የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ያወጣውንና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አጽድቆታል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመረመረ በኋላ ተቀብሎ አጽድቆታል።
ምክር ቤቱ በዚሁ ስብሰባው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትንም ሰይሟል።
በዚህም መሰረት፤
1. አቶ ለማ ተሰማ - ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ጀምበርነሽ ክንፈ
3. ወ/ሮ ሃዋ አሊ
4. አቶ አለባቸው ላቀው
5. አቶ ዘርይሁን ጴጥሮስ
6. ወ/ሮ አስካለ ጥላሁን
7. አቶ ወንድሙ ግዛው
የመርማሪ ቦርዱ አባላት ሆነው በምክር ቤቱ ተሰይመዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም

ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት የተነሳ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን አማጺ ቡድን ሲሉ ገልጸውታል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት የፌዴራል መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን ተከትሎ ሁነቱን ለመዘገብ ዜናዎችን የሰሩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ህወሓትን "አማጺ ቡድን” ሲሉ ገልጸውታል።
ጦርነቱን በማስመልከት ዘገባ ከሰሩ የመገናኛ ብዙሃን መካከል አንዱ የሆነው አልጀዚራ ህወሓትን “አማጺ ቡድን” ሲል በዘገባው ጠርቶታል።
አልጀዚራ በዚሁ ዘገባው አማጺ ቡድኑ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ራሱ በማምረት ለራሱ ታጣቂዎች አልብሶ “የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ላይ ወረራ ፈጸሙ” የሚል ክስ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠቅሶ አስታውቋል።
ህወሓት የትግራይን ህዝብ ከ20 አመታት በላይ ሲጠብቅ በኖረው የሰሜን እዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት የተነሳ መንግስት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር ሲል ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን የኢፌደሪ ጠቅለዓይ ሚኒስት ዶ/ር አብይ አህመድ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
በተመሳሳይም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፒዮ በትዊተር ገጻቸው፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል ሲሉ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ላይ መናገራቸው ይታወሳል።

በነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የግብይት ሠዓት ገደብ ተቀመጠ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በምርቶች ላይ ሊከሠቱ የሚችሉ ሠው ሠራሽ የሆኑና ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር እና ያለአግባብ የምርት ክምችት በመፍጠር እጥረቶች እንዳይፈጠሩ ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ ስራዎች እየትፕሠሩ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የኮመኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደተናገሩት፤ የነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይትን በጥብቅ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጀምሮ የሰአት ገደብ ተቀምጧል።
በዚህም መሰረት በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጥቅምት 27 ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በሁሉም የክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሠሩ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።

የሀገር ሽማግሌዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የሀገር ክህደት መሆኑን አስታወቁ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አባባ ፦ በህወሓት ውስጥ ያለ ከሀዲ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሰነዘረው ጥቃት መቼም ታሪክ የማይረሳው የሀገር ክህደት መሆኑን የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች አስታወቁ ።
የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥኝ እንደዘገበው ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይ ዙሪያ ከክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የሀገር ሽማግሌዎች በህወሓት ውስጥ ያለ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሰነዘረው ጥቃት መቼም ታሪክ የማይረሳው የሀገር ክህደት መሆኑን አስታውቀዋል። መንግሥት በአጥፊው ቡድን ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንደሚደግፉት ገልጸዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ ከመንግሥት ጎን ሆነው የሀገርና የክልሉን ሰላም አጠናክረው ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት በክልሉና በሀገሪቱ ህዝብ ላይ ሲያደርሰው ከነበረው አስከፊ ጉዳት ባለፉት ሦስት ዓመታት በሀገሪቱ የተረጋገጠውን ለውጥ ለማደናቀፍ በተለያየ የጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ ተናግረዋል።
መንግሥት የአጥፊዎችን እኩይ ሴራ በሆደ ሰፊነት ሲያልፍ መቆየቱን የጠቆሙት አፈጉባኤው፣ ህወሓት ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አመልክተዋል ። በዚህም መንግሥት በቡድኑ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደደ አስታውቀዋል።
መላው የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በመገንዘብ መንግሥት እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንዲደግፉና የሀገሪቱን እና የክልሉን ሰላም ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በውይይቱ ላይ ወቅቱ የክልሉ ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር፤ በክልሉ ከሚኖሩና ከክልሉ አዋሳኝ ክልል ህዝቦች ጋር ሰላማዊ አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።
የክልሉንና የሀገሪቱን ሰላም ማረጋገጥ የሚሰራበት ወቅት በመሆኑ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያጎለብቱ ጠይቀዋል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ መስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 28/2013

“በሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የክህደትና የባንዳነት መገለጫ ነው”
ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት
****************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት ፍጹም ከወገን የማይጠበቅ የሀገር ክህደትና የባንዳነት መገለጫ መሆኑን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን አስታወቁ።
የማበህሩ ሊቀመንበር ልጅ ዳንኤል በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የሀገሩንና የወገኑን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በርካታ ዓመታት ከቤተሰቦቹ ተለይቶ በግዳጅ ላይ ባለ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የጭካኔ፣ የሀገር ክህደትና የባንዳነት መገለጫ ነው። እንዲህ አይነቱ ወራዳ ተግባር በየትኛውም የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪና አስተዛዛቢ ነው ።
“ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የውጭ ሓይሎችን ጥቃት ለመመከት አቅሟንና አንድነቷን ማጠናከር በሚገባት በዚህ ሰዓት ከአብራኳ የወጡ ልጆቿ በራሳቸው ጠባቂዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ከማን ጋር እንደቆሙ የሚያሳይ ነው ። ይህ ጸያፍ ተግባር የሀገርን ክብር ያዋረደ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነና የጥቂት ቡድኖችን ማንነት በግልጽ ያሳየ ነው “ብለዋል ።
ሀገሪቱ በኮቪድ 19 ፤ በአንበጣ ወረርሽኝ፣ በህዳሴው ግድብ ሽኩቻ፣ በጎርፍ ተፈናቃዮች እና በውስጥ አለመረጋጋት ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ወቅት እንደገና ሌላ ችግር መፍጠር ሆን ብሎ ሀገሪቱን ለማፈራረስ የታሰበ ደባ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሰው ህይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወድም በትዕግስት ያሳለፈው ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በማሰብ እንደሆነ የዓርበኞች ማህበር ያምናል። ጥቂት የህወሓት አመራሮች ክብሪትና ነዳጅ አስይዘው በየቦታው በሚያስነሱት እሳት ዜጎች ሲሰቃዩ እንደነበር መታዘባቸውንም ገልጸዋል።
ዓርበኞች ከአባቶቻቸው የተረከቧትን ሀገር የውጭ ወራሪዎችን እየመከቱ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ አቆይተዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በዓርበኞች አጥንትና ደም የተሰራች ሀገር በባንዳዎች አትፈርስም ብለዋል። አባቶቻችን ከኢጣሊያን ፋሺስት ጋር በተፋለሙበትና የዓድዋን አኩሪ ድል ባጣጣሙበት ስፍራ እንዲህ ያለ ጸያፍ ተግባር መፈጸሙ የዓርበኞችን ማህበር እንዳስከፋም አመልክተዋል ።
ከተልእኮው ባሻገር የአርሶ አደሩን ምርት በመሰብሰብና የአንበጣ ወረርሽኝን በመከላከል ከህዝብ ጎን የቆመን ሠራዊት ማጥቃት ህዝብን ማጥፍት፤ ሀገርንም መካድ እንደሆነ ተናግረዋል። የአርበኞች ማህበር በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ እንደሚያወግዘው ገልጸዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ ህገመንግሥትን ማስከበርና የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር እንጂ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ታዛዥ መሆን አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፣መንግሥት ተገዶ ወደ ጦርነት የገባው የተቃጣበትን ጥቃት በመቀልበስ ህግና ስርዓትን ለማስከበር ነው ብለዋል። በመሆኑ የዓርበኞች ማህበር ሠራዊቱ እየወሰደ ያለውን ርምጃ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ በዲሲፒሊን የታነጸ፤ ከሀገሩ አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም መከታ የሆነ የኢትዮጵያን ስም ያስጠራ መሆኑን በመጥቀስ ፣የሀገር ኩራት የሆነን ሠራዊት ማክበርና መንከባከብ ሲገባ በራሱ ወገን ቃታ ሲሳብበት መስማታችን አሳፍሮናል ብለዋል።
በጥቂት የህወሓት አመራሮች ስብከት ተታለውና ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ሓይል አባላት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን በመስጠት ሀገሪቱን ከጥፋት እንዲታደጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የትግራይ ህዝብ ጥቅማቸው የተነካባቸው ጥቂት የህወሓት አመራሮች በሚነዱት መንገድ መሄድ እንደሌለበትና ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመቆም ሰላሙን አረጋግጦ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ጋር በፍቅር መኖር ይገባዋል ብለዋል።
መንግሥት እየወሰደ ባለው ወታደራዊ ርምጃ ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ህዝቡም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ይዞ ከመንግሥትና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፈዋል።

“የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ተሳክቷል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
. በአጭር ጊዜ ይህን ስግብግብ ጁንታ በማስወገድ ለትግራይ ህዝብ፣ ለአገር መከላከያ እና ፖሊስ ሠራዊታችን እፎይታና ሰላም በመስጠት በፍጥነት ሰብል ወደ መሰብሰብ ለመመለስ እቅድ አዘጋጅተናል
******************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- የመጀመሪያው ዙር ኦፐሬሽን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ መሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። በፍቅረ ንዋይና ስልጣን ታውሮ ለአገርና ህዝብ ደህንነት ደንታ የሌለው በህወሓት ውስጥ የመሸገው ስግብግቡ ጁንታ ሓይል ባለፉት ሁለት ቀናት በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በኢፌዲሪ የፖሊስ ሠራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በዚህ የጠላት ኃይል ላይ በተወሰደ እርምጃ ጉዞውን ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ መቻሉን አመለከቱ ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ የተወሰደውን ኦፕሬሽንና የተገኘውን ድል አስመልክተው ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ በመከላከያ ሓይላችንና በፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት ላይ ጭምር ጥቃት በመፈጸም በፍቅረ ነዋይና ስልጣን ታውሮ ለአገርና ህዝብ ደህንነት ደንታ እንደሌለው ባሳየው በህወሓት ውስጥ የመሸገው ጁንታ የጠላት ቡድን ላይ በተወሰደ የመጀመሪያ ዙር እርምጃ የቡድኑን ጉዞ ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች ተቀምጠው የተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የመጀመሪያው ዓላማ ጥቃቱን መግታት እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ጠላት በሁሉም ግንባር በፈለገው አቅጣጫ ጥቃት እየሰነዘረ በህዝባችን፣ በሠራዊታችን፣ በፖሊስ ሰራዊታችን እንዲሁምበአንዳንድ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት መግታት እንደነበር አስታውቀዋል።
ከዚህ አንጻር ጠላት ጥቃት የሚሰነዝርባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ኃይል በስፋት ያልነበረ ቢሆንም፤ ከያለበት ኃይላችንን በማንቀሳቀስ ሙሉ የሎጀስቲክስና የሰው ኃይል አቅርቦት የጨረስን ሲሆን፤ የጠላትንም ጉዞ ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ላይም ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ፣ ሁለተኛው ዓላማ፣ የመከላከያ ኃይላችን እና የፖሊስ ሰራዊት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ይሄንን ኃይል የመታደግ ወሳኝ አገራዊ ሓብቶችና ትጥቆች የመታደግ ስራ ነበር። ከዚህ አንጻር በባድመ ግንባር፣ በጾረና፣ በዛላንበሳን በመሳሰሉ በዋና ዋና ቦታ ተሰልፈው ያሉ የሠራዊት አባላት እና ትጥቆቻቸው ሙሉ በሙሉ ከጠላት ፍላጎት ውጪ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል።
በተለይ ጠላት ፊቱን አዙሮ ከውጭ በሚመጣ ሓይል በመከላከል ላይ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሓይሉን አጠናክሮ፣ አሰላለፉን ቀይሮ፣ ፊቱን አዙሮ ማንኛውም ጥቃት ለመሰንዘር ወይም ለመከላከል በሚያስችል ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥቃት ይደርስበታል የሚል ስጋት እንዳይኖር ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ሦስተኛው ዓላማ፣ የጠላት የማድረግ አቅምን ማዳከም ነው። የጠላት ሓይል የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሓብት ላይ ቀንሶ አገሩን ለመከላከል የገዛቸውን ዋና ዋና ትጥቆች፣ ሚሳዬሎች፣ ሮኬቶች በመጠቀም ጥፋት ማካሄድ እንዳይችል አቅሙን ማዳከም ነበር። እነዚህ ሦስት ዓላማዎች ሙሉ በሙሉ መሳካታቸውን አስታውቀዋል ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ወሳኝ የሚባሉ አካባቢዎች በተለይ በዳንሻ ግንባር ያለውን ጠላት ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ አከባቢውን የተቆጣጠርን ሲሆን፤ እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሁሉም አቅጣጫ የሚቀጥለውን እርምጃ እየወሰን ለህዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል። እስካሁን ባለው ሁኔታ የመጀመሪያው እቅድ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የተሳካ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፤ ሲሉ ስለ ሁኔታው አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የሚሰሩ ስራዎች የውጊያ ባህሪ፣ የግጭት ባህሪ ሁሉን ነገር በወቅቱ መናገር የሚያስቸግር ቢሆንም፤ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝባችን እየሰጠን ህግ የማስከበሩን ስራ፣ የህዝቦቻችንን ሰላም የአገራችንን ደህንነት የመከላከያ ሃይላችንን ጥንካሬና ብቃት በሚያጠናክሩ ስራዎች የምንቀጥል ሲሆን፤ ይህ ስግብግብ ጁንታ ሙሉ በሙሉ ለህግ እስከሚቀርብ፤ የጀመርነው ራስንና አገርን የመከላከል ዘመቻ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።
ከዚህ ቀጥሎ በሚደረጉ፣ በቀጣዩ እቅዳችን ላይ በሚሰሩ ስራዎች አስፈላጊ የሚባሉ መረጃዎች በየወቅቱ የምንገልጽላችሁ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄን ስግብግብ ጁንታ በማስወገድ ለትግራይ ህዝብ፣ ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ እንዲሁም ለፖሊስ ሠራዊታችን እፎይታና ሰላም በመስጠት በፍጥነት የእርሻ ስራችንን ወደ መሰብሰብ ለመመለስ የሚያስችል እቅድ ያዘጋጀን ሲሆን፤ ሙሉ ኦፕሬሽኑን ስናጠናቅቅ ለህዝባችን ዝርዝር የስራ አፈጻጸሙን የሚገልጹ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ጆ ባይደን አሸነፉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከሚያስፈልገው 270 ኤሌክቶራል ድምጽ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድርስ 284 በማግኘት ጆ ባይደን ማሸነፋቸው ተረጋግጧል።
ባይደን ከአራት ቀናት በኋላ ነው ዶናልድ ትራምፕን በመብለጥ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገው፡፡
ዲሞክራቶችን የወከሉት ጆ ባይደን በቀጣይ ለአራት አመታት አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊዎቹ ለጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በቅርበት እንደምትሰራ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የውጭ ምንዛሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲያሸሹ በነበሩ የሕወሓት ጁንታ አባላት ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞቹን እየያዘ መሆኑን መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግሥት የውጭ ምንዛሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲያሸሹ በነበሩ የሕወሓት ጁንታ አባላት ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞቹን እየያዘ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡
"ስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ ነው የኖረው፤ የዘረፈውን ገንዘብ ለማሸሽ እንዲችል የውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መንገዶችን ይጠቀማል፤ ኢትዮጵያውያን የሚልኩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ ባሉበት ሀገር በመቀበል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘረፈው ገንዘብ ከገበያው በላይ ይከፍላል፤ የውጭ ምንዛሬውንም ወደ ተለያዩ ሀገሮች ያሸሻል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
"መንግሥት ክትትል አድርጎ ወንጀለኞቹን እየያዘ ነው። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይሄንን ጁንታ ሳያውቁት ከማገዝና ሀገራቸውን ከመጉዳት እንዲቆጠቡ፣ ወንጀለኞችንም እንዲያጋልጡ፣ ገንዘባቸውን በባንክ በመላክ ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ የወጡ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው
*************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከተማ ንጉስ፡- በምዕራብ ትግራይ የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣቸው ደስተቸውን ገለጹ።
በትግራይ ክልል ከተማ ንጉስ የተገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ከከሀዲው ቡድን ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸውን መግለጻቸውንና የመከላከያ ሰራዊቱን በደስታ መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን የፌዴራል መንግስት ሊወረን ነው፣ የትግራይን ህዝብ በሀይል ሊያበረክክ ነው ሲል ቆይቶ ራሱ ቀድሞ በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ የሚወገዝ ተግባር ነው የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች፤ ይህ የሚሳየው ከላይ ያለው የህወኃት ቡድን ለራሱ ጥቅም እንጂ ለህዝብ ደንታ እንደሌላው ነው ብለዋል፡፡
የጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ አቶ ስምረት አቦይ እንደገለጹት፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን አፋኝና ለህዝብ ደንታ የሌለው ነው፡፡ ቡድኑ ለትግራይ ህዝብ እኛ ጦርነት አንገጥምም ራሳችን ብቻ የምንከላካለው እያለ ሲያታልል ቆይቶ ቀድሞ ራሱ በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተው ጥቃት የምናወግዘው ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከጦርነት የሚያተርፈው ነገር የለም ያሉት አቶ ስምረት ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለህዝቡ የሚነግረውና የሚፈጸመው ተግባር ለየቅል ነው ያሉት አቶ ስምረት፤ ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሳ የሚያሰር፣ የሚያገላታ፣ ጫናና አፈና የሚፈጸም በመሆኑ ከዚህ አፈና በአገር መከላከያና በአማራ ልዩ ሀይል ነጻ መውጣታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣን ደስተኞች ነን ያለችው በጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ ወጣት ከተማ ከፍያለው፤ ይህን ደስታችንንም ሰልፍ በመውጣት ጭምር አረጋግጠናል፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በነሱ ተላላኪ ሰዎች አማካኝነትም ህዝቡ እርስ በእርሱ በጥርጣሬና በአይነ ቁራኛ እንዲተያይ፣ የፈለገውን ሀሳብ እንዳይገልጸ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጻለች፡፡
“ህወሓት የፈለግነውን ሙዚቃ እንኳን እንዳንሰማ ያደርግ ነበር፤ የመብት ጥያቄዎችን ስናነሳ ሲያስረንና ሲያንገላታን ነበር ያለቸው ወጣቷ፤ የመከለከያ ሰራዊት ጸገዴ ወረዳን መቆጣጠሩ ነዋሪው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ተናግራለች፡፡
አሁን ከተማ ንጉስ ከተማ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑንና ህዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ታዝቧል።
በጌትነት ምህረቴ

የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በጀኔራሉ አንደበት
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ፡፡መስታወታቸው ረግፏል፤ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም።የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል፡፡የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል፡፡
ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣አሳዛኝ፣አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው፡፡በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም።በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡
በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱን እንደሚፈልጉትና እንዲጠራላችሁ የበር ጥበቃዎችን ይጠይቃሉ።ጀኔራሉም እንደማይመጡ ሲነገራቸው ተመልሰው ይሄዱና ተጨማሪ
ሀይል ይዘው መጥተው በካምፑ ላይ የጥይት መአት ማውረድ ይጀምራሉ፡፡ውስጥ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በጽናት የመመከት ስራ ውስጥ ገቡ፤ለሶስት ቀንና ሌሊት በጽናት ታገሉ፡፡
አንድ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሰራተኛ ወደ ጀነራሉ ጆሮ ተጠግቶ አካባቢውን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ከቦታል፡፡ፍላጎት ካለህ ሽማግሌዎቹ ከአካባቢው እናስወጣው ብለው ነግረውኛል፤ ውሳኔህ ምንድነው ሲል ጠየቀኝ ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ፣ የእነሱ ፍላጎት እኔም ወኔዬን ተሰልቤ የሲቪል ልብስ ለብሼ ተደብቄ ወደ አማራ ክልል እንድወጣ አልያም እኔን አታለው እንድያዝ በማድረግ ካምፕ ውስጥና በአቅራቢያው ባለው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ለመሰንዘር ያቀዱትን ጥቃት የመከላከልና የመመከት ስራ ለማሰናከል ነው፡፡በዚህም በቀላሉ ሰራዊቱንና መሳሪያውን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስበው መሆኑን ገለጹልን፡፡
እኔም ምላሼ ሽምግልናውን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን የመረጃ ሰራተኛው ከሽማግሌዎቹ ጋር ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ መገናኘት እንደሌለበት አስጠንቅቄ ነገርኩት ።አሁን ይህን ያለኝ ልጅ ቆስሎ ለህክምና ወደ ጎንደር ሄዷል።ሲመጣ ጠይቄ ዓላማቸው ምን እንደነበር የምረዳው ይሆናል፡፡ተመትቶ ስለነበረ እኔም እንዳልሞት አስቦ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ብለውናል።
የሶስት ቀን ከበባው በጣም አስቸጋሪ ነበር።24 ሰዓት ተኩስ ነው፡፡ያጠቃሉ እኛ እንከላከላለን፤ይሄዱና ምግብ በልተው ሀይል ጨምረው ያጠቃሉ፤ሲታኩሱ የነበሩት ልዩ ሀይሎች ወደ ካምፓቸው ሄደው አርፈውና ጥይት ጭነው ይመጣሉ፡፡እኛ ካለንበት ቦታ ውጭ መፈናፈኛ ስፍራ የለንም፡፡እንደ ቀለበት ዙሪያውን ከበውና ውሃ ፣ምግብ፣ጥይት የለም፡፡ያለችንን ነው በቁጠባ የምንጠቀመው ሲሉ ያብራሩት ጀነራሉ፣እኔም አልፎ አልፎ እንደ ምሽግ ከተጠቀምኩበት ግንብ ቤት እየወጣሁ ለወታደሮቼ ጥይት በቁጠባ ተጠቀሙ እያልኩ አሳስብ ነበር ሲሉ ይገልጻሉ፡፡እነሱም አላሳፈሩኝም በጽናት ተዋደቁ።የሰራዊታችን በጽናት የመከላከል ሞራል የሚገርም፣ የሚደነቅና ታምር የሚያስብል ነው ይላሉ፡፡
አርቢጂ፣ቦንብ፣መትረየስ ፤ክላሽ እንደ ዝናብ ቢያርከፈክፉብንም ለሶስት ቀናት ቀንና ሌሊት መክተናል፡፡በፍጹም እንተርፋለን ብለን አላሰብነም ፤ከቻልን እስከ መጨረሻው እንከላከላለን ፤ካልቻልን ደግሞ በመጨረሻ ላይ ራሳችንን እናጠፋለን የሚል አቋም ነበርን፡፡ግን በእግዜአብሄር ቸርነት፤በመከላከያ ሰራዊት ፈጥኖ ደራሽነት ቀለበቱ ተሰብሮ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል ብለውናል፡፡ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም፡፡
ድርጊቱ የሚያሳዝን ነው፤ በህወሓት ከሀዲ ቡድን እንዲህ አይነት ጥቃት ይፈጸምብናል ብለን አስበን፤አልምንም አናውቅም የሚሉት በሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ፤ ምክንያቱም ከኢትዮ-ኢርትራ ጦርነት ጀምሮ ትግራይ መሬት ነው እየኖርን ያለው።ህዝቡን መሪዎቹንም በደንብ እናውቃቸዋለን ብለዋል፡፡
“አብረህ እየበላህ እየጠጣህ፣ተዋልደህ ተጋምደህ፤ ትዳር መስርተህ ፣ልጆች ወልደህ፤ቤተሰብ ሆነህ በፍጹም ጥቃት ሊሰነዝርብኝ ይችላሉ ብለህ አታስብም፤ሆኖም ያልታሰበው ተፈጸመ፤ያልተጠበቀው ሆነ “ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል።
ኩርፊያና የተለያዩ መገለጫዎች ይታያሉ ፡፡ይህን ተከትሎ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ደፍረው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ገብተው ያጠቃሉ ብለን አላሰብንም።ምክንያቱም ወንድምህ ሊያኮርፍ ይችላል እንጂ ያጠቃኛል፤ይገለኛል ብለህ ፈጸሞ አትገምትም የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤ግን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ዕለተ ማክሰኞ 25ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ያለምንም ርህራሄ ዙሪያውን እንደ ቀለበት ከበውን አጠቁን ፣አጠቁን እኛም በጽናት ተከላከልን፤መከትን ብለዋል፡፡
የህወሓት ቡድን ዓላማ የመከላከያ ሰራዊትን መድፎች፣ ታንኮች፣ብረት ለበሶችን መንጠቅና መከላከያን ማፍረስ ነው፡፡ በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም ፤በራሳችን መሳሪያ ተመልሰው እኛን ለመውጋት ነበር ዕቅዳቸው፡፡ይህ አልተሳካላቸውም፡፡እኛም በያለንበት በጽናት ተዋግተን መክተናል፡፡አሁን እነሱ ባሰቡት ሳይሆን እኛ ባሰብነው መንገድ እየሄደ ነው፡፡በአጭር ጊዜ ውስጥ ጦርነቱ ይቋጫል ብለን እናስባለን ሲሉ ገልጸውልናል።
ብረጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንድ የሚገርማቸው የሚደንቃቸው ነገር አለ፡፡”እኔ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊና ተራ ጄነራል ነኝ፣በአንድ ክላሽ ጥይት ግፋ ቢል ደግሞ በስናይፐር መግደል ይችላሉ፤ ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ አርቢጂ ነው የተኮሱብን ።አርቢጂ የሚባለው መሳሪያ ደግሞ ለታንክ ወይም ለጠንካራ ምሽግ ነው የሚተኮሰው፤የእኔን ቤት ለማፍረስ ግን አርቢጂ ነው የተኮሱት ሲሉ የከሀዲው ቡድን የጭካኔ ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡
እኔ ብሞትም ቤቱ የእነሱና የህዝቡ ንብረት ነው። ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ጸጥታ ለቆምኩ፣ለአገር ሉዋላዊነትና ለህዝብ ሰላም ውድ ህይወቴን ለመስጠት በተሰለፍኩ የክህደታቸው፣የክፋታቸው ጥልቀት እኔን በአርቢጂና በቦንብ ነው ያጠቁት ሲሉ የድርጊቱን ክፋት ገልጸውታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር አብሮ እየኖረ ያለ፣ለህዝቡ የልማት ስራዎች ወደ ኋላ የማይል፣ በማህበራዊ ድጋፎች የሚሳተፍ፣ ሁልጊዜ በየዓመቱ ለአቅመ ደካሞች የሚያርስ፣የሚያርም፣የሚያጭድና አንበጣ የሚከላከል ነው። በትምህርት ቤቶች፣በጤና ጣቢያዎች፣በመንገድ ግንባታዎች በሚሳተፍ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸም የህወሓት ቡድን እወክለዋለሁ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ይላሉ፡፡
የአገሩን ዳር ድንበር የሚጠብቀውን፤የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ስብስብ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ለማውድምና ለማጥፋት ነው ጥቃቱን የሰነዘሩት ፡፡እነዚህ ሰዎች ከዚህ በኋላ ስለኢትዮጵያዊነት፣ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቢሰብኩ፣ቢለፈልፉ፣ቢቀሰቅሱ ማን ጀሮ ይሰጣቸዋል ፡፡ምክንያቱም ጥቃቱን በጽናት ለመመከት የተዋደቁት ከኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተወጣጡ ወታደሮች ናቸው ብለዋል፡፡

ጀኔራሉ በ1980ዓ.ም በወቅቱ ኢህዲን ተብሎ የሚጠራውን ትግል የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ከዚሁ ዓመት ጀምሮ ደርግ እስኪደመሰስ ድረስ በተደረጉ ውጊያዎች ተሳትፈዋል።ቆቦ አካባቢ በተካሄደው ሰላም በትግል ኦፕሬሽን፤ሰሜን ሸዋ መራኛ፣ ጁሁርና መራቤቴ አውድ ውጊያዎች ተሳትፈዋል፡፡በጎጃም ደጀን፣አምቦ፣ነቀምት፣ጅማ፣ቡሌሆራ(አገረ ማርያም) ሞያሌ ድረስ በዘለቀው አውድ ውጊያ ተሳትፈዋል፡፡በሀረርም ጸረ ሰላም ሀይሎችን በመከላከልና በማጥቃት ዘመቻ ተሳትፈዋል፡፡በሩዋንዳ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በ1986ዓ.ም ግድጃቸውን በስኬት አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲቋቋምም 20ኛ ክፍለ ጦር መድፈኛ ብርጌድ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡በኢትዮ-ኢርትራ ጦርነትም ትምህርታቸውን አቋርጠው በመሄድ ብርጌድ አዛዥ በመሆን በጾረና፣በባድመ፣በሽራሮ አዲኋላ ግንባር ተሳትፈዋል፡፡
አሁንም በዳንሻ ከተማ በትግራይ ልዩ ሀይል የተካሄደውን ከበባና ሶስት ቀናት የዘለቀ ጥቃት ወስን ወታደሮችን መርተውና አዋግተው በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ዕገዛ መከላከሉን በድል አጠናቀው የማጥቃቱን ተልዕኮ በድል እየተወጡ ይገኛሉ።
አዲስ ዘመን ህዳር 1/2013

የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራን በድሮን ቴክኖሎጂ ለመደገፍ የእስራኤል መንግስት የባለሙያዎች ስልጠና እና 27 ድሮኖችን ድጋፍ አደረገ
************************************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራን በድሮን ቴክኖሎጂ ለመደገፍ የእስራኤል መንግስት የባለሙያዎች ስልጠናና 27 ድሮኖች ድጋፍ ማድረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ድጋፍ በተደረገበት ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን እንደገለጹት፤ የበረሃ አንበጣውን ለመከላከል የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛል። የእስራኤል መንግስትም ከዚህ በፊት በገቡት ቃል መሰረት በተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ መከላከል የሚያስችሉ ድሮኖችን ድጋፍ አድርጓል።
እነዚህን ድሮኖች በመጠቀም በሌሊት ርጭት በማድረግ የመከላከል ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ በድሮኖቹ በመታገዝም የዳሰሳ ጥናት በማድረግ መረጃዎችን በመሰብሰብ ውጤታማ የመከላከል ስራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራፍ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል በድሮኖችን የታገዘ መረጃ የመሰብስብና በሌሊት ርጭት በማካሄድ የመከላከል ስራ መስራት ያስችላል ብለዋል፡፡
የእስራኤል ሉኡካን ቡድንም በሱማሌ ክልል በመገኘት ስልጠናውን ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ ለባለሙያዎች ከሰጡ በኋላ 27 ድሮኖችንና ሁለት ጀኔሬተሮችን ለስራዉ ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራውን በአግባቡ ለመተግበር እንዲያስችል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናው በሀገራችን የሚገኙ ባለሙያዎችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ብቁ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‹‹የጁንታው ፀሐይ እየጠለቀች ነው›፤ ይሄን መርዶ ጁንታው በቁሙ ተረድቶታል›› ብለዋል።
‹‹ጁንታው አሁን የሚይዘውን የሚጨብጠውን የሚያጣበት ጊዜ ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ‹‹በመሆኑም በጣዕር መንፈስ በየቦታው የመጨረሻውን የጥፋት ድግስ ይደግስ ይሆናል›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በመሆኑም ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖች በየአካባቢው ምንም ዓይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይደርስባቸው ሁሉም የወንድሞቹ ጠባቂ እንዲሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
‹‹የኢትዮጵያ ጠላት ስግብግቡ ጁንታ ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው ሕዝብ በጁንታው መከራ ያየ ሕዝብ መሆኑን አስታውሰዋል።
‹‹ጁንታው ለፍርድ እንዲቀርብ የትግራይ ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋጋ ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ሕዝቡ አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ቀንበር እሰብራለሁ፤ ጁንታውን ለፍርድ አቀርባለሁ›› ቃል ኪዳኑ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ጎንደር፡- ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም ገለፁ። ስራዊቱ ዳንሻ፣ ትርካን፣ ዲቪዥን፣ ባእኸር፣ ራውያንን እና ሁመራን መቆጣጠሩንም አስታወቁ ።
ሜጀር ጄኔራል በላይ በስፍራው ለሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኛ እንዳስታወቁት ፤ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል በምዕራብ ትግራይ ግንባር ትናንት በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ 550 የህወሓት ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል። 29 የልዩ ሃይል እና ሚሊሻ አባላትም እጃቸውን ሰጥተዋል።
ሰራዊቱ ባካሄደው ህግን የማስከበር ኦፕሬሽን በፅንፈኛው የህወሓት ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን አመልክተው፣ 115 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 11 መትረየስ፣ 2 ድሽቃ፣ 8 አር ፒጂ ከባድ መሳሪያ፣ 152 የእጅ ቦንብ፣ 2 ስናይፐር፣ 4 ኤም-14 ጦር መሳሪያ፣ 2 ኢንኮም ሬድዮ መማረኩን አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 21ሺህ 650 የክላሽ ጥይት፣ 14ሺህ 730 የመትረየስ ጥይት 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 64 የጦር ሜዳ ቀበቶ፤ 6 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ፣ 90 የክላሽ መጋዘን እና 10 የመትረየስ ዝናር መማረኩን አመልክተዋል።
በምዕራብ ትግራይ ግንባር እየተከናወነ ያለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ሰራዊቱ ዳንሻ፣ ትርካን፣ ዲቪዥን፣ ባእኸር፣ ራውያንን እና ሁመራን መቆጣጠሩንም ተናግረዋል። የሰራዊቱ ተልዕኮን የመፈፀም ብቃት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
አዲስ ዘመን ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም

ከሀዲው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ለማውገዝና እየፈጸመው ያለውን ግፍ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ በአዲስ አበባ፣ በአማራና በኦሮሚያ ከተሞች ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገለጸ
****************************
(ኢ ፕ ድ)
መቀሌ የመሸገው የህወሀሓት ከሀዲና ዘራፊ ቡድን በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ለማውገዝና ቡድኑ በንጹሀን ዜጎች ላይ እየፈጸመው ያለውን የጅምላ ግድያ ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
በከተሞቹ የሚካሄዱት ሰልፎች፤ የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ክህደትና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለማውገዝና በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ሃይል እየተወሰደ ያለወን ህግ የማስከበር እርምጃ የመደገፍ ዓላማ እንዳለው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ አንቺነሽ ተስፋዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የመከላከያ ሠራዊቱ የጽንፈኛው የህወሓት ቡድንን ወደ ህግ ለማምጣት እያደረገ ባለው ጥረት ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን የሚገልጹበትን የድጋፍ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ በመቀበሉን ተናግረዋል።
ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የደም ልገሳ መርሃግብር ደማችን ለወገናችን እና ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን በሚሉ እንደሚካሄድ ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን መሆናቸውን ለመግለጽ ሠላማዊ ሰልፍ የሚደረግ ሲሆን በሰልፉም የፀጥታ ችግሮች እንዳይፈጠር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በተገበው መንገድ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት ስራ መደረጉን አንቺነሽ አመልክተዋል።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ለማሳየት እንዲሁም ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ላሉ ሚሊሻዎች በገንዘብ እና ቁሳቁስ እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይም የኦሮሚያ ዞኖች፣ ከተሞች እና ወረዳዎችም ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ በርካታ ጥያቄዎች በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፎቹ ከነገ ህዳር 3 ቀን 2013 ጀምሮ እንዲደረጉ መፈቀዱን አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
እንደገለጹት፤ ህዝቡ ከሀዲው የህወሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን ግፍ በአደባባይ ለመቃወም በተለያየ መንገድ ጥያቄውን ሲያቀርብ ቆይቷል።
የሰልፉ ዓላማ ህገ ወጡ የትህነግ መንግሥት እየፈጸመው ያለውን ግፍና በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ያደረሰውን ክህደት ለመላው ዓለም ለማሳወቅ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ሰልፉ የሚካሄደውም በባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ባሉ የክልሉ ከተሞች ሰልፉ የማይካሄደው ከሀዲውን ቡድን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረገው ውጊያ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ አንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል በጋራ እያደረጉት ባለው ህግን የማስከበር ስራ የከሀዲው የህወሓት ቡድን ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት አካባቢው ጥሎ እየሸሸ ሲሆን፤ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊቱን የማይካንድራ ከተማን ለቅቆ ከመሸሹ በፊት በርካታ ንጹሀንን ጨፍጭፎ መውጣቱ ይታወሳል።

ተሸናፊው የህወሓት ከሀዲ ቡድን በማይካድራ ከተማ የፈጸመው ጭፍጨፋ ዋና ዓላማ በህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማሰብ ነው ሲል የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ
**********************
(ኢ.ፕ.ድ)
ተሸናፊው የህወሓት ከሀዲ ቡድን በማይካድራ ከተማ ነዋሪ በሆኑ የአማራ ተወላጆች ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ ዋና ዓላማ በህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማሰብ ነው ሲል የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።
“እየሞትንም ቢሆን እናሸንፋለን” በሚል ርዕስ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ “ወገኖቻችን ላይ በተሸናፊው የትህነግ ጦር አማካኝነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል” ያለው ፓርቲው፤ ድርጊቱ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው ሲል አስታውቋል።
“ተሸናፊው ትህነግ በወገኖቻችን ላይ ይሄን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው በህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት (Civil War) እንዲቀሰቀስ አስቦ መሆኑን እናውቃለን” ያለው ፓርቲው፤ ለአማራ ህዝብ ባቀረበው ጥሪም፤ “በተለመደው አስተዋይ ባህሪህ ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከየትኛውም ጥቃት ጥላ ከለላ ሁነህ ይህን ጊዜ እንድታሳልፈው ይሁን” ሲል አሳስቧል።
“በባህል፣ በሃይማኖት፣ በማህበራዊ ትስስር፣ አልፎም በረዥሙ የአገር ግንባታ ጉዞ ከአማራ ሕዝብ ጋር የጋራ ታሪክ ያለውን የትግራይ ሕዝብ መከታና ጋሻ ሆነህ አስተዋይነትና አብሮነት የምንጊዜም ምርጫህ እንደሆነ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተግባር እንድታሳይ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ሲልም ነው ፓርቲው መልዕክትን ለአማራ ህዝብ ያቀረበው።
የትግራይ ሕዝብ እንደትላንቱ ሁሉ፣ ዛሬም ሆነ ነገ አብሮህ ይኖራል። ዝንታለም ጠላትህ ትህነግና ወገኖችህን የጨረሰው የትህነግ ሰራዊት ነው፤ ያለው ፓርቲው፤ “ስለዚህ ትህነግ ካጠመደልህ ወጥመድ ሳትገባ፤ የወገኖችህን ደም የምትመልሰው ትህነግንና ገዳይ ሰራዊቱን እስከመጨረሻው በመፋለም መደምሰስ ሲቻል መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን” ብሏል።
የትህነግ ዘራፊ ቡድን ዓላማ ማስፈጸሚያ የሆኑት ልዩ ሃይል እና ሳምሪ የተባለው ገዳይ ቡድን በማይካድራ ከተማ የሚገኙ ንጹኀን ሰላማዊ ዜጎችን በጂምላ መጨፍጨፉ ይታወሳል።
በርካታ ንጹሀን አማራዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል።

ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው ቡድን ጋር በመሆን በውጊያው ላይ አየተሳተፈ መሆኑ ተገለፀ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጥምረት በከሀዲው የህወሓት ጁንታ ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው ቡድን ጋር በመሆን በውጊያው እየተሳተፈ መሆኑ ተገለጸ።
ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት የፈጸመውና ለመናገር የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ በፈጸመው የህወሓት ዘራፊ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ የኦነግ ባንዲራን የያዙ የሸኔ አባላት በጦርነቱ እየተሳተፉ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ሀገሩንና ህዝቡን በማገልገል ላይ በለው ሰራዊት ላይ ከሀዲው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ በውጊያው ላይ መሳተፉ እንዳስገረማቸውም ነው ሌተናል ጄኔራል ባጫ የገለጹት።
የኦነግ ሸኔ አባላት በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚታወቀውን የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከከሃዲው የህወሓት ቡድን ጋር በመሆን በሽራሮ፣ በራማ፣ በፆረና፣ እና በዛላንበሳ በኩል ውጊያ መግጠማቸውን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል።
ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ ዘራፊው የህወሓት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ እጃቸው አለበት ሲል መንግስት በተደጋጋሚ ማስታወቁ ይታወሳል።
በሀይማኖት ከበደ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተላለፈ መልዕክት
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝቷል። ጭካኔው ልብ ሰባሪ ነበር።
ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር ነው።
አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን።
ዓላማው ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው።
አላወቁም ልበ ሰፊ ሕዝብና ሠራዊት እንዳለን።
በየቦታው ስንደርስ ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊገጥመን ይችላል። ይህ ግን ለዚህ ጁንታ የመጨረሻው ነው። ጥንቃቄያችን 'ሙት ይዞን እንዳይሞት' ነው። መፍጠን አለብን፤ የተረፉትን ለመታደግና ግፍ የተፈጸመባቸውንም ለዓለም ለማጋለጥ።
የምዕራቡን የትግራይ ክልል ቀጣና ነጻ ወጥቷል። በዚያ ቀጣና ሠራዊቱ ሰብዓዊ ርዳታና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች ሕዝቡን እየመገበ፣ እያከመና እየተንከባከበ ነው።

የከሀዲው የህወሓት ቡድን መሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።
በዚህም መሰረት፦
1. ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
3. አቶ አባይ ፀሃዬ
4. ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አፅበሃ አረጋዊ
7. አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ
መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣
የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና
አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።