የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
30.5K subscribers
1.36K photos
83 videos
36 files
119 links
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡

ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
Download Telegram
Audio
"ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ"
በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
         
ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(፪)
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን

አቤት ቀንደመለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ

አዝ____

አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ
ድምጽ ሲሰማ ከራማ

አዝ____

አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው
ምድርን ሲያውኩት ቀስፈው
ሲታዘዝ የባህር ሞገድ
ምድሪቱን ሊከድናት ለፍርድ

አዝ____

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሠሩ ብሩካን
በምድር የሠሩት ትሩፋት
ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት

አዝ____

አቤት ኃጥአን ለፍርድ ሲጠሩ
በጨለማ ዓለም ሊቀሩ
የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ
መዋረድ ይሆናል አስሉ

አዝ____

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሠሩ ብሩካን
በምድር የሠሩት ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት

  " አምላካችን ይመጣል "
           መዝ፶፥፫

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ገብር ኄር
የዐብይ ጾም ስድስተኛ እሑድ(ሳምንት)


ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡

በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡

ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡

ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡

በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡

1. የአገልጋዮቹ ጌታ፡–

ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡

2. በጎ አገልጋዮች:-

በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡

3. ክፉና ሰነፍ አገልጋይ:-

ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡

የአገልጋዮቹ ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡

ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡

እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን አባቶች የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ የአገልጋዮቹ ጌታ የፍጡራን ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁም ሦስቱ አገልጋዮች በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉ ያስተምራሉ፡፡

ከዚህ የወንጌል ክፍል ምን እንማራለን?

ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዓበይት የሆኑትን ሁለቱን እንመልከታቸው፡፡

ለእያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንዳለ እንረዳበታለን

እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ፍሬን ቢፈልግም ያን ፍሬ ማፍራት የምንችልበትን ኃይል ግን የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኘንበት ከዕለተ ጥምቀት ጀምሮ እንደሚያስፈልገን መጠን እየሰጠን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበልናቸው ስጦታዎች በቁጥር እጅግ ብዙ ቢሆኑም በዓይነታቸው ግን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው እያንዳንዱ ክርስቲያን ዳግመኛ በመወለድ ምስጢር ያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋና ከልጅነት ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው (ዮሐ.3፥3)። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ ሰውየው አቅም ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ትንቢት መናገር ፣ በተለያዩ ልሳናት መናገር ፣ አጋንንትን ማስወጣት … የመሳሰሉት ከዚህኛው ዓይነት ስጦታ የሚመደቡ ናቸው (1ኛ ቆሮ.12፥4)፡፡

በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው ዓይነት ስጦታ ተቀባዮች ዘንድ ግን ብዙ የሚያሳዝኑ ችግሮች አሉ፡፡ በዳግመኛ መወለድ ምሥጢር (በ40 ና 80 ቀን ጥምቀት) ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ ጊዜ ሰጥቶ የሚያስብ ክርስቲያን ማግኘት በዚህ ዘመን በጣም አዳጋች ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ክርስቲያንነቱ ለጥምቀት በዓልና ለመስቀል ደመራ ካልሆነ ትዝ የማይለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ ከቤተ ዘመድ አንድ ሰው ምናልባትም ራሱም ሊሆን ይችላል ነፍሱ ከሥጋው ካልተለየች ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ብቅ አይልም፡፡

እግዚአብሔር ለእኛ የልጅነትን ጸጋ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ምክንያቱም ልጅነታችን ዋጋ ተከፍሎበታልና፡፡ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ልጆች የተባልነው፡፡ እኛ ልጅነትን እንድንቀበል አምላክ መከራን ተቀብሏል፡፡ የጥምቀታችን ውሃ የፈሰሰው በጦር ከተወጋው ከጌታ ጎን ነው (ዮሐ.19፥24)፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ሁሉ ሲያመለክት ”የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (1ኛ ዮሐ.3-1) እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ካሳየን የአባትነት ፍቅር በተጨማሪ ልጆቹ ስለመሆናችን የገባልንም ተስፋ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ”እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፡፡ ልጆች ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡” (ገላ.4:7) በማለት  ስለሚጠብቀን ተስፋ ነግሮናል፡፡

ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባን የመጀመሪያው መክሊታችን ልጅነታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም መክሊት እንድንሰራ የታዘዝናቸውን ምግባራት እንድናፈራ የሚጠበቅብንን ፍሬዎች ማፍራት አለብን፡፡ ያለበለዚያ መክሊቱን እንደቀበረው ሰው መሆናችን ነው፡፡

እያንዳንዱ ስጦታ እንደሚያስጠይቅ እንረዳለን

እግዚአብሔር ያለ አንድ አላማ ለሰዎች ሓላፊነትን የሚያሰከትል ስጦታ አልሰጠም አይሰጥምም፡፡ ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሰው የተሰጠው ስጦታ ለሆነ አላማ ነውና ጥያቄ አለበት፡፡ ጠያቂው ደግሞ የስጦታው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ይሁን ማን ግን ስለተሰጠው መክሊት ባለቤቱ ከፊቱ አቁሞ እንደሚጠይቀው መዘንጋት የለበትም፡፡እንግዲህ በአጠቃላይ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን  ¨ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳) ይላልና።

አሁን ባለንበት ወቅት በጎና ታማኝ አገልጋይ መሆን እንዳንችል ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የችግሮቹም መሠረታዊ ምንጭ በተጠሩበት ጸንቶ መቆም ፈጽሞ አለመቻልና ለሥጋዊ ጥቅም ብቻ በማድላት ሓላፊነትን መዘንጋት ናቸው፡፡ በሥጋዊ አምሮት ፍላጎትና ምርጫ ውስጥ ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋንና በረከትን ለማግኘት የሚያስችለንን የታማኝነት ሥራን መሥራት አይቻልምና በታማኝነት ከምናድነው ሰው ይልቅ መክሊታችንን በመቅበር ባለመታመን መሰናክል የምንሆንበት ሰው ሊበዛ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም ከእርሱ ዘንድ እንደ ዓቅማችን የተሰጠንን መንፈሳዊ ዕውቀት ሀብትና አገልግሎት ለሌላው በማድረስ መክሊታችንን ልናበዛ የምንችለውና አገልግሎታችን ወይም ክርስትናችን ውጤታማ የሚሆነው ምርጫችንን አውቀን እንደቃሉ ሆነንና ጸንተን ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሌላውን ማትረፍ አቅቶን በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ በሚያስወቅስ የስንፍና መንገድ ላይ ቆመን የምንገኘው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” (ማቴ. ፳፬፥፵፪) ብሎናል፡፡

ቃሉን የሰማንና የምናውቅ ሁላችን በሞቱ ላዳነን፣ በልጅነት ጸጋም ላከበረን፣ በትንሣኤውም ላረጋጋን፣ በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ከራሱ ጋር ላስታረቀን፣ በውኂዘ ደሙም ሕይወትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ በረከትንና ዘለዓለማዊ ደስታን ለሰጠን አምላካችን በመታዘዝ አቅማችን በሚፈቅደው አገልግሎት ጸንቶ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በአገልግሎት የመጽናት ምልክቱ ደግሞ አትራፊነት ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በአትራፊነት ይታወቃሉ፡፡ ለማትረፍ ግን ራሳቸውን ለእውነት ለአገልግሎት ለመከራ አሳልፈው በመስጠት ነው፤ በትንሹ መታመን ሲባል የእኛ አገልግሎት ከፈጣሪ ቸርነት ጋር ስለማይመጣጠን ነው፤ በብዙ እሾምሃለሁ ማለቱም በመንግሥተ ሰማያት ለዘለዓለም ከብሮ መኖርን ነው፡፡

ከቅዱሳን ነቢያትም ሐዋርያትም ሰብአ አርድእትም ሊቃውንትም የሰማነውና ያየነው እውነት ምንጊዜም ትጉህ ሠራተኛ የሚሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን፤ ምእመናንን፤ ሀገርንና ሕዝብን ለመምራት የጠራንና የመረጠን፤ በአገልግሎት ዐደባባይ ያስቀመጠን ሰዎች እጅግ ዕድለኞች ነን፤ ምክንያቱም የሕዝብን ችግርና አቤቱታ ሰምቶ ተቀብሎ መፍትሔ መስጠት ትርፋማነት ነውና፤ ትርፋማነት ደግሞ ወደ ትልቁ የሹመት መሰላል መውጣት ነው፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አገልግሎታችን ተደናቅፎ የሕዝባችን ችግር ሳይፈታ ቀርቶ የአገልግሎታችን ተቆጣጣሪ አምላካችን ቢጎበኘን “አንተ ሰነፍ አገልጋይ”
ተብለን ወደ ውርደት አዘቅት እንዳንላክ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ የመሾም የመሻር የማሳደግና የማውረድ ሥልጣን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ “ከእናንተ መካከል አንዱን እንኳ እንዳናስቸግር ቀንም ሌሊትም እንሠራ ነበር” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፱) በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ ጠንክረን ልንሠራ ይገባናል፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮
-፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪
-የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱

ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰
"ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ"
"አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ"

ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
Audio
"ገብር ኄር"

ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)

ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው።

ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ።

ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ።

ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል።
        በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
      ምዕራፍ ፬/4 ክፍል ፪/2
...........................................................


  «ግብረ አውናን»ን በተመለከተ አሳሳች ሐሳቦች
    ግብረ አውናንን በተመለከተ ከተለያየ አቅጣጫ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች አሉ:: ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ምንም እንኳን በቀጥታ ድርጊቱን ለማበረታታት የተነገሩ ባይመስሉም ብዙዎችን ከዚህ ክፉ ልማድ እንዳይወጡ ለማሰር ኃይል ያላቸው ናቸው:: ከእነዚህም ሐሳቦች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል::

ሀ) ብዙ ሰዎች «አውናን የተቀሠፈው ዘሩን በማፍሰሱ ሳይሆን ለወንድሙ ዘር ማቆምን  ስላልወደደ በምቀኝነቱ ነው» በማለት መሠረት የሌለው ሐሳብ ይሰነዝራሉ፡፡ በእርግጥ አውናን ለወንድሙ ዘር ላለማቆም ማሰቡ ምቀኛ ያሰኘዋል:: ያስቀሠፈው ዋና ምክንያት ምቀኝነቱ ነው ማለት ግን ስሕተት ነው፡፡ ምቀኝነት ሊያስቀሥፍ የሚችል ኃጢአት ቢሆንም አውናን የተቀሠፈው ግን «ዘሩን በማፍሰሱ» እንጂ በምቀኝነቱ አይደለም።
ሰው የራሱን የግል አስተያየት ወደ ጎን አድርጐ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ማድመጥ ከፈለገ አውናን የተቀሠፈበትን ዋና ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ምቀኝነትና ዘርን ማፍሰስ በጣም ይለያያሉ:: ምቀኝነት የልቡና ሐሳብ ነው:: ዘርን ማፍሰስ ግን በግልጽ የሚታይ ተግባር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ አውናን የተቀሠፈበትን ምክንያት ሲገልጽ «ሥራውም በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት» ይላል እንጂ ‹‹ምቀኝነቱ›› አይልም:: ታዲያ የአውናን ክፉ ሥራው ምን ነበር ዘሩን በምድር ላይ ማፍሰሱ አልነበረምን? ምቀኝነት በሥራ የሚገለጥ የልቡና ክፋት እንጂ በራሱ «ሥራ» አይባልምና፡፡
   ከላይ እንደተብራራው አውናን የተቀሠፈው ዘሩን በማፍሰሱ ሳይሆን በምቀኝነት ብቻ እንደሆነ አድርጐ መናገር መሠረት የሌለው የሰይጣን ትርጓሜ ከመሆኑም ባሻገር «ዘርን ማፍሰስ›› አያስቀጣም ወይም ሊያስቀሥፍ አይችልም እያሉ እንደማወጅ ነው፡፡ እንዲህ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍርድ ፈርቶ ከክፉ ሥራው ለመለስ ያለውን ወጣት ለምን ትመለሳለህ ግፋበት እንጂ እያሉ እንደመምከር ይቆጠራል፡፡ ክፉን ነገር እንደማያስቀጣ አድርጐ መተርጐም ተሳስቶ ማሳሳት ነውና ሊታረም ይገባል:: በዚህ የተሳሳተ ሐሳብ ተወግተው ክፉውን ልማድ እንደ በጐ ይዘው የሚማቅቁትን ወጣቶች ቤት ይቁጠራቸው፡፡

ለ) በመሰንጋት ራስን በራስ ለማርካት የመሞከር ተግባር በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ሆኗል:: ይህ ድርጊት ፆታና ዕድሜ አይለይም:: በአጠቃላይ ሲታይ ወንዶች ከሴቶች ቀደም ባለ ዕድሜ ቢጀምሩም ሴቶችም ከዚህ ተግባር ውጭ አይደሉም:: ጥናቱ በኛ ሀገር አይካሄድ እንጂ አንድ በአሜሪካን ሀገር የተደረገ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያመለክተው ከሆነ ከአጠቃላይ ወጣት ልጃገረዶች ሁለት ሦሥተኛው እጅ ከአጠቃላይ ወጣት ወንዶች ደግሞ ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች የተለያየ ርዝማኔ ላላቸው ጊዜያት «በማስተርቤሽን› ልማድ ይያዛሉ፡፡ ይህ አኀዝ ለወንዶች ሙሉ በሙሉ እንደማለት ነው:: ከሁሉ የሚያስደንቀው በሰባዎቹ ውስጥ ከሚገኙ አሮጊቶች ሠላሳ ሦስት እጅ ከሽማግሌዎች ደግሞ አርባ ሦስት እጅ የሚሆኑት አሁንም በዚሁ የመሰንጋት (ራስን በራስ ማርካት) ተግባር ውስጥ መገኘታቸው ነው፡፡ (ኢንካርታ ብሪታኒካ ኢንሳይኮሎፒዲያ 2004) በኛም አገር ቁጥሩ ይህን ያህል አይጋነንን እንጂ ብዙ ወጣቶች በዚህ ክፉ ልማድ መመረዛቸው በተለያየ መንገድ ይሰማል:: ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ሰዎች «ይህ ድርጊት ጤናማነትን ስለሚያመለክት የሚያሳስበው በዚህ መንገድ የማይጓዙ ሰዎች ሕይወት ነው» እስከ ማለት ደርስዋል::
   በዓለም ላይ ሴጋን መፈጸም በብዙኀኑ ዘንድ የተለመደ በመሆኑ ብቻ ድርጊቱ እንደ ተገቢና ጤናማ የሰውነት ተግባር ሊቆጠር አይችልም፡፡ ወጣቶችም በዚህ ሐሳብ በመሳሳት በድርጊቱ የተለከፉ ከሆነ ለመላቀቅ ከመጣጠር ይልቅ «ለካ እኔ ብቻ አይደለሁም!» እያሉ መጽናናት አይገባቸውም:: ይህን ተግባር ሞክረውትም የማያውቁ ከሆነ ለመሞከር ከማነሣሣት ይልቅ ጨርሶ የዚህን ክፉ ኃጢአት ጣዕም አለመቅመስ በሕይወታቸው ያለውን ፋይዳ ተረድተው ከመሞክር መታቀብ ይኖርባቸዋል::
   በዓለማችን መፋታት፣ ዝሙት፣ መግደል፣ ውርጃ፣ ባዕድ አምልኮ፣ ውሸትና መሥረቅ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተለመዱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ ተግባራት በብዙኀኑ ዘንድ መተግበራቸው ትክክል ቢሆኑ ነው እንጂ ያሰኛቸዋልን? ሴጋ መፈጸምም እንደዚሁ ነው:: ከላይ በፊደል «ሀ» እንደተጠቀሰው ሐሳብ ሁሉ ሰዎች ለክፉ ሥራቸው አጋር እንዳላቸው እያሰቡ እንዲጽናኑ ሰይጣን የዘረጋው የጥፋት ወጥመድ «ብዙዎች የሚፈጽሙት ከሆነ እንዴት ኃጢአት ይሆናል?» የሚል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን «ብዙዎች ኃጢአት ሲሠሩ አይተህ ከእነሱ ጋር አትተባበር ይላል፡፡›› ዘፀ 23÷2
ሐ) ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችና የሥነ አእምሮ ጠበብቶች «ክዕወተ ዘርዕ» ብዙ ዓይነት ሥነ ልቡናዊና አካላዊ የጤና ችግር እንደሚያስከትል በአንድ ልብ ይስማማሉ፡፡ እንዲያውም የብዙዎችን ጓዳ ከሚያንኳኳው ከ‹‹ስንፈተ ወሲብ› ጀምሮ የኩላሊትና የልብ በሽታዎች ድረስ በሴጋ አማካኝነት ሊመጡ እንደሚችሉ በሰፊው ተዘግቧል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም ጠቢባን ቃላቸው ወጥነት የሚጎድለውና ተለዋዋጭ ነው:: ስለዚህ አንዱ የካበውን ሌላው ሲንደው ይታያል፡፡
   <<የዓለም ጠቢባን ቃላቸው ወጥነት ይጎድለዋል>> ለሚለው ሐሳብ ማስረጃ የሚሆነው ብዙ ምሁራን «ሴ.ጋ» ወይም ‹‹ማስተርቤሽን› ለልዩ ልዩ በሽታ ያጋልጣል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በጭራሽ አያጋልጥም ማለታቸው ነው:: እንዲያውም ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹ «ሴጋ» ወይም ‹‹ማስተርቤሽን›› ለአንዳንድ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድልን ይቀንሳል ሲሉ ይደመጣል፡፡ ለምሳሌ:- በሀገራችን ከሚታተሙት በርካታ የግል ጋዜጦች አንዱ የሆነው ሜዲካል ጋዜጣ በ1995 በመጨረሻዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ ካሳተማቸው ጋዜጦች በአንዱ ላይ ‹‹ማስተርቤሽን» በካንሠር የመያዝ ዕድልን እንደሚቀንስ ጥናታዊ መረጃዎችንና የባለሙያዎችን አስተያየት ጠቅሶ አስፍሯል፡፡
   እንደ የሕክምና ባለሙያዎች ሁሉ የሥነ አእምሮ ጠበብቶችም «አንድ ሰው ሴጋ በመፈጸሙ ምክንያት ጉዳት ሊያገኘው የሚችለው የአእምሮና የስሜት መረበሽን የሚያስከትል የበደለኝነት ስሜት የሚሰማው ከሆነ ብቻ ነው» በማለት ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሐኪሞችና የሥነ አእምሮ ጠበብቶች እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ለስሕተት የተጋለጡ፣ ደካማ ፍጡራንና ፍጽምና የሌላቸው በመሆናቸው አመለካከታቸው በየጊዜው ይለዋወጣል:: ማን ያውቃል? ዛሬ ጉዳት አያስከትልም ያሉትን ድርጊት ነገ አንድ ያልደረሱበትን ዕውቀት ሲያገኙ ጉዳት የሞላበት ነው ይሉት ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ የዛሬ ቃላታቸውን ተቀብለው በክፉ ልማዱ ጸንቶ የተገኘ ወጣት መጨረሻው ምን ይሆን? በዓለም ጠቢባን ቃል ልቡን ከሚያሳርፍ ይልቅ በእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት ጸንቶ የሚኖር ሰው እንዴት የተመሰገነ ነው?
   የዚህ መንፈሳዊ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ዘርን በገዛ እጅ በማፍሰስ ስሜትን ለማርካት መሞከር ምን ያህል ወይም ምን ዓይነት የጤና መታወክ ይፈጥራል? የሚለውን ማብራራት ሳይሆን ምን ያህል? መንፈሳዊ ጉዳት ያስከትላል ለሚለው ጥያቄ በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::
   ምንም እንኳን ከዚህ በላይ ምንም ዓይነት የጤና ጉዳት እያስከትልም፡ ጉዳት የሚያስከትለው ድርጊቱን የሚፈጽመው ሰው የበደለኘነት ስሜት የሚሰማው ከሆነ ብቻ ነው::›› በሚል በባለሙያዎች የተሰነዘረው ሐሳብ አስተማማኝነት እንደሌለው ቢገለጽም በዚህ ክፉ ልማድ የተመረዙትንና እየተሳቡ ያሉትን ሰዎች ከድርጊታቸው እንዳይላቀቁ የሚጫወተው ሚና ግን እጅግ የከፋ ነው:: ምክንያቱም ይህ ሥራዬ የጤና መታወክ የሚፈጥርብኝ ስጸጸት ብቻ ከሆነ ጉዳት እንዳያስከትልብኝ ራሴን እንደ ጥፋተኛ እየቆጠርኩ መቆርቆር የለብኝም እያሉ እንዲጽናኑ ስለሚያደርጋቸው ነው::
  በዚህ መልኩ በክፉ ሥራቸው እንዳይጸጸቱና እግዚአብሔር የሚያመጣባቸውን የቅጣት ፍርድ እያሰቡ እንዳይፈሩ በጤና ባለሙያዎችና በሥነ አእምሮ ጠበብቶች የተሰጣቸው ምክር ምንም ዓይነት ፍርሃተ እግዚአብሔር በልቡናቸው እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ <<የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና›› በእግዚአብሔር ዘንድ የተጣሉና ረድኤት የሌላቸው እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ከክፉ ሥራቸው እንዳይመለሱ ያደርጋል:: ምክንያቱም ሰው ከክፉ ሥራው የሚመለሰው በዋናነት ክፉ ሥራው የሚያስከትልበትን ፍርድ አስቦ ነውና፡፡ ምንም ክፉ ነገር አያገኝኽም እየተባለ በባለ ሙያ
የተመከረ ሰው ምን ፈርቶ ከክፉ ሥራው ይመለሳል?
   በኃጢአት ተግባር ላይ ያለ ሰው «ምን ይመጣብኝ ይሆን?›› እያለ ማሰቡ በውስጡ እግዚአብሔርን መፍራት እንዳለ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳን ከኃጢአት መላቀቅ ባይችል ይህ ፍርሃቱ እንደ ጽድቅ ሊቆጠርለት ይችላል፡፡ ያላየውን እግዚአብሔርን መፍራት የማመን ምልክት ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚያመጣውን ፍርድ አስቦ መፍራት ከኃጢአት አንጽቶ እንደ ጻድቅ ሊያስቆጥር መቻሉን መጽሐፈ መነኮሳት በዚህ መልኩ ገልጾታል:: «ፍራህ እምእንታክቲ ምግባራት እንተ ትትኄበብ ከመ ባቲ መገሥጽ እስመ ዘከመዝ ግዕዙ ይትበልሃ ከመ ውእቱ የሐውር በአፍኣ እምፍኖታ» : «ቅጣትና ተግሣጽ እንደሚያስከትል ከጠረጠርከው ሥራ ሁሉ ተጠበቅ እንዲህ ሲፈራ የሚኖረው ሰው ከኃጢአት ውጭ ነው ይባላልና›› ማለት ነው:: ማር.ይስ.አን.16 ምዕ 1
  ሰው ሁሉ ክእግዚአብሔር ጋር እንድ መሆን የሚችለው ከእነዚህ ከሦስቱ መንገዶች ቢያንስ እንኳን በአንዱ መጓዝ ከቻለ ብቻ ነው:: አንደኛው ያለ ምንም ምክንያት በራሱ ተነሣሥቶ እንደ አብርሃም ፈጣሪውን ፈልጎ ካመነ። ሁለተኛው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በግርማ እግዚአብሔር ተገልጾ ከተመለስ፡፡ ሦስተኛ ደግሞ በክፉ ሥራው ምክንያት የሚመጣበትን ቅጣት አስቦ ከፈራ ነው፡፡ የሐዋ 9፥6፣ ማር ይስ አን 3 ምዕ1
ለምሳሌ:- እንደ ቅዱስ ወቅሪስ፡፡ ቅዱስ ወቅሪስ መልከ መልካም ነበረ። ከዕለታት በአንድ ቀን ከሴት ጋር ተቃጠረ፡፡ በዚያችም ሌሊት ራእይ አየ፡፡ ራእዩም «እርሱ ታሥሮ ከብዙ እሥረኞች ጋር በንጉሡ ፊት ቆሞ እሥረኞቹ እያንዳንዳቸው በተራ ሲመረመሩ እርሱ ግን የቀጠርኳት ሴት ባሏ አሣሥሮኝ ይሆን? እያለ ሲጨነቅና ሲፈራ በዚህ ጊዜ ጠባቂ መልዐኩ ከወዳጆቹ አንዱን መስሎ መጥቶ ይህን ሥራ ሠርተህ እንዳታሲዘኝ ማልልኝና እኔ ልዋስህ እያለ ሲያስምለው›› ነበር። ከዚያ በኋላ ሄላኔ የምትባል ደግ ሴት ነበረች ወደ እርሷ ሄዶ ያየውን ራእይ ነገራት፡፡ እርሷም ተርታ ልብስ ለብሰህ አልባሌ መስለህ ፈጣሪህን አገልግለው ይምርሐል አለችው፡፡ እርሱም እንደነገረችው አድርጐ ከፈጣሪው ታርቋል፡፡ ማር ይስ አን 3 ምዕ 1 እንዲህ ከሆነ ፍርድን አስቦ መፍራት ጻድቅ ያደርጋል ቢባል ምን ይደንቃል?
   ከክፉ ሥራ ለመመለስና ንስሐ ለመግባት ጥርጊያ ጎዳናው እግዚአብሔርን መፍራት ነው :: እግዚአብሔርን መፍራት ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ርኅራኄን እንደሚያስገኝ ከዚህ በታች የተጻፈው ታሪክ ያስረዳል:: የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልያስ <<በእግዚአብሔር ፊት ክፉን ሥራ ለመሥራት ራሱን ለሸጠ>> ለአክዓብ የሚደርስበትን ቅጣት ሁሉ በነገረው ጊዜ አክዓብ «ልብሱን ቀዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፥ ጾመም፣ በማቅ ላይም ተኛ ቅስስ ብሎም ሄደ፡፡›› ይላል:: በተለይ «ቅስስ ብሎ ሄደ» የሚለው ዐረፍተ ነገር የአክዓብን ፍርሐትና ድንጋጤ ያመለክታል:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር «ኤልያስ ሆይ አክዓብ እንደ ደነገጠ (እንደፈራ) ተክዞም እንደሄደ አየህን? በፊቴ የተዋረደ ስለሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም።›› በማለት በይቅርታ ወደ አክዓብ መመለሱን ተናግሯል:: 2ነገ 20፥27

ሰው በክፉ ሥራው «ምን ይመጣብኝ ይሆን?» እያለ ሲፈራ እግዚአብሐርን መፍራቱ እንጂ ሌላ አይደለም:: ከላይ የተጠቀሰው የአክዓብ ታሪክ እግዚአብሔርን መፍራት የሚያስገኘውን ታላቅ ጥቅምና በእግዚአብሔርም ዘንድም ያለውን ተወዳጅነት ያስረዳል፡፡ ሰይጣን ደግሞ ሰው እግዚአብሔርን በመፍራቱ ብቻ እንኳን የሚያገኘውን ጥቅም ያውቃልና የዓለምን ምሁራን አስነሥቶ በልዩ ልዩ ጐዳና ፍርሐተ እግዚአብሔርን ከሰው ልብ የሚያርቅ ንግግር ያናግራቸዋል፡፡ አንድ ጊዜ ፍርሐትና የበደለኝነት ስሜት ጤናን ሊያቃውስ እንደሚችል ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍርሐት በራስ የመተማመን ጉድለትና የብቃት ማነስ ምልክት እንደ ሆነ በማስረዳት ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት እንዳይመላለሱ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ግን ምንም ከበደል መራቅ ባይቻለን ፍርድን አስቦ መፍራታችን ብቻ እንኳን ዋጋ ያለው መሆኑን እንረዳለን፡፡ ሰይጣን በውጫዊ ማንነታችን ሰልጥኖ ኃጢአት ቢያሠራንም ፍርድን አስበን መፍራታችን በውስጣችን የምንገዛው ለእግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ውጫዊው ኃላፊና ፈራሽ ሲሆን ውስጣዊው ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ በውጫዊው ሰውነት ከመገዛት በውስጣዊው መገዛት በብዙ ይበልጣል:: እንዲሁም በአፍኣዊ ማንነታችን ኃጢአት እየሠራን ለሰይጣን ከምንገዛው ይልቅ በውስጣችን ለእግዚአብሔር የምንገባው አገዛዝ ይበልጣልና መጨረሻችን የእግዚአብሔር መሆን ነው:: ስለዚህ «ለእግዚአብሔር በፍርሐት እንገዛ›› መዝ 2፡11 ብንበድልም ፍርሐትን ከልባችን አናርቃት።

«ግብረ አውና>>ን መፈጸም ሰው መግደል ሊሆን ይችላል?
  ብዙ ሰዎች ዘር ሲክፍሉ ወይም ሲፈሳቸው ይልቁኑም አውቀው ያደረጉት ከሆነ «ሰው እንደ መግደል ይቆጠርብኝ ይሆን?» እያሉ ራሳቸውን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ግብረ አውናንን እየፈጸሙ ዘርን ማፍሰስ ሰው እንደ መግደል ይቆጠር ይሆን?
   ወንድና ሴት ሩካቤ ሲያደርጉ ከወንድ ዘር ከሴት ደግሞ ደም ተከፍለው ተዋሕዶ ባደረጉ ጊዜ ተከፍሎዋ እንደ የብርሃን ፋና ይሁን እንጂ በዚያው ጊዜ ነፍስም አብራ ትከፈላለች:: ነገር ግን ሴቶች በየወሩ ደም ሲያዩ ወንዶችም ዘር ሲወጣቸው ነፍስ እንደ ማጥፋት አይቆጠርባቸውም። እንዴት?
ምሥጢሩ እንዲህ ነው:- እነሆ እሳት በእንጨት ውስጥ መኖሩ የታወቀ ነው:: ሆኖም አንድ እንጨት ከሌላ ጋር ሳይሳበቅ ለብቻው እሳት መፍጠር አይችልም:: እሳት በእንጨት ውስጥ ይገኛል ቢባልም ቅሉ እንጨት መስበር እሳት እንደ ማጥፋት አይቆጠርም:: እንጨት ምሳሌነቱ እንደ ሴት ደምና እንደ ወንድ ዘር ሲሆን እሳት ደግሞ እንደ ነፍስ ነውና፤ ሴቶች ለብቻቸው የሚያስገኙት ደም ወንዶችም ለብቻቸው የሚከፍሉት ዘር ነፍስን ሊያስገኝ ስለማይችል ሰው እንደ መግደል ሊቆጠር አይችልም:: ሰው የሚባለው ራሱ አራት ባሕርያተ ሥጋ ሦስት ባሕርያተ ነፍስ ያሉት ፍጥረት ነውና፡፡ ስለ ነፍስና ሥጋ በአጠቃላይ ስለ ሰው ተፈጥሮ የበለጠ ለመረዳት በዚሁ መጽሐፍ የመጀመሪያ ክፍል የሕይወት አጀማመር የሚለውን ንዑስ ክፍል ያንብቡ፡፡ ግብረ አውናንን የሚፈጽሙ ሰዎች በተያያዥ ሊከሠትባቸው የሚችለው ቀጣዩ ጥያቄ ደግሞ ሩካቤ ሥጋ ፈጽመው የማያውቁ ከሆነ ‹‹ከዚህ በኋላ ድንግል ልባል እችላለሁ?» የሚል ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሆን ሐሳብ ስለ ሴቶች ድንግልና በሚያትተው ንዑስ ክፍል «ድንግል ነኝን?» በሚለው ርዕስ ሥር የሰፈረ በመሆኑ እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡

   «ግብረ አውናን» የሚያስከትለው ጉዳት
   ግብረ አውናን (ሴጋ) ውጥረትን ለፈጠረ አንድ ችግር የተሳሳተ አማራጭን መጠቀም እንደመሆኑ መጠን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ብርታትና ጥንካሬን የሚጠይቁ መንገዶችን እንድንሸሽ ያለማምዳል:: ይህ ማለት ደግሞ እጅግ ሲበዛ ሰነፍ እንድንሆን ያደርጋል ማለት ነው::
   ግብረ አውናን ኃጢአት እንደ መሆኑ መጠን በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ቅጣትን ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም ቅጣቱ እንደ አውናን ከመቀሠፍ ሊጀምር ይችላል፡፡ ዘፍ 38÷9 ሰላም ማጣት፣ ቁጭት፣ ጸጸት፣ ጭንቀት፣ መረበሽ፣ ንጹሕ ያለ መሆን ስሜትና የመሳሰሉት የግብረ አውናን እንጻራዊ ጉዳቶች ተደርገው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ክዕወተ በርዕ ሥር እየሰደደ ሲሄድ ባለበት አይወሰንም፡፡ «አንደኛውኑ ዝሙት ይሻላል›› በማሰኘት ወደ ዝሙትና ግብረ ሰዶም ሊያመራ ይችላል፡፡ ገለልተኝነት፣ ብቸኝነትን መሻትና የሥራ ተነሣሽነትን ማጣት ደግሞ ሌላው የዚህ ክፉ ልማድ ጐጂ ገጽታ ነው። የመሰንጋት ሌላው አደገኛና ጐጂ ገጽታው ደግሞ ተስፋ መቁረጥና አጉል ጸጸት እንዲሁም ከንቱ ትሕትናን ማሳደሩ ነው፡፡ አጉል ጸጸቱ እንደ ይሁዳ ዓይነት ጸጸት በመሆኑ ኀፍረተ አካልን ተናዶ እስከ መቁረጥ ለ.ያደርስ ይችላል:: ይሁዳ ራሱን እስከ መግደል የደረሰው በአጉል ጸጸት ነውና፡፡ የሐዋ 1፥16-20፤ ማቴ 27፥3-5
  አጉል ትሕትና ማለት ደግሞ በዚህ ክፉ ልማድ የተመረዙ ሰዎች ዘማርያን፣ ሰባክያን፣ መነኮሳትና በልዩ ልዩ አገልግሎትና መንፈሳዊ ሙያ የተሰማሩ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ:: መንፈሳዊ አገልግሎት ንጽሕናን የሚፈልግ በመሆኑ ኑሮአቸውና መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ሳይጣጣም ሲቀር «ማገልግል አይገባኝም!» በማለት ከትሩፋትና ከበጐ ሥራ ራሳቸውን የሚያሸሹ አሉ:: ነገር ግን ክፉ ሥራን እንጂ የትሩፋት ሥራን መሸሽ በምንም መልኩ አይበጅም፡፡ ከአገልግሎት ጋር ሆነን ያላራቅነውን ክፉ ሥራ ከረድኤተ እግዚአብሔር ተለይተን ልናርቀው አንችልም፡፡ ውሣኔያችንን አየመረመርን ከበላዮቻችን ማለትም ከመንፈሳዊ አባቶች ጋር እየመከርን በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን መኖርን መፍትሔ እናድርግ፡፡ ይኸውም ለጊዜው ነው እንጂ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ከዚህ ልማድ መለየት ብቻ ነው፡፡
  በጋብቻ ሕይወት ውስጥ አንዱ ለሌላው ወገን ደስታና እርካታ ማሰቡ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጋብቻ ግንኙነቶች ይበላሻሉ:: በጋብቻ መሃል ጭንቀትና ቅሬታም ይፈጠራል፡፡ ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ያዘወትሩት የነበረው የፆታ ብልትን በመነካካትና በማሻሸት ለመርካት የመሞከር ተግባር ወይም ሴጋ ስለ ራስ ደስታና እርካታ ብቻ የማሰብ ልምድን ያሳድግባቸዋል:: ይህ ልምድ ደግሞ በጋብቻ ውስጥ የሚገኘውን ደስታ አደጋ ላይ ይጥለዋል፡፡ ምክንያቱም ስለራስ እርካታ ብቻ በማሰብ በባልና በሚስት መሃል መተሳሰብ እንዲጠፋ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ችግር ትክክለኛውን መፍትሔ አያግኙለት እንጂ በዓለማዊያኑ ዘንድ በስፋት ለውይይት ይቀርባል፡፡ በመንፈሳዊያን ሰዎች ዘንድ ደግሞ ምንም በሰፊው ባይወያዩበት በጋብቻ ውስጥ ለሚፈጠሩ የግጭት መነሻዎች ዋነኛ ሲሆን የሚመነጨውም ከትዳር በፊት ይዘወተር ከነበረ ክዕወተ ዘርዕ (ሴጋ) አማካኝነት ነው፡፡ አንተ ወጣት ይህ ክፉ ልማድ እስከ ጋብቻ ዘልቆ እንዴት ሊጐዳ እንደሚችል ተረዳህን?

ከ«ግብረ አውናን» እንዴት መላቀቅ ይቻላል?
ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው:: የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደ ሆነ በፍጹም የሚለቅ አይመስልም፤ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል:: ይህ ክፉ ልማድም እንደ ማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመጸጸት በጠንካራ መንፈስ ከተነሡ ሊያስወግዱት ይቻላል:: ተስፋ መቁረጥ ከሁሉ ይከፋልና በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ሊወገድ የማይችል አድርጐ በመቁጠር ተስፋ አለመቁረጥ ነው::

ለ. መሰንጋት ልማድ ነው፡፡ ልማድ ደግሞ በልማድ ይሸነፋል፡፡ ጠንክረህ ከተነሣህ ይህን ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም:: ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሣትህ በፊት «ይህን ክፉ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለሁ?» በማለት ራስህን ጠይቅ፡፡ መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትጸጸት ቀርተህ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጐጂነቱ ዘልቆ ወደ ልብህ ስላልገባ ነው:: ስለዚህ መፍትሔው በመጀመሪያ ጎጂነቱን አምነህ ይህን ኃጢአት መጥላት መጀመርህ ነው፡፡ ይህ ካልሆነና የዚህን ኃጢአት ጣዕም ከልብህ ሳታወጣ ልታርቀው ብትታገል የአምላክህን ረድኤት አታገኝም። እግዚአብሔር ከኃጢአት ከመለየታችን በፊት መራራነቷን ከልብ እንድናምን ይፈልጋልና፡፡ የኃጢአት ጣዕም ከልብ ካልወጣ ለጊዜው ከኃጢአት በልዩ ልዩ ምክንያት ብንለይ እንኳን ተመልሰን አንድ መሆናችን አይቀርም፡፡

ሐ. ይህን ክፉ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ናቸው:: ከዚህ እኩይ ልማድ ለመላቀቀቅ ከፈለግህ «ተዐቅቦ›› ያስፈልግሃል፡፡ «ተዐቅቦ›› ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው፡፡ የምትከለክለውም ወደዚህ መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ከመሳሰሉት ነው:: ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም፣ በአካልም ቢሆን በምንም መልኩ ከማየት ተቆጠብ። በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት፡፡ ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ስዕሎችን፣ ጽሑፎችንና ወሬዎችን አጥብቀህ ሽሻቸው፡፡ ሥራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል? ብሎ እንደ መጠየቅ እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ::

መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ፡፡ ቦዘኔ አትሁን፤ ትጉህ ሠራተኛ ሁን:: ሥራህም በእንቅሳቃሴ የተሞላ ወይም አእምሮን ያለ ዕረፍት የሚያሠራ ይሁን። ነጋዴ ብትሆንና ገበያ ሲመጣ ሽጠህ ብትቀመጥ ከዚያ በኋላ ግን ቁጭ ብለህ ብትውል በሥራ ቦታ በመዋልህ ብቻ አእምሮህ እስካልተያዘ ድረስ በመንፈሳዊ ጎዳና ከተመለከትከው እየሠራኽ ነው አይባልም፡፡ በትርፍ ሰዓትህ የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሠራ ሥራ ፈጥረህ ሥራ:: የዝሙት ማራገቢያው የአእምሮ ቦዘኔነት ነውና፡፡

ሠ. «ሁለት ሁለት አድርጐ ላካቸው» የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ፡፡ በዚህ ክፉ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትወደድ፡፡ ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን፡፡ ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰቦችህ አንዱ ሊሆን ይችላል:: ከብቸኝነት ይልቅ መወያየትን ይልቁንም መንፈሳዊ ውይይትን ዘወትር አድርግ፡፡ በጸሎት ከሚረዱህ መንፈሳዊያን መምህራንና አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ፡፡ ከእነርሱ ጋር በመወያየትህ በጸሎታቸው እንዳይረሱህ ከማድረግ ጋር ለነፍስህ ወደብ የሚሆኑ ብዙ መንፈሳዊ ነገሮችን ትማራለህና፡፡

ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታ አትሂድ፡፡ በቂ ዕረፍት አግኝቼ የለምን? መኝታ ለምን አስፈለገኝ? ብለህ ራስህን ጠይቅ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስትተኛ ውለህ እንቅልፍ ያምርሃልና፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትተኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል:: ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ሕሊናህ ይሳባል፡፡ ሰውነትህንም በመደባበስ ፍትወትህን ለማርካት ትጥራለህ፡፡ ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ፡፡

ሲ ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና፡፡ ስትተኛም በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ:: ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር፡ አመጋገብህ በልክ ይሁን ጾምን በተገቢው መንገድ ጹም፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብብ፡፡ የመንፈሳዊ ሙያ ባለቤት ከሆንክ የምታወቀውን ዜማ ድምፅ አወጥተህ አንጐራጉር፡፡ ያም ባይሆን የምትችለውን መዝሙር ዘምር።

ሽ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሣብህ አንድ ዓይነት የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ሥራ:: ወይም ወዲህና ወዲያ ተንቀሣቀስ፡፡ ከዚህም ሁሉ ይልቅ ደግሞ ከሆነልህ መስገድህ ይመረጣል:: ሽንትን መሽናትም ጥሩ መድኃኒት ሊሆንህ ይችላል:: በየጊዜው ጸበል መጠመቅንም ቸል አትበል፡፡ ነገር ግን ይህን በምታደርግበት ጊዜ ሕዋሳተ አንስትን ከማየት በእጅጉ ተጠንቀቅ፡፡
ቀ. ሰውነትህ ሲበላህ ይልቁኑም ወደ አባለ ዘርዕ አካባቢ ከሆነ ትኩረት ሰጥተህ አታስበው፡፡ ምክንያት እንዳይሆንብህ ተጣጥበህ ንጹሕ ለመሆን ሞክር፡፡ የበላህን ቦታ ግን በምንም መልኩ አትከከው፡፡ ማከክ ሰውነትን ከማቁሰል በቀር ይህን ለመሰለ ፈተና መፍትሔ አይሆንምና፡፡ ከዚያ ይልቅ መጽሐፈ መነኮሳት «ግበር ትእምርተ መስቀል በሕሊናከ ውስተ መካነ ደዌከ› ፤ ‹ሕመም ወይም ማላከክ በተሰማህ ቦታ ላይ በሕሊናህ የመስቀል ምልክት ሥራ» ይላልና። በሚያሳክክህ ቦታ ላይ በሕሊናህ አማትብበት፡፡ በሕሊናም ማለቱ የሚያይህ ሰው ነገር እንዳይመራመርኽ ለማድረግ ነው፡፡ በተረፈ ግን አጥብቀህ ጸልይ፡፡
ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን!


በቀጣይ ምዕራፍ አምስት <<ምትረተ አስኪት>> በሚል ይቀጥላል.....

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሚያዝያ ፲፩
ዝክረ ሰማዕታተ ሊብያ
ዘጠነኛ ዓመት

አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
Audio
ሰአሉ ለነ ሰማዕታተ ሊብያ
ሰአሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን፣(2)
ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት።(2)

ከምድረ ሊብያ ተጣራ ኢየሱስ፣
በተዋሕዶ ልጆች ስሙ እንዲቀደስ፣
ኢየሱስ አምላክ ነው እያሉ በጽናት፣
መንግሥተ ሰማይን ህጻናት ተሻሟት።(2)

ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2)

በመከራ ጊዜ ሚዛን ላይ ወጣችሁ፣
በክርስቶስ ጸጋ እንደ ዕንቁ አበራችሁ፣
እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይፍን ሳትፈሩ፣
እግዚአብሔር ይመስገን በቃችሁ ለክብሩ።(2)

አዝ-----

እዩት ሲያንገላቱት ሲያዳፉት ጨክነው፣
ምንም አልቀመሰም ወንድሜ ጾሙን ነው፣
ግን እንደ ሰርገኛ በደስታ ይጓዛል፣
በሰይፍ ፊት ቆሞ ለወንጌሉ ታምኗል፣
መከራውን ንቆ ለወንጌሉ ታምኗል።

አዝ-----

ግርፋት ወይስ ሞት መታረዱ ነው ወይ፣
ከክርስቶስ ፍቅር እኛን የሚለየን፣
ያመለክነው አምላክ እውነት ስለሆነ፣
ለክብር ተፋጠኑ ልባቸው ጨከነ።(2)

ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2)

የኋልዮሽ ታስረው እንደበግ ሲነዱ፣
ይመስሉ ነበረ ለሰርግ የሚሄዱ፣
በጉድጓድ ተከተው ለቀናት ቢራቡ፣
በውኃ ጥም ዝለው አልተነዋወጹም።

አዝ-----

ገዳዮች ድል ሆኑ ሙታን ሆኑ እነርሱ፣
የተዋሕዶ ልጆች በድል ገሰገሱ፣
በደማቸው ጸዳል ዓለምን ቀየሩ፣
የኢትዮጵያ ከዋክብት በሊብያ አበሩ፣
የኢትዮጵያ ከዋክብት በዓለም አበሩ።

ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2)
           በሊቀ መዘምራን ይልማ ኅይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ እሑድ(ሳምንት)


ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ
‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከጌታው፣ ከመምህሩ ከክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤
‹‹መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ
በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል
የለምና፤›› (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡
ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ ‹‹ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን
መንግሥት ለማየት አይችልም፤›› በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ
ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ
ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡
‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ
ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ
አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም
የተወለደ መንፈስ ነውና፤›› (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡
አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- ‹‹አንተ የእስራኤል
መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን?
በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ
ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ
ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም …
ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ
እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ...፤›› እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም
‹‹ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ
ወኢተረከ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ
እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም
ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን
ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤›› (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት
ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ
ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣
ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ሮሜ ፯፥፩-፱
-፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፭፥፴፬ እስከ ፍጻሜ

ምስባኩም፦ መዝ ፲፮፥፫
"ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው"
"ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው"

ወንጌሉም፦ ዮሐ ፫፥፩-፳

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኒቆዲሞስ
@Ethiopian_Orthodox
"ኒቆዲሞስ"
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣
በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣
የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣
ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣
እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!!

ያዳምጡት!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
          ምዕራፍ አምስት
            ምትረተ እስኪት

  «ምትረተ እስኪት» ማለት አባለ ዘርዕን መቁረጥ ማለት ነው:: በሀገራችን ሌላውን መስለብ እንደ ባህል የሚነገርላቸው አንዳንድ ጎሳዎችና ብሔረሰቦች ይገኛሉ:: በዘመነ ኦሪትም ቅዱስ ዳዊት ሜልኮል የተባለች የንጉሥ ሳኦልን ልጅ ለማግባት የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ሰልቦ በማምጣት ማጫ መስጠት ነበረበት፡፡ 1ሳሙ 18፥25-27
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM