ጤና ዓዳም- Tena Adam
5.52K subscribers
191 photos
9 videos
15 files
43 links
👉 ይህ የTelegram channel ስለ ጤናዎ በጥቂቱ ግንዛቤ ያስጨብጣል።
👉 ማንኛውንም ጤና ነክ ጉዳይ እናማክራለን
👉 ማንኛውንም ከጤና ጋር የተያያዙ የAudiovisual ሥራዎች(ፊልም፡ ድራማ፡ ድርሰት ወዘተ) የማማከር ሥራ እንሰራለን

👉 ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ጤና መድረክ/Ethiopian medical platform የመፍጠር ህልም አለኝ


📝 (ጤና ዓዳም- Tena Adam 📁📂
Download Telegram
ጥቂት ስለ ኦቲዝም..
(መጋ 22/2011)

> Autism ቃሉ (Autos) ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም (ራስ) እንደማለት ነው፤ ይህም የችግሩ ተጠቂዎች ራሳቸውን ከማህበረሰቡ በመነጠል የራሳቸውን አለም እንደሚፈጥሩ ለማመልከት ነው።

> የኦቲዝም መገለጫ ባህርያት፦ ቋሚ የሆነ ማህበራዊ ተግባቦትና ግንኙነት ሳይኖር ሲቀር፣ በሚፈለገው ልክ የንግግር ክህሎት አለመዳበርና ውስን የሆነ ተደጋጋሚ ባህሪ፣ፍላጎትና ድርጊት መኖር(RRBs) ናቸው።

> የኦቲዝም ትክክለኛ መነሻ ችግር አይታወቅም። ግን የበራሂ ችግር(genetic problem)፣ በማህፀን ውስጥ ፅንሱ አስፈላጊውን የአዕምሮ እድገት አለመጨረስ፣ በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ አካባቢያዊ ምክንያቶች(መርዛማ ውሃ፣ ምግብ፣ መድኀኒት..) እንዲሁም ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ወቅትና ከእርግዝና በኋላ የሚከሰት በሽታ ሊሆን ይችላል የሚል መላምት (hypothesis) አለ።

> ምልክቶች፦
       - በአስተዳደግ ከእኩዮቻቸው ወደኋላ መቅረት(Developmental Regression)
       - የተስተጓጎለ ማህበራዊ ግንኙነት
       - ቋንቋን ለመልመድ ረጅም ጊዜ መፍጀት
       - ተመሳሳይ እድሜ ካላቸው ልጆች ጋር ግንኙነት የመመስረት ችግር
       - ለአካባቢው ያላቸው ፍላጎት መቀነስ፥ ሌሎችን የሚያስደስታቸውና የሚያጓጓቸው እነሱን አያስደስታቸውም አያጓጓቸውም(abnormal response to environmental stimuli)
         - ውስን እና ተደጋጋሚ ባህሪ፣ ፍላጎትና ድርጊት(የሰውነት እንቅስቃሴ መኖር) ወዘተ

>  መፍትሄ፦
        - ባህሪያዊ፣ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ስልጠና
       - ልዮ የሆነ የኦቲዝም ት/ቤት በመክፈት ማስተማር
      - ተጓዳኝ በሽታዎችን ማከም(ድባቴ፣ ጭንቀት...)
      - እንደማንኛውም ህፃን እንክብካቤና ፍቅር መስጠት
      - የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል(vitamins በተለይ vit B-6 and minerals በተለይ magnesium)

# መልካም የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን
@tibebegihon