ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
13.8K subscribers
3.69K photos
43 videos
45 files
539 links
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
Download Telegram
የዶዶላ - ሰብስቤ ዋሻ - ባሌ ሮቤ - ጎባ መንገድ ጥገና በተጠናከረ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2/2018 (ኢ መ አ):- ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግደው የዶዶላ - ሰብስቤ ዋሻ - ባሌ ሮቤ - ጎባ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ የመንገድ ኮሪደር የባሌ ዞን ከተሞችን የምጣኔ-ሀብትና ማኅበራዊ ትስስር ከማጠናከሩም በላይ፣ ከፍተኛ የግብርና ምርት የሚንቀሳቀስበትና ወደ ባሌ ብሔራዊ ፓርክ የሚወስድ ዋና መስመር ነው።

ይሁንና በኮሪደሩ ላይ በሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ምክንያት የሚፈጠረው ከፍተኛ የትራፊክ ጫና፣ የአፈሩ ተለዋዋጭ ባሕሪና የከርሰ-ምድር ውኃ መፍለቅ መንገዱን በመጉዳቱ ለአሽከርካሪዎችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የትራንስፖርት ፈተና ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት መንገድ አውታር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በራስ-አቅም የጥገና ሥራውን እያከናወነ ይገኛል። የጥራት ቁጥጥርና የማማከር ሥራውን ደግሞ ኢንስራድ ሲቪል ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ ከሂትኮን ኢንጂነሪንግ ጋር በጋራ እያከናወኑት ነው።

በአሁኑ ወቅት ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መደረብ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፤ የአፈር ቆረጣ፣ የድንጋይና አፈር ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ፣ የውኃ ማፋሰሻ ጥገና፣ የስትራክቸር፣ የመንገድ ዳር ምልክቶችና የደኅንነት ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ከፌደራል መንግሥት በተመደበ 225 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን ይህንን ፕሮጀክት በቀጣዩ በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ የታቀደ ሲሆን፣ ለዚህም የሚያስፈልጉ የግብዓትና የሰው ኃይል ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።

የመንገዱ መጠገን ቀደም ሲል ይስተዋል የነበረውን እንግልት በመቅረፍ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰፍን ያደርጋል። ከዚህም ባለፈ በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን እንደ ስንዴ፣ ገብስ እና ጤፍ ያሉ የሰብል ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ለማቅረብ እንዲሁም የባሌ ብሔራዊ ፓርክን የቱሪስት ፍሰት ይበልጥ ለማነቃቃት ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
4👍2
መልካም አዲስ ዓመት!
ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት
መንገዳችን፣ ኃላፊነታችን
👍166