Ethiopia Check
26K subscribers
1.38K photos
181 videos
672 links
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Download Telegram
#EthiopiaCheck Telegram Poll Result

ኢትዮጵያ ቼክ "አንድ የማህበራዊ ትስስር ገፅ፣ አካውንት ወይም ቻናል ትክክለኛ ለመሆኑ እርግጠኛ ማስረጃ ሊሆን የሚችለው የትኛው ነው?" የሚል ጥያቄን ለተከታታዮቹ ሰኞ እለት አቅርቦ ነበር።

ከአንድ ሺህ በላይ በሆኑ ሰዎች በተሰጠው መልስ መሰረት የማረጋገጫ ምልክት (verification) 76%፣ የሚያቀርበው መረጃ አይነት እና ብዛት 17%፣ የተከታይ ብዛት 4%፣ የተከፈተበት ወቅት 2% እንዲሁም የፕሮፋይል ምስል እና ስም 1% ሆኗል።

በርካታ ሰዎች በትክክል እንደመለሱት የማረጋገጫ ምልክት (verification) የአንድን ገፅ፣ አካውንት ወይም ቻናል ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በጣም ጠቃሚው ነው። ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት በርካታ አካውንቶች፣ ገፆች እና ቻናሎች ማረጋገጫ የላቸውም፣ ይህም ለሀሰተኛ አካውንቶች መብዛት ምክንያት እየሆነ ይገኛል።

ሌላው ልብ ልንለው የሚገባው ጉዳይ የማረጋገጫ ምልክት ያለው ገፅ፣ አካውንት ወይም ቻናል የሚያቀርበው መረጃ ሁሉ የተረጋገጠ ነው ማለት አለመሆኑን ነው። ማረጋገጫው ለሚቀርበው መረጃ ሳይሆን ለአካውንቱ፣ ገፁ ወይም ቻናሉ ትክክለኛነት ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ በፊት ማረጋገጫዎችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ያቀረባቸውን እነዚህን መረጃዎች ይከታተሉ፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነም ያመልክቱ:

https://ethiopiacheck.org/monday-message/how-to-verify-social-media-pages-accounts-and-channels/

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck የአርብ ሚድያ ዳሰሳ

1. ትዊተር በቀውስ ወቅት የሚኖርን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ያለመ ፖሊሲ በትናትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። “የቀውስ ወቅት የተዛባ መረጃ ፖሊሲ” (Crisis Misinformation Policy) በሚል ስያሜ ትናንት ይፋ የሆነው ይህ ፖሊሲ ትዊተር ኢትዮጵያን፣ አፍጋኒስታንና ህንድን በተመለከተ እየሰራው ያለውን ስራ እንደሚያጎለብት ገልጿል። አዲሱ ፖሊሲ በቀውስ ጊዜ የሚሰራጩ የሀሠተኛ መረጃዎችን ተደራሽነት የሚገታ ሲሆን በተለይም አሰራጩ አካውንት ቬሪፋይድ ከሆነ፣ ከመንግስት ጋር ንክኪ ያለው ሚዲያ ከሆነ እንዲሁም የመንግስት ይፋዊ አካውንት ከሆነ በተጠቃሚዎች ከመነበቡ በፊት በማስጠንቀቂያ አዘል ሽፋን ስር እንደሚቀመጥ አብራርቷል። የሀይል ዕርምጃን፣ ከድንበር ጋር የተያያዙ የልዕዋላዊነት መደፈርን፣ የጦር ወንጀልን፣ የዓለም አቀፍ ምላሽና ማዕቀብን ወዘተ የመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መልዕክቶች በፖሊሲው የተካተቱ ናቸው።

2. በመጪዎቹ ወራት በኬንያና በላይቤሪያ በሚደረጉ ምርጫዎች የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች የሚያደርሱትን ተግዳሮት ለመቀነስ ያግዛል የተባለ መገልገያን ጥቅም ላይ ማዋል መጀመሩን የተመድ የልማት ፕሮግራም ማክሰኞ ዕለት አስታውቋል። ይህ ‘iVerify’ የሚል መጠሪያ ያለው መገልገያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስንና የሰው ሀይልን በማጣመር ከምርጫ ጋር የተያያዙ ዘገባዎችን በማጣራት ለህዝብ ያቀርባል ተብሏል። ‘iVerify’ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በዛምቢያ በተደረገው ምርጫ በሙከራ ደረጃ ጥቅም ላይ ውሎ አበረታች ውጤት ማሳየቱንም የተመድ የልማት ፕሮግራም አስታውሷል። መገልገያው ከምርጫ ባሻገር ያሉ ሌሎች ርዕሰ ጉዮች ላይ ጥቅም ላይ ለማዋልና ለጋዜጠኞች፣ ለመረጃ አጣሪዎችና ለተመራማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱም ተገልጿል።

3. የናይጄሪያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ፌስቡክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ካምፓኒዎች የጥላቻ ንግግርን በመቆጣጠር ረገድ የሚጠበቅባቸውን ያህል እየሰሩ አለመሆናቸውን በመጥቀስ መውቀሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ሚንስትሩ ሌይ ሞሃመድ ወቀሳውን የሰነዘሩት ባሳለፍነው ማክሰኞ በናይጄሪያ ከፌስቡክ ተወካዮች ጋር ከተወያዩ በኋላ ነበር። ሚኒስትር ሌይ መንግስታቸው በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ፌስቡክ ይህ ነው የሚባል እርምጃ አለመውሰዱን ጠቅሰዋል።

4. የአሜሪካውን ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ከሚከተሉ 22.2 ሚሊዮን የትዊተር አካውንቶች መካከል 49.3% ያህሉ ሀሠተኛ መሆናቸውን ‘ስፓርክቶሮ’ የተሰኘ የማርኬቲንግ ኩባንያ የሠራው የኦዲት ሪፖርት ማመልከቱን ኒውስዊክ መጽሔት በሳምንቱ መጀመሪያ አስነብቧል። ስፓርክቶሮ በሀሠተኛነት የፈረጃቸው ስፓሞችን፣ ቦቶችን፣ ለፕሮፓጋንዳ የተከፈቱ አልያም መጠቀም ካቆሙ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ አካውንቶችን መሆናቸውን መጽሔቱ ጨምሮ አብራርቷል። ትዊተርን ለመግዛት የተስማማው ኢሎን መስክና ትዊተር ካምፓኒ በፕላትፎርሙ የሀሠተኛ አካውንቶችን ድርሻ በተመለከተ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

5. የአሜሪካ መንግስት ከሳምንታት በፊት ያቋቋመው የሀሠተኛ መረጃ ተመልካች ቦርድ ስራ እንዲያቆም መደረጉን ዋሽንግተን ፖስት በሳምንቱ አጋማሽ አስነብቧል። ቦርዱ ባለፈው ሰኞ ስራውን እንዲያቆም የተወሰነው በተለይም ቀኝ ዘመም ከሆኑ ፖለቲከኞችና ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከደረሰበት ከፍተኛ ትችት በኋላ መሆኑ ተገልጿል። ተቺዎች ቦርዱን ከታዋቂው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ‘1984’ መጽሐፍ “Ministry Of Truth” ጋር ማያያዛቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል። በተለይ ትችቱ ቦርዱን እንዲመሩ ከተሾሙት ኒና ጃንኮዊዝ አንጻር የበረታ እንደነበር ዋሽንግተን ፖስት ያስነበበ ሲሆን ሃላፊዋ ማክሰኞ ዕለት መልቀቂያ ማስገባታቸውንም ጨምሮ ጽፏል።

@EthiopiaCheck
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer

Footoforansiks (Fotoforensics) fayyadamuun suuraa tuttuqame (‘edit’ tolfame) akkamiin qulqulleeffachuu/mirkaneeffachuu dandeenya?
 
Viidiyoo gabaabaa Itoophiyaa Cheek qopheesse kana yaa daawwannu.

@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck Monitoring

የአዲስ አበባ ከተማ የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ ዛሬ የወጡ እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎች!

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ እንደሆነ በሪፖርተር ጋዜጣ መረጃ ወጥቶ ነበር፣ ይህ መረጃም ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን የብዙዎች መነጋገርያም ሆኖ ሰንብቷል።

ይሁንና ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ መረጃው "ሀሰት" ነው ብለው ተናግረው ነበር። ኃላፊው "በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ተደርጎ ነበቶር፣ ይህን መነሻ አድርገው አንዳንድ ግለሰቦች ለግራጫ ቀለም የመሰላ ቸውን ትርጓሜ ሲሰጡ ተመልክተናል፣ ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እንደሚዘዋወረው ተግባር ላይ የዋለ ሳይሆን ገና ለምክክር የቀረበ ነው" ብለው ከአራት ሰአት በፊት ተናግረው ነበር።

ይሁንና ከደቂቃዎች በፊት የከተማ አስተዳደሩ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል። "በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ ተገብቷል" በማለት የተመረጡትን ቀለሞች አስቀምጧል።

@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck ተጨማሪ መረጃ

በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ስለዋለው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ አንዳንድ መረጃዎች!

በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ስለዋለው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ተጨማሪ መረጃ እንድናደርሳችሁ ጥያቄ አቅርባችኋል። በዚህም መሰረት የጋዜጠኛውን እህት ትግስት ሹምዬን አነጋግረናል። የሰጠችን መረጃ እንዲህ ይቀርባል:

"ትናንት ጠዋት ላይ ለሰለሞን እንደሁሌው ቁርስ ላደርስለት ስሄድ በር የሚያንኳኳ ሲቪል የለበሰ ሰው አገኘሁ። ምን እንደሚፈልግ ስጠይቀው ሊነግረኝ አልፈለገም፣ ከዛም ሄደ። እኔም ወደቤቴ ተመልሼ ኋላ ላይ ቆየት ብዬ ሰለሞን ቤት ስመለስ ሌሎች ሲቪል የለበሱ ሰዎችን አገኘሁ። በግድ ቤቱን ክፈቺ አሉኝ፣ እኔ ደግሞ ስለተጠራጠርኩ ለጎረቤቶች ፖሊስ እንዲጠሩ ነገርኳቸው። መታወቂያ እንኳን ሊያሳዩኝ አልፈለጉም። ፖሊሶች ሲመጡ ግን እያመናጩቁኝ ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ። ሰለሞንን ፖሊስ ጣብያ ነበር ያገኘሁት። ስልኩን ቀምተው ቤቱ ላይ ፍተሻ አርገዋል። ምንም ነገር አላገኙም። ሰለሞን ከመጣ በኋላ ሁለት ሰአት አቆይተው እኔን ለቀቁኝ። አሁን ሰለሞን ሶስተኛ ፖሊስ ጣብያ ነው። ምግብ እና ልብስ አድርሼለታለሁ። ዛሬ ጠዋት ሶስተኛ አካባቢ ያለው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ቃል በቃል ባላስታውሰውም 'ብጥብጥ እንዲፈጠር አነሳስተሀል' ምናምን የሚል ክስ አንብበዋል፣ ክሱ ለብቻው ሳይሆን ሌሎችን ስዎችን ያካተተ ነበር።"

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck Ergaa Wiixataa

Gochaalee goyyomsuu gama bilbilaafii intarneetaan raawwatamaa jiran akkamiin ofirraa ittisuu dandeenya?

Goyyomsuun gama bilbilaa fi intarneetaan raawwatamu yeroo gara yerootti babal’achaa fi malootni goyyomsuus baay’achaa jiru.

Itoophiyaa Cheekis yeroo garagaraatti gochaalee goyyomsuu gama intarneetaan raawwataman saaxilaa turuunsaa ni yaadatama.

Ibsi waloo Tajaajilli Odeeffannoo fi Nageenya Biyyaalessaafii Tajaajilli Nageenya Faayinaansii Itoophiyaa tibbana baasanis “Itoophiyaa keessa yeroo dhiyootii as yakkawwan goyyomsuu miidiyaalee hawaasaa fayyadamuun raawwataman qabiyyeenis ta’e mala raawwii isaaniitin walxaxoo ta’aa dhufuu isaaniitiin dabalataan namootni baay’een miidhaasaaf akka saaxilaman taasisaa jira” jedha.

Namootni bilbila bilbiluun “baankii irraa isinif bilbilla; tajaajila ‘mobile banking’ isinif sirreessina” jechuun namootni maallaqa akka itti erganiif goyyomsaa jiraachuus dhagahaa jirra.

Baankiin Daldalaa Itoophiyaas maamiltootnisaa gochaa burjaajii kanaaf akka saaxilamneef dhiyeenya kana ibsa baasee jira.

Gochaaleen goyyomsuu gama imeelii (email), miidiyaa hawaasaa, ergaa gabaabaa akkasumas bilbila sagaleen raawwatamuu malu.

Keessattuu gareewwan fi chaanaliiwwan miidiyaalee hawaasaa kunneen akka Teelegiraama irratti geessituuwwan (link) shakkisiisoo maddifii maalummaan isaanii hin beekamne baay’inaan qoodamu.

Geessituuwwan kunis baay’inaan geessituuwwan dhaabbilee mootummaa fi miti mootummaa sirrii fakkeessun kan qophaa’anidha.

Kana malees ergaan “odeeffannoo dabalataa argachuuf geessituu kana cuqaasaa, geessituu kana yoo bantan badhaasa ni argattu” kunneen jedhan fi kan biroon waliin maxxanfamu.

Kana malees icciitiiwwan dhuunfaa keenyaa kunneen akka lakkoofsa herreega baankii, paaswordii /iggitaa/ keenyafii kunneen biroo akka laannuufis nu gaafatu.

Of eeggannoo akkamii gochuu qabna?

Wayita intarneeta fayyadamnus ta’e isaan alatti burjaajesitootaaf akka hin saaxilamneef of eeggannoo gochuun barbaachisadha.

Bilbiloota baankiiwwan fi dhaabbilee biroo irraa akka ta’e eerun nuf bilbilaman amanuufii maallaqa erguu keenyaan dura eenyummaa nama nuf bilbilee baruu fi dhuguma dhaabbata jedhame irraa nuf bilbilamuu isaa mirkaneeffachuu qabna.

Kana malees gara dhaabbata jedhamee ykn dameesaa dhiyeenya keenyatti argamutti qaamaan deemun mirkaneeffachuun filatamaadha.

Lakkoofsa herreega baankii fi paaswordii keenya kan miidiyaalee hawaasaa dabalatee icciitiin qabachuufii akka nu jalaa hin butamneefis paaswordii keenya cimsuu qabna.

“Badhaasa argachuuf kaffaltii duraa kaffalaa” jechuun yoo gaafatamne kaffaluu keenyaan dura dhugummaa nama ykn dhaabbata maallaqa nu gaafatee mirkaneeffachuu qabna.

Yeroo mara geessituuwwan nama ykn dhaabbata hin beeknerraa gama imeelii, miidiyaa hawaasaa akkasumas ergaa gabaabaan nutti ergaman cuqaasnee banuu keenyaan dura of eeggannoo gochuunis ni barbaachisa.

Yaaliiwwan goyyomsuu gama imeelii (email) keenyaan nutti ergamaniif deebii kennuu dhiisuu fi callisuunis filatamaadha.

Sababanisaas deebii kan deebisnuuf yoo ta’e imeelii keenyatti fayyadamaa jiraachuu keenya burjaajesitootni waan beekaniif imeeliiwwan biroo irra deddeebin nutti erguu danda’u.

Gessituuwwan kamiyyuu akkasumas marsariitiiwwan daawwannu sirrii fi amansiisoo /secure/ ta’uu isaanii yaa mirkaneeffannu.

Marsariitiiwwan sirriin https kan jedhun eegalu; http kan jedhu qofa yoo ta’e marsariitichi rakkoo qaba jechuudha.

Marsariitii daawwachuu barbaadnu erga bannee boodas geessituu marsariitichaa irratti jijjiiramni qubee kan hin jirre ta’uu yaa mirkaneeffannu.

Dhumarrattis gochaaleen burjaajii ykn goyyomsuu yoo nu qunnaman qaamolee seeraaf eeruu kennuun gahee keenya bahachuun ni gorfama.

@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck Explainer

ታይም መጽሔት ተጽዕኖ ፈጣሪ ያላቸውን ግለሰቦች ለመምረጥ ምን መስፈርት ይጠቀማል?

ታዋቂው የእንግሊዘኛ ቋንቋ መጽሔት ታይም ትናንት የ2022 ተጽዕኖ ፈጣሪ ያላቸውን መቶ ግለሰቦች ይፋ አድርጓል። በተጽዕኖ ፈጣሪነት ከተካተቱት መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ትምኒት ገብሩ ይገኙበታል።

ታይም መጽሔት ተጽዕኖ ፈጣሪ ያላቸውን ግለሰቦች ለመምረጥ ምን መስፈርት ይጠቀማል?

ታይም በየዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው ያላቸውን መቶ ግለሰቦች ይፋ ከማድረጉ ከሰዐታት በፊት የምርጫውን መስፈርትና የመራጮችን ማንነት የሚያስረዳ ማስታወሻ በመጽሔቱ ዋና አርታዒ በኩል ያስነብባል።

ይህን ልማድ ተከትሎም የ2022 መቶ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይፋ ከመደረጋቸው በፊት የመጽሔቱ ዋና አርታዒ ኤድዋርድ ፊልስነታል “How We Chose the 2022 TIME100” በሚል ርዕስ ምርጫውን የተመለከተ ማስታወሻ አስነብቧል።

ኤድዋርድ ፊልስነታል የ2022 ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ለመምረጥ አንድ ብቸኛ መስፈርት ጥቅም ላይ መዋሉን የገልጸ ሲሆን እሱም “ተጽዕኖ መፍጠር” (influence) መሆኑን አብራርቷል። ተጽዕኖ መፍጠር ሁለት ገጽታ አለው በማለት በማስታወሻው ላይ ያሰፈረው ዋና አርታዒው “በጎ” እና “መጥፎ” ተጽዕኖ መሆናቸውን አጽኖት ሰጥቶበታል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዜሊንስኪና የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በ2022ቱ ምርጫ መካተታቸው የተጽኖ ፈጣሪነትን ሁለት ገጽታዎች እንደሚያሳዩም በምሳሌነት ጠቅሷል።

ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን የሚመርጡት እነማን ናቸው?

ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን የሚመርጡት በታይም መጽሔት የሚሰሩ በየደረጃው ያሉ አርታዒያን ሲሆን በዜና ክፍል የሚሰሩ ጋዜጠኞች ተጨማሪ ግብዐት በማቅረብ ይሳተፋሉ።
⬆️
#EthiopiaCheck Scam Alert

‘Dhaabbatni’ maqaa ‘Fias 777’ jedhuun hojii komishinii nan hojjedha jechuun namootarraa maallaqa guuraa jiru eenyu?

Tibbana hordoftootni keenya heddu maalummaafii seera qabeessummaa dhaabbata maqaa ‘Fias’ jedhuun socho’u nu gaafachaa turaniiru.

Odeeffannoon Itoophiyaa Cheek dhiyeenya kana Tajaajila Nageenya Faayinaansii Itoophiyaa irraa argate akka agarsiisutti dhimmi ‘Fias’ Poolisii Federaalaan qoratamaa jira.

Dhaabbatni ‘Fias 777’ “dhaabbata beeksisaa hojii komishinii hojjetu” jechuun kan of ibsu yemmu ta’u “miidiyaalee hawaasaa garagaraa waliin hojjennas” jedha.

Kana malees “miseensota galmaa’anif guyyuu hojii laanna. Hojiileen kunneen baay’ee salphaadha. Cuqaasuu qofa. Yoo baay’ate daqiiqaa shan kan fudhatanidha” jedha.

“Hojiin miseensa tokkoof laatamufii maallaqni argatu sadarkaasaa irratti hundaa’un garaagarummaa qaba. Sadarkaaleen kunis VIP-0, VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4 fi VIP-5 dha” jechuunis dhaabbatichi hima.

“Akka fakkeenyaatti miseensi tokko birri 10,000 kaffaluun sadarkaan VIP-4 kennamaaf” jedha Fias 777.

Namni sadaraa VIP-4 irra jiru guyyaatti hojiilee 17 irratti cuqaasa (click godha). Hojii tokkoof birriin 18 ni kaffalamaaf. Haaluma kanaan guyyaatti birri 306 yookin immoo ji’atti birrii 9,180 akka kaffalamuuf hima.

Dhaabbatichi “Itoophiyaa keessatti hojii erga jalqabee as namoota baay’een jaalatameera. Lakkoofsi namoota galmaa’anis miiliyoona lama ta’eera” jechuun ji’a tokko dura himee ture.

Haa ta’u malee dhaabbatichi dhaabbilee kanaan dura Itoophiyaa keessatti akka hin sochoone dhorkaman akka ‘QuestNet’ fi ‘Tiens’ mala ‘pyramid scheme’ jedhamuun hojjechaa akka jiru hubanneerra.

Kunis namoota baay’ee of jalatti ijaaruun kan hojjetamu yemmuu ta’u, namootni dursanii dhaabbatichatti galmaa’an maallaqa yemmuu argatan namootni boodarra makaman heddu immoo goyyomfamanii hafu.

Dhaabbatichaaf gama Baankii Abisiiniyaa fi Baankii Daldalaa Itoophiyaatin kaffaltiin raawwatamaa akka tures ragaan Itoophiyaa Cheek argate ni mul’isa.

Maamilli ‘Fias 777’ Itoophiyaa Cheek haasofsiise, “dhaabbatichi Itoophiyaa keessatti galmees ta’e waajjira hinqabu. Abbootii qabeenyaas hin beeknu” jedheera.

Yeroo keessa dhaabbaticharratti komiiwwan ka’uu kan himu maamilichi, “gaafii yemmuu gaafannu ‘Fias keessaa ni ari’amtu’ nun jedhu. Iftoomina hinqabu” jechuunis hima.

Dhaabbatni ‘Fias’ Itoophiyaa keessatti galmaa’era jedhus kun sirrii akka hintaane Waajjira Galmee Daldalaa Ministeera Daldalaatii mirkaneeffanneerra.

Itoophiyaa Cheek nama ‘bakka bu’aa dhaabbatichaati’ ofiin jedheen waa’ee hojii dhaabbatichaa kan gaafate yemmuu ta’u, “namootni gama Feesbuukii, TikTok fi Yutuubiitiin qabiyyee yemmuu cuqaasan lakkoofsi daawwattootaa ni dabalaafi. Kanaafis Feesbukii irraa kaffaltii ni arganna. Isaan waliin hojjenna” jedheera.

Haa ta’u malee geessituun gara miidiyaalee hawaasaa kunneenii geessu akka hin jirre ilaaluu dandeenyerra.

Namni ‘ani bakka bu’aa dhaabbatichaati’ jedhe kun waliigaltee Feesbuukii waliin qaban akka nutti agarsiisan kan gaafanne yemmuu ta’u, “ana bira hin jiru. Harka namoota biyya alaa jiranii jira” nun jedheera.

Dabalataan marsariitiiwwan burjaajesitoota sakatta’an ‘Scam Advisor’ fi ‘Scam Detector’ jedhaman marsariitiin ‘Fias 777’ marsariitii burjaajesitootaa akka fakkaatu agarsiisu.

-https://www.scamadviser.com/check-website/fias777.com

-https://www.scam-detector.com/validator/fias777-com-review/

Namootni heddu birrii dhibbaa hanga 10,000 gama baankiitiin dhaabbatichaaf kaffalaniiru.

Akkuma olitti eerame dhimmi ‘Fias’ Poolisii Federaalaan qoratamaa jiraachuu Itoophiyaa Cheek Tajaajila Nageenya Faayinaansii Itoophiyaarraa odeeffateera.

Dhaabbata kanaan dabalataan qaamolee gochaalee burjaajii/goyyomsuu gama intarneetaan raawwatamurratti hirmaachuun shakkaman kunneen biroo irratti hordoffiin adeemsifamaa akka jirus dhageenyerra.

Itoophiyaa Cheekis hawaasni burjaajii/goyyomsuu gama intarneetaan raawatamurraa akka of eegu dhaama.

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck Doctored Image Alert

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በአማራ ክልል የጀመርነው ህግ የማስከበር ስራ በተሳካ ሁኔታ እየሄደ ነው” በማለት ለኢቢሲ መናገራቸውን የሚገልጽ የስክሪን ቅጂ (screenshot) ትናንት እና ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲጋራ ተመልክተናል።

የስክሪን ቅጂው ከኢቢሲ የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ የሚጠቁም ሲሆን የአቶ ሽመልስን ፎቶ፣ ተናገሩት የተባለውን መልዕክት እንዲሁም የኢቢሲ መለያ (logo) የተሰናሰኑበት ምስል በዜናው አካልነት አብሮ ይታያል።

ኢትዮጵያ ቼክ የስክሪን ቅጂውን ትክክለኛነት ለማወቅ ባደረገው ማጣራት የተባለው መልዕክት በኢቢሲ የፌስቡክ ገጽ ላይ ቀርቦ እንዳልነበር እና በቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተለቀቀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል። ለዚህም የስክሪን ቅጅውን ይዘቶች መርምሯል፣ ንጽጽር አካሂዷል እንዲሁም ይዘቶችን በተመለከተ ከኢቢሲ የሳይበር ሚዲያ ክፍል ጋር ተነጋግሯል።

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ስክሪን ቅጂ የተጠቀመው የፎንት አይነት ኢቢሲ በማህበራዊ ሚዲያ ለግንባር-ምስሎች (thumbnail images) ከሚጠቀምበት የፎንት አይነት የተለየ ነው። ኢትዮጵያ ቼክ በርከት ያሉ የኢቢሲ ግንባር-ምስሎችን የመረመረ ሲሆን ሚዲያው የሚጠቀመው ‘ኖኪያ’ የተባለ የፎንት አይነት በመካከለኛ ድምቀት (medium boldness) መሆኑን አስተውሏል። የኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ክፍልም ለግንባር ምስሎች ኖኪያ ፎንት በመካከለኛ ድምቀት እንደሚጠቀም አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ ሌላ ለንጽጽር የተጠቀመው የዜና አጻጻፍ ይትባህሉን (style) ነው። ኢቢሲ በማህበራዊ ሚዲያ በሚያጋራቸው ዜናዎች በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ከሆነ ከትምህርተ ጥቅሱ በኃላ የተናጋሪውን ማንነት ብቻ እንደሚያስቀምጥ አስተውለናል። በስክሪን ቅጅው ላይ ግን በትምህርተ ጥቅሱና በተናጋሪው ማንነት መካከል “..ሲሉ..” የሚል ያልተለመደ አያያዥ ቃል ገብቷል። የኢቢሲ ሳይበር ክፍል በማህበራዊ ሚዲያ ዐርዕስተ ዜና ሲጽፍ ይህን ጨምሮ ሌሎች አያያዥ ቃላቶችን ከትምህርተ ጥቅሱ በኃላ እንደማይጠቀም አብራርቷል።

በተጨማሪም በስክሪን ቅጅው ላይ የሚታየው የአቶ ሽመልስ ፎቶ የቆየ ሲሆን ፎቶው የተወሰደው ፕሬዝደንቱ የ2013 ዓ.ምን የኢድ አልፈጥ በዓል ምክንያት በማድረግ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

በመጨረሻም ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተዘዋወሩ ያሉት ሁሉም የስክሪን ቅጂዎች ዜናው ከተለጠፈ 18 ደቂቃ እንደሆነው ይጠቁማሉ። ከዛ ውጪ በሌላ ሰው በሌላ ደቂቃ ላይ የተወሰደ የስሪን ቅጂ አለመኖሩ እንዲሁም በሌሎች ሚዲያዎች ተመሳሳይ መልዕክት አለመተላለፉን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ከኢቢሲ የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰዱ ተደርገው የሚጋሩ የስክሪን ቅጂዎች እየጨመሩ የመጡ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ በፊት የማጋለጥ ስራ መስራቱ ይታወቃል። የኢቢሲ የሳይበር ሚዲያ ክፍል ለኢትዮጵያ ቼክ እንደገለጸው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲህ ያሉ ድርጊቶች መበራከታቸውንና ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ሀሰተኛ የስክሪን ቅጅ የሚዲያውን ስም በመጠቀም እንደሚሰራጭ አስረድቷል።

ሆን ተብለው እና ተቀናብረው የሚለቀቁ ፅሁፎችን፣ ምስሎችን እንዲሁም ቪድዮዎችን ሳናረጋግጥ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck Scam Alert

'Fias 777' እንታይ እዩ?

‘Fias 777' ብዝብል ሽም ናይ ኮሚሽን ስራሕ ከምዝሰርሕ ኣፍሊጡ ካብ ብዙሓት ሰባት ገንዘብ እናኣከበ ዝርከብ ‘ትካል’ እንታይ እዩ?

'Fias 777' ብዝብል ሽም ዝንቐሳቐስ ትካል መንነትን ሕጋዊነትን ብዝምልከት ብርክት ዝበሉ ተኸታተልትና እናሓተቱና ቀንዮም እዮም።

እቲ ትካል ንባዕሉ “ናይ ኮሚሽን ስራሕ ዝሰርሕ ትካል” ኢሉ ዝጽውዕ እንትኾን “ምስ ዝተፈላለዩ ናይ ሶሻል ሚዲያ ኔትዎርካት ንሰርሕ ኢና” ይብል። ብምቕጻል’ውን “ብመዓልቲ ንዝተመዝገቡ ኣባላት ስራሕ ንህብ ኢና። እቶም ስራሓት ከዓ ቀለልቲ እዮም። ክሊክ ምግባር ጥራሕ እዩ ዘድሊ። እንተበዚሑ 5 ደቒቓ እዮም ዝወስዱ። ሓደ ኣባል ዝወሃቦ መጠን ስራሕን ዝረኽቦ ገንዘብን ከከም ደረጅኡ ይፈላለ እዩ። እቶም ደረጃታት VIP-0፣ VIP-1፣ VIP-2፣ VIP-3፣ VIP-4ን VIP-5ን እዮም” ይብል።

ከም ኣበሃህላ እቲ ትካል ንኣብነት ሓደ ኣባል ብVIP 4 ደረጃ 10,000 ብር ከፊሉ ደረጃ ይወሃቦ እዩ። ብመዓልቲ ክሊክ ዝገብሮም ን17 ስራሓት ኮይኑ፣ ንሓደ 18 ብር ይኽፈሎ። እዚ ድማ ብመዓልቲ 306 ብር ወይ ከዓ 9,180 ብር ይረክብ እዩ” ይብል።

ከም ገለጻ እቲ ትካል ኣብዚ ሐዚ እዋን “ኣብ ውሽጢ ኢትዮጵያ ካብ ዝጅመረሉ ጊዜ ኣትሒዚ ካብ ሓፋሽ ህዝቢ ፍቕሪ ረኺቡ ቁጽሪ እቶም ዝተመዝገቡ ከዓ 2 ሚሊየን በጺሑ እዩ” ይብል።

ይኹን እምበር እቲ ትካል ቅድሚ ሐዚ ኣብ ኢትዮጵያ ምንቅስቓስ ከይገብሩ ተኣጊዶም ከምዝነበሩ QuestNetን Tiensን ዝኣመሰሉ ናይ ፒራሚድ ቀመር መሰረት ከምዝገበሩ ትካላት ከምዝሰርሕ ምርኣይ ክኢልና ኢና። እዚ ከዓ ብዙሓት ሰባት ኣብትሕቲ ካሊእ ክኣትዉ ብምግባር ዝስራሕ ኮይኑ ቀዲሞም ዝኣተዉ ሰባት ገንዘብ ክረኽቡ ከለዉ ብርክት ዝበሉ ግን ይታለሉ እዮም።

ነቲ ትካል ዝዋሃብ ክፍሊት ብኣቢሲኒያ ባንኪን ብኢትዮጵያ ንግዲ ባንኪን ኣቢሎም ከምዝፍጸሙ ኢትዮጵያ ቼክ ዝረኸቦ መረዳእታ ይሕብር።

ነዚ ብዝምልከት ዘዛረብናዮ ሓደ ናይቲ ትካል ተጠቃማይ “እቲ ትካል ኣብ ኢትዮጵያ ምዝገባ ኾነ ቢሮ የብሉን፣ ናይቲ ትካል በዓል ዋናታት’ውን ኣይንፈልጦምን” ኢሉ ኣብዚ ሰሙን እዚ ብዙሕ ጥርዓናት ክስምዑ ከምዝጀመሩ ይገልጽ። “ሕቶ እንተሓቲትና ካብ Fias ክትባረሩ ኢኹም ይብሉና፣ ንጹር ኣሰራርሓ የብሉን” ብምባል ምስራሕ ከምዝቐጸለ ግን ይገልጽ።

እቲ ትካል ኣብ ኢትዮጵያ ከምዝተመዝገበ እንተገለጸ’ኳ እዚ ትኽክል ከምዘይኮነ ካብ ንግዲሚኒስቴር ቤ/ጽ ምዝገባ ንግዲ ኣረጋጊጽና ኢና።

ብኻሊእ መዳይ እቲ ትካል ዝሰርሖ ስራሕ እንታይ ከምዝኾነ ኢትዮጵያ ቼክ ዝሓተቶ ሓደ ናይቲ ትካል ወኪል እየ ዝብል ውልቀ ሰብ “ሰባት ናይ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ቲክቶክን ዩትዩብን ምስልታት ክጸቕጡ ከለዉ ተመልከቲ ይበዝሐሎም፣ ነዚ ከዓ ካብኒ ፌስቡክ ክፍሊት ንረክብ ኢና፣ ምሳኣቶም’ውን ብሓባር ንሰርሕ ኢና” ኢሉ እዩ። ኮይኑ ግና ናብዞም ማሕበራዊ ሚዲያታት ዝወስድ ሊንክ ከምዘየለ ርኢና ኢና።

ነዚ ብዝምልከት ምስ ፌስቡክ ኣለና ንዝበሉዎ ውዕሊ ከርእይ ዝተሓተተ ናይቲ ትካል ተወካሊ ኢዬ ዝበለ ውልቀ ሰብ “ኣብ ኢደይ የለን፣ ወጻኢ ዓዲ ምስ ዘለዉ ሰባት እዩ ዘሎ” ኢሉ መልሲ ሂቡ እዩ።

ብተወሳኺ ከዓ Scam Advisorን Scam Detectorን ዝተብሃሉ ንዘታልሉ መርበብ ሓበሬታታት ዝከታተሉ ትካላት፣ ነቶም ገጻት መጭበርበርቲ ከምዝመስሉ ዘውጽኡዎ ሪፖርት ይሕብር እዩ።

-https://www.scamadviser.com/check-website/fias777.com
-https://www.scam-detector.com/validator/fias777-com-review/

ኢትዮጵያ ቼክ ነዚ ጉዳይ ብዝምልከት ካብ ደሕንነት ግልጋሎት ፋይናንስ ኣብ ቀረባ እዋን ዝበጽሖ መረዳእታ ከምዝሕብሮ ናይ Fias ጉዳይ ብፌደራል ፖሊስ እናተመርመረ ይርከብ። ካብዚ ትካል ብተወሳኺ ብርክት ዝበሉ ናይ ኦንላይን ምጭብርባር (scam) ተግባራት ኣብምስታፍ ንዝተጠርጠሩ ኣካላት ኽትትል እናገበረ ከምዝኾነ ተፈሊጡ ኣሎ።"

ክሳብ ሐዚ ብርክት ዝበሉ ሰባት ካብ ቁሩብ ኣማኢት ብር ክሳብ ዓሰርተ ሺሕ ብር በቶም ክልተ ባንክታት ኣቢሉም ነቲ ትካል ከፊሎም እዮም። ይኹን እምበር ኢትዮጵያ ቼክ ካብ ከምዚ ዓይነት ናይ ምጭብርባር ተግባራት ሰባት ንባዕሎም ክሕልዉ ይመክር።

@EthiopiaCheck
#EthiopiaCheck Fake Account Alert

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የዶክተር ይልቃል ከፋለን ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካውንቶች መኖራቸውን ተመልክተናል!

ከአካውንቶቹ መካከል እ.አ.አ መስከረም 2021 ዓ.ም የተከፈተና ‘Dr Yilkal Kefale Asres’ የሚል መጠሪያ ያለው ይገኝበታል፣ አካውንቱ በአሁኑ ሰዐት ከ1,889 በላይ ተከታዮች አሉት።

ይህ የትዊተር አካውንት በተለይ ባለፉት ጥቂት ቀናት በርካታ መልዕክቶችን ሲያጋራ የተመለከትን ሲሆን በዚህም በመቶዎች የሚቆጠር ግብረመልስ ከተከታዮቹ እንደሚያገኝ አስተውለናል።

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ይህ የትዊተር አካውንት ሀሠተኛ መሆኑን እና የሚያጋራቸው መልዕክቶችም የፕሬዝደንቱ አለመሆናቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።

የዶክተር ይልቃል ከፋለ ትክክለኛ የትዊተር አካውንት በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የተያያዘው መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ በፊት አሳውቆ ነበር: https://twitter.com/AserseKefale?t=8S3vHxY_DA6NxOhQ1A4bOw&s=09

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የዘወትር መልዕክታችን ነው።

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck Scam Alert

“በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለ20 ሺህ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል አመቻችቷል” በማለት እየተጋራ ስለሚገኝዉ አሳሳች መረጃ!

‘US Embassy Addis Ababa’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል “አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል” ብሎ መረጃ አጋርቷል።

የዕድለኞች የትራንስፖርት፤ የመኖሪያ ቤትና የመኪና ወጪ በኤምባሲዉ እንደሚሸፈንም ጽፏል።

ስለዚህም የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን በቴሌግራም ቻነሉ አማካኝነት እንዲመዘገቡና ተመዝጋቢዎችም ሙሉ ስማቸዉን፤ ስልክ ቁጥራቸዉን እንዲሁም አድራሻና መሰል ግላዊ መረጃዎቻቸዉን እንዲልኩም ይጠይቃል።

የዚህን መረጃ ትክክለኛነትና እዉን የቴሌግራም ቻነሉ የኤምባሲዉ መሆኑን ለማጣራት ኢትዮጵያ ቼክ በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲን ጠይቋል።

ኤምባሲዉ በአሜሪካ የስራና የቪዛ ዕድሎችን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ሀሰተኛ መረጃዎች እየተጋሩ መሆኑን አስታዉቋል።

“የአሜሪካ መንግስት በኢሜይል፤ ፌስቡክ ሚሴንጀር፤ ቴሌግራም ወይም ሌላ ማህበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት ግላዊ መረጃዎችን አይጠይቅም” ብሏል።

ትክክለኛ የስራ ዕድሎችን በድረ-ገጹ ላይ እንደሚለጥፍና ሰዎች ለአጭበርባሪዎች እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ኤምባሲዉ ጠይቋል።

ይሁን እንጂ ኤምባሲዉ ‘US Embassy Addis Ababa’ የሚል ስምና ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል (https://t.me/+FqnK-k2b8-4xZGJk) የእርሱ ስለመሆኑም ሆነ ስላለመሆኑ ያለዉ ነገር የለም።

የስራ ዕድል እናመቻቻለን እና መሰል ዘዴዎችን በመጠቀም በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶችን በብዛት እያየን ነዉ።

ስለሆነም የማህበራዊ ትስስር ገጾችንና የመረጃዉን ትክክለኛነት ከመረጋገጣችን በፊት ግላዊ መረጃዎቻችንን ከማጋራትም ሆነ ክፍያዎችን ከመፈጸም እንቆጠብ እንላለን።

መሰል መረጃዎችን ለማየትና ስለተለያዩ መረጃ ማጣሪያ ዘዴዎች ለማወቅ የኢትዮጵያ ቼክን ድረ-ገጽ https://ethiopiacheck.org/ ይጎብኙ።

@EthiopiaCheck
⬆️
#EthiopiaCheck የአርብ ሚድያ ዳሰሳ

1. አለም አቀፉ የፖሊስ ህብረት (ኢንተርፖል) በሳይበር ወንጀል የሚጠረጠርን ቡድን ዋና መሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ዕረቡ እለት አስታውቋል። የወንጀል ቡድኑ ሽንገላን (phishing) እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግለሰቦችና በድርጅቶች ላይ የኢንተርኔት ማጭበርበር ይፈጽም ነበር ተብሏል። የ37 ዓመቱን ናይጀሪያዊ ተጠርጣሪ ለመያዝ ከናይጀሪያ ፖሊስ የሳይበር ቡድን ጋር መቀናጀቱን የገለጸው ኢንተርፖል አራት ህጉራትን ያካለለ ኦፕሬሽን መከወኑን አብራርቷል። ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚደረጉ ማጭበርበሮች በሀገራችን እየጨመሩ መምጣቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ ኃይል ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ቼክ ድርጊቱን በተመለከተ በርከት ያሉ የማጣራትና የማንቃት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱም ይታወቃል።

2. የዝንጀሮ ፈንጣጣ (monkeypox) ስለተባለው በሽታ ዘገባ የሚሰሩ የሰሜን አሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች የቆዩና ጥቁር አፍሪካውያንን የሚያሳዩ ፎቶዎችን መጠቀማቸው አግባብ አይደለም ሲል መቀመጫውን ናይሮቢ፣ ኬንያ ያደረገው የአፍሪካ ፎሬን ፕሬስ አሶሴሽን በሳምንቱ መጀመሪያ ባወጣው መግለጫ ቅሬታውን አሰምቷል። አሶሴሽኑ በሽታው በሰሜን ንፍቀ ክበብ በሚገኙ ሀገሮች በተከሰተበት ሁኔታ እንዲህ ያሉ ፎቶዎችን መጠቀም ጥቁር ቀለም ባለቸው ሰዎች አንጻር የቀጠለውን መገለልና አሉታዊ ዕይታ የሚያስቀጥል ነው ሲል ተችቶታል። ይህን አይነቱን የፎቶ አጠቃቀም በርከት ያሉ ሰዎች በተለይ በትዊተር ሲተቹ የተስተዋለ ሲሆን አሰራሩ ባለፉት ጥቂት ቀናት መሻሻል ማሳየቱን ኢትዮጵያ ቼክ ታዝቧል።

3. “በሀሠተኛ መረጃ አሰራጭነት መፈረጅ” የጋዜጠኞች ዋና ተግዳሮት መሆኑን ሲሲዮን የተባለ ዓለም አቀፍ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ነክ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ተቋማ ይፋ ያደረገው ዓመታዊ ጥናት ጠቆመ። ተቋሙ በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ ያደረገው ይህ ጥናት 37% የሚሆኑ ጋዜጠኞች በሀሠተኛ መረጃ አሰራጭነት የሚደርስባቸውን ፍረጃ መከላከልና ታማኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ለመቀጠል የሚያደርጉት ጥረት የሙያቸው ዋና ተግዳሮት መሆኑን ተናግረዋል። ሲሲዮን የ2022 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የሚዲያ ሁኔታ የሚዳስሰውን ን ጥናት ለመስራት በ17 ሀገሮች የሚገኙና ከ2,000 በላይ በሆኑ የሚዲያ ተቋማት የሚሰሩ 3,800 ጋዜጠኞችን በጥናቱ አካቷል።

4. በመጭው መስከረም ሊደረግ ቀን የተቆረጠለትን የብራዚል አጠቃላይ ምርጫ ከሀሠተኛና የተዛባ መረጃ የጸዳ ለማድረግ ቴሌግራምና የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በስምምነቱም ቴሌግራም በፕላትፎርሙ የሚሰራጩ ሀሠተኛ መረጃዎች የመለየትና ዕርምጃ የመውሰድ፣ ምርጫውን የተመለከቱ ጥያቄዎች የሚስተናገዱበት ቻት-ቦት መክፈት እንዲሁም ከፍርድ ቤቱ ጋር ግንኙነት መመስረት የሚሉ ተካተውበታል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከወራት በፊት ቴሌግራም መተግበሪያ በብራዚል ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል ዕቀባ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

5. ዩትዩብ የዩክሬን ጦርነትን በተመለከተ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ አሰራጭተዋል ያላቸውን 9,000 ቻናሎችን መዝጋቱንና ከ70,00 በላይ ቪዲዮዎችን መሰረዙን ዘጋርዲያ ጋዜጣ በሳምንቱ መጀመሪያ አስነብቧል። ዩትዩብ ስለተዘጉት ቻናሎች ማንነትና ስለቪዲዮዎቹ ይዘት ዝርዝር መረጃ አለመስጠቱንም ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል።

@EthiopiaCheck
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer

በዛሬው የቪድዮ ማብራርያችን ጉግል ማፕን በመጠቀም ምስሎች የት ቦታ እንደተነሱ ማጣራት (geolocating) እንዴት ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።

@EthiopiaCheck