Ethiopian pilots (ambitious)👩‍✈️✈️
3.17K subscribers
544 photos
56 videos
7 files
93 links
We aimed to inspire young students and to provide latest information about aviation
Download Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የለውጥ አስመዝጋቢ የእውቅና ሽልማትን አሸነፉ። በኦክቶበር 27 2021 በአቪየሽን አመራር ስራ አስፈጻሚዎች መድረክ/በአቪየተርስ አፍሪካ ታወር በተዘጋጀው መድረክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቋማዊ አመራር ሽልማት ዘርፍ 2021ን የእውቅና ሽልማትንም ተቀዳጅቷዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ

@ethiopianpilots
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው አለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የላሊበላ ቅርንጫፍ ቢሮ ፣በ1960።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/,የአውሮፓ ህብረት አቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/, CAAC, ECAA እንዲሁም ሌሎች በርካታ የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ጥልቅ ምርመራና ፍተሻ ካደረጉና ዳግም ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ የማክስ አውሮፕላናችንን ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውናል፡፡ ለደህንነት ቅድሚያ እንደመስጠታችንና ማክስ አውሮፕላንን ወደ ስራ ለመመለስ ከመጨረሻዎቹ አየር መንገዶች ተርታ እንደምንሆን በገባነው ቃል መሰረት እስካሁን 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደበረራ በመመለስ ከ330 ሺህ በላይ በረራዎችን አድርገዋል፡፡ የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ መሃንዲሶች፣ የአውሮፕላን ጥገና ባለሞያዎች እንዲሁም የበረራ አስተናጋጆች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻችንን ወደ በረራ ለመመለስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተዋል፡፡ ከእኛ ጋር አብረውን እንዲበሩ ተጋብዘዋል፤ ለበረራው ሲመጡ እርስዎን ሞቅ ባለ አቀባበል ለመቀበል ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የኢድ አልፈጥር በአል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡላዋዮ፣ ዚምባብዌ ከጥቅምት 2022 ጀምሮ በረራ የሚጀምር መሆኑን በደስታ ያበስራል፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለአየር መንገ ዳችን ብሎም ለአፍሪካ አሕጉር የመጀመሪያ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃም ከቀዳሚዎቹ አየር መንገዶች አንዱ የሚያደርገንን ቦይንግ 787- “ድሪምላይነር” አውሮፕላን ተረክበን ማብረር ከጀመርን አስር አመታትን አስቆጥረናል። በአቪየሽኑ ኢንደስትሪ ባለን ጉልህ የመሪነት ስፍራ እንዲሁም ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር በቆየው የረጅም ግዜ ደንበኝነታችን ኩራት ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737- MAX አውሮፕላን “Insulation Blankets” ማምረት ጀመረ። “Insulation Blankets” አውሮፕላን በከፍተኛ ጫማ ላይ ሲበር ከሚፈጠር ቅዝቃዜ እንዲሁም የአውሮፕላን ሞተር ድምፅ የሚከላከል የአውሮፕላን የውስጥ አካል ነው። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። https://bit.ly/3S2aSMN

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የአህጉራችን ትልቁ የልህቀት ማዕከል የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በዛሬው ቀን በመልቲ ክሩ ፓይለት ፍቃድ ፕሮግራም እና በንግድ ፓይለት የስልጠና ፍቃድ መርሃ ግብር 236 ፓይለቶችን አስመርቋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን እያበሰረ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡ በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምር ይገልፃል።
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ባሉበት ቦታ ሆነው ድረ ገፃችንን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችንን ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለክቡራትና ክቡራን ደንበኞቻችን!
የኢትዮዽያ አየር መንገድ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ተረከበ። አውሮፕላኑ 30 በመቶ “sustainable aviation fuel (SAF)” የተሰኘ የአውሮፕላን ነዳጅ የተጠቀመ ሲሆን ይህም በ2050 የካርበን ልቀትን ወደ ዜሮ ለማድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አቪየሽን ኢንደስትሪውን በሚመሩና በሚቆጣጠሩ አካለት  የተያዘውን ውጥን ከግብ ለማድረስ የሚረዳ ነው። አየር መንገዳችን የተረከበው ይህ አውሮፕናል 10 ቶን የሚመዝን ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ቁሳቁስም ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መጥቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የመንግስት ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ መልኩ ተከብሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህን ቀን አስመልክቶ ወደ እንግሊዝ ለንደን በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ያደርጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓለምአቀፍየሴቶችቀን
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia