Ethiopia Check
26.4K subscribers
1.46K photos
182 videos
741 links
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Download Telegram
ሰላም የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች፣

የመረጃ ማጣራት ስራችንን በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ስናከናውን መቆየታችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ እነዚህን መረጃዎች በድረ-ገፃችን www.ethiopiacheck.org ላይ በየቋንቋዎቹ ገፆች ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን። በዚህም መሰረት:

ለአማርኛ: https://ethiopiacheck.org/
ለአፋን ኦሮሞ: https://ao.ethiopiacheck.org/
ለትግርኛ: https://tig.ethiopiacheck.org/

ኢትዮጵያ ቼክ።

@EthiopiaCheck
#FakeAccountAlert በዶ/ር አለሙ ስሜ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር በሆኑት በዶ/ር አለሙ ስሜ ስም እና ምስል የተከፈተ የትዊተር አካውንት በርካታ አነጋጋሪ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሆነ ተመልክተናል።

አካውንቱ ህዳር 2014 ዓ/ም ላይ የተከፈተ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ አካውንቱ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጦ ነበር። በወቅቱም ዶ/ር አለሙ ስሜ አካዉንቱ የርሳቸዉ እንዳልሆነና ተመሳስሎ የተከፈተ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረው ነበር።

ይሁን እንጂ ይህ አካዉንት የተለያዩ መረጃዎችን ማሰራጨት ከመቀጨሉ በተጨማሪ አምና ታህሳስ ወር ላይ 650 የነበረዉ የተከታዮቹ ብዛት አሁን ላይ ከ10,000 በላይ ደርሷል።

ከትዊተር አካዉንቶች በተጨማሪ በርካታ የፌስቡክ አካዉንቶችና ገጾች የግለሰቡ ስምና ምስልን በመጠቀም መከፈታቸዉንም ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ዶ/ር አለሙ ስሜ አንድ የፌስቡክ ገጽ እንዳላቸዉ ገልፀውልናል: /https://www.facebook.com/Dralemu.official/

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የሁልግዜ መልዕክታችን ነው።

@EthiopiaCheck
#FactCheck ይህ “በቦረና ዞን ዝናብ ዘነበ” በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል ወቅታዊ የዞኑን ሁኔታ አያሳይም።

ይህ በርከት ያሉ ከብቶች ከወንዝ ውሀ ሲጠጡ የሚያሳይ ምስል ከሰሞኑ በቦረና ዞን የዘነበዉን ዝናብ የሚያሳይ መሆኑን በመጠቀስ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲጋራ ተመልክተናል።

https://ethiopiacheck.org/home/borena-zone-severe-drought-rain-%e1%89%a6%e1%88%a8%e1%8a%93/
#FactCheck Suuraan ‘Booranatti roobni roobe’ jechuun marsaalee hawaasaarratti qoodamaa jiru kun dogongora.

Suuraan wayita loon bishaan dhugan agarsiisu kun ‘rooba tibbana godina Booranaatti roobe agarsiisa’ jechuun marsaalee hawaasaa irratti bal’inaan qoodamaa jiraachuu hubannee jirra.

https://ao.ethiopiacheck.org/home/odeeffannoo-sobaa-godina-booranaatti-roobni-roobe-jechuun-qoodamaa-jiru-booranaatti/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer

ቢንግ (Bing) የተባለውን የድረ-ገፅ ማሰሻ በመጠቀም ምስሎችን እንዴት ማጣራት እና በምልሰት መፈለግ እንደሚቻል በዚህ ኢትዮጵያ ቼክ ባዘጋጀው ቪድዮ ላይ እንመልከት። 

@EthiopiaCheck
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer

ቢንግ (Bing) ዝተብሃለ መርበብ ሓበሬታ ተጠቒምና ከመይ ምስልታት ምጽራይን ብግልባጥ ምእላሽን ከምዝከኣል ኢትዮጵያ ቼክ ኣብ ዘዳለዋ እዛ ሓጻር ቪዲዮ ንርአ።

@EthiopiaCheck
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer

Marsariitii ‘Bing’ fayyadamuun akkamiin suuraalee barbaaduufii mirkaneessuun akka danda’amu baruuf viidiyoo Itoophiyaa Cheek qopheesse kana yaa daawwannu.

