Ethio Matric
74.1K subscribers
762 photos
11 videos
108 files
203 links
Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ

ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support
Download Telegram
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ

ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምዝገባ ማካሄድ እንዳለባቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ድጋሚ በግላቸው የሚፈተኑ ተፈታኞች https://register.eaes.et በሚለው የራስ-አገዝ ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም መመዝገብ እንደሚኖርባቸው ገልጿል።

ምዝገባ ያላከናወነ ተማሪ በፈተናው ላይ መሳተፍ የማይችል መሆኑን አግልግሎቱ አሳውቋል፤፤
ለመላው እስልምና ተከታዮች እንኳን ለ ዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳቹ፡፡

ዒድ ሙባረክ
🗓 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል !

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ መጋቢት 15 ቀን 2018 ከቀኑ 11 ሰዓት 30 እንደሚጠናቀቅ፣ ያልተመዘገበ እንደማይፈተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።

በጀት ከተመደበ፣ ፈተና አስፈጻሚዎች ከተሰማሩ በኋላ አዲስ ተመዝጋቢ ቢቀርብ ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ አስረድተዋል። ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። 

ተመዝጋቢዎች ከ9 እስከ 11 የተማሩበት ውጤት ሊኖራቸው እና አሁን ላይ 12ኛ ክፍል እየተማሩ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። ድጋሚ ለሚፈተኑ ደግሞ 750 ብር ክፍያ በመፈጸም ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ ማስገባት፣ https://register.eaes.et ላይ መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ይህም 150 ብሩ ለምዝገባ፣ ለእያንዳንዱ ስድስት ፈተና 100 ብር ተደርጎ ተሰልቶ፣ ተፈታኞች " ቢያንስ ኮስት ሸር " እንዲያደርጉ እና  " ከፍዬ ነው " በሚል ለፈተናው ትኩረት እንዲሰጡ ታስቦ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።

ተፈታኞች በመረጡበት የፈተና ማእከል መፈተን እንደሚችሉ ያስረዱት እሸቱ (ዶ/ር)፣ " ለምሳሌ አምና አርባምንጭ የተፈተነ ተማሪ፣ ዘንድሮ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሆነ ለመፈተን አርባምንጭ መሄድ ሳይጠበቅበት አዲስ አበባ ካሉ ትምህርት ቤት አንዱን መርጦ የግል ተፈታኝ ሆኖ ይፈተናል " ብለዋል።

የዜናው ምንጭ: ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Economics 2017 ፈተና ካሁን ጀምሮ Ethio Matric አፕሊኬሽን ላይ መካተት ጀምሯል

ለመረዳት እንዲመች እንዲመች Near Perfect የሆነ ማብራሪያ ነው ያዘጋጀንላቹ፡፡
የናቹራሎች Maths 2017 ፈተና ዛሬ ምሽት Ethio Matric አፕሊኬሽን ላይ ተካትቷል፡፡

ለመረዳት እንዲመች እንዲመች Almost Perfect የሆነ ማብራሪያ ነው ያዘጋጀንላቹ፡፡
ዛሬ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች በድጋሚ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1️⃣ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ
እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ ሲሆኑ

በማህበራዊ ሳይንስ
እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2️⃣ ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል። የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት (Common Contents) ላይ ያተኩራል። ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን ይሆናል።

ምንጭ፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት