“የሕዝባችንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንሰራለን”
-አቶ ጎይቶኦም በርሀ የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይን ሕዝብ ከችግር ለማላቀቅና በክልሉ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በክልሉ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ ሕጋዊ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡
በትግራይ የሚመሰረተው የሽግግር መንግሥት ከትግራይ ውጭ ያሉ ፓርቲዎችን ያቀፈና በውይይት የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=92834
ወቅታዊ፣ትኩስና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ይከተሉ‼️
👉የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ፤ https://twitter.com/PressEthio
👉 የዩትዩብ ቻናላችንን ስብስክራይብ ያድርጉ፤ https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
👉 ቴሌግራም ቻናላችንን ስብስክራይብ ያድርጉ ፤ https://t.me/ethpress
👉 የኢፕድ ድረ ገጽን ይጎብኙ ፤ https://www.press.et

ከአበባና ፍራፍሬ ዘርፍ ከ407 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
***************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ከሆልቲካልቸር ዘርፍ ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወጪ ንግድ ከ407 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የሆልቲካልቸር ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብደላ ነጋሽ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሆልቲካልቸር ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እየተሻሻለና እየጨመረ ነው ፡፡ ባለፉት ስድስት ወራትም ከአበባ፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ የወጪ ንግድ ከ407 ሚሊዮን 643 ሺህ ዶላር በላይ ተገኝቷል፡፡
.
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=92852

በክልሉ በስድስት ወራት 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 ግማሽ የበጀት ዓመት ሶስት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ ጉዱራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 ዓ.ም አስር ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በስድስት ወራት አፈፃፀም ሶስት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ይህም ከእቅዱ አንጻር 70 ከመቶ ነው፡፡
ከባለፈው ተመሳሳይ የግማሽ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው የገለፁት የቢሮ ሃላፊው፤ በ2015 ዓ.ም እጅግ የሰፋ እና የተለጠጠ ዕቅድ መያዙንም ጠቁመዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=92847

"ኢትዮጵያ የጉባኤውን ተሳታፊዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተቀብላ በደስታ ሸኝታለች" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
👉 ጉባኤውን 1ሺህ ጋዜጠኞች ሽፋን ሰጥተውታል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከየካቲት 11 እስከ 12 ቀን በተካሄደውን 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎችን ጉባኤ ተሳታፊዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተቀብላ ማስተናገዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታወቀ።
የህብረቱን ጉባኤን ከአንድ ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን ሰጥተውታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መልስ አለም እንደገለጹት፣ ጉባኤው ስኬታማ ነበር፣ በሚዲያዎች በኩልም አስፈላጊውን ሽፋን አግኝቷል።
ኢትትዮጵያ የጉባኤው ተሳታፊዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተቀብላ በደስታ ሸኝታለች። በጉባኤ ላይ አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆኑ ከሌሎች አህጉራት የመጡ በርካታ ሀገራት ተሳትፈዋል።
በጥቅሉ 53 ሀገራት ተሳታፊ ነበር፣ የ29 ሀገራት መሪዎችም ተገኝተዋል፤ የ14 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 358 የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማት መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል። 297 ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መምጣታቸውንና 43 የቻርተር በረራዎች እንደነበሩ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
የፓን አፍሪካኒዝምን መንፈስ እንደገና ያነቃቃ ነበር ያሉት አምባሳደሩ፣ የኢትዮጵያ መሪዎች ከተለያዩ በርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል።
እንደ አምባሳደሩ ማብራሪያ፣ ጉባኤን 1ሺህ ጋዜጠኞች ሽፋን ሰጥተውታል። ከሀገር ውስጥ 332 ጋዜጠኞች ሽፋን መስጠታቸው ገልጸዋል ምስጋና አቅርበዋል። ጉባኤ አስፈላጊውንና በቂ ሽፋን እንደተሰጠውም ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ

አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ-አቢጃን-ኒው ዮርክ የሚያደርገውን የቀጥታ በረራ በድጋሚ ሊጀምር ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ-አቢጃን-ኒው ዮርክ የቀጥታ በረራ ከግንቦት 21 ቀን 2015 ጀምሮ በድጋሚ እንደሚጀምር አስታወቀ።
በረራው እ.አ.አ ከሰኔ 2019 ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት እ.አ.አ መጋቢት 2020 መቋረጡን አመልክቷል።
ወደ ኒው ዮርክ የሚደረገው የቀጥታ በረራ በድጋሚ እ.አ.አ ጥቅምት 2020 በቶጎ ሎሜ በኩል ተጀምሮ እንደነበር ገልጿል።
ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሚጀመረው የአዲስ አበባ- አቢጃን-ኒው ዮርክ የቀጥታ በረራ በሳምንት ለአራት ቀናት እንደሚደረግ አየር መንገዱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው “ የድጋሚ በረራው መጀመር አስደሳች ነው፤ ለመንገደኞችም ተጨማሪ አማራጭ የሚሰጥ ነው” ብለዋል።
በረራው በአሜሪካ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የአየር ትራንስፖርት ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል።
በተያያዘ ዜና አየር መንገዱ ከግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አሜሪካዋ አትላንታ ከተማ አዲስ የመንገደኞች በረራ እንደሚጀምር ገልጿል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች እና የካርጎ መዳረሻዎች እንዳሉት በመግለጫው አመልክቷል።

ባለሀብቶች በአቪዬሽን ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
**************
(ኢ ፕ ድ)
ለትራንስፖርት ተደራሽ ባልሆኑ የአገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ በትንንሽ አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ለመድረስ እንዲቻል ባለሃብቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው እንዲሰማሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ በሰጡት መግለጫ የአየር ትራንስፖርት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሁለንተናዊ እድገት ሚናው የጐላ ነው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አራት አለም አቀፍ ኤርፖርት ደረጃ የተሰጣቸውን ጨምሮ 22 መደበኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋትና የህዝብ ቁጥር አንጻር በቂ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ባለሃብቶች ለትራንስፖርት ተደራሽ ባልሆኑ የአገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ በትንንሽ አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ለመድረስ የሚያስችሉ ግንባታዎች ላይ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል። ለቱሪዝም እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአቪዬሽን ሬጉሌሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ምስራቅ ጥላሁን በበኩላቸው፣ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የሚሰማሩ የከተማ አስተዳደሮች፣ ክልል መስተዳድሮችና የግል ባለሀብቶች ወደ ኢንቨስትመንት የሚሰማሩበት የአሰራር ማቀፍ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የሚታወስ ነው።
በሞገስ ተስፋ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተከናውኗል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሰታወቀ።
አሰተዳደሩ ባለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምና በቀጣይ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተካሂዷል። በመደበኛ፣ ወቅታዊና ከባድ ጥገና በአጠቃላይ 5,123 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራ ተከናውኗል።
በበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ለተከናወኑ ተግባራት 26.27 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል።

የፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ መኖሪያ ቤት የነበረው ታሪካዊ ቅርስ ዕድሳት ተጠናቆ ተመረቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካ ኤምባሲ ከዓለም ቅርሶች ፈንድ ጋር በመተባበር በአሜሪካ ግቢ የሚገኘውን በፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የታነፀ ታሪካዊ ሕንፃ አድሶ አስመረቀ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካን ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ የአሜሪካ ኤምባሲ ከዓለም ቅርሶች ፈንድ ጋር በመተባበር ታሪካዊ ቅርሱን የማደስ ሥራ አጠናቆ አስመርቋል። https://www.press.et/?p=92930

የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ለሆቴል ዘርፉ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተገለጸ
***************
(ኢ ፕ ድ)
36ተኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን የሆቴል ዘርፍ በማነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ሲሉ ኢትዮጵያን ስካይላይትና የሒልተን አዲስ አበባ ሆቴሎች አስታወቁ።
https://www.press.et/?p=92907

የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ የባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለው ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጄኔቫ ቢሮ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው በጄኔቫ የተመድ ቢሮ ዳይሬክተር ጄኔራል ለሆኑት ታቲያና ቫሎቫያ የሹመት ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከዳይሬክተር ጄኔራሏ ጋር በነበራቸው ውይይት መንግሥት በጄኔቫ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጸዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው ጄኔቫ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ያኒት አበራን ጨምሮ የሚሲዮኑ ባልደረቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ በቅርቡ በተደረገው የአምባሳደሮች ሹመት ወደ ጄኔቫ ከመዛወራቸው በፊት በአውስትራሊያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎጂ ሆነዋል
👉 ሁለት ሚሊዮን 200 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል
👉 ከ604 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግሥት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።
በድርቁ ከሁለት ሚሊዮን በላይ እንስሳት መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተጠቁሟል።
https://www.press.et/?p=92996