ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
13.2K subscribers
3.36K photos
43 videos
45 files
481 links
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
Download Telegram
የጥንቃቄ መልዕክት!!
👍23
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተዘጋጀው "የአፍሪቃ ከተሞች ፎረም" ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናቶች በሚቆየው ፎረም ላይ ከ 47 በላይ ሀገራት፣ ከ30 በላይ የአህጉሪቱ ከተማ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡ ከ1ሺህ 500 በላይ ተሣታፊዎች በዚሁ መድረክ ላይ እንደሚታደሙ ይታመናል።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወነው ይኸው መድረክ "ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው። ፎረሙ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና በአፍሪካ ኅብረት አጋርነት የተሰናዳ ሲሆን ፣ ሀገራችን በዲፕሎማሲ፣ በማኅበረ-ኢኮኖሚ እንዲሁም ፖለቲካዊ መስኮች የምታተርፍበት ስለመሆኑም ተገልጿል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍194
መልዕክት!!

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍151
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መልካም አዲስ ዓመት!
ምርጥ መንገዶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና!
👍163
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ የትምጌታ አስራት ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ሆነው ተሾመዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ቤተሰብም ክቡር ሚኒስትር ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት እንኳን ደስ አሎት እያለ መጪው የስራ ጊዜዎ የስኬት እንዲሆንልዎ  መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍5312
ማሳሰቢያ!!
👍383
ነባሩ የአዲስ አበባ - ሞጆ - መቂ መንገድ ከባድ ጥገና በመካሄድ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14/2017 ዓ.ም 108 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ነባሩ የአዲስ አበባ - ሞጆ - መቂ መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ፡፡


የዚህ መንገድ አካል የሆነው በቢሾፍቱ በሚገኘው አየር ኃይል መግቢያ እስከ ፈጣን መንገድ መግቢያ ድረስ ያለው 5.3 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ነው ፡፡ ከዚህም ባሻገር ከገላን ወደ ሞጆ በሚወስደው መንገድ ላይ አልፎ አልፎ ያጋጠሙ ከባድ ብልሽቶች ጥገና ሲደረግላቸው ቆይቷል ፡፡ በቀጣይም እንደጉዳቱ መጠን እየታየ በሌሎች ቦታዎች ላይም ጥገናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል ፡፡

አሁን ላይ በዓለምገና ዲስትሪክት አማካኝነት ተገቢው ጥገና እየተካሄደለት የሚገኘው ይኸው መንገድ በዚሁ ዓመት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ እና በቀጣይም ተገቢ ክትትል እንደሚደረግለት ተገልጿል፡፡

በመስመሩ በርካታ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን ፣ የመንገዱ መጠገን ከዚህ ቀደም የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላል ተብሎ ይታመናል፡፡

እንደሚታወቀው ለመንገዶች ግንባታ እና ጥገና የሚውለው መዋዕለ ንዋይ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ተገቢውን አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ሁሉም ባለንብረትና አሽከርካሪ በህግ በተደነገገው የክብደት መጠን መሰረት በመጫን ግዴታውን ሊወጣ ይገባል፡፡

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍102👎1