በጎውን ሰው ከቦረና አናግረነዋል📞
ማስተር አብነት ከበደ‼️
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ማስተር አብነት ከበደ ይባላል። የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተራቡትን በማብላት የታረዙትን በማልበስ ይታወቃል። በዚህ በጎ ምግባሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አጀንዳ የሆነውን ወጣት የኢፕድ ዘጋቢዎች አግኝተውታል።
ማነህ? ስለበጎነት ምን አነሳሳህ? በጎነትህ ለብዙዎች የተጋባ ምግባር ነውና እስኪ እንወቅህ አልነው። ዘርዝሮም ነገረን።
ማስተር አብነት በአንድ ቀን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ አስር መኪና የዕለት ደራሽ ምግብ ወደ ቦረና እየተጓጓዘ መሆኑን ነግሮናል።
ማስተር አብነት ከበደ ዛሬ ለኢፕድ በሠጠው በዚሁ መረጃው እንደገለፀው፤ በድርቅ ለተጎዱ የቦረና ወገኖች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን በሚልኩት ገንዘብ የዕለት ደራሽ የሚሆን ነገር በማቅረብ ላይ ነው።
በአንድ ቀን ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ወደ አስር መኪና የሚሆን የዕለት ደራሽ ምግብ ወደ ስፍራው እየደረሰ ነው ያለው ማስተር አብነት፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ካላው ላይ በመቀነስ ለእነዚህ ዜጎች በመድረስ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
በተለያዩ ወረዳዎች በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የተለያዩ ዕርዳታዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል።
ቦታው ላይ ያለው ሁኔታ በጣም ልብ የሚሰብር ነው፤ በውሃና በምግብ እጥረት ምክንያት አረረጋውያን እየተጎዱ ስለሆነ ሁሉም ሠው አቅሙ በፈቀድለት መጠን ሊያግዝ ይገባል ብሏል።
በሃይማኖት ከበደ

ባለሀብቶች በ‹‹ድሮን›› ቴክኖሎጂ ላይ መሠማራት ይችላሉ
************
(ኢ ፕ ድ)
ባለሃብቶች ከአቪዬሽን ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ላይ መሠማራትና የድሮን አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ:: በኤሮ ስፔስ ማኑፋክቸሪንግ ላይም ባለሃብቶች መሳተፍ የሚችሉበት ዕድል ተፈጥሯል::
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93379

“የዓድዋን ድል በመዘከርና በዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ ለሌላ ድል እንዲሰለፉ ማድረግ ያስፈልጋል”
– ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የዓድዋን ድል በሚመጥን መልኩ በሚገባ በመዘከርና በዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ ለሌላ ድል እንዲሰለፉ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ተናገሩ።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዓድዋን ድል ከማክበር አንጻር እስካሁን የመጣንበት ሂደት እንደታሪኩ ግዙፍነት አይደለም።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93375

127ኛውን የዓድዋ በዓል በታሪካዊው ይስማ ንጉስ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)
127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊው ይስማ ንጉስ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፈ አቶ አባይ መንግስቴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በክልል ደረጃ ታሪካዊ በሆነውና የውጫሌ ውል በተፈረመበት ይስማ ንጉስ በድምቀት ለማክበር የተለያዩ የዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93378

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን ቦረና ዞን ገብተዋል
***************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን ቦረና ዞን ገብተዋል፡፡
እንደ ኦቢኤን ዘገባ ልዑክ ቡድኑ ከድርቅ ማገገም በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ከነዋሪዎቹ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስምንተኛው የአፍሪካ ተማሪዎች ምገባ ቀን እየተከበረ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
ስምንተኛው አገረ በቀል የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን " የአገር ውስጥ የምገባ ፍጆታ ግዥ ስረአትና ቀጠናዊ የአቅርቦት እሴቶችን በማሳደግ ቀጣይነት ያለው አገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባን ማሻሻል" በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመከበር ላይ ነው።
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር አገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎችን ጤንነት ለመጠበቅና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚያግዙ ተግባራት ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ አህጉርም ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚደግፍ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ከአምስት ነጥብ ሶስት ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን እየመገበች መሆኗን አስታውቀዋል።
የብራዚል አምባሳደር በኢትዮጵያ ጃንዳራ ፌረር ዶሳንቶስ፣ የትምህርት ቤት ምገባ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ የአመጋገብ ስርአትን የሚጠብቅ እንዲሁም የትምህርት ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎችን የሚደግፍ ነው ብለዋል።
በዚህ ዙሪያ ብራዚል የዳበረ ተሞክሮ እንዳላትና ይህንኑ ልምድ ለአፍሪካ አገራት ለማጋራትና ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩ፣ ተማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሞሐመድ ቤልሆሲንና የአለም አቀፍ ድርጀቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በአዲሱ ገረመው