ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
13.2K subscribers
3.35K photos
43 videos
45 files
480 links
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
Download Telegram
የሳውላ -ቃቆ ሎት-2 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እየተካሄደ ይገኛል

ጂንካ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ) ፡ በደቡብ ኦሞ ስር የሚገኘው የሳውላ -ቃቆ ሎት- ሁለት መንገድ ፕሮጀክት በራስ ሀይል ነው እየተካሄደ የሚገኘው ።

የግንባታው አሁናዊ አጠቃላይ አፈፃፀም 64 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህንኑ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ለመቀጠል እየተሰራ ነው።

በእስካሁኑ የግንባታ እንቅስቃሴ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ የአፈር ቆረጣ እና የሙሌት የድሬኔጅ ፣ የሰቤዝ ፣የግንብ ፣እንዲሁም የቤዝ ኮርስ ስራዎችን በመሰራት ላይ ነው ።

29 ነጥብ7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሳውላ -ቃቆ የመንገድ ፕሮጀክት በግራቭል እና ዲቢኤስቲ ደረጃ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሶዶ ዲስትሪክት በራስ ሀይል እየተገነባ ነው።

ፕሮጀክቱን ለማካሄድ አገልግሎት ላይ የሚውለውን 442,339,654.92 ብር የሚሸፈነው ኢትዮጵያ መንግስት ነው።

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የመንገድ መሰረተ ልማት ያልተዘረጋበት መንገድ በመሆኑ ለመንገዱ ተጠቃሚዎች እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

የሳውላ- ቃቆ መንገድ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታን የሚያስተናግድ ይሆናል።

ይህ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ- ጂንካ ለመጓዝ በኮንሶ አርባምንጭን በማቋረጥ 784 ኪሎ ሜትር ይወስድ የነበረ ሲሆን የመንገዱ መገንባት ከጂንካ -ቃቆ- ሳውላ- በወላይታ ሶዶ -አዲስ አበባ ለመሄድ በተሽከርካሪ እስከ 150 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል።

የመንገዱ መገንባት በርካታ ዞኖችን ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን እንደ ጫሊ፣ በኒታ፣ አሾ እና ሌሎችንም በመንገድ መሰረተ ልማት የሚያገናኝ ይሆናል።

ይህ መንገድ የተሽከርካሪዎችን የጉዞ ጊዜን በማሳጠር ያሰቡት ቦታ መድረስ ከማስቻሉም ባለፈ ካላስፈላጊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ወጪ በመቀነስ መንገዱ የጎላ አስተዋጾዖ ይኖረዋል።

በዞኑ በስፋት የሚገኘውን የማር እና የሰብል ምርቶችን እንደ በቆሎ ማሽላ እንዲሁም የቅባት እህሎችን የለውዝ ምርት ውጤቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ በጥራት እና በፍጥነት በማድረስ አምራችና ሸማቾችን ያገናኛል።

በመንገድ ፕሮጀክቱ ውስጥ አነስተኛ፣ ከፍተኛ ፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦዎች፣ ከልቨርቶች እንዲሁም የድልድዮች ግንባታ ተካቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐር ቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን የማማከር እና የመቆጣጠር ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ የጎን ስፋት ትካሻን ጨምሮ በከተማ 14 ሜትር ስፋት ሲኖረው በገጠ 7 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍14
በበጀት አመቱ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለመንገዶች ጥገና ተገቢዉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኢ መ አ):- በበጀት አመቱ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለመንገዶች ጥገና ተገቢዉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፤ ለመንገዶች ጥገና የሚውል መዋእለ ነዋይ የማሰባሰብ ሥራም ይከናወወናል ።

በአዋጅ ቁጥር 66/1989 ተቋቁም የመንገድ ጥገና ገቢ የማሰባሰብ ተግባራትን ያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ከየካቲት 1 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር መቀላቀሉን ሥራው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፈንድ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የመንገዶች ጥገና ሥራው በዋና በዋናነት በፌዴራል ደረጃ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች፣ በክልሎችና በክልሎቹ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሚከናወን ነው፡፡

የመንገድ ፈንድ ገቢ የሚሰበሰበው ለመንገድ ጥገና ከተጣለ የነዳጅ ታሪፍ፣ ተሽከርካሪ ዘይት እና ቅባት ሽያጭ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ ከመንገድ ጠቀሜታ ክፍያ፣ በክብደት ላይ የተመሠረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ እንዲሁም በሕግ ከተፈቀደ ክብደት በላይ በመጫን ከሚጣል ቅጣት ላይ ነው።

በተለያዩ መንገዶች ገቢ ከመሰብሰብ ባለፈም የተሰበሰበውን ገንዘብ ለመንገድ ኤጀንሲዎች በተቀመጠላቸው ቀመር መሠረት ማከፋፈል እና ለመንገድ ኤጀንሲዎች የተሰጠው ገንዘብ ለታለመት ዓላማ መዋሉን የመከታተል ሥራ ይሰራል።

በተጨማሪም ፈንዱ በ2017 በጀት ዓመት ክብደት ላይ የተመሠረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ማደሻ ክፍያ በዲጅታል አማራጭ እንዲጀመር ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እየተደረጉ ይገኛሉ።

የመንገድ ፈንድ በከፍተኛ የሀገር ሀብት የተገነቡ መንገዶች እና ድልድዮች በተቀመጠላቸው የዲዛይን ዕድሜ መሠረት እንዲያገለግሉ፣ አስፈላጊው ጥገና እንዲደረግላቸው እና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ፣ ለፌዴራል (ለመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶች )፣ ለከተማ እና ክልል መንገድ ኤጀንሲዎች በየዓመቱ የበጀት ድልድል ያደርጋል።

በዚህ ዓመትም የመንገድ መልሶ ግንባታ (Rehabilitation)፣ የመንገድ ማሻሻያ (Upgrading) ሥራ ቁልፍ የትኩረት መስኮች ላይ የተለያዩ ግቦችን ተቀምጠው እየተሠራ ይገኛል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍12
call paper En.jpg
2.1 MB
CALL FOR PAPERS


Office of the Conference Secretariat
Ethiopian Roads Administration (ERA),
Ras Abebe Aregay Street,
Post Office Box: 1770,
Website: www.iloethiopia2025.gov.et
👍6
በዲስትሪክቱ የጥገና ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢመአ) ፡- የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ የመደበኛና ወቅታዊ የጥገና ስራዎች በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የኮምቦልቻ ዲስትሪክት በ2017 በጀት ዓመት የወልዲያ ከተማ አስፋልት ስራ ፕሮጀክትን ጨምሮ 1,070 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ስራዎችን ለማካሄድ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

በበጀት ዓመቱ እነዚህን የጥገና እና የግንባታ ስራዎች ለማካሄድ ለዲስትሪክቱ የተመደበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 1,234,465,659 (አንድ ቢሊየን ሁለት መቶ ሰላሳ አራት ሚሊየን አራት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ብር) ነው፡፡

በዚህም ረገድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ 387,161,309 ብር ወጪ በማድረግ 320 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ በርካታ ስራዎችን በራስ ሀይል ለማከናወን ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ቴዎድሮስ ስሜነህ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ እና ኢትዮ ካናዲያን ቢዝነስ ግሩፕ በተባሉ የግል የስራ ተቋራጮች እንዲሁም በአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት 16,110,103 ብር ወጪ በማድረግ 13.88 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራዎችን ለማከናወን ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በዲስትሪክቱ ባለፉት የበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ 403,271,412.99 ብር ወጪ በማድረግ 333.67 ኪሎ ሜትር ወይም የዕቅዱን 89.39 በመቶ ስራ ለማከናወን ተችሏል፡፡

በአካባቢው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የጸጥታ እና የወሰን ማስከበር ችግሮች በዲስትሪክቱ ስራዎች ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድሩም ፤ ዲስትሪክቱ እነዚህን ችግሮች በመቋቋም በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍6