EthioTube
8.49K subscribers
10.2K photos
56 videos
7 files
3.3K links
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
Download Telegram
በቆቦ ከተማ ለህወሀት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በቆቦ ከተማ በጋሪ ብረቶች ውስጥ ተደብቆ ለህወሃት ቡድን ሊደርስ የነበረ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ፣ በከተማው ፓሊስና በሕዝባዊ ሚኒሻ ሠራዊቱ አማካኝነት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅ /ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታደሰ ተሰሜ በበኩላቸው፤ ጋሪው የተሰራው ሙሉ በሙሉ ውስጡ ክፍት በመሆኑ፤ ሥም የተፃፈበት ብር በእያንዳንዱ ብረት በማድረጋቸው ላለመያዝ የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም የቆቦ ከተማ ህዝብም ይሁን የፀጥታ አካሉ በመግባባቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ከቆቦ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
ኮለሬል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆነት ኮለሬል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ የፌደራልጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።

ኮለሬል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበተ በኋላ፤ በነጋታው  ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው ለ6 ወር በገላን ፓሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታሶሮ እንደነበርና ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስር ላይ እንደነበሩ ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

በኮለሬል ገመቹ አያናን በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል  የምርመራ መዝገብ እንዳልተከፈተበት የፌደራል ፖሊስ ቀርቦ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮሚያ ፖሊስ  ቀርቦ በኮለሬል ገመቹ የእስራት ሁኔታን እንዲያስረዳ ታዞ በትናንትናው የችሎት ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለዛሬ በይደር ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ መርምሮ ኮለሬል ገመቹ አያና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
በአፍሪካ ቀን ላይ ሆነን ለአህጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
"በዘንድሮው የአፍሪካ ቀን ላይ ሆነን ለአህጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን" አሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የሚከበረውን የአፍሪካ ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም "አያቶቻችን የነበራቸውን ሰላማዊ፣ የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ቁርጠኛ ነን" ብለዋል።

የአፍሪካ ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ግንቦት 25 በየዓመቱ ይከበራል።

ቀኑም የዛሬው የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሆኖ የተመሰረተበትን ቀን መሰረት በማድረግ መከበር ጀምሯል።

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
በኢትዮጵያ ከአመታት በፊት የተነገረው የነዳጅ ማውጣት ጉዳይ የውሃ ሽታ ሆነ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
በኢትዮጵያ በወርቅ፣ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እና ልማት ተሰማርተው የነበሩ 55 ኩባንያዎች ፈቃድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንዲቋረጥ መደረጉን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ተስፋ በጣለባቸው በሁለቱ ዘርፎች ፈቃድ ያላቸው ሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኩባንያዎቹ ፈቃድ መቋረጥ ይፋ የተደረገው፤ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ የመስሪያ ቤታቸውን ያለፉትን ዘጠኝ ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ትናንት ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ነው። በሪፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ብቻ 52 የወርቅ እና የሌሎች ማዕድናት ፈቃድ ተቋርጧል። ለተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እና ልማት የተሰጡ ሶስት ፈቃዶችም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲቋረጡ መደረጉንም አክለዋል።

ፈቃዳቸው ከተቋረጠባቸው ኩባንያዎች መካከል በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ እና ልማት ፈቃድ የነበረው የብሪታንያ ኩባንያ እንደሚገኝበት በሚኒስቴሩ ሪፖርቱ ተጠቅሷል። “ኒውኤጅ” የተባለው ይኸው ኩባንያ ፈቃዱን ያጣው “ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ” መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር በሪፖርቱ አስታውቋል።

የቻይናው ፖሊ ጂሲኤል ፔትሮሊየም ሆልዲንግ ኩባንያ አስር ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በሶማሌ ክልል ነዳጅ ፍለጋ የጀመረ ነው። 

ከአራት ዓመታት በፊት በቁፋሮ ላይ ከነበሩ  ጉድጓዶች መካከል ሦስቱ ተጠናቀው ድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት መጀመሩ የተበሰረውም በዚሁ ኩባንያ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ የአገሪቱ የዘመናት የነዳጅ ፍለጋ ስኬት ታየበት የተባለው ሙከራ እንደታለመው አለመጓዙን መንግስት አምኗል።

ይህን ዜና ተከትሎ በሁለት ዓመታት ይጠናቀቃል የተባለ 767 ኪ.ሜ ወደ ጂቡቲ የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ለመገንባት ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ይሁን እንጂ አገሪቱ ወደ ውጭ ለመላክና ገቢ ለማግኘት ተስፋ የጣለችበት ጋዝና ነዳጅ እንደ ውጥኗ መጓዝ አለመቻሉን የማዕድን ሚንስትሩ ታከለ ኡማ አልሸሸጉም። 

ፖሊ ጂሲኤል የተባለው ኩባንያ አራት የፍለጋ ስምምነትና አንድ የልማትና ምርት ፈቃድ ያለው ሲሆን፤ ኩባንያው በዘጠኝ ዓመታት ስራውም የሚጠበቅበትን ስራ አላከናወነም። ይህም በመሆኑ አገሪቱ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተጠቁሟል። በአገር ደረጃ የተያዘውና ዘርፈ  ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት የተፈጥሮ ጋዝ ልማት በተያዘለት ጊዜ እውን እንዳይሆን አድርጓል።

የፋይናንስ ውስንነነትና የቴክኒክ አቅም ችግር አለበት የተባለው ፖሊ ጂሲኤል ኩባንያ  እስከ ሰኔ መጨረሻ 2014 ዓ/ም. ማስተካከያ ካላደረገ ስምምነቱ እንደሚቋረጥ ተነግሮታል።  ሪፖርተር ጋዜጣ  መጋቢት 18 ይዞት በወጣው ፅሁፉ ኩባንያው ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ለማምረት ከሚያስፈልገው አጠቃላይ መዋዕለ-ነዋይ ውስጥ 30 በመቶውን ከሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በፊት በብሔራዊ ባንክ እንዲያስመዘግብ ማስጠንቀቂያ ደርሶታል። 

ምንጭ፦ ዋዜማ , ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በቅርቡ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ CPj ጠየቀ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በቅርቡ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና ባለስልጣናት የፕሬስ አባላትን ትንኮሳ ማቆማቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ሲፒጄ በትናንትናው እለት አስታውቋል።

በአማራ ክልል መንግስት ከግንቦት 19 ጀምሮ ቢያንስ 11 ጋዜጠኞችን እና የሚዲያ ሰራተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን “የህግ አስከባሪ ኦፕሬሽን” ሲል በጠራው እና በሕገወጥ እንቅስቃሴ ከ4,500 በላይ ሰዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር አውያለሁ ማለቱን ሲፒጄ አስታውሷል ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የአሻራ ሚዲያ እና የንስር ብሮድካስት ሰራተኞችን ጨምሮ፣ የኢትዮ ነቃት ሚዲያ መስራች እና ዋና አዘጋጅ መስከረም አበራ የግል ብሮድካስቲንግ ገበየሁ ሚዲያ መስራች እና ባለቤት አቶ ሰለሞን ሹመዬ እንደሚገኙበት ሲፒጄ ገልፆል።

ግንቦት 7 ከቀኑ 5፡30 ላይ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኘውን አሻራ ሚዲያ ስቱዲዮን በመውረር አምስት ሰራተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአሻራ ሚዲያ ዳይሬክተር ኤልያስ ደባሱ እና የጋዜጠኛ ጋሻዬ ንጉሴ ባለቤት አቶ ብሌን ጫኔ ለሲፒጄን በስልክ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ወቅት ፖሊስ ማዘዣ አለማሳየቱን እና ላፕቶፖች እና ውጫዊ ሃርድ ድራይቭን ጨምሮ የቢሮ ቁሳቁሶችን መውሰዱን ኤልያስ ለሲፒጄ ተናግሯል። በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች ለአጭር ጊዜ መጎብኘት የቻሉት ብሌን ግንቦት 20 ጧት ከባህርዳር ከቤተሰብ ወይም ከጠበቃዎች ጋር ሳይገናኙ 185 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰሜን ንፋስ ስልክ መውጫ ትንሽዬ ከተማ ወደሚገኝ እስር ቤት ተዛውረዋል።

