4-3-3 World News 🫆
2.29K subscribers
1.11K photos
85 videos
23 links
ፈጣን መረጃ ከፈለጉ ወደ እኛ ጎራ ብለው ይጎብኙ፤
ይህ የሁላችንም ድምፅ ነው!!!
Download Telegram
የህክምና ባለሙያዎች ያነሱት የደሞዝ ጥያቄ ልክ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይሄን ያሉት ከመላዉ ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ባካሄዱት ዉይይት ላይ ነዉ።

ጥያቄዎች መቅረብ ያለባቸው በስሜት ሳይሆን ተገቢ በሆነ መንገድ መሆኑንም ገልፀዋል።

በጤና ሙያተኛነት እና በቅንነት ደክመዉ ችግር ጓዳቸዉ ስለገባ ያነሱት ጥያቄ እንዳለ ሁሉ፤ የፓለቲካ ኪሳራ የገጠማቸዉ እና  ሀኪም መሣይ ፓለቲከኞች ያነሷቸው ጥያቄዎችን መመልከታቸውን አንስተዋል።

ጋዎን ብዙ ሰዉ የሚድንበት ዕምባውም  የሚያብስበት መሆኑንና ሊከበር እንደሚገባዉ አንስተው፤ በጤና ባለሙያው ስም የሚንቀሳቀሱ ከለበሱት ግን ሊከበር እንደማይችል ተናግረዋል።

የጤና ባለሙያዎች በደሞዝ ክፍያና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ከመንግሥት ምላሽ አላገኙም በሚል ለአንድ ወር ገደማ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡


ሊዲያ ደሳለኝ

@Ethionew_433 @Ethionew_433
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹 የእስራኤል አየር ኃይል በቴህራን የመንግሥት ኢላማዎች ላይ "ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ከባድ" ጥቃቶችን እያካሄደ ነው ተባለ

በከተማው ሰሜናዊ ክፍል የተገኙ የጥቃት ቪዲዮዎች በኢራን ሚዲያ ተለቀዋል።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
🇪🇹 የኢትዮጵያ መንግሥት ለሕክምናው ዘርፍ የሚመድበው በጀት ወደ 130 ቢሊየን ብር እንዳሳደገ ገለፀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሀገሪቱ የጤና ባለሞያዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት የተናገሩት ነው፡፡

መንግሥት ለሕክምናው ዘርፍ 70 ቢሊየን አካባቢ ይመድብ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ አክለውም ባለፈው ዓመት መንግሥት 9 ቢሊየን ብር ለመድኃኒት ግዥ ድጎማ ማድርጉን ገልጸዋል።

የሀገሪቱ መሪ መንግሥት ለሕክምናው ዘርፍ የሚያወጣው ወጪ ከየትኛውም የጎረቤት ሀገር እንደሚበልጥ ተናግረዋል።

የጤና ዘርፍ በጀት እያደገ ቢመጣም ካለው ፍላጎት አንጻር ገና መሆኑንም ጠቅሰዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

@Ethionew_433 @Ethionew_433
❤4👍1
ኢራን ከእስራኤሉ የአየር ጥቃት በኋላ ሚሳይል መተኮስዋ እና ድሮኖች ወደ እስራኤል መላክዋ ተሰምቷል። እስከአሁን ጥቃት አድርሷል አላደረሰም የወጣ መረጃ የለም።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
🔥6🥰1
የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ፡- ማንንም አላጠቃንም ፣ በማንም ጥቃት መፈጸሙን አንቀበልም። ከየትም ይምጣ ለጥቃት እጅ አንሰጥም።

@Ethionew_433
👍6🥰5👏1
የተኩስ አቁም‼️

የአሜሪካው ፕሬዚደንት በኢራን እና እስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሷል አሉ‼️

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን እና እስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ገለፁ።
ሁለቱ አገራት ግን በይፋ የተኩስ አቁም ስለመደረሱ ያሉት ነገር የለም።

ኢራን እስራኤል የምትፈጽመውን ጥቃት የምታቆም ከሆነ እርሷም ሚሳዔሎችን ማስወንጨፍ እንደምታቆም ተናግራለች።
ትናንት ምሽት ኢራን በኳታር ወደሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ሚሳዔሎችን አስወንጭፋ ነበር።

ይህ ከሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው ትራምፕ በኢራን እና እስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ያሳወቁት።

ትራምፕ ሁለቱም አገራት በ24 ሰዓታት ውስጥ ጥቃት መፈጸማቸውን ያቆማሉ ብለዋል።

ነገር ግን ከዚያ በኋላም እስራኤል በኢራን የሚገኙ ዒላማዎች ላይ ድብደባ መፈፀሟ ተሰምቷል።

እስራኤል ሁለቱ አገራት በቀጣዮቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ተኩስ ያቆማሉ ለሚለው የትራምፕ መግለጫ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠችም።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
❤3👍3👏1
🚨 የኢራንና - የእስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ሆነ

◦የመጨረሻው ዙር ኢራን የሚሳኤል ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከመጀመሩ ከደቂቃዎች በፊት መተኮሱን SNN ዘግቧል።

@Ethionew_433
◆ ከተኩስ አቁም ስምምነት ከደቂቃዎች በፊት ◆

◦ኢራን ንጋት ላይ በእስራኤል ላይ በፈፀመቺው ጥቃት 6 እስራኤላውያን ሲገደሉ በርካቶች እስካሁን በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብረዋል።
ኢራን የቤር ሼባ ከተማን ኢላማ አድርጋ በፈፀመቺው ጥቃት ነው አራት እስራኤላውያን የተገደሉት።

◦እስካሁን በጥቃቱ በርካታ ህዝብ በፍርራሽ ውስጥ የተቀበረ መሆኑን የእስራኤል አደጋ ጊዜ ቡድን አስታውቋል። በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
ከፍርስራሹ ውስጥ ህይወት የማዳን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን እስራኤል ገልፃለች። 7 ወለል ያለው ህንፃም በሙሉ ወድሟል።

◦ምንም እንኳ ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነትን ይፋ ቢያደርግም የኢራን የዛሬው ጥቃት ጠንከር ያለ ነበር። እስራኤልም የአየር ክልሏን ዘግታለች።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
❤4👍4
ኔታንያሁ፡- ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማታገኝ ቃል ገብቼላችኋለሁ።

ኢራን የኑክሌር መርሃ ግብሯን እንደገና ለመገንባት ብትሞክር እናጠፋታለን። በኦክቶበር 7 በታሪካችን እጅግ የከፋ አደጋ ደረሰብን ነገርግን ምላሽ ሰጥተናል።

@Ethionew_433
🇮🇱🇺🇸/🇮🇷 ሰበር፡- የእስራኤል ቻናል 14 እስራኤል ኢራን ያልተጠቃ ሚስጥራዊ የኑክሌር ጣቢያ እንዳላት ገምታለች፣ ነገር ግን የት እንዳሉ ማንም አያውቅም።'

@Ethionew_433
😱1
ትራምፕና ኤርዶሃን በአንድ መድረክ

የአሜሪካ  እና ቱርክ ፕሬዚዳንቶች በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ በኒዘርላንድስ ተወያዩ፡፡

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶሃን እና ዶናልድ ትራምፕ በተለይም በእስራኤል -ኢራን ጦርነት ዙሪያ ትኩረት ሰተው ተወያይተዋል።

የዶናልድ ትራምፕን የተኩስ አቁም ጥረትም አድንቀዋል ኤርዶሃን፡፡

በ ዘ ሄግ ኒዘርላንድስ እየተካሄደ ባለው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (ኔቶ) ስብሰባ ላይ ነው መሪዎቹ ተገናኝተው በጦርነቱ ዙሪያ ያወሩት።

የአንካራው ኤርዶሃን በቴል አቢቭ እና ቴህራን መካከል ያለውን ጦርነት በተኩስ አቁም ለመቋጨት ትራም የተጫወቱትን ሚና በበጎ ተመልክተውታል፡፡

ምንም እንኳን እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌለኛው ላይ ክስ እያቀረቡ ጦርነቱን ሊያስቀጥሉት ቢችሉም ትራምፕ ለተኩስ አቁም በር ከፍተዋል፡፡

በጋዛ ስላለው ቀውስ እንዲሁም የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት በውይይት ስለመፍታት መሪዎቹ ተነጋግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

በ-ቢኒያም ካሴ

@Ethionew_433 @Ethionew_433
❤2
🇮🇱እስራኤል ሁሉንም ዓለም አቀፍ ህጎች እና ደንቦች ጥሳለች - የቀድሞ የእስራኤል የፓርላማ አባል

◦በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት የሚቀጥል ከሆነ ቴል አቪቭ “ኢራናዊ፣ ወታደራዊ፣ ሳይንቲስቶች ወይም ሲቪሎች ሁሉንም ነገር እስካልጠፋ ድረስ እረፍት አትሰጥም” ሲሉ የአረብ ብሄራዊ ፓርቲ ሃላፊ እና የቀድሞ የእስራኤል ክኔሴት አባል መሀመድ ሀሰን ካናን ተናግረዋል።

◦እስራኤል በኢራን እና በጋዛ ውስጥ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ደንቦች እና ህጎች እንዲሁም የሰብአዊነት መርሆዎችን በመጣስ በጦርነት እና በትጥቅ ግጭቶች ወቅት የሰብአዊ መብቶችን እና የሲቪሎችን ጥበቃን የሚጥሱ ወንጀሎችን ፈጽማለች ።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚨 ባኖን: ስለሚደብቁት የተኩስ አቁም እውነታ 🚨

◦ስቲቭ ባኖን ከኢራን ጋር የተኩስ አቁም ምክንያት የሆነውን ትክክለኛ ምክንያት አጋልጧል። ዲፕሎማሲ አልነበረም - የእስራኤል ህልውና ነው ሲል እውነቱን አጋልጧል።

◦"የተኩስ አቁም እስራኤልን ለመታደግ ያህል ነበር እዚህ ያለው ድብቅ ታሪክ ነው። ከማኘክ በላይ መንገዱን ነክሰው ነበር... ይህ (የተኩስ አቁም) የሚያስፈልጋቸው እስራኤል የመከላከያ ጥይቶች ስላለቁባት ነው።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
🔥4❤2
በሕንፃ ላይ የሚከሰት እሳት አደጋን የማጥፋት ሥራን ቀለል ያደረጉት ድሮኖች

አስቸጋሪ የነበረውን በሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ላይ የሚነሳን የእሳት አደጋ የማጥፋት ሥራን ቀለል ያደረጉ ድሮኖች በሀገረ ቻይና ተሠርተዋል። 

በምሥሉ ላይ እንደምትመለከቱት፣ በሼንዘን ግዛት ከእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች ጋር የተቆራኙ ቻይና-ሠራሽ የእሳት ማጥፊያ ድሮኖች ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ላይ ሊነሣ የሚችልን እሳት የማጥፋት ልምምድ ላይ ተሰማርተው ይታያሉ።

አሁን በሥራ ላይ ያሉት የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች ማጥፋት የሚችሉት እስከ 100 ሜትር ከፍታ ላይ ያለን እሳት ሲሆን፣ እነዚህ ድሮኖች ግን እስከ 151 ሜትር ርዝመት ባላቸው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች (ባለ 34 ወለሎች ሕንፃ) ጫፍ ላይ የተነሣን እሳት ጭምር ለማጥፋት እንደሚችሉ የፒፕልስ ዴይሊ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ያሳያል።

@Ethionew_433 @Ethionew_433
❤2