ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
13.2K subscribers
3.35K photos
43 videos
45 files
480 links
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
Download Telegram
የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረግ ሀገራዊ ጥረት የመንገድ ዘርፍ የሚገኝበት ደረጃ እና የተሰጠው ትኩረት ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ለዘርፉ በመስጠት በየበጀት ዓመቱ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመመደብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመተግበር ላይ የሚገኘው፡፡

ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በርካታ የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ፕሮጀክቶች እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ እነዚህንም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ለማስፈፀም የሚያስችሉትን የቅርብ ክትትል ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በዚህ ረገድ በ2017 በጀት ዓመት ይኸው ተግባር የቀጠለ ሲሆን የበጀት ዓመቱን እቅድ ተከትለው በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኙት ዋና ዋና ስራዎች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ነባር መንገዶችን ማጠናከር፡- በአገልግሎት ላይ ያሉ መንገዶች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የማጠናከርያ ስራዎችን በማከናወን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ የማድረግ ሥራ ነው፡፡ በዚህም መሰረት 15 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን በማጠናከር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች ብዛት 4 ሲሆኑ ፡፡
> 1 በግንባታ ላይ ያለ ፣
> 3 ወደ ግንባታ ለመሸጋገር በሂደት ላይ ያሉ ናቸው፡፡

2. የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል፡- አገልግሎት ላይ ያሉ ነባር መንገዶችን ደረጃቸውን ከፍ በማድረግና በማሻሻል ከጠጠር ወደ አስፋልት እና በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ማሳደግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት 330 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን የማሻሻል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች ብዛት 78 ናቸው፡፡

3. የአዳዲስ መንገዶች እና የፍጥነት መንገዶች ግንባታ :- ጨረታ ወጥቶላቸው የተፈረሙና ወደ ስራ የሚገቡ አዳዲስ መንገዶችን እንዲሁም የፍጥነት መንገዶች ማከናወን ያጠቃልላል፡፡ በ2017 የበጀት ዓመት 778 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የአዳዲስ መንገዶች እና የፍጥነት መንገዶች ግንባታ ይከናወናል፡፡በዚህ ፕሮግራም ውስጥ 232 ፕሮጀክቶች ተካተዋል፡፡

4. የመንገዶች ከባድ ጥገና/Overlay Projects፡- የተበላሹ እና ነባር መንገዶችን በከፍተኛ ደረጃ የመጠገን ስራ የሚሰራበት ነው፡፡
> በ2017 በጀት ዓመት 144 ኪሎ ሜትር የመንገዶች ከባድ ጥገና/Overlay Projects ለማከናወን እቅድ ተይዟል፡፡

5. ወቅታዊ እና መደበኛ የመንገድ ጥገናዎች፡- መንገዶችን በመደበኛነት የመጠገን እና በየጊዜው የመንገዶችን ብልሽት በማየት በወቅታዊነት የሚጠገኑ መንገዶች የሚካተቱበት ነው፡፡ በ2017 በጀት ዓመት በወቅታዊ እና መደበኛ ጥገና 14,412 ኪ.ሜ ጥገና ይከናወናል፡፡

> 67 በመደበኛ ጥገና የሚካሄድላቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
> 41 ወቅታዊ ጥገና የሚከናወንባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

6. የመያዣ እና ማጠናቀቂያ ሥራ ፡- በውሉ መሰረት (guaranty) የሚያዝ በጀት እና የፕሮጀክቱ ፊዚካል ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ የተወሰነ ሲቀራቸው ለማጠናቀቅ የሚያዝ በጀት ነው፡፡
> ከነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል ውስጥ 5 የመያዣ እና ማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ የሚቀራቸው ናቸው፡፡
> ከአዳዲስ እና ከፍጥነት መንገዶች ግንባታ ውስጥ 14 የመያዣ እና የማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ የሚቀራቸው ናቸው፡፡

7. ቅድመ ዝግጅት፡- በዲዛይን ሂደት ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች የሚያዝ በጀት ነው፡፡፡
> ከአዲስ መንገዶች ግንባታና የፍጥነት መንገድ ውስጥ 5 በቅድመ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍163
የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 75 ነጥብ 2 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኢ መ አ):- በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 75 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል።

አሁን ላይ እየተሠሩ ከሚገኙ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰቤ ቤዝ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ እንዲሁም የጠጠር ማምረት ሥራዎች ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የአስር አነስተኛ እና ከፍተኛ ድልድዩች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል። ፕሮጀክቱ ባጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ በኢ መ አ በኩል ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 36 ነጥብ 42 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተካሄደ ይገኛል። በለስ ኮንሰልቲንግ የግንባታውን ጥራት የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ይሠራል።

ለግንባታው የተመደበው 1,018,952,362.90  (አንድ ቢሊዮን አስራስምንት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺ ) ብር በፌደራል መንግስት ነው የሚሸፈነው።

የአካባቢው የቀድሞ ገጽታ ምንም ዓይነት የመንገድ መሠረተ ልማት ያልነበረው ሲኾን፥ በኅብረተሰቡ ጥያቄ መሠረት እንዲሁም ቦታው ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር፣ በመንግስት ተወስኖ አሁን ላይ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።

በአካባቢው የሚስተዋለውን ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ተከትሎ የግንባታ ጥሬ እቃ እና ማሽነሪዎች በቀላሉ ማቅረብ አለመቻል እንዲሁም የሥፍራው አስቸጋሪ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ የፕሮጀክቱ ፈተና መኾናቸው ተመልክቷል።

የመንገዱ መገንባት በተለይም በመንገድ እጦት ተራርቆ የቆየውን የደባርቅ እና ጃናሞራ ሕዝብ በቅርበት እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ የሚያገናኝ ነው። በመንገዱ ክልል እና በዙሪያው የሚገኙ የበለስ፣ ወይና፣ ሚጊራ እና መሰል ከተሞች ዕድገት ያፋጥናል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን 8 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ያሳጥረዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ እንደመኾኑም የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩል የጎላ ሚና ይጫወታል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍131
የሳውላ -ቃቆ ሎት-2 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እየተካሄደ ይገኛል

ጂንካ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ) ፡ በደቡብ ኦሞ ስር የሚገኘው የሳውላ -ቃቆ ሎት- ሁለት መንገድ ፕሮጀክት በራስ ሀይል ነው እየተካሄደ የሚገኘው ።

የግንባታው አሁናዊ አጠቃላይ አፈፃፀም 64 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህንኑ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ለመቀጠል እየተሰራ ነው።

በእስካሁኑ የግንባታ እንቅስቃሴ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ የአፈር ቆረጣ እና የሙሌት የድሬኔጅ ፣ የሰቤዝ ፣የግንብ ፣እንዲሁም የቤዝ ኮርስ ስራዎችን በመሰራት ላይ ነው ።

29 ነጥብ7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሳውላ -ቃቆ የመንገድ ፕሮጀክት በግራቭል እና ዲቢኤስቲ ደረጃ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሶዶ ዲስትሪክት በራስ ሀይል እየተገነባ ነው።

ፕሮጀክቱን ለማካሄድ አገልግሎት ላይ የሚውለውን 442,339,654.92 ብር የሚሸፈነው ኢትዮጵያ መንግስት ነው።

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የመንገድ መሰረተ ልማት ያልተዘረጋበት መንገድ በመሆኑ ለመንገዱ ተጠቃሚዎች እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

የሳውላ- ቃቆ መንገድ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታን የሚያስተናግድ ይሆናል።

ይህ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ- ጂንካ ለመጓዝ በኮንሶ አርባምንጭን በማቋረጥ 784 ኪሎ ሜትር ይወስድ የነበረ ሲሆን የመንገዱ መገንባት ከጂንካ -ቃቆ- ሳውላ- በወላይታ ሶዶ -አዲስ አበባ ለመሄድ በተሽከርካሪ እስከ 150 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል።

የመንገዱ መገንባት በርካታ ዞኖችን ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን እንደ ጫሊ፣ በኒታ፣ አሾ እና ሌሎችንም በመንገድ መሰረተ ልማት የሚያገናኝ ይሆናል።

ይህ መንገድ የተሽከርካሪዎችን የጉዞ ጊዜን በማሳጠር ያሰቡት ቦታ መድረስ ከማስቻሉም ባለፈ ካላስፈላጊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ወጪ በመቀነስ መንገዱ የጎላ አስተዋጾዖ ይኖረዋል።

በዞኑ በስፋት የሚገኘውን የማር እና የሰብል ምርቶችን እንደ በቆሎ ማሽላ እንዲሁም የቅባት እህሎችን የለውዝ ምርት ውጤቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ በጥራት እና በፍጥነት በማድረስ አምራችና ሸማቾችን ያገናኛል።

በመንገድ ፕሮጀክቱ ውስጥ አነስተኛ፣ ከፍተኛ ፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦዎች፣ ከልቨርቶች እንዲሁም የድልድዮች ግንባታ ተካቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐር ቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን የማማከር እና የመቆጣጠር ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ የጎን ስፋት ትካሻን ጨምሮ በከተማ 14 ሜትር ስፋት ሲኖረው በገጠ 7 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍14