ጠይም | Teyim 🌹
4.38K subscribers
133 photos
18 videos
1 file
24 links
Download Telegram
ጥሩ ሽልማት ያለው አጭር ግጥምን በተረዱት መልኩ ተንትኖ የመጻፍ #ቻሌንጅ ከ #ጠይምበረንዳ!

አገር ውስጥ ላላችሁ ሶስት አሸናፊዎች አሪፍ ሽልማት ይኖረናል። እንዲሁም ጥሩ የተጻፉትን ፕሮግራማችን ላይ በድምጽ እናቀርባለን።

ከዚህ በታች ያለውን ባለ አንድ ስንኝ ቅኔያዊ ግጥም፣ ሀሳብ በተረዳችሁት መልኩ (ስምና ወርቅ አውጥታችሁ) በዝርው፣ በወግ፣ ወይም በአጭር ታሪክ ደንብ፣ ይማርካል ባላችሁት መልኩ ተንትናችሁ ጽፋችሁ እስከ አርብ በአስተያየት መስጫው ላይ አኑሩት። የጽሁፍ መጠን ቢያንስ ሁለት አንቀጽ። ከዚያ በላይ እስከፈለጋችሁት መርዘም ይችላል።

የመጨረሻ ቀን: አርብ መጋቢት 10 ቀን 2012

ርዕሱ: የጉዞ ተስፋ ወደ 'ተስፋ ምድር'
.
.
.
ይሸሸጋል ማ ዘንድ-ሮ-ሮም - አትሰማም ከብዷል ኑሮ ለ'ሷም!

/ዮሐንስ ሞላ/

@yohanesml ጽሁፋችሁን በዚህ መላክ ትችላላችሁ።

ጠይም በረንዳ - Chocolate Porch (ሰብስክራይብ ካላደረጋችሁ፣ ብታደርጉ በሳምንት እሁድ ለግማሽ ሰዓት፣ አትቆጩበትም የምንለውን ፕሮግራም እናስደምጣችኋለን። https://www.youtube.com/channel/UCm4O2Giga2vulDjeP7edJCQ)

ተሳተፉ! ወዳጆቻችሁ ይሳተፉ ዘንድ ሼር አድርጉት!!
🤎 ታርፉበታላችሁ! ታተርፉበታላችሁ! #ጠይምበረንዳ
የገና በዓልን ለምታከብሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ እያልን፣ በዓሉን በማስመልከት ይኽንን ልዩ ዝግጅት እንጋብዛለን። በዓሉን በጥሩ ስሜት እንድትቀበሉት እና እንዲያልፍ እንመኛለን። #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ።
ከገጠሩም ከከተማውም የተቆነጠረ አዝናኝ ጨዋታ። #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታተርፋላችሁ። ታርፋላችሁ።
በዓሉን ለምታከብሩ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ከወደዳችሁት ወዳጆቻችሁንም ወደ በረንዳችን ጋብዟቸው።
አጭር ጨዋታ ከ"ሕልም ብርሀን ዕድሜ" ደራሲ ከቤዛ (ያዴል) ትዕዛዙ ጋር። መጽሐፉንም እንሸልማለን። #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ።
አጭር ጨዋታ ከ"ሕልም ብርሀን ዕድሜ" ደራሲ ከቤዛ(ያዴል) ትዕዛዙ ጋር፤ ክፍል 2። ለ10 ሰዎች ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄም አለን። ተሳተፉ። ተሸለሙ። #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ።
🤎 በፍቅር ቀን (Valentine's Day) ጠይሙ በረንዳችን ላይ ተሰይመን፣ ከአልጋው ባሻገር ተጨዋውተናል። #ጠይምበረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ወዳጅ ዘመዶቻችሁንም ወደ በረንዳችን ጋብዟቸው። ሀሳብ አስተያየታችሁን ጻፉልን።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሁሉ ልናየውው፣ ልናስብበት የሚገባ። #ጠይምበረንዳ​ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩት። ሀሳብ አስተያየታችሁን ብታሰፍሩም ደስ ይለናል።