@EthiopiaCheck
⬆️
#ScamAlert ኢንተርኔትንና ተያያዥ የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ከሰሞኑ የታየ ለየት ያለ የማጭበርበር ድርጊት

ኢንተርኔትንና ተያያዥ የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም አይነተ-ብዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ይፈጸማሉ። ኢትዮጵያ ቼክም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሚዲያ ቅኝትና ክትትል በማድረግ እንዲሁም ከተከታታዮቹ የሚደርሱትን ጥቆማዎች መሰረት በማድረግ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ሲያጣራና ሲያጋልጥ ቆይቷል። 

ከነዚህም መካከል እንደ ኢሉሚናቲ፣ 666 ፣ ሉሲፈር ወዘተ ያሉ አምልኮዎችን (cults) በመቀላቀል በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያግኙ የሚሉት በጣም የተለመዱ ናቸው።

ከሰሞኑም በኢትዮጵያ ህጋዊ እውቅና እንዳለው የሚገልጽና በአባልነት ለሚቀላቀሉ በርካታ ጥቅማ ጥቅሞች እንደሚያስገኝ የሚያስተዋውቅ ጽሁፍ በፌስቡክና በቴሌግራም ሲዘዋወር ተመልክተናል። 

ማስታወቂያው የተለያዩ ስሞችን በመጠቀም በተከፈቱ የፌስቡክ አካውንቶች የሚጋራ ሲሆን አባል ለመሆን መታወቂያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት፣ ጉርድ ፎቶና ቅድመ ክፍያ እንደሚያስፈልግ ይገልጻል። 

ይህን ለመፈጸምም በ0989266370 የስልክ ቁጥር እንዲደውሉ ይጋብዛል።

ኢትዮጵያ ቼክ ከላይ የተጠቀሰውን የስልክ ቁጥር እና በስልክ ቁጥሩ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ማጣራት አድርጓል። 

ማስታወቂያውን የሚያጋሩ ሰዎች ህጋዊ እውቅና አለን ቢሉም እውቅናቸው ለማሳየት ፍቃደኛ አልሆኑም። በተጨማሪም ከስልክ ቁጥሩና በስልክ ቁጥሩ ከተከፈተ የቴሌግራም ቻናል ውጭ በአካል ለመገኘትም ሆነ አድራሻቸውን ለመግለጽ አልፈቀዱም። ይልቁንም ቅድመ ክፍያ ብሩንና ዶክመንቶቹን መላክን እንደ ቅድመ ሁኔታ ይጠቅሳሉ።

በተጨማሪም በሚያጋሯቸው ይዘቶች ላይ ባደረግነው ማጣራት የተለመዱ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ አስተውለናል።  


እንዲሁም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ዳሰሳ ይህን የመሰሉ በርካታ ማስታወቂያዎች በተለያዩ ስሞችና ስልክ ቁጥሮች በተለይም በፌስቡክ ግሩፖች በስፋት እንደሚጋሩ ተመልክቷል። 

የሚዲያ አጠቃቀም ንቃታችንን ከፍ በማድረግ ይህን ከመሰሉ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች እራሳችንን እንጠብቅ። 

@EthiopiaCheck
#VerificationNotice ኢትዮጵያ ቼክ ለዚህ የቴሌግራም ቻናሉ የማረጋገጫ ምልክት አግኝቷል። አንዳንድ ተመሳስለው የተከፈቱ ቻናሎች ስላሉ ይህን ማረጋገጫ ያለውን ብቻ በመከተል ትክክለኛ መረጃዎቻችንን ይከታተሉ።

@EthiopiaCheck
#FakeAccountAlert የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነን ስምና ምስል በመጠቀም ከቀናት በፊት የተከፈተ የትዊተር አካውንት!

የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነን ስምና ምስል በመጠቀም ከቀናት በፊት የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል። አካውንቱ አሁን ላይ 741 ተከታዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ሲያጋራ አስተውለናል። በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረ-መልሶችን በማግኘት ላይ ይገኛል።

ከላይ የተጠቀሰው አካውንት የእርሳቸው አለመሆኑን ዶር ወዳጄነህ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።

በተመሳሳይ የዶ/ር ወዳጄነህን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተና አሁን ላይ ከ3,600 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽም የእርሳቸው አለመሆኑን የገለጹ ሲሆን በስማቸው የተከፈተ የትዊተርም ሆነ የፌስቡክ ገጽ እንደሌላቸውም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ወዳጄነህ በተለያዩ ሚዲያዎችና መድረኮች በተለይም ማህበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ አስተያየቶች በመስጠት ይታወቃሉ።

ተመሳስለዉ የተከፈቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ እናድርግ።

@EthiopiaCheck