#EthiopiaCheck Fake Account Alert
የፍትህ ሚንስትር በሆኑት በአቶ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ስምና ፎቶን በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል!
አካውንቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተከፈተ ሲሆን አሁን ላይ ከ2,240 በላይ ተከታዮች አሉት። የፍትህ ሚኒስቴር ይህ የትዊተር አካውንት የአቶ ጌዲዮን አለመሆኑን ዛሬ አስታውቋል።
አቶ ጌዲዮን ምንም አይነት የትዊተር አካውንት እንደሌላቸው የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ በተጠቀሰው ሀሠተኛ አካውንት የሚተላለፉ መልዕክቶችም የሚኒስትሩ አለመሆናቸውን ጨምሮ አስታውቋል።
ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።
@EthiopiaCheck

“ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድ የትዊተር አካዉንት የላቸዉም”--- የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ቼክ
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካዉንቶች የተለያዩ መልክቶችን እየለጠፉ ይገኛሉ።
በተለይ ከ4,000 በላይ ተከታዮች ያሉት አካዉንት በትላንትናዉ ዕለት ብቻ ከ10 በላይ መልክቶችን ለጥፏል።
ኢትዮጵያ ቼክ ይህንና መሰል የትዊተር አካዉንቶች እዉነተኛነት ለማረጋገጥ በሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ስርጭትና ዲጂታል ሚዲያ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ አብዲዴቅ መሀመድን አናግሯል።
እርሳቸዉም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድ አሁን ላይ የትዊተር አካዉንት እንደሌላቸዉ ነግረዉናል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ የተረጋገጠ የፌስቡክ አካዉንት እንዳላቸዉም ነግረዉናል (https://www.facebook.com/mustafa.omer.146)።

#EthiopiaCheck Telegram Poll Result
ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለት "የጥላቻ ንግግር፣ ሀሰተኛ መረጃ ወይም አደገኛ ፅሁፍ ተጋርቶ ተመልክተው ሪፖርት አርገው ያውቃሉ? ከሆነ በየትኛው መተግበርያ ላይ?" የሚል ጥያቄ ለቴሌግራም ተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር፣ ከአንድ በላይ መልስ መምረጥ እንዲቻልም ክፍት ተደርጎ ነበር።
በአጠቃላይ አንድ ሺህ ሰዎች ድምፅ በመስጠት የተሳተፉ ሲሆን ውጤቱም 64% ፌስቡክ፣ 22% ሪፖርት አድርጌ አላውቅም፣ 18% ትዊተር፣ 18% ዩትዩብ፣ 12% እንዴት ሪፖርት እንደሚደረግ አላውቅም፣ 11% ቴሌግራም እንዲሁም 2% ኢንስታግራም ብለው መልስ ሰጥተዋል።
ውጤቱ እንደሚያሳየው በርከት ያሉ ሰዎች ፌስቡክ ላይ ሪፖርት አርገው እንደሚያውቁ ገልፀዋል፣ ነገር ግን አሁንም ብዙዎች ሪፖርት አርገው እንደማያውቁ ወይም ሪፖርት እንዴት እንደሚደረግ እንደማያውቁ ገልፀዋል።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች አደገኛ መልእክቶችን እንዲሁም ሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል ስርዐት አላቸው፣ እነዚህን የሚያስረዱ የተለያዩ ፅሁፎችን እና ግራፊክሶችን ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ ያቀርባል።

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል!
ከገጾቹ መካከል ይህ “Oda Bultum University- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ” የሚል ስያሜ የሚጠቀምና ከ11,340 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተገለጸው የፌስቡክ ገጽ ሀሠተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል። በገጹ የሚተላለፉ መልዕክቶችም ዩኒቨርሲቲውን እንደማይወክሉ ገልጿል።
ትክክለኛው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ ከ14,530 በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://www.facebook.com/OBUEthiopia
ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።
@EthiopiaCheck
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል!
ከገጾቹ መካከል ይህ “Oda Bultum University- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ” የሚል ስያሜ የሚጠቀምና ከ11,340 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተገለጸው የፌስቡክ ገጽ ሀሠተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል። በገጹ የሚተላለፉ መልዕክቶችም ዩኒቨርሲቲውን እንደማይወክሉ ገልጿል።
ትክክለኛው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ ከ14,530 በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://www.facebook.com/OBUEthiopia
ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።
@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck Explainer
የጥላቻ ንግግር ያለውን የፌስቡክ ፖስት እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?
በአንድ ሰው ወይም በተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ ብሔርን፣ ብሔረሰብንና ህዝብን፣ ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ከተመለከቱ በቀላሉ ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
የጥላቻ ንግግሩን በፌስቡክ ከተመለከቱ:
1. ከጽሁፉ ከላይ በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት ነጠብጣቦች (…) ይጫኑ
2. ቀጥሎ የተዘረዘሩ ምርጫዎችን ይመለከታሉ፣ ‘Find support or report post’ የሚለውን ይምረጡ
3. ከዚያም ‘Hate speech’ የሚለውን ይምረጡ
4. ‘Race or ethnicity’, ‘Religious affiliation’ የሚሉናሌሎች ምርጫዎችን የሚያገኙ ሲሆን የጥላቻ ንግግሩ ትኩረት ነው የሚሉትን ይምረጡ
5. በመጨረሻም ‘Submit; የሚለውን ይጫኑ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Explainer
የጥላቻ ንግግር ያለውን የፌስቡክ ፖስት እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?
ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን ይህን አጭር ቪድዮ ይመልከቱ።

የጥላቻ ንግግር ያለውን ፅሁፍ በቴሌግራም ከተመለከቱ እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?
በአንድ ሰው ወይም በተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ ብሔርን፣ ብሔረሰብንና ህዝብን፣ ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር በቴሌግራም ከተመለከቱ በቀላሉ ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
1. ንግግሩን ወይንም መልዕክቱን ካስተላለፈው አካውንት ከላይ በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት ነጠብጣቦች ይጫኑ
2. ቀጥሎ ‘Report’ የሚለውን ይምረጡ
3. ከዚያም ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ‘Violence’ የሚለውን ይምረጡ
4. ቀጥሎም የጥላቻ መልዕክት የሆነውን ጽሁፍ፣ ፎቶ ወይንም ቪዲዮ ይምረጡ
5. በመጨረሻም ‘Send Report’ የሚለውን ይጫኑ

⬆️
#EthiopiaCheck Explainer
Ameerikaan yoom irraa eegalee Itoophiyaa carraa daldala qaraxa irraa bilisaa /AGOA/ irraa haquuf karoorfatte?
Dheengadda Onkololeessa 23, 2014 pirezidaantiin Ameerikaa Joo Baayidan biyyaalee Afriikaa sadi; Itoophiyaa, Giiniifi Maalii carraa daldala qaraxa irraa bilisaa ‘African Growth and Opportunity Act (AGOA)’ jedhamuun beekamu irraa haquuf karoora akka qaban ergaa Kongirasii biyyattiif dabarsaniin beeksisanii jiru.
Sababni tarkaanfii kanaas Itoophiyaa keessatti sarbamni mirgoota namoomaa jiraachuu akka ta’e barreessaniiru.
Namootni heddu immoo tarkaanfiin kun guyyuma dheengaddaarraa eegalee hojiirra akka ooletti miidiyaalee hawaasummaarratti yeroo barreessan mul’ata.
Haa ta’u malee prezidaantiin US Joo Baayidan xalayaa isaanii keessatti akka kaa’anitti biyyaalee sadeen Mudde 23, 2014 (akka lakkoofsa faranjootaa January 1, 2022) irraa eegalee carraa daldala qaraxa irraa bilisaa /AGOA/ irraa haquuf yaada akka qabanidha kan himan.
Ji’oota lamaan itti aanan keessattis biyyaaleen sadeen ulaagaalee carraa daldalaa kana keessa turuu isaan dandeessisu guutuuf fooyya’iinsa taasisaa jiraachuu isaanii akka hordofanis himaniiru.
Kanaafis dhimmi carraa daldala qaraxa irraa bilisaa irraa haqamuu Itoophiyaa wanta yeroo ammaa hojiirra oole osoo hintaanee karoora haala kana booda jiru irratti hundaa’uun hojiirra ooludha.
Carraan daldala qaraxa irraa bilisaa (AGOA) maali?
Carraan daldala qaraxa irraa bilisaa (AGOA) carraa daldalaa Ameerikaan biyyaalee Afriikaa Sahaaraa gadiif laattefi biyyaaleen qaraxa malee omishaalee isaanii gabaa Ameerikaatiif ittin dhiyeessanidha.
Biyyaaleen Afriikaa Sahaaraa gadiis fayyadamtoota carraa kanaa ta’uuf ulaagaalee guutuu qaban qabu.
Kunneen keessaayis biyyaaleen kunneen olaantummaa seeraafi mirgoota namoomaa fooyyeessuuf hojjechuu akka qaban ajaja.
Bara 2020 keessas biyyaaleen Afriikaa 38 fayyadamtoota carraa daldala qaraxa irraa bilisaa (AGOA) akka ta’an ragaan waajjira Pirezidaantii Ameerikaa agarsiisa.

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Explainer
Maxxansa Feesbuukii haasaa jibbiinsaa qabu akkamiin ‘report’ gochuun danda’ama?
Viidiyoo gabaabaa Itoophiyaa Cheek qopheesse kana daawwadhaa!

#EthiopiaCheck Fake News Alert
የኬንያው Citizen TV ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች ብሎ ያወጣው መረጃ የተሳሳተ ነው!
‘Citizen TV’ የተባለው የኬንያ ቴሌቪዝን ጣቢያ በትናንትናው ዕለት “ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች” የሚል መረጃ አስረጭቶ ነበር። የቴሌቪዥን ጣቢያው ኬንያ ከ800 ኪሎሜትር በላይ የሚረዝመውን የሁለቱን ሀገራት ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን ለዘገበበት ዜና ምንጭ አልጠቀሰም።
የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት (Kenya Police Service) ዛሬ እንዳስታወቀው የኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር መዝጋቱን በተመለከተ በሚዲያ የተሰራጨው መልዕክት የተሳሳተ መሆኑን አስታውቋል (https://twitter.com/NPSOfficial_KE/status/1456224083046191108?t=eCburFhxFnfqE1pTwCOrCQ&s=19)
“አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ መንገድ እንደዘገቡት ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር አልተዘጋም” ያለው የኬንያ ፖሊስ “ያደረግነው በድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ቁመናችንን ማጠናከር ነው” ሲል አብራርቷል። የኬንያ ፖሊስ በተጨማሪም በድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ገልጿል።
የኬኒያ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት “አጎራባች” ባላቸው ሀገሮች እየታዩ ነው ካላቸው የጸጥታ ሁኔታዎች አኳያ አምስት ነጥቦችን የያዘ መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ከነጥቦቹ መካከል በድንበር አካባቢ የጸጥታ ቁጥጥርን ማጠናከር የሚል ይገኝበታል።

የጥላቻ ንግግር የተላለፈበትን የዩትዩብ ቻናል ከተመለከቱ በዚህ መልኩ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ!
1. ከቪዲዮው ከታች በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት ነጠብጣቦች ይጫኑ
2. ቀጥሎ ‘Report’ የሚለውን ይምረጡ
3. ከዚያም ከተዘረዘሩት መካከል ‘Hateful or abusive content’ የሚለውን ይምረጡ፤ ይህን ሲደርጉ ከስሩ ምርጫዎች የሚመለከቱ ሲሆን ‘Promotes hatred or violence የሚለውን ይምረጡ
4. ቀጥሎም የጥላቻ ንግግሩ ስንተኛው ደቂቃ ላይ እንደሚገኝ ይጻፉ
5. በመጨረሻ ‘Report’ የሚለውን ይጫኑ

ዘረባ ጽልኢት ዝሓዘ ፌስቡክ ፖስት ብኸመይ ሪፖርት ይግበር?
ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዎ ነዚ ሓጺር ቪዲዮ ንኽርእዩ ንዕድም።
@EthiopiaCheck
ዘረባ ጽልኢት ዝሓዘ ፌስቡክ ፖስት ብኸመይ ሪፖርት ይግበር?
ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዎ ነዚ ሓጺር ቪዲዮ ንኽርእዩ ንዕድም።
@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck Explainer
የጥላቻ ንግግር ያለበትን ፅሁፍ ትዊተር ላይ ከተመለከቱ በዚህ መልኩ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ!
1. ከጽሁፉ ከላይ በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት ነጠብጣቦች ይጫኑ
2. ቀጥሎ ‘Report tweet’ የሚለውን ይምረጡ
3. ከዚያም ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ‘It’s abusive or harmful’ የሚለውን ይምረጡ
4. ቀጥሎም ‘It directs hate against a protected characteristic’ የሚለውን ይምረጡ
5. ‘Me, Someone else, A group of people’ የሚሉ ምርጫዎችን የሚመለከቱ ሲሆን የጥላቻ ንግግሩ ትኩረት ነው የሚሉትን ይምረጡ
6. ከዚያም እንደምርጫዎ ‘Skip’ ወይንም 'Add1’ የሚለውን ይጫኑ
7. በመጨረሻ ከላይ በቀኝ በኩል ‘Done’ የሚለውን ይጫኑ

Haguugduu afaaniifi funyaanii (maaskii) godhattanii sochii jabeenya qaamaa hojjechuun rakkoo akkamii fida?
Weerara dhibee COVID-19 hordofee itti fayyadamni haguugduu afaaniifi funyaanii (maaskii) daran dabaleera.
Fageenya qaamaa eeggachuun dabalataan haguugduu afaaniifi funyaanii godhadhuun maloota dhibee COVID-19 itti ittifnu keessaati.
Haa ta’u malee Dhaabbatni Fayyaa Addunyaa (WHO) namootni wayita sochii jabeenya qaamaa hojjetan haguugduu afaaniifi funyaanii akka hin godhanne gorsa.
Sababi isaammoo haguugduun afaaniifi funyaanii dandeettii harganuu keenya waan xiqqeessufi.
Kana malees maaskii godhatanii sochii jabeenya qaamaa hojjechuun haguugduun afaaniifi funyaanii dafqaan dafee akka jiidhufi harganuun akka nu rakkisu taasisa.
Dabalataanqlubbu qabeeyyiin xixxiqqoo (microorganisms) akka guddatanis taasisa.
Kanaafuu wayita sochii jabeenya qaamaa hojjennu haguugduu afaaniifi funyaanii keenya baafannee namoota biroorraa fageenya keenya eeggachuun ta’uu qaba.
Odeeffannoowwan birootif akkasumas odeeffannoowan akka isinif mirkaneessinu barbaaddan nubiraan gahuuf marsariitiifi toorawwan midiyaalee hawaasummaa Itoophiyaa Cheek daawwadhaa.
Feesbuukii: https://www.facebook.com/EthiopiaCheck/
Marsariitii: https://ethiopiacheck.org/
Tiwiitara: https://twitter.com/EthiopiaCheck?s=09
Teelegiraama: https://t.me/ethiopiacheck

በአርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስም እና ፎቶ ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶች!
"ድሽታ ግና" በሚል ተወዳጅ ስራው እውቅና ያገኘው አርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስሙን እና ፎቶውን በመጠቀም በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች እንደተከፈቱ ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ቅኝት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሰባት አካውንቶች በስሙ ተከፍተው ይገኛሉ።
በተለይ በትናንትናው እለት በምስሉ ላይ የሚታየውን ፅሁፍ አርቲስቱ እንደፃፈ ተደርጎ በአንድ የሀሰተኛ አካውንት አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ደረጃ በተለይ ፌስቡክ ላይ ተሰራጭቷል።
ግንቦት ወር ላይ አርቲስቱ ለኢትዮጵያ ቼክ ትክክለኛው አካውንቱ ይህ እንደሆነ አስታውቆ ነበር: https://www.facebook.com/tariku.gankise

Odeeffannoon “Komishiniin Gamtaa Afriikaa waajjirasaa yeroof gara iddoo biraatti jijjiirufi” jechuun miidiyaalee hawaasummaarratti naanna’aa jiru “soba” jedhame.
Odeeffannoon ‘Komishiniin Gamtaa Afriikaa waajjirasaafi hojjettootasaa Itoophiyaa jiran yeroof gara biyya biraatti geeddaruufi’ jedhu miidiyaalee hawaasummaarratti naanna’aa tureera.
Fuulawwan miidiyaalee hawaasummaa odeeffannoo kana maxxansanis maddi isaanii xalayaa keessoo dura taa’aan komishinichaa Muusa Faakii Mahamat hojjettoota komishinichaaf qoodan ta’uu himu.
Haa ta’u malee ibsa Komishiniin Gamtaa Afriikaa baaseen odeeffannoon kun soba ta’uu himeera.
Dubbi himaan dura taa’aa komishinichaa Ebba Kaloondoo, “odeeffannichi sobafi bu’uura dhugummaa kan hinqabnedha” jedhaniiru.
Odeeffannoowwan birootif akkasumas odeeffannoowan akka isinif mirkaneessinu barbaaddan nubiraan gahuuf marsariitiifi toorawwan midiyaalee hawaasummaa Itoophiyaa Cheek daawwadhaa.
@EthiopiaCheck
Odeeffannoon “Komishiniin Gamtaa Afriikaa waajjirasaa yeroof gara iddoo biraatti jijjiirufi” jechuun miidiyaalee hawaasummaarratti naanna’aa jiru “soba” jedhame.
Odeeffannoon ‘Komishiniin Gamtaa Afriikaa waajjirasaafi hojjettootasaa Itoophiyaa jiran yeroof gara biyya biraatti geeddaruufi’ jedhu miidiyaalee hawaasummaarratti naanna’aa tureera.
Fuulawwan miidiyaalee hawaasummaa odeeffannoo kana maxxansanis maddi isaanii xalayaa keessoo dura taa’aan komishinichaa Muusa Faakii Mahamat hojjettoota komishinichaaf qoodan ta’uu himu.
Haa ta’u malee ibsa Komishiniin Gamtaa Afriikaa baaseen odeeffannoon kun soba ta’uu himeera.
Dubbi himaan dura taa’aa komishinichaa Ebba Kaloondoo, “odeeffannichi sobafi bu’uura dhugummaa kan hinqabnedha” jedhaniiru.
Odeeffannoowwan birootif akkasumas odeeffannoowan akka isinif mirkaneessinu barbaaddan nubiraan gahuuf marsariitiifi toorawwan midiyaalee hawaasummaa Itoophiyaa Cheek daawwadhaa.
@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck Monday Message
ተመሳስለው የሚከፈቱ የትዊተር አካውንቶችን ለመለየት እንዲችሉ እነዚህን ነጥቦች ያስተውሉ!
ባለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያን በተመለከተ በሚደረጉ የትዊተር መስተጋብሮች ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ረገድ ፈረንጅ/ምዕራባዊ በመምሰል የሚከፈቱ አካውንቶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ አካውንቶች በአጭር ጊዜ በርካታ ተከታይ ሲያገኙ የሚስተዋል ሲሆን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችንም በማስራጨት በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ። እርስዎም እንደዚህ ባሉ ሀሠተኛ አካውንቶች ተጽዕኖ ስር ላለመውደቅ ከመከተለዎና መልዕክቶቻቸውን ከማጋራትዎ በፊት የሚከተሉትን ምርመራዋች ይከውኑ:
- የፕሮፋይል ስምንና የማንነት ገላጭ ጽሁፍን (Bio) በጥንቃቄ ይመልከቱ፣ አሠሳ (search) ያድርጉ።
- ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚሹ ሀሠተኛ የትዊተር አካውንቶች የምዕራባውያንን ስም መጠቀም የሚመርጡ ሲሆን በማንነት ገላጭ ጽሁፋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምር ተቋማት ወዘተ ሠራተኞች እንደነበሩ ይገልጻሉ። እንደዚህ አይነት አካውንቶች ሲመለከቱ ስማቸውንና በማንነት ገላጭ ጽሁፋቸው የተጠቀሱ ተቋማትን በመጠቀም አሠሳ ያድርጉ። እውነተኛ ከሆኑ በተቋማቱ ድረገጾች፣ በሊንክድኢን (LinkedIn) ወይንም በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ ያገኟቸዋል።
- የፕሮፋይል ስሙንና የአካውንቱን URL ስምረት ይመርምሩ። በአብዛኛው እውነተኛ አካውንቶች የፕሮፋይል ስማቸውና የአካውንት URL ስምረት ይኖረዋል። በአንጻሩ በርከት ያሉ ሀሠተኛ አካውንቶች ስማቸውን በየጊዜው የመቀያየር ልምድ ስላላቸው የፕሮፋይል ስማቸውና የአካውንት URL ስምረት የተዘባ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ በሀሠተኛነት የጠረጠሩት አካውንት የፕሮፋይል ስሙ ‘Jhon Anderson’ ከሆነና የአካውንቱ URL “twitter.com/belete-gedamu” የሚል ከሆነ ሀሠተኛ የመሆን ዕድሉ ከፍ ያለ ስለሚሆን ጥንቃቄ ያድርጉ።
- የፕሮፋይል ምስላቸው እውነተኛ ስለመሆኑ ያጣሩ። ተጽኖ ለማድረግ በመሻት የሚከፈቱ ሀሠተኛ የተዊተር አካውንቶች በሰው መሰል ፊቶች (fake-face) አምራች ድረ-ገጾች የተመረቱ ፎቶዎችን ወይንም የሌላ ሰው ምስል ይጠቀማሉ። ጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች (Google Reverse Image Search)፣ ቲንአይ (Tineye)፣ ያንዴክስ (Yandex) እና ሌሎችን ሪቨርስ ኢሜጅ ፈላጊ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የፎቶውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ይሞክሩ።
- አካውንቱ የተከፈተበትን ጊዜ ይመልከቱ። ብዙዎቹ ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚሹ ሀሠተኛ የትዊተር አካውንቶች በቅርብ የተከፈቱ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ ሲሆን አንዳንዶቹ የቆዩም ሊሆኑ ይችላሉ። ከወራት ወይንም ከሳምንታት በፊት የተከፈቱና ተሳትፏቸው ጎላ ያለ አካውንቶች ከሆኑ እውነተኛ ላይሆኑ ስለሚችሉ ይጠንቀቁ። በአንጻሩ አካውንቶቹ ከዓመታት በፊት የተከፈቱ ከሆኑ ተጨማሪ ማጣራት ያድርጉ። አካውንቶቹ ስም አለመቀየራቸውን፣ ተሳትፎ የሚያደርጉበት መጠን በጊዜ ሂደት አለመቀየሩን ወዘተ ይመርምሩ።
- በተጨማሪም የፕሮፋይል ስማቸውንና የትዊተር ሃንድላቸውን (username/handle) ስምረት፣ የተከታዮቻቸውን ብዛትና ማንነት፣ የሚከተሏቸውን ሰዎችና ተቋማት ማንነት፣ የሚያጋሯቸው መልዕክቶች ጥራትን (tweet quality) ወዘተ ስለአካውንቱ እውነተኛነት ወይንም ሀሠተኛነት የሚነግረን ነገር ስለሚኖር በጥንቃቄ ይመርምሩ።
- እንደ ቦቶሜትር (Botometer) ያሉ የትዊተር አካውንት እንቅስቃሴና መረጃ የሚጠቁሙ መተግበሪያዎችን መጠቀምም ስለ አካውንቱ የበለጠ ለማወቅ ይረዳል። እነዚህ መተግበሪያዎች ስለ አካውንቱ እንቅስቃሴ ጊዜና ቦታ፣ የሃሽታግ አጠቃቀም፣ የተከታዮች ማንነት፣ የቋንቋ ምርጫ ወዘተ በቂ መረጃ ይሰጣሉ። አንዳንዶቹ መተግበሪያዎች እንቅስቃሴውን በማጤን የአካውንቱን ትክክለኛነት በቁጥር ይመዝናሉ።

#EthiopiaCheck Update
በኢትዮጵያ የፌስቡክ፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል!
በኢትዮጵያ የፌስቡክ እና ፌስቡክ ሚሴንጀር እንዲሁም ቴሌግራምና ዋትስአፕ የተወሰኑ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን ተመልክተናል።
ኔትብሎክስ የተሰኝዉ አለም አቀፉ የኢንተርኔት ክትትል ተቋምም ይህን በመረጃ አስደግፎ አውጥቷል። አገልግሎቶቹ ዛሬ ከሰአት ጀምሮ እንደተቋረጡም ተቋሙ በድረ-ገጹ አስነብቧል።
የአገልግሎቶቹ መቋረጥ ምክንያትም “የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተሰርቆ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቋል” የሚሉ መረጃዎች መዘዋወር ከጀመሩ በኋላ እንደሆነም ተገልጿል።
ይሁንና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰአት በሰጡት መግለጫ የፈተናው ሂደት በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸው "ምንም ዓይነት ፈተና፣ በማንም፣ በምንም፣ በየትም ቦታ አልተሰረቀም" ብለዋል። ነገር ግን ፈተናውን ፎቶ በማንሳት የመኮረጅ ሙከራ ያደረጉ አራት ተማሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ከኢመደኤ እና ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካም። አሁንም ሙከራ እያረግን ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ስናገኝ ይዘን እንቀርባለን።