ጠይም | Teyim 🌹
11.7K subscribers
126 photos
17 videos
1 file
8 links
Download Telegram
to view and join the conversation
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛዛሬ ነጻነት ላበቁን ወገኖች

እንኳን አደረሰን!
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሁሉ ልናየውው፣ ልናስብበት የሚገባ። #ጠይምበረንዳ​ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩት። ሀሳብ አስተያየታችሁን ብታሰፍሩም ደስ ይለናል።
እጥር ምጥን ያሉ አሪፍ ጨዋታዎች ይዘናል። ጠይምበረንዳ​​ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ።
‹‹ ….. ኃይለስላሴ ከዙፋናቸው ወረዱ›› አለች…. ዕንባ እየተናነቃት (እናቴ ለምታውቀውም ይሁን ለማታውቀው ዕድለ ቢስ ታዝናለች)

‹‹መቼ?››

‹‹እንዴት አልሰማህም? የት ነበርክ?›› (እየተናፈጠች)

እንደ ተረት አልናገረው ታሪኬን፤ እንደዙፋን የሚያበሩ እርጥብ የቴቢ ከንፈሮች ላይ ላይ ነበሩ ከንፈሮቼ……. ቀልቤም፡፡

እነዛ ጊዜዎች… ነጋ ጠባ ‹ተነሳ ተራመድ› ሲባል፤ የተማሪ ፖለቲከኞች ፎቶ በየቦታው ሲሰቀል፣ ለእኔ ምንም አልነበሩም፡፡ ‹አማን አማን አንዶም› ሲባል፡፡ ‹አቆርቁዋዥ ይውደም› ሲባል፡፡ ሁሉ ሲባል….. ልቤ በመውደድ ቀጭን ገመድ አዲስ አባ ሰማይ ላይ ተሰቅላ ነበር፡፡

ሲባል ‹ተነሳ› ከአልጋዬ ቀና ብዬ መስኮት ከፍቼ በጠዋት ፀሀይ ስር ወዳጄ ቴቢን ደብቆ የያዘውን የእናቷን የትደነቂያለሽን ቤት ማየት፡፡ በችኮላ ፊቴን መታጠብ፣ ልብሴን መልበስ…..

ሲሉ ‹ተራመድ› ቁርሴን ሳልጨርስ መንገድ አቁዋርጬ ቀዝቃዛ ሃረጎች ያቆፈነኑት በረንዳ ላይ በር እያንኳኳሁ …. እሷም በሩን ከእናቷ ቀድማ ከፍታ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ቤቷ ጀርባ አልፈን፣ የጎረቤቷን የሰይፉን ቤት እያየን ጥቁር ቆዳዋን ከእናቷ ደብቃ ስስማት ሎሚ ሎሚ አለኝ አፌን . . ."

አዳም ረታ "መረቅ"

🧡
የምንሰበውን አየር መምረጥ ብንችል ፤ እኔ ለመኖር የሚያስፈልገኝ ከጥምልምል ፀጉሮቹ መካከል የምምገው የአናቱን ጠረን ነው ብዬ እርሱን እንደምመርጥ ማን ያምናል ?

በስስት በማቅፈው ራሱ ላይ ባሉ ፀጉሮቹ መካከል በምቀብረው አፍንጫዬ በኩል ለእልፍ ዘመን የሚበቃ ሃሴት እንደምምግ ብናገር ማንስ ይገባዋል?

መባረክ በቁንዳላው መሃል በፀጉሩ ዘለላዎች ልክ እንደሆነ እንኳን ሌላው ሌላው እርሱ ራሱስ መች ያውቃል?

ግን እኔ አውቅለት የለ? 💙💙💙

(ኤልሳ ሙሉጌታ)
በአማን ነጸረ ትግራይ ላይ በአካል ካዩት እና ከሰሙት ያካፈሉንን ዳሰሳ ይዘናል።ጠይም በረንዳ​​ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ። ወዳጆቻችሁንም ጋብዟቸው።
ስትመጪ
ክንዴ በስተራስጌ ክንፍ አቆጠቆጠ
የደጅ አፌ ዳገት፣ ዐይኔ ፊት ቀለጠ

ስትሄጂ
ጸሐዩ ፈረጠ፣ ቁልቁለቱ አበጠ
የቀዬው አብሪ ትል በጽልመት ተዋጠ።

በዳፍንታም አለም፣ ጠባቂ ሲተጋ
እንኳን ቀን ጨልሞ፣ ሌሊቱ ሲነጋ...

መምጣትና መሄድ ቀን ይቀያይራል፥
ምላስሽ ያጎድፋል፣ ምላስሽ ያጠራል
ትንፋሽሽ ያጠፋል፣ ትንፋሽሽ ያበራል።

(ዮሐንስ ሞላ)

💟 💟 💟
በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የተፈጸመውን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የያዝነውን በረንዳችን ላይ አቅርበነዋል። ጠይምበረንዳ​​ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ። ወዳጆቻችሁን ወደ በረንዳችን ጋብዟቸው።
የኢትዮጵያን የዘር ጭፍጨፋ በተመለከተ የGenocide Watch የዘር ጭፍጨፋ ደረጃዎችን አይተናል። ጠይም በረንዳ ላይ ብትቆዩ ታርፋላችሁ። ታተርፋላችሁ። ሌሎች ይሰሙ ዘንድም ሼር በማድረግ ጋብዟቸው።
አብራችሁን ብትቆዩ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ሌሎች ይሰሙ ዘንድም ሼር በማድረግ ጋብዟቸው።
በቅርብ ጊዜ በየቦታው የሚነሱ የእሳት አደጋዎችን በተመለከተ በረንዳችን ላይ ተጫውተናል። አብራችሁን ብትቆዩ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ።
እውን ድምፄ ዋጋ አለው?

"እስከዛሬ ስንቴ ድምፄን ሳሰማ ማን ሰምቶኝ ያውቅና ነው አሁን ድምፅሽ ዋጋ አለው የሚሉኝ? እንዴት? ማንን አምናለሁ ?
እውን በምርጫ ብቻ? ሂሂ የማይመስል ነገር" እያልኩ እያሰብኩ ነበር ለመምረጥ ወደምመዘገብበት ጣቢያ የሄድኩት
ከሩቅ ጀምሮ የሚሰማ የዳዊት ፅጌ ድምፅ ተቀበለኝ
"ለውዲቷ ... ለእናት ኢትዮጵያ
ታጥቄ ጠንክሬ የምሰዋላት ነኝ ..."

የሆነ ጥግ አንዲት ሴት ወይዘሮ የአገር ባህል ልብሷን ለብሳ ቡና ታፈላለች ። አሳላፊ ረዳት አጠገቧ አለች። ፈንዲሻው ፈክቷል። ዕጣኑ ይትጎለጎላል ... ቤቱ ቀድሞ የጀበና ቡና መሸጫ ሆኖ በተጓዳኝነት የምርጫ ጣቢያ ሆኖ እያገለገለ መሰለኝ።
የባህር መዝገብ ላይ የምታሰፍር ፤ የግል መረጃን ከመታወቂያ አመሳክራ የምትመዘግብ አንዲት ሴት ... ካርዱን ፅፎ የሚሰጥ ሌላ ሰው ... ከእኔ በፊትና በኋላ የመጡ አንድ አምስት ተመዝጋቢዎች መላ አካሏ በቆርቆሮ የተዋቀረ ቤት ውስጥ አለን ...
ቡና እጠጣ እንደሁ ተጋበዝኩ ...
"ይብቃኝ አልኩ"

በህይወት ብዙ አማራጮች አሏት። ቡና መጠጣትና አለመጠጣት ... በተቻለኝ አቅም አማራጮቼን ሳሰፋ ነው የምኖረው ... የሚገድቡኝን ነገሮች አልወድም ። ይሄንን ካርድ ካልወሰድኩ ደግሞ አለመምረጥ ነው አማራጬ ... ዝምታዬ ደግሞ ምንም ዋጋ የለውም ...
ድምፄ 0.01% ም ቢሆን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ድምፅ አልባነቴ ግን በእርግጠኝነት ምንም ለውጥ አያመጣም !!!
ስለዚህ ለመምረጥ ተመዘገብኩ ...

እንደው በምናልባት ገዢው አሸንፋለሁ በሚል ልበ ሙሉነት ለፕሮፖጋንዳ ጥቅም ምርጫውን ነፃና ፍትሐዊ ካደረገው ፤
እንደው በምናልባት የመሰረቅ እድሉ ካነሰ ፤ እንደው በምናልባት ገለልተኛ ታዛቢዎች ካሉ ፤
እንደው በምናልባት ሂደቱ ግልፅ ከሆነ ፤ እንደው በምናልባት ቆጠራው ከታመነ ፤ ውጤቱ ይፋ አደራረጉ እውነት ከሆነ ...እንደው በምናልባት...

እውን በምርጫ ብቻ?

በርግጥ ምርጫ የዲሞክራሲያዊ ስርአት አንዱ መገለጫ ነው። ስልጣን በፈጣሪ በመመረጥ በመቀባት? ወይስ በኃይል በጡንቻና በአፈሙዝ? ወይስ በሕዝብ በመመረጥ? ስልጣን ከሕዝብ ይሁንታ ይመነጫል ። ስልጣን በምርጫ ብቻ።
ድምፄ ዋጋ የለውም ስል እሰጋለሁ ። ዝምታዬ ደግሞ ምንም ዋጋ እንደሌለው አውቃለሁ ። ቢሆንም ቢሆንም ...ድምፄ ተሰርቋል ለማለትም መጀመሪያ ድምፄን መስጠት አለብኝ።
ስለዚህ ለመምረጥ ተመዘገብኩ !
(በፅጌረዳ ጎንፋ )
ለክርስትና አማኞች ሁሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ።

💚💛❤
ለክርስትና አማኞች ሁሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ። ሌሎች ይሰሙ ዘንድም ሼር በማድረግ ጋብዟቸው። ሰብስክራይብ! ሀሳብ አስተያየታችሁን ጻፉልን። ወዳጆቻችሁም እንዲሰሙ ጋብዟቸው!
50 ጊዜ ቃል ገብተህ 50 ጊዜ ቃልህን ብታጥፍ፥ ለ51ኛ ጊዜ ቃልህን ትጠብቅ ዘንድ በተስፋ ትጠብቅኻለች... 50 ጊዜ ብታስቀይማት፥ 50 ጊዜ ትረሳልኻለች... 50 ጊዜ ብታጠፋ፥ 50 ጊዜ ይቅር ትልኻለች... (ዝም ብለህ ከሰማህ፥ ወላ አንተ ላስቀየምኻት 50 ጊዜያት፥ 50 ጊዜ ይቅርታ ልትጠይቅኽም ትችላለች።)

50 ጊዜ ብታጠፋና ቢቆጡህ፥ 50 ጊዜ ትሸፍንልኻለች... 50 ጊዜ ብትወድቅ፥ 50 ጊዜ አንስታህ፣ ‘ወፌ ቆመች’ ብላ ታጠነክርኻለች... 50 ጊዜ ብትጠይቃት፥ 50 ጊዜ ትመልስልኻለች... 50 ጊዜ 'ምን አገባሽ?' ብትላት፥ ለ51ኛ ጊዜ አስተያየት ትሰጥኻለች... 50 ጊዜ ጠብቃህ ብትቀርባት፥ ለ51ኛ ጊዜ ትጠብቅኻለች... 50 ጊዜ ከሰው ጋር ብትጣላ (ደብድበኽም መጣኽ ተደብድበኽ፥ ጉዳይዋ ከመጋጨትኽ ጋር ነው)፥ 100 ጊዜ ትገስፅኻለች... (ለአንዱ፥ ኹለት፤ ...በልጅነት፥ 100 ጊዜ ትቀጣሀለች።) 

“ለታክሲ” ብለህ 50 ብር ብትሰጣት፥ ግማሽ ኪሎ ስጋ ገዝታ ምሳህን ታሸበርቅልኻለች... በርሱ ተናደህ፥ 50 ጊዜ እያስታወስኸው ብትወቅሳት፥ 50 ጊዜ፥ “ምናጣሁ? ኑርልኝ!” ትልኻለች... አንተ ለበላኸው 50 ጊዜ ትመርቅኻለች... እርምህን አንድ ነገር ብታደርግላት፥ 50 ጊዜ ትቆጥርልኻለች... 50 ጊዜ በርሱ ምክንያት የሆነብህን ጉድለት እያሰበች ትሳቀቃለች... 50 ጊዜ ለቤተሰቡና ለወዳጆቿ ነግራ ታስመርቅኻለች።

1ቀን ካመመህ፥ 50 ቀን ታስታምምኻለች... 50 ዓይነት የባህል መድኃኒት አዘጋጅታ ትጠበብብኻለች... ድነህ ወጣህ ቢባል እንኳን፥ 50 ቀን ስለህመምህ ትጠይቅኻለች፤ ረስተኸው እንኳን አትረሳውም። መድኀኒት መዋጥ ራሱ እሷ ናት የምታስታውስህ... 

ረጅም እድሜና ጤና ለእናቶቻችን! በሕይወት የሌሉትም ሁሉ በሰላም ይረፉ!

መልካም የእናቶች ቀን!

ዮሐንስ ሞላ "የብርሃን ሰበዞች"
የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራች ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ነፍስ ይማር። ለቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናት ይሁን። ወ/ሮ ዘሚ የጀመረችውን ሥራ መቀጠልና ትሩፋቷን ማቆየት ከሁላችንም የሚጠበቅ ነውና፣ ኒያ ፋውንዴሽንን በምንችለው ሁሉ፥ በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ ጊዜ በመስጠት እና በበጎ ፍቃድ ሥራ እንድንደግፍ አደራ እንላለን።

የሰላም እረፍት ይሁንልሽ። እናመሰግናለን።

💚💛❤
ከጤና ባለሞያው ሲሳይ ክንፈ (PhD) ጋር፣ በኮቪድ 19 ክትባት ዙሪያ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮችን አንስተን ቆይታ አድርገናል። ጠይም በረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ።
በወንዶች ዙሪያ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነጥቦች! ጠይም በረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ። ወዳጆቻችሁንም ጋብዟቸው።
በሮፍናን "ሶስት" እንጎቻ (EP) ሙዚቃ ዙሪያ ያዘጋጀነውን ተጋበዙ። ጠይም በረንዳ ላይ ብትቆዩ፣ አጭር የእረፍት ጊዜ ታሳልፋላችሁ። ታርፋላችሁ፣ ታተርፋላችሁ። ወዳጆቻችሁም እንዲሰሙ ጋብዟቸው!
የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ነፍስ ይማር! ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ መጽናናት ይሁን።