Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ያዘጋጀውን ድጋፍ ወደ ስፍራው ላከ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ከተለያዩ ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ያሰባሰበውን ድጋፍ ዛሬ ማለዳ ወደ ስፍራው ላከ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፉ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች መሰባሰቡን ተናግረዋል።

ድጋፉ 250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን ጠቅሰው ድጋፉም በቀጣይ ሁተኛ ዙር እንደሚደረግም አመላክተዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ በዞኑ የተከሰተው ድርቅ በተከታታይ በክልሉ 10 ዞኖች ዝናብ አለመዝነቡን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።

በዛሬው እለት በተደረገው ድጋፍ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ፣የውሃ ቦቴዎች ይገኙበታል።

በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ድርቅ 4 ነጥብ 3 ሚልዮን ዜጎች ድጋፍ እንደሚሹ ክልሉ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።
“በትግራይ ሽግግር መንግስት የአንድ ፓርቲ የበላይነት እንዳይፈጠርና እንደገና ወደ ችግር እንዳይገባ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል” አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ
********************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ በሚመሰረተው የትግራይ ሽግግር መንግስት የአንድ ፓርቲ የበላይነት እንዳይፈጠርና እንደገና ወደ ችግር እንዳይገባ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ተናገሩ።
በሀገራቸው ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ሲቪክ ማህበራትን እንዲሁም ዲያስፖራውን ሊያካትት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93303
ክልሉ በሌማት ቱሩፋት አንድ ሺህ የንብ ቀፎዎችን ለማሠራጨት እየሠራ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብር አንድ ሺህ የንብ ቀፎዎችን ለማሰራጨት እየሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቤኒሻንጉል ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ በተለይ የሌማት ቱሩፋት ከተጀመረ ጀምሮ ከፍተኛ የንብ ማነብ ስራ ለማካሄድ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡ የሌማት ቱርፋት ፕሮጀክት ከተጀመረ አንስቶ ከአንድ ሺህ በላይ የንብ ቀፎዎችን ለ10 መንደሮች ለማሰራጨት እቅድ ተይዞ ስራ ተጀምሯል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93300
ባንኮቹ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የማህበረሰቡን እኩል ተሳታፊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው
************
(ኢ ፕ ድ)
ከወለድ ነጻ ባንኮች ማህበረሰቡ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆን ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ።
የሂጅራ ባንክ የሸሪያ ቦርድ አማካሪና ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከወለድ ነጻ ባንኮች ከወለድ ነጻ የሆነ አገልግሎት የሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች በፋይናንስ ዘርፉ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93309
ለ30 ሺህ ዜጎች ነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በወራቤ፣ በጅማ እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ 30 ሺህ ዜጎች ከፓኪስታን የሚመጡ ዜጎች ነጻ የዓይን ሕክምና ሊሰጡ መሆኑ ተገለጸ።
የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ያሲን ፋውንዴሽን በትናንትናው ዕለት በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በወራቤ፣ በጅማ እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ 30 ሺህ ዜጎች ነፃ የዓይን ሕክምና ከፓኪስታን በሚመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ይሰጣል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93308
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአለም የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ አባል ሆነ
***************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን የአለም የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ አባል ሆነ።

ከኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች አለምቀፍ ልምዶችን የሚቀስምበት፣ አለምአቀፋዊ የኢንቨሰትመንት ፕሮሞሽንን በምቹ የኢንቨትመንት ካባቢ፣ በድጋፍና ክትትል እና ዕድል እና አምራጮች ዙሪያ የሚሰራበት ሲሆን በሀገራችን ለሚያለሙ ኢንቨስተሮችም አለምአቀፋዊ የኢንቨስትመንት ዕይታዎች እና የአሰራር ሂደቶች እንዲጎለብቱ የሚሰራ ይሆናል፡፡
“ዓድዋ ለኢትዮጵያውያን የማይጠፋ አርማቸው፣ የማያረጅ ጌጣቸው፣ ከሩቅ የሚታይ ምልክታቸው፣ ዓለም የሰማው ድምጻቸው፣ የተባበረ ክንዳቸውና ከፍ ያለ ክብራቸው ነው፡፡ ዓድዋን ኢትዮጵያውያን ይመኩበታል፤ ያከብሩታልም”
በጎውን ሰው ከቦረና አናግረነዋል📞
ማስተር አብነት ከበደ‼️
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

ማስተር አብነት ከበደ ይባላል። የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተራቡትን በማብላት የታረዙትን በማልበስ ይታወቃል። በዚህ በጎ ምግባሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አጀንዳ የሆነውን ወጣት የኢፕድ ዘጋቢዎች አግኝተውታል።

ማነህ? ስለበጎነት ምን አነሳሳህ? በጎነትህ ለብዙዎች የተጋባ ምግባር ነውና እስኪ እንወቅህ አልነው። ዘርዝሮም ነገረን።

ማስተር አብነት በአንድ ቀን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ አስር መኪና የዕለት ደራሽ ምግብ ወደ ቦረና እየተጓጓዘ መሆኑን ነግሮናል።

ማስተር አብነት ከበደ ዛሬ ለኢፕድ በሠጠው በዚሁ መረጃው እንደገለፀው፤ በድርቅ ለተጎዱ የቦረና ወገኖች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን በሚልኩት ገንዘብ የዕለት ደራሽ የሚሆን ነገር በማቅረብ ላይ ነው።

በአንድ ቀን ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ወደ አስር መኪና የሚሆን የዕለት ደራሽ ምግብ ወደ ስፍራው እየደረሰ ነው ያለው ማስተር አብነት፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ካላው ላይ በመቀነስ ለእነዚህ ዜጎች በመድረስ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

በተለያዩ ወረዳዎች በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የተለያዩ ዕርዳታዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል።

ቦታው ላይ ያለው ሁኔታ በጣም ልብ የሚሰብር ነው፤ በውሃና በምግብ እጥረት ምክንያት አረረጋውያን እየተጎዱ ስለሆነ ሁሉም ሠው አቅሙ በፈቀድለት መጠን ሊያግዝ ይገባል ብሏል።

በሃይማኖት ከበደ
ባለሀብቶች በ‹‹ድሮን›› ቴክኖሎጂ ላይ መሠማራት ይችላሉ
************
(ኢ ፕ ድ)
ባለሃብቶች ከአቪዬሽን ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ላይ መሠማራትና የድሮን አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ:: በኤሮ ስፔስ ማኑፋክቸሪንግ ላይም ባለሃብቶች መሳተፍ የሚችሉበት ዕድል ተፈጥሯል::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93379
“የዓድዋን ድል በመዘከርና በዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ ለሌላ ድል እንዲሰለፉ ማድረግ ያስፈልጋል”
– ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የዓድዋን ድል በሚመጥን መልኩ በሚገባ በመዘከርና በዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ ለሌላ ድል እንዲሰለፉ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ተናገሩ።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዓድዋን ድል ከማክበር አንጻር እስካሁን የመጣንበት ሂደት እንደታሪኩ ግዙፍነት አይደለም።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93375
127ኛውን የዓድዋ በዓል በታሪካዊው ይስማ ንጉስ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)
127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊው ይስማ ንጉስ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፈ አቶ አባይ መንግስቴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በክልል ደረጃ ታሪካዊ በሆነውና የውጫሌ ውል በተፈረመበት ይስማ ንጉስ በድምቀት ለማክበር የተለያዩ የዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93378
በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን ቦረና ዞን ገብተዋል
***************
(ኢ ፕ ድ)

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን ቦረና ዞን ገብተዋል፡፡

እንደ ኦቢኤን ዘገባ ልዑክ ቡድኑ ከድርቅ ማገገም በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ከነዋሪዎቹ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ስምንተኛው የአፍሪካ ተማሪዎች ምገባ ቀን እየተከበረ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)

ስምንተኛው አገረ በቀል የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን " የአገር ውስጥ የምገባ ፍጆታ ግዥ ስረአትና ቀጠናዊ የአቅርቦት እሴቶችን በማሳደግ ቀጣይነት ያለው አገር በቀል  የትምህርት ቤት ምገባን ማሻሻል" በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመከበር ላይ ነው።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር አገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎችን ጤንነት ለመጠበቅና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚያግዙ ተግባራት ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ አህጉርም ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚደግፍ እንደሆነ ጠቅሰዋል። 

ኢትዮጵያ ከአምስት ነጥብ ሶስት ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን እየመገበች መሆኗን አስታውቀዋል።

የብራዚል አምባሳደር  በኢትዮጵያ ጃንዳራ ፌረር ዶሳንቶስ፣ የትምህርት ቤት ምገባ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ የአመጋገብ ስርአትን የሚጠብቅ እንዲሁም የትምህርት ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎችን የሚደግፍ ነው ብለዋል።

በዚህ ዙሪያ ብራዚል የዳበረ ተሞክሮ እንዳላትና ይህንኑ ልምድ ለአፍሪካ አገራት ለማጋራትና ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ፣  ተማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣  በአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሞሐመድ ቤልሆሲንና የአለም አቀፍ ድርጀቶች ተወካዮች  እየተሳተፉ ይገኛሉ። 

በአዲሱ ገረመው