የጊንጪ - ካቺሴ - ጩሉጤ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ምዕራፍ 1፡ ጊንጭ - ሽኩቴ (ኪ.ሜ 59) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 72 በመቶ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የወረዳና የቀበሌ ከተሞችን የሚያስተሳስረው የጊንጪ - ካቺሴ - ጩሉጤ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ምዕራፍ 1፡ ጊንጭ - ሽኩቴ (ኪ.ሜ 59) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 72 በመቶ ደርሷል፡፡
በአሁናዊው የፕሮጀክቱ የግንባታ እንቅስቃሴም የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ስራ፣ የሰብቤዝ፣ ቤዝ ኮርስ ፣የስትራክቸር ስራ እንዲሁም 48 ከ.ሜ የሚሆን የአስፋልት ንጣፍ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
62.2 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍነው ይኸው መንገድ በወረዳ 19 ሜትር ፣በከተማ 19 ሜትር፣በቀበሌ 14.2 ሜትር ፣ በገጠር 10 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው፡፡
በመንገዱ የግንባታ ሂደት የፀጥታ እና ያለመረጋጋት ችግሮች አጋጥመው የነበረ ቢሆንም ኢመአ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ጥረቶች አሁን ላይ የመንገዱ ግንባታ በእቅዱ መሰረት በመከናወን ላይ ነው።
ይህንን ግንባታ እያካሄደ የሚገኘው ሀገር በቀሉ የሥራ ተቋራጭ ገምሹ በየነ ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭ ሲሆን ፎርትረስ ኢንጂነሪንግ ኮንሰልታንትስና አሶሼትስ ሀ.የተ.የግ.ማህበር የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ እያከናወኑት ይገኛሉ፡፡
ለፕሮጀክቱ የሚውለው (898,273,177 ) ስምንት መቶ ዘጠና ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሰባት ብር በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡
መንገዱ ቀድሞ በጣም የተበላሸ እና ለትራንስፖርት አመቺ ያልነበረ መንገድ ሲሆን በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ መገንባቱ የአካባቢው ህብረተሰብ ምቹ የመንገድ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡
የጊንጪ - ካቺሴ - ጩሉጤ መንገድ በስሩ የሚገኙትን ወረዳዎችን፣ ከተሞችን እና ቀበሌዎችን በቅርበት ከማገናኘት ጎን ለጎን በአካባቢው የሚመረቱ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች እና የቁም እንስሳት ለገበያ ለማውጣት የሚያግዝ ይሆናል ፡፡
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍17
የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ በመልካም የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ነው
አዲስ አበባ መጋቢት 26 ፣ 2017 (ኢ መ አ):- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮምቦልቻ ከተማ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የኮምቦልቻ ከተማ የአስፋልት ኮንክሪት ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ በመልካም የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛል።
ለመንገዱ ግንባታ 1,138,807,808 (አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር ) ወጪ በፌደራል መንግስት ተመድቧል፡፡
ግንባታው በሀገር በቀሉ ዮንአብ ኮንስትራክሽን እየተከናወነ የሚገኘውና 7 ነጥብ 58 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ይህ መንገድ የመንገድ ትከሻን እና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ 20.6 ሜትር አጠቃላይ የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡የመንገዱን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራ ሃገር በቀሉ ኢትዮ ኢንፍራ ኢንጂነሪንግ እያከናወነው ይገኛል ፡፡
አሁን ላይ ከመንገድ ፕሮጀክቱ 24.7 በመቶ የሚሆነው ሥራ የተገባደደ ሲሆን የአፈር ጠረጋ ፣ የአፈር ቁፋሮ፣ የአፈር ሙሌት፣ የማፋሰሻ ቱቦ በማምረት በመንገዱ ላይ የመግጠም ፣የሰብ ቤዝ ፣የድልድይ እና የደጋፊ ግንብ ስራዎች በሂደት ላይ ያሉ ሲሆን በእስካሁኑም የአራት ድልድይ ስራዎችን ማጠናቀቅ ተችሏል።
በፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ ወቅት የጸጥታ ችግር፣የወሰን ማስከበር ችግር ፣የካሳ ክፍያ በወቅቱ አለመከፈል፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ለስራ ተቋራጩ ለስራ በቂ የሆነ የመስሪያ ቦታ ከንብረት ነፃ በማድረግ መስጠት አለመቻሉ፣ ለምርጥ ድንጋይ ማምረቻ የሚሆን ቦታ (Quarry Site)አለመገኘቱ፣ የሲሚንቶ፣ ነዳጅ፣ብረት እና ሌሎች የግንባታ ግብአቶች እጥረት አጋጥመዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኮምቦልቻ አካባቢ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሠራ ይገኛል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ከባድ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማው ሳይገቡ ለማስተናገድ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓቶች ምርት ማውጫ በመሆን ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ በመሆኑ በከተማዋ ውስጥ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የመንገድ ኘሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ የመስተዳድር አካላት፣ የክልሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ ትብብር እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያሳስባል፡፡

👍9❤1👎1