የተሽከርካሪ አስተዳደርን በቴክኖሎጂ የሚያዘምነው "ኢ-ፍሊት" ሥርዓት በተቋሙ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡
ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ - የተቋሙን ተሽከርካሪዎች ወደ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መረጃ አያያዝ ሥርዓት ለማስገባት ያለመ የ"ኢ-ፍሊት" (e-Fleet Management System) የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ዛሬ ተሰጥቷል። ለተቋሙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አሽከርካሪዎች የተዘጋጀው ይህ ሥልጠና፤ መንግሥት የተሽከርካሪዎችን አጠቃቀም፣ የነዳጅ ፍጆታንና የጥገና አስተዳደርን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመምራት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ ተቋማዊ አሠራርን በማዘመን ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሥራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባይነህ አለማየው እንደገለጹት ይህ አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ቀደም ሲል በወረቀትና በሰው ኃይል ይከናወኑ የነበሩ የተሽከርካሪ ስምሪት፣ የነዳጅና የጥገና ጥያቄዎችን እንዲሁም የዘይትና ቅባት ፍጆታን በዘመናዊ መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል። ይህም በሥራ ላይ ግልጽነትንና ቅልጥፍናን ከማስፈን ባለፈ፣ የተቋሙን ሀብት በብቃትና በቁጠባ ለማስተዳደር የሚጫወተው ሚና የጎላ በመሆኑ ሠራተኞች ለሥርዓቱ ትግበራ ስኬታማነት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽመልስ ቦጋለ በበኩላቸው ሥልጠናው ተሳታፊዎች ስለ አዲሱ ቴክኖሎጂ በቂ ግንዛቤ አግኝተው በቀጥታ ወደ ተግባር እንዲገቡ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የኤሌክትሮኒክስ ሲስተም የሀገርን ሀብት ከብክነት ለመታደግና የተቋሙን ንብረቶች በአግባቡ ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም በሥልጠናው ወቅት ተብራርቷል።

👍13
የትምባሆ ኢንዱስትሪ አሳሳች ስልቶችን ለማጋለጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::
ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም/አዲስ አበባ -- በአገራችን ለ34ኛ ግዜ በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ39ኛ በፓናል ውይይትና ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት የተከበረው የትምባሆ ጭስ ነፃ ቀን መሪ ቃሉም ለኒኮቲንና ትንባሆ ሱስ አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ በሚል ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ለተሳታፊዎችና ለሚዲያዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የመድኃኒት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ ትምባሆ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ የጤና እና የኢኮኖሚ ጉዳቶች ለውሳኔ ሰጪዎችና ለህብረተሰቡ በማሳወቅ ቁጥጥሩን ለማጠናከር መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪውን ጣልቃ ገብነት በመከላከል ረገድ በወሰደችው ጠንካራ እርምጃ የ2025 የዓለም አቀፍ ተሸላሚ መሆኗም በታላቅ ስኬት ተጠቅሷል።
ትምባሆ ኢንዱስትሪው በተለይ ወጣቶችንና ህፃናትን በሱስ ለመጥለፍ እንደ ከረሜላ እና ጣፋጭ ፍራፍሬ ያሉ ማራኪ ጣዕሞችን መጨመር እጅግ አሳሳችና ድብቅ ስልቶችን እየተጠቀመ ይገኛል።እነዚህ ስልቶች ተጠቃሚዎች ሱስን ለማቆም ያላቸውን ዕድል የሚቀንሱና አዲስ ትውልድን ለዕድሜ ልክ የጤና እክል የሚዳርጉ በመሆናቸው የኢንዱስትሪውን ጭንብል በመግፈፍ የሕዝብ ጤናን መጠበቅ እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት አጋሮች ተናግረዋል።

👍11