Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን የኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት፤ በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ ተማሪዎቻቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማስታወቂያ ማውጣታቸዉን አስታውሶ፤ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ለጊዜዉ መገታቱን ገልጿል።

የሚኒስቴሩ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፤

❶ እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪወች በግቢያችሁ እንድትቆዩና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ

❷ እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
"በከሃዲና ፅንፈኛ ቡድን ሴራ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን አይናድም"
*******************************************************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የሰጠው መግለጫ፤
ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በሃገራችን እየተካሄደ ባለው ሁለንተናዊ ለውጥ የትግራይ ህዝብ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በእጅጉ የሚጎዱ ተግባራትን ሲያካሂድ የቆየው በህወሃት ውስጥ መሽጎ የሚገኝ የማይለወጥና ቆሞ ቀር ቡድን ራሱን ከለውጡ ጋር በማላመድ የሃገራችንን ትንሳኤ ለማረጋገጥ በሚደረገው የለውጡ ጉዞ ውስጥ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ይሁንና ይህ አጥፊና ህገ ወጥ ቡድን ከጅምሩ ጀምሮ ለውጡ እንዲደናቀፍ የተለያዩ ሴራዎችን በመሸረብ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፤አካል እንዲጎድል፤ንብረት እንዲወድምና በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
ይባስ ብሎ የሰራዊታችንን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲገድብ የቆየው አሸባሪ ቡድን የሃገር ምልክትና የኢትዮጵያ ህዝቦች ተምሳሌት በሆነው በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ከፍቷል፡፡
የሃገር መከላከያ ሰራዊታችን የሃገርን ሉአላዊ ክብር ለማስጠበቅ በተሰማራበት የትግራይ ክልል በጽንፈኛና ከሃዲ ቡድኖች የተሰነዘረበትን ጥቃት በተደራጀ መልኩ በታላቅ ሃገራዊ ፍቅርና የጀግንነት ስሜት እየመከተ ይገኛል፡፡
ጽንፈኛውና ከሃዲው ቡድን አነስተኛ የሰው ሃይል ባለበት የሰራዊታችን ካምፖች ድንገተኝነትን ተጠቅሞ ጥቃት ቢፈፅምም ጀግናው ሰራዊታችን ግን ወትሮም ዋጋ ከፍሎ ሃገርን ማዳን ልምዱ ነውና የተቃጣበትን ጥቃት ለመመከት ፅንፈኞችን በመፋለም ላይ ነው፡፡
በሃገር ንብረት ዘረፋ፤በግድያ ፤በአካል ማጉደልና በሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚታወቀው ከሃዲውና ጽንፈኛው ቡድን በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሰራዊታችንንና የሌሎች ሃገራትን ዪኒፎርም አስቀድሞ አመሳስሎ በማምረትና የራሱን ሃይል በማልበስ ገድለናል፤ማርከናል የሚል የተለመደ ማደናገሪያውን የክልሉን ሚዲያ ተጠቅሞ በመንዛት ላይ ይገኛል፡፡
እውነታው ግን ጀግናው ሰራዊታችን በታላቅ ጀግንነት፤በፍፁም የሃገር ፍቅር ስሜትና በአንድነት መንፈስ የፅንፈኛውና የከሃዲውን ጥቃት መመከቱ ነው፡፡
እንደሚታወቀው እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትፍረስ የሚለው የስልጣን ጥመኛው ቡድን ያሰባሰበው የልዩ ሃይልና ሚሊሻ በአንዳንድ አካባቢዎች የመዋጋት ፍላጎት የሌለው ሲሆን መንግስት ዋስትና እንዲሰጠውም ይፈልጋል፡፡
ተገዳችሁና ሳትፈልጉ ወደ ጦርነት የገባችሁ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል አባላት!
በሰላማዊ መንገድ ወደ አጎራባች ክልሎችና በአቅራቢያችሁ ወዳለው የመከላከያ ሰራዊት ከገባችሁ መንግስት ሙሉና አስተማማኝ ዋስትና እንደሚሰጣችሁ ያረጋግጥላችyል፡፡
ውድ የትግራይ ህዝቦች!
ሰላማችሁን ለማስጠበቅ ከሃያ አመታት በላይ ከጎናችሁ ተሰልፎ የተዋደቀውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት፤ችግራችሁን እየተካፈለና ልማታችሁን እየደገፈ አብሯችሁ በመልካም ወንድማማችነት የኖረውን ይህንን ጀግና ሰራዊት፤መውጋት ታሪክ ይቅር የማይለው የትግራይን ህዝብ የማይመጥን ከመሆኑ ባሻገር በዓለም ታሪክ አንድ መደበኛ ጦር በደባና በአሻጥር በገዛ ወገኑ ተወግቶ የማያውቅ መሆኑን ተረድታችሁ በዚህ አሳፋሪ ድርጊት ባለመሳተፍና ከሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ የተለመደ ጀግንነትና ቁርጠኝነታችሁን እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርብላችyለን፡፡
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች!
የሃገርን ሉአላዊ ክብር ለማስጠበቅ የቆመን ሰራዊት፤ሃገር እንጂ ብሄር የሌለውን ሰራዊት ፤የኢትዮጵያ ህዝቦች ትክክለኛ ተምሳሌት የሆነን ህብረ ብሄራዊ ሰራዊት፤ከሃገር አልፎ በአለም አቀፍ ሰላም ላይ ዝናና አክብሮትን ያተረፈን ሰራዊት ማጥቃት ሃገርን ተኩሶ እንደ መግደልና የኢትዮጵያውያንን ክብር እንደ መንካት ይቆጠራል፡፡
የሃገር መከላከያ ሰራዊት ትናንት ከላብ ጠብታ እስከ ህይወት መስዋእትነት በመክፈል ዛሬም በገንዘቡና በጉልበቱ መላ ህዝቡን እየደገፈ የመጣ ምስጋና እንጂ ጥቃት የማይገባው የህዝብ ልጅ መሆኑን አስታውሳችሁ ይህንን ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት እንድታወግዙትና የሃገራችንን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለማስከበርና አጠናክሮ ለማስቀጠል በምንወስደው እርምጃ ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችን
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት
ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
መንግስትና ህዝቡ ከሀዲ ቡድኑ እየፈጸመ ያለውን አሳፋሪ ተግባር ለማክሸፍና የውርደት ካባውን ለማከናነብ መረባረብ አለባቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ
**********************
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግስትና ህዝቡ ከሀዲ ቡድኑ እየፈጸመ ያለውን አሳፋሪ ተግባር ለማክሽፍና የውርደት ካባውን ለማከናነብ መረባረብ አለባቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
ከሀዲ ቡድኑ እየፈጸመ ያለውን አሳፋሪ ተግባር ለማክሽፍና የውርደት ካባውን ለማከናነብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የክብር፣ የሉዓላዊነት መለያ የሆነው የመከላከያ ሰራዊት በተልዕኮ ላይ እያለ በገዛ ወገኑ፣በካሀዲ ቡድን ጥቃት ተፈጸሞበታል፡፡
ቡድኑ ከትናትናው ዕለት ጀምሮ ልዩ ሀይሉን በማንቀሳቀስ በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ለማካሄድ ከፍተኛ ርብርብ በማሄድ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ደመቀ፤ ይህ ድርጊት የክፋት የመጨረሻው ጥግና ጡት ነካሽነት በመሆኑ መንግስትና ህዝቡ ይህን አሰፋሪ ተግባር ለማክሽፍ እና የውርደት ካባውን ለማከናነብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መረባረብ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፤ የተፈጠረው ግጭት በአጠቃላይ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ሳይሆን ከተወሰኑ ጥቅመኛ ስብስቦች ጋር የተፈጠረ መሆኑን የክልሉ ህዝብ ሊረዳ ይግባል ብለዋል።
በጌትነት ምህረቴ
“የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት መቀበል አለበት” - - - ዶ/ር አብርሃም በላይ
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር
*************************
(ኢ.ፕ.ድ)
የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት መቀበል አለበት ሲሉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ።
የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት በመቀበል ከአማራ ህዝብ ጋር በሰላም እንዲቀላቀልና ከአካባቢው መስተዳድር አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ፈጣን ሰላማዊ ሽግግር ለማስፈን የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርግ ዶ/ር አብረሀም ጠይቀዋል።
ለአመታት ዋጋ እየከፈለ ባለው የአገር የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በወሰደው አሳፋሪ የጥቃት ትንኰሳና ዝርፊያ መነሻነት የፌደራሉ መንግስት መጠነ ሰፊ ህግ የማስከበር እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን ዶ/ር አብረሀም ተናግረዋል።
በአይነቱና በታሪክም ፍፁም እንግዳ የሆነ የክህደት ተግባር ለአገራቸው አንድነትና ክብር ለአመታት መስዋእትነት ለከፈሉ ህዝቦች ጠላፊው ቡድን ያለውን ንቀት ያሳየበት ነው፤ ያለዑት ዶ/ር አብረሀም፤ በዚህ የለየለት እብደቱም የአገርን ሉአላዊነት አደጋ ላይ የጣሰ በመሆኑ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃዎች በሙሉ እየተወሰደበት ይገኛል ብለዋል።
መንግስት ሰላምና መረጋጋትን በመላው ትግራይ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የህግ ተግባራትን በመደበኛው የህግ አግባብ ለማስፈፀም አዳጋች መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዛሬው እለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጁን ተናግረዋል።
"በአገር ላይ የተቃጣውን የክህደት ተግባር መላው የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ሐይል እና ከመላው የአገራችን ህዞቦች ጋር በጋራ በመቆም በፅናት እንድትመክቱና ይህንን አስከፊ የክህደት ተግባርም በጥብቅ በማውገዝ ከመንግስት ጎን እንትቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል፤ ዶ/ር አብረሀም።
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃን እንደምታከናውን አስታወቀች።
*****************************************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃን ለማከናወን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መስማማታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወቃል።
ጉብኝቱን እና የተደረጉ ውይይትችን በማስመልከት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦሜር ጋማር ኤልዲን እንደተናገሩት፤ ሁለቱ አገራት በተለይም በድንበርና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች “በድንበር፣ በልማትና በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የአል-ቡርሀን ጉብኝት የተካሄደው የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሱዳን የድንበር አካባቢዎችን ለመቆጣጠር እና በግዛቷ በኩል የአማፅያን ጥቃቶችን በመከላከል ለኢትዮጵያ ስታደርግ የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የሁለቱን ህዝቦች ፍላጎት መሰረት በማድረግ መስራት እንደሚያሰፈልግም መሪዎቹ ተስማምተዋል ብለዋል ፡፡
የድንበር ጥቃቶችን ለመከላከልና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ሁለቱ አገራት መስማማታቸውንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በወንድማገኝ አሸብር
በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን የኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት፤ በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ ተማሪዎቻቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማስታወቂያ ማውጣታቸዉን አስታውሶ፤ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ለጊዜዉ መገታቱን ገልጿል።
የሚኒስቴሩ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፤
❶ እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪወች በግቢያችሁ እንድትቆዩና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ
❷ እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት የህዝቦችን ደህንነትና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታወቀ
***^*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት የህዝቦችን ደህንነትና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታወቀ።
ከትናንት ምሽት ጀምሮ በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የታጠቀ የህወሃት ሃይል ጥቃት በማድረስ ጉዳት ለማስከተል፣ በህዝቦች ደህንነትና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋ በመጋረጥ ሀገሪቱን ለማፍረስ ሙከራ ማድረጉን የኢፌዲሪ መከላከያ አስታውቋል ።
"መከላከያ ሰራዊታችን የተቃጣበትን ጥቃት በመመከትና በማክሸፍ የህዝቦችን ደህንነትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል" ብሏል።
ይህንኑ በአስተማማኝ መልኩ በመፈጸም ስኬታማ ተግባር በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር እየሰራን እንደምንገኝ ለህዝባችን ማስታወቅ እንወዳለን ሲልም ነው መከላከያ የገለጸው።
ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ መሽጋገሩን አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊይ ተኩስ በተከፈተበት ካምፖች ሁሉ በጠንካራ መከላከል ዉጊያ የከሃዲዉን ሃይል በጀግንነት መክቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት ይገኛል፡፡

መከላከያ ሰራዊትና የአማራ የጸጥታ ሃይል ተቀናጅተዉ በሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር በተባለ ቦታ የእብሪተኛዉ ቡድን የሰነዘረዉን የማጥቃት ዉጊያ በብቃት በመመከት በዚህ ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

"ሰራዊታችን በዛሬዉ እለት ከሰዓት በኋላ በወሰደዉ ቅንጅታዊ የማጥቃት እርምጃ ከቀራቅር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበረዉን የእብሪተኛዉ አጥፊ ቡድን ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ቦታዉን በሰራዊታችን ቁጥጥር ሥር አዉሎታል" ብሏል፡፡

ጀግናዉ ሰራዊት በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ በዚህ ነብሰ በላ ቡድን ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችንም መማረኩን አሥታውቊል ፡፡
ህወሓት መቀሌ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሜሪካ አስታወቀች
***********
(ኢ.ፕ.ድ)

ህወሓት መቀሌ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፒዮ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንደገለጹት፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል።

የህወሓትን ጥቃት ተከትሎ የተወሰደው እርምጃ እንዳሳሠባቸው ገልጸው፤ ሁኔታዎች በአፋጣኝ ወደነበሩበት እንዲመለስ ጠይቀዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ህወሓት በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙንና መንግስት ተገዶ ወደጦርነት መግባቱን መግለጻቸው ይታወሣል።

ህገመንግስቱን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ ሲባልም ትናንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ የሚሆንና ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ያወጣውንና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አጽድቆታል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመረመረ በኋላ ተቀብሎ አጽድቆታል።
ምክር ቤቱ በዚሁ ስብሰባው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትንም ሰይሟል።
በዚህም መሰረት፤
1. አቶ ለማ ተሰማ - ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ጀምበርነሽ ክንፈ
3. ወ/ሮ ሃዋ አሊ
4. አቶ አለባቸው ላቀው
5. አቶ ዘርይሁን ጴጥሮስ
6. ወ/ሮ አስካለ ጥላሁን
7. አቶ ወንድሙ ግዛው
የመርማሪ ቦርዱ አባላት ሆነው በምክር ቤቱ ተሰይመዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት የተነሳ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን አማጺ ቡድን ሲሉ ገልጸውታል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት የፌዴራል መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን ተከትሎ ሁነቱን ለመዘገብ ዜናዎችን የሰሩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ህወሓትን "አማጺ ቡድን” ሲሉ ገልጸውታል።

ጦርነቱን በማስመልከት ዘገባ ከሰሩ የመገናኛ ብዙሃን መካከል አንዱ የሆነው አልጀዚራ ህወሓትን “አማጺ ቡድን” ሲል በዘገባው ጠርቶታል።

አልጀዚራ በዚሁ ዘገባው አማጺ ቡድኑ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ራሱ በማምረት ለራሱ ታጣቂዎች አልብሶ “የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ላይ ወረራ ፈጸሙ” የሚል ክስ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠቅሶ አስታውቋል።

ህወሓት የትግራይን ህዝብ ከ20 አመታት በላይ ሲጠብቅ በኖረው የሰሜን እዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት የተነሳ መንግስት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር ሲል ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን የኢፌደሪ ጠቅለዓይ ሚኒስት ዶ/ር አብይ አህመድ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

በተመሳሳይም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፒዮ በትዊተር ገጻቸው፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል ሲሉ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ላይ መናገራቸው ይታወሳል።
በነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የግብይት ሠዓት ገደብ ተቀመጠ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በምርቶች ላይ ሊከሠቱ የሚችሉ ሠው ሠራሽ የሆኑና ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር እና ያለአግባብ የምርት ክምችት በመፍጠር እጥረቶች እንዳይፈጠሩ ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ ስራዎች እየትፕሠሩ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ የኮመኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደተናገሩት፤ የነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይትን በጥብቅ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጀምሮ የሰአት ገደብ ተቀምጧል።

በዚህም መሰረት በሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጥቅምት 27 ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በሁሉም የክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሠሩ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የሀገር ክህደት መሆኑን አስታወቁ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አባባ ፦ በህወሓት ውስጥ ያለ ከሀዲ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሰነዘረው ጥቃት መቼም ታሪክ የማይረሳው የሀገር ክህደት መሆኑን የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች አስታወቁ ።
የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥኝ እንደዘገበው ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይ ዙሪያ ከክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የሀገር ሽማግሌዎች በህወሓት ውስጥ ያለ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሰነዘረው ጥቃት መቼም ታሪክ የማይረሳው የሀገር ክህደት መሆኑን አስታውቀዋል። መንግሥት በአጥፊው ቡድን ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንደሚደግፉት ገልጸዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ ከመንግሥት ጎን ሆነው የሀገርና የክልሉን ሰላም አጠናክረው ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት በክልሉና በሀገሪቱ ህዝብ ላይ ሲያደርሰው ከነበረው አስከፊ ጉዳት ባለፉት ሦስት ዓመታት በሀገሪቱ የተረጋገጠውን ለውጥ ለማደናቀፍ በተለያየ የጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ ተናግረዋል።
መንግሥት የአጥፊዎችን እኩይ ሴራ በሆደ ሰፊነት ሲያልፍ መቆየቱን የጠቆሙት አፈጉባኤው፣ ህወሓት ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አመልክተዋል ። በዚህም መንግሥት በቡድኑ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደደ አስታውቀዋል።
መላው የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በመገንዘብ መንግሥት እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንዲደግፉና የሀገሪቱን እና የክልሉን ሰላም ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በውይይቱ ላይ ወቅቱ የክልሉ ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር፤ በክልሉ ከሚኖሩና ከክልሉ አዋሳኝ ክልል ህዝቦች ጋር ሰላማዊ አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።
የክልሉንና የሀገሪቱን ሰላም ማረጋገጥ የሚሰራበት ወቅት በመሆኑ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያጎለብቱ ጠይቀዋል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ መስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 28/2013
“በሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የክህደትና የባንዳነት መገለጫ ነው”
ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት
****************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት ፍጹም ከወገን የማይጠበቅ የሀገር ክህደትና የባንዳነት መገለጫ መሆኑን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን አስታወቁ።
የማበህሩ ሊቀመንበር ልጅ ዳንኤል በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የሀገሩንና የወገኑን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በርካታ ዓመታት ከቤተሰቦቹ ተለይቶ በግዳጅ ላይ ባለ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የጭካኔ፣ የሀገር ክህደትና የባንዳነት መገለጫ ነው። እንዲህ አይነቱ ወራዳ ተግባር በየትኛውም የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪና አስተዛዛቢ ነው ።
“ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የውጭ ሓይሎችን ጥቃት ለመመከት አቅሟንና አንድነቷን ማጠናከር በሚገባት በዚህ ሰዓት ከአብራኳ የወጡ ልጆቿ በራሳቸው ጠባቂዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ከማን ጋር እንደቆሙ የሚያሳይ ነው ። ይህ ጸያፍ ተግባር የሀገርን ክብር ያዋረደ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነና የጥቂት ቡድኖችን ማንነት በግልጽ ያሳየ ነው “ብለዋል ።
ሀገሪቱ በኮቪድ 19 ፤ በአንበጣ ወረርሽኝ፣ በህዳሴው ግድብ ሽኩቻ፣ በጎርፍ ተፈናቃዮች እና በውስጥ አለመረጋጋት ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ወቅት እንደገና ሌላ ችግር መፍጠር ሆን ብሎ ሀገሪቱን ለማፈራረስ የታሰበ ደባ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሰው ህይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወድም በትዕግስት ያሳለፈው ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በማሰብ እንደሆነ የዓርበኞች ማህበር ያምናል። ጥቂት የህወሓት አመራሮች ክብሪትና ነዳጅ አስይዘው በየቦታው በሚያስነሱት እሳት ዜጎች ሲሰቃዩ እንደነበር መታዘባቸውንም ገልጸዋል።
ዓርበኞች ከአባቶቻቸው የተረከቧትን ሀገር የውጭ ወራሪዎችን እየመከቱ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ አቆይተዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በዓርበኞች አጥንትና ደም የተሰራች ሀገር በባንዳዎች አትፈርስም ብለዋል። አባቶቻችን ከኢጣሊያን ፋሺስት ጋር በተፋለሙበትና የዓድዋን አኩሪ ድል ባጣጣሙበት ስፍራ እንዲህ ያለ ጸያፍ ተግባር መፈጸሙ የዓርበኞችን ማህበር እንዳስከፋም አመልክተዋል ።
ከተልእኮው ባሻገር የአርሶ አደሩን ምርት በመሰብሰብና የአንበጣ ወረርሽኝን በመከላከል ከህዝብ ጎን የቆመን ሠራዊት ማጥቃት ህዝብን ማጥፍት፤ ሀገርንም መካድ እንደሆነ ተናግረዋል። የአርበኞች ማህበር በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ እንደሚያወግዘው ገልጸዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ ህገመንግሥትን ማስከበርና የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር እንጂ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ታዛዥ መሆን አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፣መንግሥት ተገዶ ወደ ጦርነት የገባው የተቃጣበትን ጥቃት በመቀልበስ ህግና ስርዓትን ለማስከበር ነው ብለዋል። በመሆኑ የዓርበኞች ማህበር ሠራዊቱ እየወሰደ ያለውን ርምጃ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ በዲሲፒሊን የታነጸ፤ ከሀገሩ አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም መከታ የሆነ የኢትዮጵያን ስም ያስጠራ መሆኑን በመጥቀስ ፣የሀገር ኩራት የሆነን ሠራዊት ማክበርና መንከባከብ ሲገባ በራሱ ወገን ቃታ ሲሳብበት መስማታችን አሳፍሮናል ብለዋል።
በጥቂት የህወሓት አመራሮች ስብከት ተታለውና ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ሓይል አባላት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን በመስጠት ሀገሪቱን ከጥፋት እንዲታደጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የትግራይ ህዝብ ጥቅማቸው የተነካባቸው ጥቂት የህወሓት አመራሮች በሚነዱት መንገድ መሄድ እንደሌለበትና ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመቆም ሰላሙን አረጋግጦ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ጋር በፍቅር መኖር ይገባዋል ብለዋል።
መንግሥት እየወሰደ ባለው ወታደራዊ ርምጃ ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ህዝቡም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ይዞ ከመንግሥትና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፈዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 28/2013
“የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ተሳክቷል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
. በአጭር ጊዜ ይህን ስግብግብ ጁንታ በማስወገድ ለትግራይ ህዝብ፣ ለአገር መከላከያ እና ፖሊስ ሠራዊታችን እፎይታና ሰላም በመስጠት በፍጥነት ሰብል ወደ መሰብሰብ ለመመለስ እቅድ አዘጋጅተናል
******************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- የመጀመሪያው ዙር ኦፐሬሽን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ መሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። በፍቅረ ንዋይና ስልጣን ታውሮ ለአገርና ህዝብ ደህንነት ደንታ የሌለው በህወሓት ውስጥ የመሸገው ስግብግቡ ጁንታ ሓይል ባለፉት ሁለት ቀናት በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በኢፌዲሪ የፖሊስ ሠራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በዚህ የጠላት ኃይል ላይ በተወሰደ እርምጃ ጉዞውን ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ መቻሉን አመለከቱ ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ የተወሰደውን ኦፕሬሽንና የተገኘውን ድል አስመልክተው ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ በመከላከያ ሓይላችንና በፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት ላይ ጭምር ጥቃት በመፈጸም በፍቅረ ነዋይና ስልጣን ታውሮ ለአገርና ህዝብ ደህንነት ደንታ እንደሌለው ባሳየው በህወሓት ውስጥ የመሸገው ጁንታ የጠላት ቡድን ላይ በተወሰደ የመጀመሪያ ዙር እርምጃ የቡድኑን ጉዞ ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች ተቀምጠው የተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የመጀመሪያው ዓላማ ጥቃቱን መግታት እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ጠላት በሁሉም ግንባር በፈለገው አቅጣጫ ጥቃት እየሰነዘረ በህዝባችን፣ በሠራዊታችን፣ በፖሊስ ሰራዊታችን እንዲሁምበአንዳንድ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት መግታት እንደነበር አስታውቀዋል።
ከዚህ አንጻር ጠላት ጥቃት የሚሰነዝርባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ኃይል በስፋት ያልነበረ ቢሆንም፤ ከያለበት ኃይላችንን በማንቀሳቀስ ሙሉ የሎጀስቲክስና የሰው ኃይል አቅርቦት የጨረስን ሲሆን፤ የጠላትንም ጉዞ ሙሉ በሙሉ ማስቆም፣ መግታትና ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ላይም ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ፣ ሁለተኛው ዓላማ፣ የመከላከያ ኃይላችን እና የፖሊስ ሰራዊት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ይሄንን ኃይል የመታደግ ወሳኝ አገራዊ ሓብቶችና ትጥቆች የመታደግ ስራ ነበር። ከዚህ አንጻር በባድመ ግንባር፣ በጾረና፣ በዛላንበሳን በመሳሰሉ በዋና ዋና ቦታ ተሰልፈው ያሉ የሠራዊት አባላት እና ትጥቆቻቸው ሙሉ በሙሉ ከጠላት ፍላጎት ውጪ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል።
በተለይ ጠላት ፊቱን አዙሮ ከውጭ በሚመጣ ሓይል በመከላከል ላይ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሓይሉን አጠናክሮ፣ አሰላለፉን ቀይሮ፣ ፊቱን አዙሮ ማንኛውም ጥቃት ለመሰንዘር ወይም ለመከላከል በሚያስችል ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥቃት ይደርስበታል የሚል ስጋት እንዳይኖር ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ሦስተኛው ዓላማ፣ የጠላት የማድረግ አቅምን ማዳከም ነው። የጠላት ሓይል የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሓብት ላይ ቀንሶ አገሩን ለመከላከል የገዛቸውን ዋና ዋና ትጥቆች፣ ሚሳዬሎች፣ ሮኬቶች በመጠቀም ጥፋት ማካሄድ እንዳይችል አቅሙን ማዳከም ነበር። እነዚህ ሦስት ዓላማዎች ሙሉ በሙሉ መሳካታቸውን አስታውቀዋል ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ወሳኝ የሚባሉ አካባቢዎች በተለይ በዳንሻ ግንባር ያለውን ጠላት ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ አከባቢውን የተቆጣጠርን ሲሆን፤ እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሁሉም አቅጣጫ የሚቀጥለውን እርምጃ እየወሰን ለህዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል። እስካሁን ባለው ሁኔታ የመጀመሪያው እቅድ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የተሳካ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፤ ሲሉ ስለ ሁኔታው አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የሚሰሩ ስራዎች የውጊያ ባህሪ፣ የግጭት ባህሪ ሁሉን ነገር በወቅቱ መናገር የሚያስቸግር ቢሆንም፤ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝባችን እየሰጠን ህግ የማስከበሩን ስራ፣ የህዝቦቻችንን ሰላም የአገራችንን ደህንነት የመከላከያ ሃይላችንን ጥንካሬና ብቃት በሚያጠናክሩ ስራዎች የምንቀጥል ሲሆን፤ ይህ ስግብግብ ጁንታ ሙሉ በሙሉ ለህግ እስከሚቀርብ፤ የጀመርነው ራስንና አገርን የመከላከል ዘመቻ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።
ከዚህ ቀጥሎ በሚደረጉ፣ በቀጣዩ እቅዳችን ላይ በሚሰሩ ስራዎች አስፈላጊ የሚባሉ መረጃዎች በየወቅቱ የምንገልጽላችሁ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄን ስግብግብ ጁንታ በማስወገድ ለትግራይ ህዝብ፣ ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ እንዲሁም ለፖሊስ ሠራዊታችን እፎይታና ሰላም በመስጠት በፍጥነት የእርሻ ስራችንን ወደ መሰብሰብ ለመመለስ የሚያስችል እቅድ ያዘጋጀን ሲሆን፤ ሙሉ ኦፕሬሽኑን ስናጠናቅቅ ለህዝባችን ዝርዝር የስራ አፈጻጸሙን የሚገልጹ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
አዲስ ዘመን ጥቅምት 28/2013
ጆ ባይደን አሸነፉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከሚያስፈልገው 270 ኤሌክቶራል ድምጽ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድርስ 284 በማግኘት ጆ ባይደን ማሸነፋቸው ተረጋግጧል።
ባይደን ከአራት ቀናት በኋላ ነው ዶናልድ ትራምፕን በመብለጥ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገው፡፡
ዲሞክራቶችን የወከሉት ጆ ባይደን በቀጣይ ለአራት አመታት አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡
ጆ ባይደን አሸነፉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከሚያስፈልገው 270 ኤሌክቶራል ድምጽ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድርስ 284 በማግኘት ጆ ባይደን ማሸነፋቸው ተረጋግጧል።
ባይደን ከአራት ቀናት በኋላ ነው ዶናልድ ትራምፕን በመብለጥ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገው፡፡
ዲሞክራቶችን የወከሉት ጆ ባይደን በቀጣይ ለአራት አመታት አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊዎቹ ለጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በቅርበት እንደምትሰራ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲያሸሹ በነበሩ የሕወሓት ጁንታ አባላት ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞቹን እየያዘ መሆኑን መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

መንግሥት የውጭ ምንዛሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲያሸሹ በነበሩ የሕወሓት ጁንታ አባላት ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞቹን እየያዘ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

"ስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ ነው የኖረው፤ የዘረፈውን ገንዘብ ለማሸሽ እንዲችል የውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መንገዶችን ይጠቀማል፤ ኢትዮጵያውያን የሚልኩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ ባሉበት ሀገር በመቀበል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘረፈው ገንዘብ ከገበያው በላይ ይከፍላል፤ የውጭ ምንዛሬውንም ወደ ተለያዩ ሀገሮች ያሸሻል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

"መንግሥት ክትትል አድርጎ ወንጀለኞቹን እየያዘ ነው። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይሄንን ጁንታ ሳያውቁት ከማገዝና ሀገራቸውን ከመጉዳት እንዲቆጠቡ፣ ወንጀለኞችንም እንዲያጋልጡ፣ ገንዘባቸውን በባንክ በመላክ ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ የወጡ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው
*************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከተማ ንጉስ፡- በምዕራብ ትግራይ የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት ከአፋኙ የህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣቸው ደስተቸውን ገለጹ።
በትግራይ ክልል ከተማ ንጉስ የተገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ከከሀዲው ቡድን ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸውን መግለጻቸውንና የመከላከያ ሰራዊቱን በደስታ መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን የፌዴራል መንግስት ሊወረን ነው፣ የትግራይን ህዝብ በሀይል ሊያበረክክ ነው ሲል ቆይቶ ራሱ ቀድሞ በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ የሚወገዝ ተግባር ነው የጸገዴ ወረዳ ነዋሪዎች፤ ይህ የሚሳየው ከላይ ያለው የህወኃት ቡድን ለራሱ ጥቅም እንጂ ለህዝብ ደንታ እንደሌላው ነው ብለዋል፡፡
የጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ አቶ ስምረት አቦይ እንደገለጹት፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን አፋኝና ለህዝብ ደንታ የሌለው ነው፡፡ ቡድኑ ለትግራይ ህዝብ እኛ ጦርነት አንገጥምም ራሳችን ብቻ የምንከላካለው እያለ ሲያታልል ቆይቶ ቀድሞ ራሱ በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተው ጥቃት የምናወግዘው ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከጦርነት የሚያተርፈው ነገር የለም ያሉት አቶ ስምረት ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለህዝቡ የሚነግረውና የሚፈጸመው ተግባር ለየቅል ነው ያሉት አቶ ስምረት፤ ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሳ የሚያሰር፣ የሚያገላታ፣ ጫናና አፈና የሚፈጸም በመሆኑ ከዚህ አፈና በአገር መከላከያና በአማራ ልዩ ሀይል ነጻ መውጣታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ቡድን ነጻ ስላወጣን ደስተኞች ነን ያለችው በጸገዴ ወረዳ የከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ ወጣት ከተማ ከፍያለው፤ ይህን ደስታችንንም ሰልፍ በመውጣት ጭምር አረጋግጠናል፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በነሱ ተላላኪ ሰዎች አማካኝነትም ህዝቡ እርስ በእርሱ በጥርጣሬና በአይነ ቁራኛ እንዲተያይ፣ የፈለገውን ሀሳብ እንዳይገልጸ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጻለች፡፡
“ህወሓት የፈለግነውን ሙዚቃ እንኳን እንዳንሰማ ያደርግ ነበር፤ የመብት ጥያቄዎችን ስናነሳ ሲያስረንና ሲያንገላታን ነበር ያለቸው ወጣቷ፤ የመከለከያ ሰራዊት ጸገዴ ወረዳን መቆጣጠሩ ነዋሪው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ተናግራለች፡፡
አሁን ከተማ ንጉስ ከተማ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑንና ህዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ታዝቧል።
በጌትነት ምህረቴ
የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በጀኔራሉ አንደበት
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ፡፡መስታወታቸው ረግፏል፤ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም።የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል፡፡የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል፡፡
ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣አሳዛኝ፣አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው፡፡በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም።በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡
በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱን እንደሚፈልጉትና እንዲጠራላችሁ የበር ጥበቃዎችን ይጠይቃሉ።ጀኔራሉም እንደማይመጡ ሲነገራቸው ተመልሰው ይሄዱና ተጨማሪ
ሀይል ይዘው መጥተው በካምፑ ላይ የጥይት መአት ማውረድ ይጀምራሉ፡፡ውስጥ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በጽናት የመመከት ስራ ውስጥ ገቡ፤ለሶስት ቀንና ሌሊት በጽናት ታገሉ፡፡
አንድ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሰራተኛ ወደ ጀነራሉ ጆሮ ተጠግቶ አካባቢውን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ከቦታል፡፡ፍላጎት ካለህ ሽማግሌዎቹ ከአካባቢው እናስወጣው ብለው ነግረውኛል፤ ውሳኔህ ምንድነው ሲል ጠየቀኝ ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ፣ የእነሱ ፍላጎት እኔም ወኔዬን ተሰልቤ የሲቪል ልብስ ለብሼ ተደብቄ ወደ አማራ ክልል እንድወጣ አልያም እኔን አታለው እንድያዝ በማድረግ ካምፕ ውስጥና በአቅራቢያው ባለው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ለመሰንዘር ያቀዱትን ጥቃት የመከላከልና የመመከት ስራ ለማሰናከል ነው፡፡በዚህም በቀላሉ ሰራዊቱንና መሳሪያውን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስበው መሆኑን ገለጹልን፡፡
እኔም ምላሼ ሽምግልናውን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን የመረጃ ሰራተኛው ከሽማግሌዎቹ ጋር ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ መገናኘት እንደሌለበት አስጠንቅቄ ነገርኩት ።አሁን ይህን ያለኝ ልጅ ቆስሎ ለህክምና ወደ ጎንደር ሄዷል።ሲመጣ ጠይቄ ዓላማቸው ምን እንደነበር የምረዳው ይሆናል፡፡ተመትቶ ስለነበረ እኔም እንዳልሞት አስቦ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ብለውናል።
የሶስት ቀን ከበባው በጣም አስቸጋሪ ነበር።24 ሰዓት ተኩስ ነው፡፡ያጠቃሉ እኛ እንከላከላለን፤ይሄዱና ምግብ በልተው ሀይል ጨምረው ያጠቃሉ፤ሲታኩሱ የነበሩት ልዩ ሀይሎች ወደ ካምፓቸው ሄደው አርፈውና ጥይት ጭነው ይመጣሉ፡፡እኛ ካለንበት ቦታ ውጭ መፈናፈኛ ስፍራ የለንም፡፡እንደ ቀለበት ዙሪያውን ከበውና ውሃ ፣ምግብ፣ጥይት የለም፡፡ያለችንን ነው በቁጠባ የምንጠቀመው ሲሉ ያብራሩት ጀነራሉ፣እኔም አልፎ አልፎ እንደ ምሽግ ከተጠቀምኩበት ግንብ ቤት እየወጣሁ ለወታደሮቼ ጥይት በቁጠባ ተጠቀሙ እያልኩ አሳስብ ነበር ሲሉ ይገልጻሉ፡፡እነሱም አላሳፈሩኝም በጽናት ተዋደቁ።የሰራዊታችን በጽናት የመከላከል ሞራል የሚገርም፣ የሚደነቅና ታምር የሚያስብል ነው ይላሉ፡፡
አርቢጂ፣ቦንብ፣መትረየስ ፤ክላሽ እንደ ዝናብ ቢያርከፈክፉብንም ለሶስት ቀናት ቀንና ሌሊት መክተናል፡፡በፍጹም እንተርፋለን ብለን አላሰብነም ፤ከቻልን እስከ መጨረሻው እንከላከላለን ፤ካልቻልን ደግሞ በመጨረሻ ላይ ራሳችንን እናጠፋለን የሚል አቋም ነበርን፡፡ግን በእግዜአብሄር ቸርነት፤በመከላከያ ሰራዊት ፈጥኖ ደራሽነት ቀለበቱ ተሰብሮ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል ብለውናል፡፡ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም፡፡
ድርጊቱ የሚያሳዝን ነው፤ በህወሓት ከሀዲ ቡድን እንዲህ አይነት ጥቃት ይፈጸምብናል ብለን አስበን፤አልምንም አናውቅም የሚሉት በሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ፤ ምክንያቱም ከኢትዮ-ኢርትራ ጦርነት ጀምሮ ትግራይ መሬት ነው እየኖርን ያለው።ህዝቡን መሪዎቹንም በደንብ እናውቃቸዋለን ብለዋል፡፡
“አብረህ እየበላህ እየጠጣህ፣ተዋልደህ ተጋምደህ፤ ትዳር መስርተህ ፣ልጆች ወልደህ፤ቤተሰብ ሆነህ በፍጹም ጥቃት ሊሰነዝርብኝ ይችላሉ ብለህ አታስብም፤ሆኖም ያልታሰበው ተፈጸመ፤ያልተጠበቀው ሆነ “ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል።
ኩርፊያና የተለያዩ መገለጫዎች ይታያሉ ፡፡ይህን ተከትሎ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ደፍረው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ገብተው ያጠቃሉ ብለን አላሰብንም።ምክንያቱም ወንድምህ ሊያኮርፍ ይችላል እንጂ ያጠቃኛል፤ይገለኛል ብለህ ፈጸሞ አትገምትም የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤ግን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ዕለተ ማክሰኞ 25ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ያለምንም ርህራሄ ዙሪያውን እንደ ቀለበት ከበውን አጠቁን ፣አጠቁን እኛም በጽናት ተከላከልን፤መከትን ብለዋል፡፡
የህወሓት ቡድን ዓላማ የመከላከያ ሰራዊትን መድፎች፣ ታንኮች፣ብረት ለበሶችን መንጠቅና መከላከያን ማፍረስ ነው፡፡ በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም ፤በራሳችን መሳሪያ ተመልሰው እኛን ለመውጋት ነበር ዕቅዳቸው፡፡ይህ አልተሳካላቸውም፡፡እኛም በያለንበት በጽናት ተዋግተን መክተናል፡፡አሁን እነሱ ባሰቡት ሳይሆን እኛ ባሰብነው መንገድ እየሄደ ነው፡፡በአጭር ጊዜ ውስጥ ጦርነቱ ይቋጫል ብለን እናስባለን ሲሉ ገልጸውልናል።
ብረጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንድ የሚገርማቸው የሚደንቃቸው ነገር አለ፡፡”እኔ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊና ተራ ጄነራል ነኝ፣በአንድ ክላሽ ጥይት ግፋ ቢል ደግሞ በስናይፐር መግደል ይችላሉ፤ ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ አርቢጂ ነው የተኮሱብን ።አርቢጂ የሚባለው መሳሪያ ደግሞ ለታንክ ወይም ለጠንካራ ምሽግ ነው የሚተኮሰው፤የእኔን ቤት ለማፍረስ ግን አርቢጂ ነው የተኮሱት ሲሉ የከሀዲው ቡድን የጭካኔ ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡
እኔ ብሞትም ቤቱ የእነሱና የህዝቡ ንብረት ነው። ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ጸጥታ ለቆምኩ፣ለአገር ሉዋላዊነትና ለህዝብ ሰላም ውድ ህይወቴን ለመስጠት በተሰለፍኩ የክህደታቸው፣የክፋታቸው ጥልቀት እኔን በአርቢጂና በቦንብ ነው ያጠቁት ሲሉ የድርጊቱን ክፋት ገልጸውታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር አብሮ እየኖረ ያለ፣ለህዝቡ የልማት ስራዎች ወደ ኋላ የማይል፣ በማህበራዊ ድጋፎች የሚሳተፍ፣ ሁልጊዜ በየዓመቱ ለአቅመ ደካሞች የሚያርስ፣የሚያርም፣የሚያጭድና አንበጣ የሚከላከል ነው። በትምህርት ቤቶች፣በጤና ጣቢያዎች፣በመንገድ ግንባታዎች በሚሳተፍ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸም የህወሓት ቡድን እወክለዋለሁ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ይላሉ፡፡
የአገሩን ዳር ድንበር የሚጠብቀውን፤የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ስብስብ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ለማውድምና ለማጥፋት ነው ጥቃቱን የሰነዘሩት ፡፡እነዚህ ሰዎች ከዚህ በኋላ ስለኢትዮጵያዊነት፣ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቢሰብኩ፣ቢለፈልፉ፣ቢቀሰቅሱ ማን ጀሮ ይሰጣቸዋል ፡፡ምክንያቱም ጥቃቱን በጽናት ለመመከት የተዋደቁት ከኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተወጣጡ ወታደሮች ናቸው ብለዋል፡፡