Ethiopian pilots (ambitious)👩‍✈️✈️
3.61K subscribers
549 photos
57 videos
7 files
95 links
We aimed to inspire young students and to provide latest information about aviation
Download Telegram
Ethiopian pilots (ambitious)👩‍✈️✈️
Photo
አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡


@ethiopianpilots
WELCOME- ET-AXT
BRAND NEW BOEING 787-9 IS ON THE WAY TO ADDIS FROM EVERETT.

@ethiopianpilots
Forwarded from Natnael Mekonnen
አየር መንገዱ ስምንት አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚረከብ ተገለጸ!!

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካዘዛቸው 26 አውሮፕላኖች ውስጥ ስምንቱን በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚረከብ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ ተጨማሪ 26 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግና ከኤርባስ ከተሰኙ ግዙፍ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች ድርድር በማድረግ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል። ከተገዙት አውሮፕላኖች መካከል አየር መንገዱ ስምንት የመንገደኛ አውሮፕላኖች በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚረከብም ነው የገለጹት።

ቀሪዎቹ የመንገደኞች አውሮፕላኖች በቀጣይ ጊዜያት እንደሚገቡ ገልጸው፤ አየር መንገዱ ሌሎች ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለማስገባት እቅድ እንዳለው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አየር መንገዱ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ የመዳረሻ ሥፍራዎችን ከማስፋት አኳያ በቀጣይ ጥቅምትና ሕዳር ስድስት የበረራ መዳረሻዎች እንደሚጨምር ተናግረዋል። እነዚህ የበረራ መዳረሻዎች በአብዛኛው የአውሮፓ አገራትን እንዲሁም አንድ አፍሪካ አገርን ትኩረት እያደረገ መሆኑን በመጠቆም፤ ስፔን ማድሪድ፣ እንግሊዝ ለንደን-ጋትዊክ፣ ኔዘርላንስ አምስተርዳም፣ ቬትናም ሃኖይና ማዕከላዊ አፍሪካ ባንጓይ የአየር መንገዱ አዳዲስ መዳረሻዎች እንደሚሆኑም ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በተያዘው በጀት ዓመት ገቢውን በ22 በመቶ ለማሳደግ እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ለዚህም ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአሁኑ ወቅት 145 አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፤ 134 ዓለም አቀፍና 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት።
Various field of study are out
Including trainee pilot

For any help and inquiries @deva350
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies
@ethiopianpilots
Happy new year
ET-BAA
A NEW ETHIOPIAN AIRLINES CARGO AIRCRAFT IS ARRIVING TO ADDIS ALL THE WAY FROM EVERETT, BOEING COMPANY ✈️

@ethiopianpilots
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
የኢትዮጵያ አይሮፕላን ምዝገባ ኮድ ከ ET-A ወደ ET-B ተሸጋገረ።

ኢትዮጵያ በሲቪል አቪዬሽን ከ80 ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን በዓለም ዓቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የአይሮፕላን ምዝገባ (Aircraft Registration) ኮድ መሠረት የሀገሩን መለያ የሚገልጹት ሁለት ፊደላት "ET" የሚለው ሆኖ ተመዝግቦላታል።

እነዚህ የመለያ ፊደላት ወይም ቁጥሮች ለሁሉም ሀገራት የተለያየ የሚሰጥ ሲሆን ለአብነትም የኬንያ "5Y" ፤ የኡጋንዳ "5Y" ፤ ቻይና "B"፤ ግብጽ "SU" ፤ ጀርመን "D" መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያ የተሰጣት መለያ ፊደላት ከስያሜዋ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ "ET" መደረጉ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበረን የዲፕሎመሲ አቅም፣ የቴክኖክራቶቻችን ብቃት እና ለአቪዬሽን የሰጠነው ቦታ ትልቅ በመሆኑ ጭምር የተገኘ ይሆናል ተብሎ ይታመናል።

በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በኩል የሚመዘገቡ ማናቸውም አይሮፕላኖች "ET" ን በማስቀደም፣ አንድ ጭረት (-) ካደረጉ በኋላ ባለ ሦስት አሐዝ ወይም ሆሄ ይጠቀማል።

በኢትዮጵያ የሲቪል አቪዬሽን ታሪክ አስካሁን ET-A ብሎ ጀምሮ ነበር ሁለቱ ፊደላት የሚቀጥሉት (ለምሳሌ፣ ET-ANY) ከዚህ በኋላ ግን ይህ የአይሮፕላን ምዝገባ ኮድ ወደ ET-B ተሸጋግሯል።

በ ET-B ፊደላት ዘር እና ብዜት ለመቀጠል፣ የመጀመርያው አይሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው Boeing 777 ዕቃ ጫኝ አይሮፕላን ትናንት እኩለ-ሌሊት ላይ ከኤቨሬት ሲአትል ተነስቶ  በካፒቴን ዘላለም አንዳርጌ ዋና አብራሪነት እየተመራ የ16 ሰዓታት በረራ በማድረግ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሷል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ (Boeing 777-200LR) የጭነት አውሮፕላን ሲሆን አውሮፕላኑ ዘመናዊ ባለሁለት ሞተር ያለው መሆኑንና ከመቶ ቶን በላይ ጭነት የመሸከም አቅም እንዳለውም ተጠቅሷል።

አየር መንገዱ Echo Tango Alpha (ET-A) እየተባለ ለ75 ዓመታት የተጠራበትን ስያሜ ከዚህ ቀን ጀምሮ በመተው Echo Tango Bravo (ET-B) እያለ የሚጠራ ይሆናል ማለት ነው።

ይህ የአይሮፕላን ምዝገባ ኮድ፣ የግሉን አየር መንገዶችንም የሚጨምር ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በኢትዮጵያ ለሚመዘገቡ የግል አየር መንገዶች፣ አገልግሎቱ፣ የቁጥጥር (Regulatory) እና ፈቃድ ሰጪነት (Certifying)  ተግባር የሚያከናውን ይሆናል።

Credit : ኤሮቶፒያ የአቪዬሽን ሚዲያ፤ ዮናታን መንክር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#HappeningNow

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰው ኃይል ሀብቱን ለማሳደግ፤ በራሱ ፍልስፍና እና ጠንካራ የስልጠና ሂደት ያሰለጠናቸውን 627 የአሺዬሽን ባለሙያዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

ይህ በዚህ ዓመት በቅርቡ ካስመረቃቸው ከ1,500 የአሺዬሽን ባለሙያዎች ጋር ሲደመር፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነው ተብሏል።

ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመረቀውና በቅርቡ ከአካደሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያደገው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ አየር መንገዱ በ2035 ለወጠነው ዕቅድ ብቁ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

Credit : ኤሮቶፒያ የአቪዬሽን ሚዲያ፤ ዮናታን መንክር

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 🛫🛫The Pilot's🛬🛬 (🇳ate)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑BREAKING NEWS

A Japan Airlines passenger plane carrying 379 people appeared to have collided with a coast guard aircraft with six people on board. Footage shows the plane coming in to land before catching fire. The coast guard aircraft was being used to transport supplies after Japan suffered multiple devastating earthquakes. All passengers and crew from the commercial aircraft were evacuated, but five out of six coastguards were unaccounted for
@aviation_village
በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Forwarded from Natnael Mekonnen
ዛሬ በመቐለ ምን አጋጠመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከቀኑ 8:00 መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ ጎማው አከባቢ ባጋጠመው ችግር በፓይለቱ ድንቅ ብቃት ሰዎችን ሳይጎዱ ሊያርፍ ችሏል።