"ኡማ ቲቪ " Tv
43.2K subscribers
27K photos
1.02K videos
13 files
4.68K links
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
Download Telegram
"ኡማ ቲቪ " Tv
Photo
የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ ባለበት ከቀጠለ ለምክክሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ የአማራ ክልል መጅሊስ አስታወቀ

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ አሠራር ሳይሻሻል ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ለምክክሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ በዛሬው እለት አስታወቀ። ምክር ቤቱ በአማራ ክልል ከዕውቅና ውጪ ሙስሊሙን በማግለል ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያ ዙር ጉባዔ ማካሄዱን ገልጿል።

ምክር ቤቱ ይህንኑ ዛሬ ግንቦት 12/2016 ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ለአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር እና ለክልሉ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ላይ አስታውቋል።

በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጀውሐር ሙሐመድ በተጻፈው ደብዳቤ፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሉ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ያሳተፈው የኔ የሚለውን ብቻ እንደሆነ ተጠቁሟል።

አካሄዱን የተቸው ምክር ቤቱ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን ያገለለ ሀገራዊ ምክክር የሚፈለገውን መልካም ውጤት ያመጣል የሚል እምነት እንደሌለውም አብራርቷል።

ምክር ቤቱ በደብዳቤው፣ አሁን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል እየሄደበት ይገኛል ያለውን አሠራር እንዲያሻሽል ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ የሚያካሄደውን የተሳታፊ አካላት ልየታ በፍትሐዊነት በድጋሚ እንዲቃኝ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥያቄ ቀርቦለት ነበር።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኮሚሽኑ በሚያካሄደው ምክክር ላይ የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳ እንዲካተት፣ የተሳታፊ አካላት ልየታ በፍትሐዊነት በድጋሚ እንዲቃኝ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳላገኘ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አደርገዋለሁ ላለው ምክክር ተወካይ ያስመርጣሉ ተብለው ከተለዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ መምህራን እና የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የተገለሉ ኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ዕድሮች እና የንግዱ ማኅበረሰብ ተካተዋል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተዘለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሳምንት በፊት በእስላማዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ከሚሠሩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና አንቂዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ በምክክር ኮሚሽኑ የተሳታፊ አካላት ልየታ የተመረጡ ሙስሊሞች ቁጥር ከ2 በመቶ በታች እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
ድሮ ሽማግሌ ለትዳር ጥየቃ ሲላክ አይመለስም ነበር። ትዳር የተከበረ ነዋ 👉 ቤተሰብ ታዲያ የጠየቃትን ለሰው አጭተው ከሆነ "እሷን ሰጥተናል ባይሆን ታናሿም ታላቋም አለች፣ ያጎቷ ልጅም አለች የፈለገውን ይምረጥ ይባላል። ሽማግሎቹ በሳምንቱ አፕሊኬሽን ፎርም ቀይረው ይገባሉ። ይህ አይነት ትዳር ታዲያ የፍች ብዛቱ (divorce rate) አነስተኛ ነበር። ምክንያቱ ደሞ የፍቅር ውልደቱና እድገቱ ጉልምስናውም ይሁን ትዝታው ከተጣመርክ በኋላ ስለሚሆን ነው።

እስቲ ያገባችሁ ሰዎች ተዋውቃችሁ ኒካህ ለማድረግ ምን ያህል ጊዚ ፈጀባችሁ ስንት አመት ቆታችሁ። እኔ ከጋብቻ በፊት 3 ቀን ፈጅቶብኛል። እና 24 አመት ኖርን አልሀምዱሊላህ።

ኢትዩጵያ ውስጥ ያለው የፍች ስርጭት እንደ አንድ ጥናት (Muntasir etal 2018) ይሄን ይመስላል:: በአብዛሀኛው ሙስሊም የበዛበት አካባቢ ፍች ያነሰ ይመስላል። እንደ አገር ግን ከ4ቱ ትዳር አንዱ እየፈረሰ ነው ። እርግጥ አንዳንድ ቦታ ከ2ቱ አንዱ እየፈረሰ ነው

Kb
የ የ1445 አ.ሒ /2016 አ.ል ሑጃጆች ጉዞ ተጀመረ
****
የ1445 አ.ሒ /2016 አ.ል የሐጅ ጉዞ ከዞን ሶስት የሃጅ የምዝገባ ጣቢያዎች ከጅግ ጅጋ እና ከጎዴ የመጀመሪያዎቹን ሑጃጆች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች በበገኙበት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 13/2016 ከጧቱ 1:00 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡
ይገኛሉ ‼️

ግንቦት 18 በከተማችን ኮምቦልቻ በሚዘጋጀው አገር አቀፍ የምስጋናና የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ይገኛሉ ‼️
ይህ ነገር የፖሊስ አባላት ባልሆኑትም ላይ ሊቀጥል ይገባል፣ ሚሌ፣ካሳጊታ፣ አዋሽ ፈንታሌ ወደ መተሃራ፣ አዳይቱና ኡንድፎ የሚያስቸግሩ ልጆች አሉ።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የከባድ መኪና ሹፌር በማስቆም
ሲያስፈራራ እና ሲያንገላታ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርምራ እየተጣራ ይገኛል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የከባድ መኪና ሹፌርን በማስቆም ሹፌሩ ሲያስፈራራ እና ሲያንገላታ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እንደተጀመረበት የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራሊ ገልጸዋል።
ኮምሸነረ ጄኔራሉ ይህ አሽከርካሪ ላይ በግድ መንገደኛ የመጫን ተግባር ከፖሊስ ዲሲፕሊን ውጭ የሆነ ተግባር በመሆኑ የአፋር ክልል ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ተመጣጣኝ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጠዋል ።
ኮሚሽነር ጄነራሉ ይህ ተግባር የህዝብ ልጅ እና በህዝባዊ ወገንተኝነቱ የሚታወቀው የአፋር ፖሊስ እንደማይወክል አሰረድተዋል።
ሳዑዲ ዐረቢያ ምዕመናን በዑምራ ቪዛ ወደ መካ ከተማ መግባት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ቀናት ብቻ ነው አለች


የሳዑዲ ዐረቢያ ሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ወደ መካ መግባት የሚችሉትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች፡፡ ሚኒስቴሩ ከጁመዐ ግንቦት 16 አንስቶ እስከ ሰኔ 19//2016 የሐጅ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ብቻ ወደ መካ መግባት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ላይ ቀነ ገደብ ያስቀመጠችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ሑጃጆችን በመቀበል ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ ከሑጃጀቹ መካከል 45 ኢትዮጵያውንን የያዘው የሳዑዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ንጋት ላይ መዲና መድረሱ ተነግሯል፡፡

ከመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሑጃጆችን የምታስተናግደው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ሑጃጆችን ብቻ ለማስተናገድ በሚል ካስቀመጠችው ቀነ ገደብ በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ የሚገቡ ምዕመናን ላይ መቀጮ እንደምትጥል ከዚህ ቀደም ማሳሰቢያ መስጠቷ ይታወሳል፡፡ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ያወጣው የመቀጮ ደንብ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ነው፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ የሚገቡ ምዕመናን ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ 10 ሺሕ የሳዑዲ ዐረቢያ ሪያል ነው፡፡ መቀጮው ተፈጻሚ የሚሆነው ከውጪ ሀገራት ወደ ሳዑዲ የሚገቡ ምዕመናን ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ዜጎችም ላይ ነው ተብሏል፡፡ ደንቡን በተደጋጋሚ የሚጥሱ የውጪ ሀገራት ዜጎች 100 ሺሕ ሪያል ተቀጥተው ከሳዑዲ እንደሚባበሩ እንዲሁም ዳግመኛ እንዳይገቡ እገዳ እንደሚጣልባቸው የሐጅ እና ዑምራ ሚኒቴር መግለጫ ያመለክታል፡፡

አዲሱ ደንብ ከምዕመናን በተጨማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ በዚህም ያለ ፍቃድ የትራንስፖርት አገልግሎ በሚሰጡ ላይ የ6 ወር እስር እንዲሁም 50 ሺሕ ሪያል መቀጮ ይጣላል፡፡ የትራንስፖርት አገለግሎት ሰጪው የሚጠቀምበት ተሽከርካሪ ሊወረስ እንደሚችልም ደንቡ ያትታል፡፡
ሳዑዲ (መካ መዲና) ይህን ሰሞን ሙቀት እየጨመረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ... እናም ሀጅ ሚመጡ ሰዎች ስለ አየር ሁኔታ ኢንፎርሜሽን ቢኖራቸው እና ስለ አለባበሳቸው ቢያስቡበት እና ቢዘጋጁበት መልካም ነው (እንዲሁም ቀደም ብለው ነፍስየን ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል) ፤ ሀጅ ሲቀርብ ደግሞ ሙቀት ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል ....
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአል-ረህማን እንግዶችን መዲነቱል ሙነወራ ይዞ ገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳፈሩት የ1445 ዓ.ሒ የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲነቱል ሙነወራ ገቡ።

ሐጃጆቹ መዲና አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዲነቱል ሙነወራ የገቡት የአል-ረህማን እንግዶች 263 ሲኾኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 55 ያህል ሴቶች መሆናቸውን የአቀባበል አሥተባባሪው አቶ አብዲ ሲራጅ ተናግረዋል።

መዲነቱል ረሱል (ሶ.ዐ.ወ.) የገቡት ሐጃጆች በቆይታቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ እና ስለ ጤናቸው ጉዳይ አስፈላጊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

የ1445 ዓ.ሂ. የአል-ረህማን እንግዶች በመዲና በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ቆይታ መስጂድ ቂብለተይንን፣ ኡሑድ ተራራን፣ በዚሁ ስፍራ ሸሂድ የሆኑትን የነሐምዛን ቀብር ይዘይራሉ።

በመጨረሻም በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዳ በቡድን ኾነው ከዘየሩ በኋላ፣ ወደ መካ እንደሚጓዙ ከመስተንግዶ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት