ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
13.2K subscribers
3.35K photos
43 videos
45 files
480 links
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
Download Telegram
ነባሩ የአዲስ አበባ - ሞጆ - መቂ መንገድ ከባድ ጥገና በመካሄድ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14/2017 ዓ.ም 108 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ነባሩ የአዲስ አበባ - ሞጆ - መቂ መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ፡፡


የዚህ መንገድ አካል የሆነው በቢሾፍቱ በሚገኘው አየር ኃይል መግቢያ እስከ ፈጣን መንገድ መግቢያ ድረስ ያለው 5.3 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ነው ፡፡ ከዚህም ባሻገር ከገላን ወደ ሞጆ በሚወስደው መንገድ ላይ አልፎ አልፎ ያጋጠሙ ከባድ ብልሽቶች ጥገና ሲደረግላቸው ቆይቷል ፡፡ በቀጣይም እንደጉዳቱ መጠን እየታየ በሌሎች ቦታዎች ላይም ጥገናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል ፡፡

አሁን ላይ በዓለምገና ዲስትሪክት አማካኝነት ተገቢው ጥገና እየተካሄደለት የሚገኘው ይኸው መንገድ በዚሁ ዓመት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ እና በቀጣይም ተገቢ ክትትል እንደሚደረግለት ተገልጿል፡፡

በመስመሩ በርካታ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን ፣ የመንገዱ መጠገን ከዚህ ቀደም የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላል ተብሎ ይታመናል፡፡

እንደሚታወቀው ለመንገዶች ግንባታ እና ጥገና የሚውለው መዋዕለ ንዋይ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ተገቢውን አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ሁሉም ባለንብረትና አሽከርካሪ በህግ በተደነገገው የክብደት መጠን መሰረት በመጫን ግዴታውን ሊወጣ ይገባል፡፡

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍102👎1
የቆሼ - ሚቶ - ወራቤ መንገድ ፕሮጀክት አስፋልት ወደ ማንጠፍ ምዕራፍ ተሸጋገረ

ወራቤ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኢ መ አ):- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞንን ከማረቆ ልዮ ወረዳ ጋር የሚያገናኘው የቆሼ - ሚቶ - ወራቤ መንገድ ፕሮጀክት አስፋልት ወደ ማንጠፍ ምዕራፍ  ተሸጋግሯል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 73 ኪሎሜትር የሚሸፍን ኾኖ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው።

አሁን ላይ የ11 ነጥብ 2 ኪሎሜትር አስፋልት ንጣፍ፣ የ68 በመቶ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የ60 በመቶ ሰብቤዝ እንዲሁም የ16 በመቶ የቤዝኮርስ ሥራዎች ተከናውነዋል። በተጨማሪም ግንባታው የትራፊክ እንቅስቃሴውን እንዳያስተጓጉል ለተለዋጭ መንገዱ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል። የኹለት ድልድዮች ግንባታን ጨምሮ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ እንዲሁም የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች ግንባታ ሥራም በፕሮጀክቱ ተካትቷል።

ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሥራ አሁን ላይ 41 ኪሎሜትሩ ወይንም 56 በመቶው ተጠናቅቋል። የግንባታውን ቀሪ ሥራዎች ባጠረ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

የመንገድ ግንባታውን ሀገር-በቀሉ የንኮማድ ኮንስትራክሽን የሚያከናውን ሲኾን፥ የጥራት እና ቁጥጥር ሥራውን ሽላዲያ አሶሼትስ ከሂትኮን አማካሪ መሀንዲስ ጋር በጋራ በመኾን ይሠራሉ።

ለግንባታ ሥራው 1,850,695,155.03 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሐምሳ ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ) ብር በፌደራሉ መንግስት ተመድቧል።

የመንገዱ ነባር ገጽታ 63 ኪሎሜትሩ በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲኾን፥ ቀሪው ምንም ዓይነት የመንገድ መሠረተ ልማት አልነበረውም። አሁን ላይ መንገዱ በወረዳ የእግረኛ መንገድን ሳይጨምር 14 ሜትር፣ በገጠር ቀበሌ የመንገድ ትከሻን ሳይጨምር 7ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በመገንባት ላይ ነው የሚገኘው።

ይኽ ፕሮጀክት የማረቆ እና የስልጤ ሕዝብ ሁለንተናዊ ትስስር ከማጎልበቱም ባለፈ በመንገድ ክልል እና በዙሪያው የሚገኙ የኡዳሳ፣ ጦራ፣ ዳሎቻ እና መሰል ከተሞች ዕድገት የሚያፋጥን ነው።

ከዚህ ቀደም ከቆሼ ከተማ ተነስቶ የስልጤ ዞን መናገሻ ወራቤ ከተማ ለመድረስ የሚፈጀውን 3 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1ሰዓት በማሳጠር፣ በአካባቢው በስፋት የሚታወቁትን የበርበሬ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ እና መሰል የጥራጥሬ እና የአዝርዕት ምርት ውጤቶች በፍጥነት እና በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል። ለመኪና መለዋወጫ የሚወጣውን አላስፈላጊ ወጪ እና የነዳጅ ብክነትም የሚያስቀር ነው።

የአባያ ሐይቅ (የስልጤ ሐይቅ)፣ አሹቴ ፏፏቴ እንዲሁም አይናጌ ዋሻ የተሰኙ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን ለጎብኝዎች ምቹ በማድረግ ረገድም የመንገድ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍172
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መልካም በዓል!
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
4👍3
የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረግ ሀገራዊ ጥረት የመንገድ ዘርፍ የሚገኝበት ደረጃ እና የተሰጠው ትኩረት ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ለዘርፉ በመስጠት በየበጀት ዓመቱ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመመደብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመተግበር ላይ የሚገኘው፡፡

ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በርካታ የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ፕሮጀክቶች እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ እነዚህንም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ለማስፈፀም የሚያስችሉትን የቅርብ ክትትል ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በዚህ ረገድ በ2017 በጀት ዓመት ይኸው ተግባር የቀጠለ ሲሆን የበጀት ዓመቱን እቅድ ተከትለው በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኙት ዋና ዋና ስራዎች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ነባር መንገዶችን ማጠናከር፡- በአገልግሎት ላይ ያሉ መንገዶች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የማጠናከርያ ስራዎችን በማከናወን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ የማድረግ ሥራ ነው፡፡ በዚህም መሰረት 15 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን በማጠናከር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች ብዛት 4 ሲሆኑ ፡፡
> 1 በግንባታ ላይ ያለ ፣
> 3 ወደ ግንባታ ለመሸጋገር በሂደት ላይ ያሉ ናቸው፡፡

2. የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል፡- አገልግሎት ላይ ያሉ ነባር መንገዶችን ደረጃቸውን ከፍ በማድረግና በማሻሻል ከጠጠር ወደ አስፋልት እና በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ማሳደግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት 330 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን የማሻሻል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች ብዛት 78 ናቸው፡፡

3. የአዳዲስ መንገዶች እና የፍጥነት መንገዶች ግንባታ :- ጨረታ ወጥቶላቸው የተፈረሙና ወደ ስራ የሚገቡ አዳዲስ መንገዶችን እንዲሁም የፍጥነት መንገዶች ማከናወን ያጠቃልላል፡፡ በ2017 የበጀት ዓመት 778 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የአዳዲስ መንገዶች እና የፍጥነት መንገዶች ግንባታ ይከናወናል፡፡በዚህ ፕሮግራም ውስጥ 232 ፕሮጀክቶች ተካተዋል፡፡

4. የመንገዶች ከባድ ጥገና/Overlay Projects፡- የተበላሹ እና ነባር መንገዶችን በከፍተኛ ደረጃ የመጠገን ስራ የሚሰራበት ነው፡፡
> በ2017 በጀት ዓመት 144 ኪሎ ሜትር የመንገዶች ከባድ ጥገና/Overlay Projects ለማከናወን እቅድ ተይዟል፡፡

5. ወቅታዊ እና መደበኛ የመንገድ ጥገናዎች፡- መንገዶችን በመደበኛነት የመጠገን እና በየጊዜው የመንገዶችን ብልሽት በማየት በወቅታዊነት የሚጠገኑ መንገዶች የሚካተቱበት ነው፡፡ በ2017 በጀት ዓመት በወቅታዊ እና መደበኛ ጥገና 14,412 ኪ.ሜ ጥገና ይከናወናል፡፡

> 67 በመደበኛ ጥገና የሚካሄድላቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
> 41 ወቅታዊ ጥገና የሚከናወንባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

6. የመያዣ እና ማጠናቀቂያ ሥራ ፡- በውሉ መሰረት (guaranty) የሚያዝ በጀት እና የፕሮጀክቱ ፊዚካል ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ የተወሰነ ሲቀራቸው ለማጠናቀቅ የሚያዝ በጀት ነው፡፡
> ከነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል ውስጥ 5 የመያዣ እና ማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ የሚቀራቸው ናቸው፡፡
> ከአዳዲስ እና ከፍጥነት መንገዶች ግንባታ ውስጥ 14 የመያዣ እና የማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ የሚቀራቸው ናቸው፡፡

7. ቅድመ ዝግጅት፡- በዲዛይን ሂደት ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች የሚያዝ በጀት ነው፡፡፡
> ከአዲስ መንገዶች ግንባታና የፍጥነት መንገድ ውስጥ 5 በቅድመ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍163