስፖራው በግድቡ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ የሚሞክሩ ሥራዎችን በመቃወም ከፍ ያለ ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑንም ገልጸዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=37447
www.press.et
ባለፉት አራት ወራት ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የወታደሩ ህይወት - ከመጋረጃው ጀርባ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የሰራዊቱ አኗኗር ከግንባር መልስ በተለይም በእረፍት ሰዓት ላይ አዝናኝ ገጽታ አለው። አንዳንዶች ቢጫ ጀሪካኖችን በመጉረድ የቡና ማቅረቢያ ረከቦት ሲያዘጋጁ ሌሎች ደግሞ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲኮችን በመቁረጥ ቡና እና ሻይ መጠጫዎችን ያዘጋጃሉ።
በየአካባቢው የተገኘው ቡና ተቆልቶ በተከፈተ ጣሳ ላይ ሊወቀጥም ይችላል። ምክንያቱም ጁንታው ቡድን የሰራዊቱን ንብረት ዘርፎ ሲሄድ ያልሰባበረው እና ያላወደመው አይነት እቃ የለም ማለት በሚያስደፍር ሁናቴ በየማዘዣ ጣቢያዎቹ ከኤሌክትሪክ እቃ አንስቶ እስከ ቢሮ መሳሪያዎች ድረስ የነበሩ ንብረቶች ተበላሽተዋል፤ አሊያም ጠፍተዋል።
በሚያሳዝን ሁናቴ የሰራዊት አባላት በገንዘባቸው የገዟቸው አነስተኛ ቡና እና ሻይ ማፍያዎች እንኳን በአካባቢው እንደሌሉ ከጁንታው ጥቃት በኋላ አካባቢውን የተቆጣጠሩ የሰራዊት አባላት ሲናገሩ ይደመጣል።
የሰባተኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክፍለጦር አባል የሆነችው ወታደር እታገኝ ሞላ፣ ሰራዊቱ በእረፍት ሰዓቱ የሚያሳልፍባቸው የካምፕ ውስጥ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች በመውደማቸው ጓደኞቿ ድብርት (ድበታ) እንዳይገባቸው የበኩሏን ጥረት እንደምታደርግ ነገረችን።
ለቀረጻ ሙያው ልዩ ፍቅር ያላት እና በካሜራ ቀረጻ ሙያ ለአንድ ዓመት በሰራዊቱ ያገለገለችው እንስት፤ በህግ ማስከበር ዘመቻ ደግሞ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፋ ተተኳሾችን እና መሳሪያዎችን በማቀበል በኦርዲናንስ ሙያ አገልግላለች።
ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ መልስ በሚኖራት የእረፍት ጊዜ ደግሞ፣ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው አካባቢዎች ሻይ እና ቡና በማፍላት ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ታደርጋለች። በአካባቢዋ የምታገኛቸውን ምግብ ማዘጋጃ ቁሶች በማሰባሰብ አምባሻ በመጋገርም ተወዳጅ ባለሙያ መሆኗን አስመስክራለች።
በተለይ ኮቾሮ ብስኩት በሚበላባቸው አብዛኛው የግንባር ቦታዎች ላይ፣ ስቃጥላ የተሰኘውን የታሸገ የሰራዊቱ ምግብ በልዩ ሁኔታ በማብሰል በፍቃደኝነት ለሰራዊት አባላት ታቀርባለች።
“ይህን ማድረጌ ሰራዊቱ በእረፍት ጊዜው ድብርት ውስጥ እንዳይገባ እና ዘመቻውን ዓላማ እንዳይዘነጋ በማሰቤ ነው” የምትለው ወታደር እታገኝ፤ በማንኛውም ሙያ ላይ በመተጋገዝ ለመስራት መምረጧን ነግራናለች።
ከግዳጅ መልስ በሚኖረው ቆይታ የእታገኝ ቡና እየተፈላ ስለውሏቸው እና ስለጓዶቻቸው ጀግንነት እየተወራ ሳቅ እና ጨዋታው ይደራል። ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትና የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩት የሰራዊት አባላትም አንድነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ የተጋገረውን አምባሻም ሆነ የተፈላውን ቡና አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለው በጋራ በመቋደስ ቀናቸውን በደስታ ያሳልፋሉ።
ሃምሳ አለቃ ሄኖክ ከተማ፣ እንደ ወታደር እታገኝ ሁሉ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው ቦታዎች አምባሻ መጋገሩን እና ቡና ማፍላቱ የሚያዘወትር የአውራምባ ማህበረሰብ የስራ ባህልን የተላበሰ ወታደር መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ።
እሱም ቢሆን፣ በልጅነቱ ቤት ውስጥ እንጀራም ሆነ ሌሎች ስራዎችን በመከወን ወላጆቹን ያግዝ እንደነበር ነው የነገረን። ያ የልጅነት ልምዱ ደግሞ ሰራዊቱ ውስጥም እንዳገዘውና በእረፍት ጊዜው የተለያዩ ደረቅ ምግቦችን እያዘጋጀ ለጓደኞቹ ለማቅረብ እንዳላስቸገረው ገልጾልናል።
https://www.press.et/Ama/?p=37458
www.press.et
የወታደሩ ህይወት – ከመጋረጃው ጀርባ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

ቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ::
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከስፖርት ማህበረሰብ፣ አርቲስቶችና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን ጃንሜዳን የማጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ ከፒያሳ ወደ ጃንሜዳ የተዘዋወረውን የአትክልት መገበያያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ በማንሳት ለጥምቀት በዓልና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይመለሳል ብለዋል።
የአትክልት መገበያያ ስፍራዎችን በሌሎች አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች ከነገ ጀምሮ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ሙሉ በሙሉ ይሸጋገራሉ ብለዋል፡፡
ነጋዴዎች ወደ ጋርመንት በሚዘዋወሩበት ሁኔታዎች ዙሪያ ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎችን ተዘዋውረው አነጋግረዋል፡፡
በቦታው የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት የከተማ አስተደዳሩ ላደረገው ድጋፍ ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት በተዘጋጀው ቦታ ለመዘዋውር ዝግጁ መሆናቸውን የኢስ አበበ ከተማ ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ ነው
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ዳቪድ ስቴንማን ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ሃላፊነት በነበሩበት ወቅት ኢትዮጵያዊያን ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል በሚል የክስ አቤቱታ ማስገባቱን የዘ ታይምስ ዘገባ ያሳያል።
ዶክተር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ አባል የሆኑበት ፓርቲ ለፈጸማቸው የሰዎች መግደል፣ መታሰርና መገረፍ የእርሳቸው ውሳኔ ትልቅ ድርሻ ስለነበረው በዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ ይገባል ብሏል ዳቪድ ስቴንማን ለፍርድቤቱ ባቀረበው አቤቱታ።
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም አባል የሆኑበትና በኢህአዴግ ውስጥ አባል ድርጅት የነበረው ህወሓት በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ በነበረው የበላይነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች የእርሳቸው ውሳኔ ትልቅ ድርሻ ነበረው ብሏል ዳቪድ ስቴንማን።
ዳቪድ ስቴንማን በዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ላይ የዚህ አይነት ክስ በማቅረቡ ከእርሳቸው በተቃራኒ ላሉ ወገኖች ወግኖ ነው የሚሉ ድምጾች እንደሚሰሙ ጠቅሶ፤ “የእኔ ውግንና ለአንድ ነገር ብቻ ነው፤ እሱም ሰላም ነው” ብሏል።

የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሜ/ጄኔራል ከድር አራርሶ ፍርድ ቤት ቀረቡ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ዕዝ ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ።
ተከሳሹ የሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ከተባሉ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች ህገ-መንግስቱን እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል የመናድ ሙከራ በማድረግ እና የሀገር ክህደት ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠርጥረው የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ተጠርጣሪው መንግስት በትግራይ ክልል የነበረ የጦር መሳሪያ ወደ መሃል ሃገር እንዲመጣ ሲፈለግ መሳሪያው ከመቐለ እንዳይወጣ የተቃወሙና ሰዎችን ያደራጁ መሆኑን እና ከቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከነበሩት አቶ አብዲ ኢሌ ጋር በመሆን የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችን እንዳስጨፈጨፉ ማስረጃ እንደለው ፖሊስ አስታውቋል።
መርማሪ ፖሊስ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ባንኮች የገንዘብ ልውጦችን ለማጣራት፣ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ከያሉበት ለመያዝና ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ያላቸውን የወንጀል ግንኙነት በማስረጃ ለመለየት ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ከሰማ በኋላ የተጠርጣሪውን ምላሽ ያዳመጠ ሲሆን፣ ተጠርጣሪው ወንጀሉ ከተፈጸመበት ወቀት አስቀድሞ በሃምሌ 2012 ዓ/ም ጀምሮ ለህክምና ውጭ ሀገር እንደነበሩና የቀረበላቸውን ክስ የማይቀበሉት እንደሆነና የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና መብት ውድቅ አድርጎ ተጠርጣሪው ከተጠረጠሩበት ወንጀል አንጻር መረጃ ሊያጠፋ ይችላል ብሎ ስላመነ መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ስምንቱን ቀን በመፍቀድ ለታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ/ም መርማሪ ፖሊስ መረጃውን አጠናክሮ እንዲመጣ ችሎቱ ማዘዙን ከፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።