በቅርቡ ቢያንስ 11 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች መታሰራቸው፣ አሁንም የሚያሳየው መንግስት ለፕሬስ ነፃነት እና የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚከለክል መሆኑን እንደሚያሳይ በመጠቆም "ባለሥልጣናት ሁሉንም ያለምንም ክስ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስራት፣ ጭቆና እና ሳንሱር ሳይፈሩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማረጋገጥ አለባቸው።" ሲሉ የ Cpj የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጀላ ተናግራለች።

ምንጭ፦ ሲፒጄ

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አሳወቁ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ትናንት ማምሻውን ባሰፈሩት መልዕክት አብን ባለፈው የካቲት አካሂዶት በነበረው ጊዜያዊ የአስፈፃሚ ሪፎርም ላይ ንቅናቄው በቀጣይ 3 ወር ውስጥ የሚያካሂደው ሪፎርም ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ወደ ሥራ አስፈፃሚ እንዲመለሱ የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኖ እንደነበር አስታውሰዋል።

አክለውም ”ወደ አመራርነት የመመለስ ፍላጎት ባይኖረኝም የድርጅቴ ውሳኔ ስለነበር ውሳኔውን ተቀብየው ቆይቻለሁ።” ብለዋል።

”ለአጭር ጊዜ ብየ የተመለስኩበት ጊዜ ስለተጠናቀቀ፣ እንዲሁም ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በምገልፃቸው ምክንያቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአብን ሥራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ የለቀቅሁ ሲሆን፤ በማኮ አባልነት ግን የአብን ሪፎርም በስኬት እስኪጠናቀቅ የምቀጥል ይሆናል።“ ሲሉም ገልፀዋል።

ዶ/ር ደሳለኝ “የንቅናቄው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አብን ተጠናክሮ ሲቆም፤ ደግሞ ልክ ከአብን ሊቀ መንበርነቴ በገዛ ፈቃዴ እንደለቀቅሁት ኹሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴንም በገዛ ፈቃዴ በመልቀቅ አዳዲስ መሪዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ መወሰኔን እገልፃለሁ።“ ያሉ ሲሆን ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል።


የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 27 አትሌቶች ይሳተፋሉ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
ኢትዮጵያ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ግንቦት 19 እና 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ27 አትሌቶች ትወከላለች


27 አትሌቶችን ጨምሮ 32 አባላት ያሉት የሻምፒዮናው ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ ዳሬ ሰላም ማቅናቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አትሌቶቹ በሁለቱም ጾታዎች ከ100 ሜትር እስከ 5 ሺህ ሜትር ባሉ ርቀቶችና የሜዳ ተግባራት በ20 የውድድር አይነቶች እንደሚሳተፉ ገልጿል።

ከ18 ዓመት በታች 15 እንዲሁም ከ20 ዓመት በታች 12 አትሌቶች ይሳተፋሉ።

በሻምፒዮናው ላይ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶች ከሐምሌ 25 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በኮሎምቢያ ካሊ በሚካሄደው የዓለም የ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የመሳተፍ እድል እንደሚያገኙ ተነግሯል።

ምንጭ፦ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
በርካታ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት እና ባዛር ሊከፈት ነው

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

ከ250 በላይ ዓለማቀፍ የንግድ ተቋማት እና የአገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ዓለማቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ሊከፈት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 12ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ግንቦት 25 ቀን 2014 በይፋ ይከፈታል፡፡

“የኢትዮጵያን ይግዙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን እና ገበያ ልማት ማዕከል ለአምስት ቀናት ይቆያል።

የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ለተሳታፊዎች የገበያ ትስስር፣ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጥምረት እና በአገር ውስጥ እና በውጪ አምራቾች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ማድረግን አልሞ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ ከኮቪድ ሥርጭት በኋላ የመጀመሪያው መሆኑን ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናይጄሪያ ገብተዋል

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የናይጄሪያዋ ዋና ከተማ አቡጃ መድረሳቸውን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram: https://t.me/ethiotubemedia