Ethiopian Media Authority
3.01K subscribers
2.93K photos
188 videos
8 files
1.31K links
This channel is an official channel of Ethiopian Media Authority (EMA).
EMA is an autonomous government organization accountable to the House of Peoples’ Representatives of the FDRE.
Download Telegram
ባለሥልጣኑ በሚያከናውናቸው የሚዲያ ክትትል ስራዎች ዙሪያ የለታሪክ ኢትዮጵያ የራድዮ አድማጮች እና የሚዲያ ተከታታዮች ማህበር ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከለታሪክ ኢትዮጵያ የሬዲዮ አድማጮች እና የሚዲያ ተከታታዮች ማህበር አባላት ጋር ባለሥልጣኑ በሚያከናውናቸው የክትትል ስራዎች እና የክትትል አግባቦች ላይ ያተኮረ የውይይት አድርጓል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ማህበሩ ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው ስራዎች እያደረገ ስላለው ተሳትፎ አድንቀው፤ማህበሩ በሀገራዊ ምክክር፤በምርጫ እና ቀጠናዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ባለሥልጣኑ ለሚሰራቸው የሚዲያ ክትትል ስራዎች የሚያደርገውን የአጋዥነት ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም በመገናኛ ብዙኃን ስነ-ምግባር መርሆዎችና በሚዲያ ህጎች ላይ ያተኮረ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ከማህበሩ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
🙏21🕊1💯1
በስድስት ወራት ውስጥ ለ39 ተቋማት የፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጠ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ለ39 የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገልግሎት ተሰጥቷል።

በባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙኃን ፍቃድ፣ ምዝገባና እውቅና ዘርፍ በመመዝገብ የፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገልግሎት ከተሰጣቸው መካከል 23ቱ በብሮድካስት፣ በቋሚ የዜና ወኪል እና በአጭር ግዜ ዘገባ ፍቃድ የወሰዱ ድርጅቶችና ተቋማት ሲሆኑ፤ 16 ያህሉ ደግሞ በማስታወቂያና በሚዲያ ፕሮግራም ዝግጅት የስራ ዘርፎች ነው።
👍3
እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
🙏7
በኢትዮጵያ 309 መገናኛ ብዙኃን ተመዝገበውና ፈቃድ አግኝተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ

በአሁኑ ስዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህጋዊ መንገድ ፈቃድና ምዝገባ አግኝተዉ የሚንቀሳቀሱ የብሮድካስት፣ የበይነ መረብ፣ የህትመት እና የዉጭ መገናኛ ብዙኃን ቁጥር 309 ደርሷል፡፡

በዚህም መሰረት 175 የብሮድካስት፣ 20 የህትመት፣ 35 የዉጭ ሚዲያ ክሮስፖንዳንት፣ 73 የበይነመረብ፣ አምስት የክፍያ ኢንተርኔት ብሮድካስት፣ አንድ ነፃ የኢንተርኔት ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በባለሥልጣኑ ምዝገባ እና ፈቃድ አግኝተዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 254ቱ በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 55ቱ ደግሞ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
በባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራትም ለ39 የመገናኛ ብዙኃን በፍቃድና ክትትል ዘርፍ የፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፉት ዓመታት የዘርፉን እድገት ለማፋጠን ባካሄደዉ የህግ እና የአሰራር ለዉጥ መገናኛ ብዙኃኑ በቁጥር፣ በዓይነት እንዲሁም በተደራሽነት እድገት እንዲያስመዝግቡ አስችሏል፡፡

በመሆኑም በቅርብ ዓመታት በተደረገው የሚዲያው ምህዳር መሻሻል መገናኛ ብዙኃን ለዜጎች መረጃ የማግኘት መብትና ብቁ መገኛ ብዙኃን በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችሉ በኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል አማካኝነት ለጋዜጠኞች እየተደረገ ያለው ፕሮፌሽናል ስልጠና ስራ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙኃን አዋጁንና ሌሎች የሀገሪቱን ህግጋት መሰረት በማድረግ የብሮድካስት አገልግሎት የፈቃድ ሁኔታን ይወስናል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
ጥር 13/2018 ዓ.ም
👍81😍1
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በየዓመቱ ለሚያዘጋጀው የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ደረጃን የሚያሳይ ሪፖርት ያወጣል፡፡ ለሪፖርቱ እንዲረዳ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲመለሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfZy2gf0-36gRcPwjmcI81jRUyekMQyclKV3u8c21sgM21K2A/viewform?usp=header

____

Gaafannon kun abbaan taayitaa miidiyaa itoophiyaa gabaasa waggaa tamsa’iinaa haasaa jibbinsaa fi odeeffannoo sobaa sassaabuuf kan qopha’eeadha. Gaafanno kana guutuuf eeyyamamoo waan taataniif galatooma.

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScJ2h97AGYk-y7DWdwxtkvgTKvb2SzBDWJzL5ehcHTViH00zw/viewform?usp=header

____

በዓል መዚ መራኸብቲ ሓፋሽ ኢትዮጵያ በቢዓመቱ ምውዛዕ ዘረባ ፅልኢትን ስኑዕ ሓበሬታን ዘለሉ ብርኪ ዘርኢ ሪፖርት የዳልው እዩ፡፡ ምእንታን ንሪፖርቱ ክሕግዝ ዝስዕቡ ሕቶታት ንክምልሱልና ብክብሪ ንሓትት፡፡

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdCphcv_rlTfjEyg52iIX8GDr7tYdSNnG3PlEL_cTlsPJj92A/viewform?usp=header
1👍1😍1
የኢትዮጵያ አርታዒያን ማህበር ለተሻለ የሚዲያ ምህዳር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጋር እንደሚሰራ አስታወቀ

የኢትዮጵያ አርታዒያን ማህበር Editors Guild Ethiopia (EGE) በኢትዮጵያ ለተሻለ የሚዲያ ምህዳር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ማህበሩ ይህንን ያስታወቀው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀይማኖት ዘለቀ እና የባለስልጣኑ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በብሔራዊ ጥቅሞችና አጀንዳዎች፣ የቀጣናዊ፣እህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ አገራችን ያላትን ወሳኝ ሚና በብቃት ለመወጣት የምታደርገውን ጥረት በቂ ግንዛቤ እንዲያዝበት በማድረግ ረገድ ሁለቱ አካላት በትብብር በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ አርታዒያን ማህበር ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ ደረሰ ንጋቱ ማህበሩ በአገራችን የሚዲያው ዘርፍ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራትና የአለም አገራት ካሉ የሚዲያ ባለሙያዎችና አርታኢያን ....

ተጨማሪ ያንብቡ : https://www.facebook.com/share/p/17i9d5VFQA/
👏1